ግጥም
4.28K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ከልቡ ሳይመክር ሰው እየመከረ
ለእራሱ ሳይገባው እያደናገረ
ስንቱ ነው በምላስ ተስፋን የሰበረ
የመከረ መስሎት ብሶትን የሚያብስ
በሰው ጉዳይ ገብቶ ስቆ የሚያስለቅስ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍53
በበጎች ሀገር ላይ የቀበሮ እረኛ
ከአህዮች ጉባኤ ቆሞ የጅብ ዳኛ
ለፍርድ የማይመች ለሰሚውም ግራ
ጭብጥ በሌለው ዘመን እውነት አይወራ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏2
በህይወት እያለህ ላንተ ያልደረሱ
ሞትህን ሲሰሙ የአዞ እንባ የሚያፈሱ
ለምን አረፈ ነው ከስቃይ መከራ
ደረት የሚመቱት ሁሉም በየተራ።
ጭብጥ በሌለው ዘመን እውነት አይወራ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6👏1
#ላንተም_ካራ_አለልህ

በበሬዎች ጥጋብ ሳሩ ነው ተበዳይ
በአጎረስኩ ተነከስኩ መከራውን የሚያይ
ግጠውት ግጠውት ሆዳቸው ሲሞላ
ያነግሉታል በእግር ያሳር ፍዳ በላ።
ጥጋበኛ በሬ ከመስኩ እየዋለ
እረስ እረስ ሲሉት ኑ ግጠሙኝ አለ።
ላንተም ካራ አለልህ እዳው ይቆይሀል
ሰው የሚባል ፍጡር ቅርጫ ያደርግሃል
በሳሩ የዋልከው ግፍና መከራ
ላንተም ቀኑን ቆጥሮ ይሰዋሀል ካራ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍61🔥1
#በሁለት_ማንነት

በሰው አምሳል ቅኝት እያደባ ነዋሪ
ግዜ እየጠበቀ ክፋትን ቀማሪ
ላይ ላዩን ቅንነት
ውስጥ ውስጡን ግን ክፋት
አጣምሮ የያዘ ልቡን የሸሸገ
በክፋት በተንኮል ቀስ በቀስ ያደገ
ሰው ድብቅ እባብ ነው በጥርሱ የሚኖር
በሁለት ማንነት አለምን የሚዞር።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👏1
React በማረግ አብሮነታችሁን አሳዩኝ
8👍1
ትቀመጥ ጎጆዬ ብዙ ምስጢር አላት
በፍጹም አትንኳት ቀን እስኪወጣላት
ደሳሳ ብቶንም በባላ የቆመች
የክፉ ቀን ቅርሴ መሸሸጊያዬ ነች
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍2
ይጥላል ያነሳል ግዜ በፈረቃ
አንድ ላይ አይደምቁም ፀሐይ ከጨረቃ
ለሁሉም ግዜ አለው ደምቆ የሚያበራበት
በአንድ ላይ አትፈካም ፈረቃ ናት ህይወት!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍1
#በባዶ_ብርጭቆ

በውስጣቸው ጉድለት በባዶነት ገዝፈው
አልሞላ ሲላቸው በብሽቀት ተውጠው
ችርስ ይባባላሉ በባዶ ብርጭቆ
ጥጋብ ነው እያሉ ሀገሩ ተጨንቆ
ከትላንቱ ስህተት መማር ተስኗቸው
የድንቁርና ጥግ ጋራው ከልሏቸው
እየተሸሸጉ በብሔር ዣንጥላ
ሀገር ምን አባቱ ቢሞላ ባይሞላ
ችርስ ነው ዜማቸው በባዶ ብርጭቆ
ጥጋብ ነው እያሉ ሰው ሁሉ ተጨንቆ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍5👏3
ያልታደለ ከንፈር ለሐሜት ያደረ
ከምስጋና እርቆ በክፋት የኖረ
የሰው ስጋን በልቶ ከቶ ላይጠረቃ
ካልታጀበ ይላል ሀሜት በሙዚቃ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍11👏4
#ከምድር_የተረጨ

