ግጥም
4.74K subscribers
23 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#አንቺ_ምን_አለብሽ

ባልጠበቀ ስንኝ በላላ ቋጠሮ
ውበትሽን ለመግለጽ ስጭር እንደ ዶሮ
ቤት መታ ቤት ደፋ እያልኩኝ ለእራሴ
ስደክም ስባክን ስትጨነቅ ነፍሴ
አንቺ ምን አለብሽ ተኝተሽ አልሚ
ክረምቱን በሙቀት ሳይበርድሽ ክረሚ
ብዙ አድናቂ ያለሽ ሲጭር የሚያነጋ
ውበትሽን አወዳሽ የገጣሚ መንጋ
ቃላትን አዋቅሮ ይጭራል ይጽፋል
ውበትሽን ለመግለጽ ስንኝ ይቋጥራል
አንቺ ተኝተሻል አይገድሽ አይሞቅሽ
ይብላኝ ለማይተኛው ቆሞ ለሚያልምሽ
በክረምቱ ቆፈን ብርድ እያነዘረው
ሲያስብሽ አዳሪው እልፍ አላፍ ጫሪ ነው።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
19👍4👏3
#በሰበብ_አፍቃሪ

ጊዜ እየሄደ ነው ሲነጋና ሲመሽ...
ቀን እየቆጠረ፣
ከኔ የመራቅህ ምስጢር ሳይፈታ...
እንደተቋጠረ፣
እኔው ነኝ ያለሁት ካስቀመጥከኝ ቦታ
እንደተቀመጥኩኝ፣
መተህ ፣ከነገርከኝ ብዬ እየጠበኩኝ፣
ስወጣ ስገባ ከተጣራህ ብዬ ሰላምታ
እያሰብኩኝ፣
ፀጉሬ ከፀጉሬ ተጋምዶ ተሳስሮ፣
ቁጭት ልቤን ሲለኝ አካሌን ሰርስሮ፣
ያየኝ ከንፈር ሲመጥ በአይኔ እንጉርጉሮ፣
አለሁኝ አለሜ ምስጢር እስኪፈታ
ህይወቴ ተቋጥሮ፣
እንደው ታውቀኝ ይሆን ብታየኝ
ምናልባት፣
የመውደድን ደጅ የፍቅርህን እናት፣
ይቅር አታውቀኝም እንኳን ላንተ ቀርቶ፣
ለኔም እንግዳ ነኝ ያልዘራሁት ፈርቶ፣
ባውቀው ምን አለበት ምን እንደበደልኩህ፣
ጥፋቴ ከሆነ እኔው በሸኘሁህ፣
የልቤ ጥያቄ ውስጤን እያመሰው፣
ምን አረክሺው ሲለኝ ምኔን ልመልሰው፣
እንኳን ላንተ ቀርቶ ገራገር ነኝ ለሰው፣
ሂጂ አምጪው ለሚለኝ ለናፈቀህ ቤቴ፣
ጃስሚኔን ለበላው ላስቀረኝ ባጥንቴ፣
ምን ብዬ ልመልስ፣
ምን አንደበት አለኝ የቋጠርከው
ሚስጢር እስኪፈታ ድረስ፣
ምን አድርጌው ይሆን እያልኩኝ ስጠብቅ ልሰማ ከቃልህ፣
ማትመጣውን እንተን በምስጢርህ ሰበብ አለሁኝ ሳፈቅርህ፡፡
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
12👏4💔3😢2
#አደን

አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሣደድኳት።
ኗሪ ሆንኩኝ እንደፍየል
በነብርና ቅጠል መሀል።

አቤት አለች ያልጠራኋት
የጠራኋት ድምፅም የላት።
ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ ምላት ከኔ ርቃ።

አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
እረፍት አጥቼ ስባክን
የዕድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
14👍3👏1
#ድሮ_የኔ_እያለች

ድሮ የኔ እያለች
መርጣ የማትለብስ~ፋሽን ማትከተል
ይሄን ያንን ግዛ~ልሽቀርቀር የማትል
አቅም ስለሌለኝ~በልኩ ምትዘንጥ
በአላት ተውባ~ልቤን የምታቀልጥ

