ግጥም
4.77K subscribers
23 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ለሰው_የሚታየው!

በአይናችን ቦይ መስመር የሚንዠቀዠቀው
የሚታየው እንባ ጎርፍ ሆኖ የሚወርደው
የብዙ አመት ህመም የስቃይ ምንጭ ነው
በልባችን ኩሬ በግድ ተገድቦ ታፍኖ የኖረው
በጉንጫችን ዳገት ቁልቁል መስመር ሰርቶ
በሐይል አስገድዶ ሁለት ቅንድብ ገፍቶ
የአንድ ቀን አይደለም ድንገት የሚመጣ
በጥቂት ሀዘን ቁልፍ ተከፍቶ የሚወጣ
የከራረመ ነው የዘለላ ድምር
ከልባችን ሳሎን ቀድሞ የሚቋጠር
ሲሞላ ግድቡ የሚወርደው ጥሶ
ከታቻምናው አምና ዘንድሮን ቀንሶ
ከገደብ ያለፈው የተራረፈው ነው
ቅጥሩን እየጣሰ ለሰው የሚታየው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
      ስንታየሁ ሀብታሙ
14👍7
#ቀን_ቀን_አትሳቂ

ቀን ቀን አትሳቂ የማታው ይበቃል
ፉጡር ሞኝ አይደለ
ፈገግታሽን ብሎ ከፊጣሪ ይርቃል
ይህ ሁሉ ከሚሆን
ሰሪ እየተናቀ ስሬት ከሚወደስ
ልክ ስለሆነ
ነገር እና ግብሩን አንዳንዴ መቀነስ
ጨረቃ ብቻዋን
ፅልመትን ለመግፈፍ አቅሟ ስላነሰ
ማታ ማታ ሳቂ
ፈገግታሽ ያድናት ሳቅ እየፀነሰ
እርግጥ
ልክ እንደቀን ሁሉ
ማታውም ማታ ነው በእሱ የተሰራ
ግን ደግሞ
የሰው ልጅ በሙሉ
የጠቆረን ሁሉ ሴጣን ነው እያለ ሰርክ ከተጣራ
ባይገናኝ እንኳን ነገር እና  ውሉ
ሰው ብሎ ከጠራሽ ሰዋሰው በሙሉ
ነጭን ነፁ አድርገሽ ሁኚ ልክ እደሰው
ጠቁሩን አሳንሶ ነጭ እንደቀደሰው

አይጭነቅሽ ከቶ
ደግሞ እንዳታስቢ
ያለሽበት ሀገር ይሄንን አይፈቅድም
አድዋ ለጥቁር ነው ለነጮች አይሰግድም
ምክንያቱም
ታሪክ ተረት ተረት ሆኖ ቢፀና እንኳን
ነጭ ሆኖ መድመቅ ነው በጥቁርነት ድንኳን
ከጠቆረ ሰማይ ፊቱ አለች ጨረቃ
ፅልመት ለመጋፈፍ አርፍዳ ምትነቃ
ደግሞም እንደውነታው ደግሞም እንደሀቁ
ጨላማ ሲኖር ነው ንጋት መታወቁ
የፅልመት አድማቂ የንጋት ምልክት
እስቲ ፈገግ በይ አብሪ እንደከዋክብት
እ...........ሰ.....ይ !
አሁን ደግ አደረግሽ
ብርሃንሽ ወጣ ፅልመት እየቸረሽ
እ...........ሰ.....ይ !
አሁን ገና አበጀሽ
ጥቅሩን ተንተርሰሽ ነጭ ነጩን ፈጀሽ
አየሽ
አሁን ተረዳሽኝ
ስቀሽ አነጋሽኝ
ስጣጣር ብውልም ለሞት ተሰይሜ
ፈገግ ያልሽ ለታ
ኖሪያለሁ እላለው መቃብር ላይ ቆሜ
እ ...............ሰ...................ይ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   በእውቀቱ ስዩም
12👏4👍3🔥3
#ተባብለን_ባይ_ባይ

ደህና ሁን ደህና ሁኚ ተባብለን ነበር
ያለቀ ሲመስለን የጀመርነው ፍቅር
አሁን ምን አመጣው የትዝታን ፈረስ
ከአንቺ ከእኔ እያለ ናፍቆት ሊያመላልስ
ሰው አላለያየን በፍቅራችን ገብቶ
ሰበቡ የእኛው ነው የገመድነው ላልቶ
አሁን ከረፈደ ከሌላ ተላምደን
ትዝታችን መጥቶ ምን ፍጠሩ ሚለን?
አንቺም የሌላ ነሽ እኔም የሌላ ሰው
ትዝታሽ ከእኔ ቤት ምን አመላለሰው
አርፎ መኖር እንጂ ችሎ እንደነገሩ
በክራሩ ቅኝት እያንጎራጎሩ!!!
እህል ውሃ እንዲህ ነው አገናኝቶ ነጣይ
ሳንጀምር ቋጨነው ተባብለን ባይ ባይ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
💔166😱4👍2👌2
#ነይ_ግጥም_እናንብብ