ውበት ነው አትበሉ ሲመስል አለላ
በፈሰሰው ደም ነው ሰማዩ የቀላ
የግፋችን ምስጢር በፀሐይ ተጋልጦ
እያየን ነው ቁልቁል በትዝብት አፍጥጦ
ከሰማዩ ደምቆ የሚታየው ቅኔ
ከምድር የተረጨ ደም ነው ባይ ነኝ እኔ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍92
#በጎች_ተጠንቀቁ!!

በቀበሮ መንጋ በግ እያስጠበቁ
ተበልተው ተበልተው በየተራ አለቁ
እረኛ ባሉት ነው ሁሉም የሚጠቁ
በቀበሮ ዘመን በጎች ተጠንቀቁ።
አህያ አይሰጥም ለጅብ ባላደራ
ጠፋብኝ ነው መልሱ ለፍርድ ቢጠራ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍7🔥1
ሲወድቅ ሳያነሱት ሲነሳ መገፍተር
እንዲህ ሆኖ ቀረ የዚህ ዓለም ነገር።
በወደቀ ዛፍ ላይ ከበዛበት ምሳር
አሁን ምን ግፍ አለ ከዚህ በላይ አሳር።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍111
በደሌን ደብቄ ስጠጣ ስጠጣ
የማይሸሸገው አያ ስካር መጣ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍3
#አፈር_አለበሱት

ድረሱልኝ ብሎ ሲጣራ ሳይመጡ
ሞቱን እድር ሲያውጅ በጥሩንባ ወጡ
ለቀብሩ ማድመቂያ ውድ አበባ ይዘው
ከሩቅም ከቅርብም ሌት ተቀን ተጉዘው
አፈር አለበሱት በከንፈር መጠጣ
ሲቸግረውማ ያኔ ማንስ መጣ?!!!
ከጥቂቶች በቀር የቅን ልብ ባለቤት
የጠየቀው የለም እያለስ በህይወት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍7😢1
ዛሬ ሳቅ ቢወደድ ቢጠፋ ደስታ
ፈገግ እንላለን በትላንት ትዝታ
መቆዘም ቢበዛ ሀዘን በዝቶ ዛሬ
በትላንት ጥሩ ቀን ፈገግ አልኩኝ ዞሬ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍7🔥1
ድሮም በጅብ ቆዳ የተሰራ ክራር
ቅኝቱ እንብላው ነው መች ያዜማል ፍቅር
ቢደረድሩትም ቢገርፉት አምርሮ
የጅብ ቆዳ ክራር ሆድ ነው ዞሮ ዞሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🔥6👍3
🤔Share አድርጉ❤️
#በይቅርታ_ጋሻ

ከበደሉህ በላይ በዳይ ልብ ከኖረህ
አንተስ ከበዳዮች በምን ትለያለህ?
የተሻለ በዳይ ካልተባልክ በስተቀር
ቂምን በቂም አጥቦ አይገኝም ፍቅር
የክርስቶስ ጀግና መሆንን የሚሻ
ጠላቱን ይማርከው በይቅርታ ጋሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍123
#ማር_ከመሆን_ማማ

ማሩን ሊሰሩብሽ ንቦች ሲሰናዱ
ውሎሽ ከዝንብ ሆኖ ተመልሰው ሄዱ
አበባ ነሽ ብለው ለክብርሽ ሲመጡ
ከቆሻሻ ስፍራ ተገኘሽ ከድጡ!!!
አይ አለመታደል የዘመን ዝቅታ
ማር ከመሆን ማማ መውረድ ከከፍታ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍63
ውሃ ቅዳ ብለው ወንፊት እየሰጡ
ከቶ ግፍ አይፈሩም ሲፈስ ሲቆጡ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
5👏2