አሁን የሱ ሆና
በየ ቡቲክ ዞራ~ደስ ያላትን ገዝታ
ኮስሞቲክስ ቀያይራ~መርጣ ተቀብታ
እንደልቧ ሆና~ከቤት የምትወጣ
እንደድሮ ችግር~ጭንቅ የሌላት ጣጣ

ድሮ የኔ እያለች
ፍቅሬ ራበኝ ስትል~ሆቴል ማልጋብዛት
ከቤቴ ሰርቼ ~ በፍቅር ማጎርሳት
አንዳንዴ ከሌለ~ሲርበኝ ተርባ
እህል የማትቀምስ~እቤት እስክገባ

አሁን የሱ ሆና
ከአልጋ ላይ ሳትወርድ~አዛ አሰርታ
ወይን ሆቴል ሄዳ~ደስ ያላትን በልታ
በጥጋብ የምትኖር~ረሀብ የማያውቃት
እሱ መጣ ቀረ~የማያስጨንቃት

ድሮ የኔ እያለች
በግራችን ተጉዘን~ሲደክማት ምናርፈው
ጥላስር ቁጭ ብለን~የምናሳልፈው
ማታማታ አቅፌ~ወክ ብዬ ማዞራት
ስንቴ ደጋግሜ~ፍቅሬን የምነግራት

አሁን የሱ ሆና
መኪና ይዛለች~የደከመ ካለ ቆማ ትሸኛለች
በግር ላለመሄድ-ከሁሉ አብልጣ ትጠነቀቃለች
ደሞ የምን ድካም~ከወክ የሚመጣ
ፈልሰስ ትላለች~ገቢና ተቀምጣ

ድሮ የኔ እያለች
ላፍታ እንኳን ከጎኔ~ችዬ ማላርቃት
በስስት እያየው~እቅፍ የማደርጋት
አማረኝ ያለች ቀን~ፍቅርን ሰጥቼ
ከቅዱሱ መዓድ~አብሬያት በልቼ

አሁን የሱ ሆና
በትልቅ አልጋ ላይ~ብቻዋን ተኝታ
ፍቅር ራበኝ የሚል~ያን ልማዷን ትታ
መቅበጥ ሚባል የለም~ከእቅፉ መግባት
ፍቅርም የሚሰሩት~እሱ ያሰኘው እለት

ድሮ የኔ እያለች
ከፍቷት ስታለቅስ~ክንዴን አንተርሼ
አቅፌ እየሳምኩ~እንባዋን አብሼ
ከስሬ ሸጉጬ~ላስቃት ምጥረው
እውነት ይሁን ውሸት~ምቀበጣጥረው

አሁን የሱ ሆና
ሲከፋት ስታዝን~ብቻዋን አልቅሳ
እራሷን አፅናንታ~እንባዋን አብሳ
የትላንቱን ፍቅር~በብር አስረስቷት
ለስጋዋ ደርሶ~ለነብስ አሳጥቷት
ደስታዋዬን በገንዘብ~ካልገዛው ትላለች
እንዴት ትሆን ይሆን~አፈላልጋ ካጣች።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
15👍8👏2
#ነበረ_ምኞቴ!!

ታንክ ወደ ትራክተር፣
ክላሽም ለቀንበር፣
መትረጊስ ማረሻ፣
ጥይት ተሰብስቦ ይጣል ከቆሻሻ፣
አልቢን ማጭድ ይሁን ከምንሽር ጋራ፣
ሞርተር ይቅለጥና ድልድይን እንስራ፣
ቦንብም መንገድ ይስራ ከድማሚት አብሮ፣
በሞርተር ቀለሐ ይሰራ ከበሮ፣
ነበረ ምኞቴ የዘላለም ህልሜ፣
ማየትን የምሻው ሀገሬ ላይ ቆሜ፣
ግን ሰው ክፉ ነው ታንክ ባይኖረውም፣
ድንጋይን ተጠቅሞ መግደል አያቆምም።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
24👍6👏3
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መልካም ፋሲካ
10👍1🙏1
#ድሃዉስ_አንተ_ነህ