ውደጅኝ አልልም
ፍቅር እረቂቅ ነው…
ሚስጥሩ ውስብስብ፤
ይልቅ ጠጋ በይኝ !?
ክንዴን አንተርሼሽ…
ውብ ግጥም እናንብብ።

ታምሪያለሽ የኔ ዓ'ለም
ከ'ዓይኖችሽ ቅፅበት
ምትሀት ይዘንባል፤
ሳቅሽ ፏፏቴ ነው፣
እንደመላክ ቀለም 
ከውበት ይጠራል።

ነይ ግጥም እናንብብ
ነይ ውበት እንሳል
ነይ ዜማ እንቀምር፤
እንቆቅልሽ አይደል
ግዜ ይፈታዋል
የኔ'ና አንቺን ነገር

ድምፅሽ እረቂቅ ስልት
የቤትሆቨን ጣዕም
የሞዛርት ቅማሬ፤
ወደድኩሽ የኔ ዓለም
የፍቅርሽን ቅኔ
እንደአዲስ ተምሬ።

ውደጅኝ አልልም
የመውደድ ሚዛኑ
ስለሆነ  መውደድ፣
ነይ ግጥም እናንብብ?
ይቺን ምድር ለቀን፣
እኔና አንቺ እንበድ ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
17👍5🥰4🔥1
#አገር_በሚያልፍበት_ባዘቦት_መንገዱ

አገር በሚያልፍበት ፥ ባዘቦት ጎዳና
በሁሉም ሰው ፊት ላይ ፥ትካዜ ተስሎ
ሲመስል  ደመና
ማን ከማን ተሽሎ
ማን ማንን ሊያጽናና?
በዕንባ  ስፍር  እንጂ የምንለያየው
ክንብንቡን ገልጦ፥ ቀረብ ብሎ ላየው
ሁሉም ልቅሶ ላይ ነው ::
በየትኛው ዘመን  ፥ይፈርሳል ድንኳኑ
የምስራች መምጫው መቼ ይሆን ቀኑ?
ብየ ብጠይቅም
መልሱን ግን አላውቅም::
አገር በሚያልፍበት፥  ባዘቦት መንገዱ
ባስፋልት  በሐዲዱ
መርዶ እየዘለለ
ብስራት ግን ይድሀል
በዚህ ሁሉ መሀል
እኔን ስታስቢ
ፈገግታሽ ፤ ከናደው   
ፊትሽ አካባቢ
ያንዣበበውን ጉም
በሕይወት መኖሬ፥  አለው ትልቅ  ትርጉም::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
12
#ልንገርሽ_ጨረቃ

በገጣሚ ብዕር በስንኝ ቋጠሮ
በዜማ ቀማሪ በድምጽ እንጉርጉሮ
እየተሞላቀቅሽ በአፍቃሪ ደብዳቤ
በሰአሊ ቀለም በሸራ ላይ ድቤ
አሞጋሽ ሲበዛ በስምሽ ዘማሪ
ፀሀይ ልሁን አትበይ ጨረቃ ተይ ፍሪ
ደራሲ ነው እንጂ ብዕር አንጠፍጥፎ
በሰው ህሊና ላይ ያተመሽ አግዝፎ
ሰአሊው ነው እንጂ ውበትሽን አድምቆ
የሌለሽ ማንነት ከፀሀይ ላይ ሰርቆ
ገጣሚ ነው እንጂ በስንኝ ቋጠሮ
ዜመኛው በዋሽንት በድምጽ እንጉርጉሮ
አንቺን ያገዘፉሽ በሌለሽ ከፍታ
በምናብ አስውበው በፍቅረኞች ኩታ
የተራ ተራ ነሽ ልንገርሽ ጨረቃ
ፀሀይ ትበልጣለች እጅግ ብዙ ልቃ
በአሞጋሽ ግርግር በዘፋኝ እስክስታ
በጨለማ አድናቂ ሲሰጥሽ ከፍታ
ፀሀይ ነኝ አትበይ አቅምሽን እወቂ
በሰው ህሊና ላይ ገዝፈሽ አትድመቂ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
7👍5👏3
​በቀን ውስጥ ለምናባክነው ጊዜ ትርጉም የሚሰጥ፣ አእምሮን የሚያድስ እና የነገ ማንነታችንን የሚቀርጽ አንድ ምርጥ ቻናል ልጋብዛቹ

⭕️በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኟቸው፦

📜 የታዋቂ ሰዎች የሕይወት ጉዞ፦ ከውድቀት እስከ ስኬት ማማ ያደረሳቸው እውነተኛ ታሪኮች!