መቼም ሠዉ ነኝ እና በፍቅርህ ብረታ፤
ከእለት ባንዱ ቀን አመሻሽ ላይ ማታ፤
ፍቅርህ በርትቶብኝ አበባ ታቅፌ ቆሜ ከበራፍህ ፤
እኔ አንተን መዉደዴን ማፍቀሬን ስነግርህ ፤
" ስምሽ ማነው አንቺ የኔ እህት ፤
ታወቂያለሽ አይደለ ደሀ እኮ አያፈቅርም"
ብለህ በማጣቴ ፍቅሬን አኩሠሀል ፤
አንተን በመዉደዴ ስቀህ ተሣልቀሀል፡፡

እርግጥ ነው እዉነት ለመመሥከር ፤
አንተ ባለ መኪና አባትህ ኢንቨስተር፤
እናትህ ነጋዴ ወንድምህ ማናጀር ፤
እህትህ ዝነኛ አለምን የምትዞር ፤

የሀብታችሁ ብዛት ገዝፏል ከተራራ ፤
አጎትህ አክስትህ ናቸዉ ዲያሥፖራ፡፡

ነገር ግን ወዳጄ ቅምጥሉ አበቤት ፤
አንተ እንደምትልኝ የሠዉ ድሃ ማለት፤
ያልሆነ ነጋዴ ያልሠራ ቪላ ቤት ፤
መኪና የሌለው መሪ ያልዘወረ ፤
ድያስፖራ ሆኖ ወንዝ ያልተሻገረ ፤

ድሀ ማለተ ላንተ እንዲያ ከመሠለህ ፤
እኔ አፍቃሪህ ሣልሆን ድሀዉስ አንተ ነህ፡፡

ይልቅስ
ደርሶ መኩራራትህን እርግፍ አርገዉ እና ፤
መወደዴን ተረድተህ ከልቤ ግባ እና ፤
ይልቅስ ላሣይህ ልብህም ይዝናና

ገንዘብ የማይገዛዉ ከገበያ ያልዋለ፤
ከሀብታም ተነጥቆ ለኛ የታደለ ፤
ሺ ፍቅር ሺ ጤና ከድሀ ቤት አለ ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
23👍3🔥3👏3
#ላንቺ_ስል!

ፍቅሬ.............
እውነት እልሻለሁ እምልልሻለሁ
ከምነግርሽ በላይ እኔ እወድሻለሁ
..............ስለ ፍቅር ሲባል
የፈለገ ይምጣ ያልሆንኩት ልባል
ችግር ቢበዛብኝ
ነገር ቢከብድብኝ
ለፍቅርሽ ብገረፍ ክንዴ ቢደማብኝ
ተጎዳሁ አልልም ጎኔ ካለሽልኝ
ሃገር ላገር ስዞር የተንገላታሁት
ስቃይ አልለውም ላንቺ ስል የሆንኩት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
        ነጋሲ ሃበሽ
👍109🥰5
#የቱ_ጋር_መሰለህ....

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።

የቱ ጋር መሰለህ?

በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴትን ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።

የቱ ጋር መሰለህ?

የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በዋዛ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ስትዘነጋ ፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።

ትዝ አለህ?

ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።

ያን ጊዜ ተከፋህ!

ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።

ትዝ አለህ?

መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?

ትዝ አለህ?

በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?

ትዝ አለህ?

የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
‘አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ? ‘
ብለህ ስትቆዝም … ?

እንዲያ ነው አይዋ…
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።

ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
‘ኧረ ስከን’ ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
  ሚካኤል አስጨናቂ
16
#ደቃቃ_ጎልያዶች

ምን ከንቱ ቢመስል ፥ ነገር ሲጀማምር
ንቀህ አትጣለው ፥ በውል ሳትመረምር።
ድራጎን አይደለም ፥ ዳይኖሰር፣ አንበሳ
ቁጭ ብድግ አርጎ ፥ ያሳየን አበሳ።
ባክቴርያና ቫይረስ ፥ ባይን የማናያቸው
የሰው ልጅ ደመኞች ፥ ጥቃቅኖች ናቸው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   በርናባስ ከበደ
💯13👏73👍3
#በስካር_አይደለም

በየጎዳናው ላይ የሚንገዳገደው፣
እጅ እያወራጨ ለብቻ የሚያወራው፣
እንዴት አደርክ ሲሉት በቃ ዝም !የሚለው፣
በጨዋታ መሐል በሀሳብ የሚነጉደው፣
ለብቻው በማውራት መኪና የሚስተው፣
ጎዳናውን ሞልቶ የሚርመሰመሰው፣
በስካር አይደለም አቅሉን የነቀለ፣
በኑሮ ነው እንጂ ጉልበቱ የዛለ!
በስካርም መዝገብ ስሙ የሰፈረ፣
የከፋው ምስኪን ነው ሳይኖር ያኗኗረ!
ተፋፍሮ ነው እንጂ ያልከበደው የለም፣
በኑሮ ውድነት ሁሉም ነው ሰካራም፣
ስካር ከየት መጥቶ ? ተርፎ ከሚበላ?!!!
ኑሮ ነው አዙሪት ልቆ የተገኘው ከጠጅ ከጠላ!
የእኔ አይነቱ ምስኪን ለእብደት የቀረበው፣
ሰክሮ ነው አትበሉ ኑሮን ተግቶ ነው!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
17👍3😭1
#ማን_ልበልሽ?

የቁንጅና ውበት፣አሟልቶ የሰጠሽ፤
በጥበብ አስጊጦ፣በፁቭ የተሰራሽ፤
ከራስ ፀጉርሽ፣እስከ እግር ጥፍሮችሽ፤
ጠቢባን በውበት፣የተራቀቁብሽ፤
ደራሲው በድርሰት፣ቃላትን አዋዶ፤
ሰዓሊው በብሩ ፣ቀለማት አዋህዶ፤
ገጣሚው በግጥሙ፣ በቃላት ተጠቦ፤
እንደ ጅረት ውሀ፣እውቀትን አዝንቦ፤
በሙዚቃ ዜማ፣ቢገልፅሽ አስውቦ፤
ሊገልፅሽ ቢሞክር፣በድርሰት ከትቦ፤
ሙሉነት ጎደለው፣አንችነትሽ በልጦ፤
በጥበባት ኮከብ፣በደማቅ ተጊጦ፤
ሞናሊዛየ ነሽ፣ዘመን ተሻጋሪ፤
የዳቬንች አርት፣ሁሌ ምታበሪ፤
እንቁ የእግዜር ስራ፣ምትታይ አብበሽ፤
ሚስጢሬ ሆንሽብኝ፣ስምሽን ማን ልበልሽ?
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
👏126👍3
#ስሞታ_አቀርባለው

በሚያላዝን ቀኔ ገጠመኝ አላውቅም
ለከበደኝ ለአይኔ ሽሙጥ አያምረኝም
ዳገቱን ብቆፍር ጥቅም አገኝ ብዬ
ከዘብጥያ ባድር እንደ ጥሬ እንሻፎ
ባልተማማልኩበት ትቢያ ስር ተጥዬ
ሽቅብ ስመለከት ህማሞቼን ጥዬ

ረግፎ ለታየው ለዚህ ስጋ ለባሽ
ጽዋውን ለቃኘው ለታዛቢው ቢጤ
እንክርዳዱን ቀማሽ…………………..

በደሌን ይቅር በል አስበኝ እያልኩኝ
የልብ ሀዘኔታ ብሶት እያስቃኘው
የክስመቴን ክፋይ ህሊና ቢቀልበው
ክፋት ሲከረፋ እምባ ጣሬን ላየው
ስሞታ አቀርባለው………………።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
       ✍️ ኢያሱ ከበደ
7👍2🔥2
#ኦና_ብዕር…!!
ህያበይ……💗
ስሜት ያጣ
አልቦ ታሬክ
ትርጉም የለሽ  ኦና ስንኝ
ቃል ሰድሬ
እንድቋጥር
ቀልቤን ገዝቶ ያሸፈተኝ

ፍች የራቀው
ትርጉም ያጣ የገረጣ
የተምታታ
ዝብርቅ ያለ ቅጡን ያጣ

ሰዋሰዉ የነተበ
ሽንቁርቁሩ
……በቃል መርፌ የተሰፋ
ሚስጥር ቅኔው
ትርጉም ፍቺው
………ህብረ ቃሉ የከረፋ

ለዛ የራቀው
ግራ የገባው ስንኩል ዜማ
ጣር ያዘለ
የህመም ቅኝት እንዳሰማ

ኩሩ ልቤን
ከመጀነን ከኩራቱ
ከከፍታው ከዘይኒቱ

ቁልቁል ስቦ
እመቀመቅ ወስዶ የጣለ
በአንቀልባው
እልፍ መውደድ ፍቅር ያዘለ

ጀምበር መሳይ
ጠይም ነፍሱ በበጎነት የተኳለ
አንድ አንቺ እንጂ
አንቺን መሰል ወዴት አለ?

ኧረ እንደውም …
ልክ እንደዚህ
ኦና ብዕር አልቦ ግጥም
ቃል ደርድሬ እንድገጥም
ፈጥኖ ደርሶ
ምስኪን ልቤን ቀድሞ ያነቃ
ከመውደድሽ የገዘፈ
ከየት ሊገኝ ብርቱ አለቃ?

ልክ እንደዚህ…
በአፍታ ስለቴ በውልብታ
ዝብርቅ ያለ የተምታታ
ቅኔ እንድቀኝ
ቶሎ ንቃ  ተነስ ያለ
ፍቅርሽ እንጂ
ሌላ ቀስቃሽ ወዴት አለ?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
  ዳግም ሄራን
13
#ሀሁ

ፊደል ላስቆጥርሽ እጅሽን ደግፌ በምቾት ታቅፌ
ፊደል ላስቆጥርሽ ባንቺነትሽ ፍቅር በመውደድ ፈዝዤ ደንዝዤ
አቡጊዳ ልበል መቁጠሪያውን ይዤ
አይንሽን እያየው በፍቅርሽ ፈዝዤ
ባንቺነትሽ ግርማ እኔነቴን ትቼ
ፊደል ላስቆጥርሽ መቁጠሪያውን ይዤ
ከሀ ይጀምራል የሁሉም መነሻ
ምነው አንቺን ለኔ ባረገሽ መሸሻ
የመጀመሪያዬ የእስትንፋሴ ዋሻ
ባደረገሽ አንቺን ለኔ መነሻም መድረሻ
ያኔ የኔታ የፊደሉ ጌታ
ፊደል ሲያስቆጥሩን ቁጭ አርገው በተርታ
እንሰማቸው ነበር በዝምታ ቃታ
የድምጣቸው ቃና የፊደሉ ሞገስ
ማህሌት ሚመስል ቅዳሴ ሚሰለስ
ጥዑም ነው ዜማቸው እጅግ የሚማርክ
ለቅዳሴ ቤቱ ይፈለጋል በሰርክ
ማህሌት ሲሰማ ሰአታቱ ሲቀርብ
ይሰማን ነበረ ድምጣቸው ከርቀት
የሚገርመኝ ነገር በሀ አስመስዬ ያንቺን ስም መጥራቴ
በሁ አስመስዬ ስልሽ ነው ህይወቴ
ምን ተሰማሽ ታድያ ንገሪኝ በሞቴ
ልቤም ከጅሎሻል አንድ በይኝ እቴ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
14👏4🥰2
#ልብን_እየሰጡ!

ከቆሻሻ ጉድጓድ ዝንብ እያባረሩ፣
ማርን ይናፍቃል የጉድ ነው ሀገሩ፣
ልብ ለሌለው ሰው ልብን እየሰጡ፣
ፍቅር የለም ማለት ገላ እያጋለጡ፣
ጉልቻ ቢለወጥ ወጥን ላያሳምር፣
ከሺ ቢጋደሙ መች ይሆናል ፍቅር፣
ይቆሽሻል እንጅ ቤተ መቅደስ ገላ፣
እግር ስለ ዞረ መች የልብ ሊሞላ!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
🔥13👏64❤‍🔥3👍2
#የፈጣሪ_ቅኔ

" አፈር ነበርክና ትሆናለህ አፈር "
እንዲል ቃለ-እግዚአብሔር
ጭቃ ቤት ውስጥ ሆኜ የማስበው ሁሉ
ከስንት ሰው አካል እንደተሰራ ነው
ግድግዳው በሙሉ፡፡

እግዜር ግን ሲገርም!!!

የተጠናወተው የሙስና አባዜ -
የሰው ባለ-ጊዜ
በእሳትና ሴራ
ፎቅ ቤቱን ሊሰራ
የድሆች ቤት ሲያፈርስ፣
ገበያ ሲያተራምስ፣
አንዳንዴም ሲያቃጥል
በሳት- እያጋየው፤
የነገው 'ራሱን በአሽሙር አሳየው፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
አማኑኤል አለሙ
16👍51
#ቢታሰር_ቀለበት

ጣትሽ ላይ ያሰርኩት ቀለበቱ ላልቶ
ጠፋብሽ ወይ ውዴ ቃልኪዳን ዘንግቶ
ለነገሩ ይጥፋ ድሮም አልጠበቀም
ልብ ካልታሰረ በጣት ፍቅር የለም
እሰርልኝ አልሽኝ አሰርኩ ተበድሬ
ጥለሽው ተመለሽ አበቃ ትዳሬ
ልብሽን ሸሽገሽ ጣትሽን ዘርግተሽ
በደለኝ አልሽ አሉ ቃልኪዳን አፍርሰሽ
እንዳይሆን እንዳይሆን በጥድፊያ ነገሩ
ልብ ሳይግባባ ጣት በጣት ማሰሩ
ከንቱ ድካም ብቻ ፍቅር አይመሰርት
አልማዝ ወርቅ መርጦ ቢታሰር ቀለበት።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
14👍5🥰2
#አልወድሽም_እንጂ!

አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ
አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽማ
አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ
በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ
አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ
ያው እንደነገርኩሽ
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም
ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም
ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ይሰማሉ
የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው ዕያሉ
ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው
እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው
አልወድሽም እንጂ
አልወድሽም እንጂ
እኔ ከወደድኩሽ
ያው እንደነገርኩሽ
አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ
ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ
እኔማ ስወድሽ
ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ
እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ
እምልልሻለሁ "አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽ ብዬ"
ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ
እኔ ከወደድኩሽ
እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን
እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን
ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን
አትጠራጠሪ
አልወድሽም እንጂ የወደድኩሽ ዕለት
ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት
እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ
ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ
አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም
እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም
ግን....
እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ
ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ
የሚወዱሽ አሉ
እኔ ከወደድኩሽ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምንድን ይሆናሉ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
🔥10👏75
#እማ...

ምድር ሲሰለችሽ መሄድ ስትፈልጊ በቅቶሽ ስትጠሪ
ሰባቱንም ሰማይ ላውርድልሽና አንዱን መርጠሽ ኑሪ
አትጠራጠሪ ከእነርሱ በአንዱ ነዉ ሚኖረው ፈጣሪ  
ለአፍታ ዞር ብለሽ አንቺን ካጣውማ ድንገት ብትቀሪ
ይነጣጠላሉ ነፍስና ሥጋዬ ሆነዉ ለቀባሪ

እማ...

ለኔ እኮ ጠረንሽ የአንገትሽ ሥር ሽታ ከናርዶስ ይልቃል
በእስትንፋስሽ ብቻ ውስጤ በሐሴት ሞልቶ ዝንታለም ይኖራል
ላልነቃ ልተኛ እራሴን አሻሽተሽ ሽጉጥ አርጊኝና ከደረትሽ ወለል
ከዚህ አለም ክፋት ከዚህ አለም ተንኮል ከእምነትሽ ልጠለል
ጣቶችሽ በላዬ ሲንሸራሸሩማ ምድርን ለቅቄ ደርሼ ከራማ
የደስታ ጥግ ሥር ከምንጩ ጠጥቼ መንፈሴን አድሼ በሰማይ ከተማ
በእሳት ሠረገላ በዳመና መንገድ በመላዕክት ዜማ
ታጅቤ መጣለሁ እራሴን ሳስታውስ አንቺ ስትናፍቂኝ
ከጎኔ እያለሽ ከእቅፍሽ ውስጥ ሆኜ ያጣውሽ ሲመስለኝ

እማ...

ስጪኝ መቀነትሽን ወገብሽን ዞሮ ሀዘንና ደስታን የሚካፈልሽን
የደረሰብሽን በሆድሽ ያለውን ችለሽ የኖርሽውን
እሱ ይነግረኛል ያንቺን ጥንካሬ ለእኔ የሆንሽውን
ስንት ጊዜ ታመሽ ስንት ጊዜ እንደ ዳንኩ በፀሎት በምልጃሽ
ስንት ጊዜ ርቦሽ ስንት ጊዜ  ጠምቶሽ እኔን እያስቀደምሽ
እራስሽን ክደሽ በዚያ ፅኑ ፍቅርሽ ልጄን ልጄን እያልሽ

እናም እናትዬ

ምድር ሲሰለችሽ መሄድ ስትፈልጊ በቅቶሽ ስትጠሪ
ሰባቱንም ሰማይ ላውርድልሽና አንዱን መርጠሽ ኑሪ።
አትጠራጠሪ ከእነርሱ በአንዱ ነዉ ሚኖረው ፈጣሪ
ለአፍታ ዞር ብለሽ አንቺን ካጣውማ ድንገት ብትቀሪ
ይነጣጠላሉ ነፍስና ሥጋዬ ሆነዉ ለቀባሪ
አይበለውና
እንደው አይበለውና አምላክ መጥቶ ደጅሽ
ወይ መለዓኩን ልኮ የሞት ፅዋ አስይዞ ከእኔ ሊነጥልሽ ተረኛ ነሽ ቢልሽ
በእማ ቀልድ አላውቅም ከገዛ ዙፋኑ እኔው ተሰይሜ
እፋረደዋለው ከእግዜር ችሎት ቆሜ እስከቻለ አቅሜ
ሺ ሟች ሞልቶ በሀገር መንገደኛ ገስጋሽ እሷን ያየኽብኝ
ምን ኖሮኝ ልኖር ነዉ እሷኑ ሰጥተኸኝ መልሰህ ብትነጥቀኝ
እናም ልለምንህ ባለህ ሀይል ሁሉ አትጠቀምብኝ
እንዲህ ጠይቃለው ስለ እናትህ ስትል እናቴን ተውልኝ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    አማኑኤል ብርሃኑ

ሺህ ዓመት ኑሪልኝ እናቴ
መልካም የእናቶች ቀን ❤️
17😢5👍2
#በልኬ_ብቀደድ

ገና ያኔ ሳውቅሽ
በቀላል ላሰምጥሽ
እናቴ አሜሪካ
አባቴም ጀማይካ
እኔም ለመዝናናት ልቤ ደስ እንዲለው
በሳምንት በሳምንት ዱባይ እሄዳለው
ብዬ የነገርኩሽ
እሱንን ሰርዢው
ውስጥሽ እንዳትይዢው

ስልክ ስትደውይ
ሄሎ የኔ ፍቅር ጋራጅ ነው ያለሁት
መኪናዬን አሞት ቁሜ 'ያሰራሁት
እና አትመጣም አሁን ብለሽ ስትጠይቂኝ
ባላሰብኩት መንገድ ስታጨናንቂኝ
እ... እመጣልሽ ነበር አላለቀም እንጂ
ትንሽ እንዳላረፍድ በታክሲ አርገሽ ሂጂ
ብዬ የነገርኩሽ
እሱንን ሰርዢው
ውስጥሽ እንዳትይዢው

ደግሞ በሌላ ቀን እስኪ ጋብዘኝ ስትይ
ባክሽ ዛሬ ብታይ የኔ ቀኔ አይደለም
ገንዘብ ስለጨረስኩ ኪሴ ምንም የለም
ባንክ ሄጀ እያለ ለመያዝ ወረፋ
ያጋጣሚ ነገር ኤቲኤሜ ጠፋ
እና በዚ ምክንያት ማታ ላይ አልጠጣም
የብላክ ሌብል ብር የትም አላመጣም
ብዬ የነገርኩሽ
እሱንን ሰርዢው
ውስጥሽ እንዳትይዢው

እውነታው ይሄ ነው
በነገርኩሽ ምኞት ደስ እንኳ ብሰኝም
አይደለም መኪና ኤቲኤም የለኝም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ነጋሲ ግደይ
👏16😁127😱2🤣21