📚 ከመጽሐፍት ዓለም፦ የሺህ ገጽ መጽሐፍትን ጭማቂ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ!

🎭 Dark Psychology፦ የሰውን አእምሮ የማንበብ እና የማሳመን ጥበብ (ሚስጥራዊ ጥቆማዎች)!

📖 ቁልፍ ትምህርቶች፦ ለስኬትዎ አቋራጭ የሚሆኑ የጥበብ መንገዶች!

💥 አነቃቂ ጥቅሶች፦ ሞራልዎ ሲወድቅ ስንቅ የሚሆኑ ብርቱ ቃላት!

አልማዝን ለማግኘት መቆፈር ያስፈልጋል፤ ጥበብን ለማግኘት ግን "Join" ማለት ብቻ በቂ ነው! 😉

​አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇👇👇

🔗 https://t.me/BIOGRAPHY_TEACH
🔗 https://t.me/BIOGRAPHY_TEACH
🔗 https://t.me/BIOGRAPHY_TEACH

👍21
#ዋ!... ያቺ አድዋ

ዋ!...
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…
ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብጽዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና…
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ!... ዓድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው፣ በለው- በለው!
ዋ! … ዓድዋ …
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እደገና፡፡
… ዋ! … ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የዐለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…🇪🇹
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን
7🥰1😱1
#ይድረስ_ለናፈቅሽኝ

የናፈቅሽኝ ለታ
ሀሳቤ ሲምታታ
ስትናፍቂኝ ጊዜ
ሲጫነኝ ትካዜ
ያስታወስኩሽ ለታ ያሰላሰልኩሽ ለት
በተቃርኖ አለም ውስጥ መንፈሴ ሲዋትት
አንቺ ትዝ ያልሽኝ ቀን
በቁሜ ስባንን
ጠራራ ላይ ቁሜ ብርዱ ውስጤ ገብቶ
በጨረቃ ብርሀን ላበቴ በርክቶ
ጠጠር ላይ አንጥፌ ደልቶኝ እተኛለሁ
ፍራሽ ብርድልብሱ ሲያቃዠኝ አድራለሁ
ትውስ ያልሽኝ ጊዜ
በምድረ በዳው ላይ በሰው ተከብቤ
በሁካታው መሀል ሰላሜን ደርቤ
ሲርበኝ ጠጥቼ ሲጠማኝ በላለሁ
ቀን ተኝቼ ውየ ሌሊት ቁሜ አድራለሁ
ስትናፍቂኝ ጊዜ እንዲህ ያደርገኛል
በሌለው አለም ውስጥ ያለሁ ይመስለኛል
ወደሗላ እያየሁ ወደፊት መራመድ
ከሰው ተለይቼ ከአራዊት የምለምድ
በረሀ ወጥቼ በጫካው ውስጥ ኗሪ
የምትመጪበትን እልፍ ቀን ቆጣሪ
ትውስታየን ሁሉ ትውስታሽ አዝሎ
በመናፈቅ ብዛት አካሌ ጎስቁሎ
ደሞስ ስትናፍቂኝ ምናለ ያልሆንኩት
ያንቺን ቀን ስቆጥር የኔን ቀን ዘለልኩት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
21👍5
#Ads
🔨 ሀመር ፈጣን ዕጣ  🔨
"ዕድልዎን በሀመር ይቅረጹ!"

​የመጀመሪያው ዙር ፈጣን ዕጣ ተጀምሯል! አነስተኛ ብር ከፍለው ትልቅ ሽልማት የሚያሸንፉበት ዕድል እንዳያመልጥዎ።

🎁 የዚህ ዙር ሽልማት፦ [1ኛ ዕጣ 2,000 ብር, 2ኛ ዕጣ 600 ብር እና 3ኛ ዕጣ 200 ብር]

🎟️ የአንድ ዕጣ ዋጋ፦ [200 ብር ብቻ]

👥 አጠቃላይ የሰው ብዛት፦ [16 ሰው ብቻ]

እንዴት መሳተፍ ይቻላል?

1️⃣ ያልተያዘ ቁጥር በመምረጥ ግሩፕ ላይ የመረጡትን ቁጥር ይፃፉ።

2️⃣  [በንግድ ባንክ ወይም በቴሌ ብር ወይም በሲቢኢ ብር ወይም በMPESSA] ክፍያውን ይፈጽሙ።

3️⃣ የከፈሉበትን ደረሰኝ (Screenshot ወይም message) ግሩፕ ላይ ይላኩ።

4️⃣ የመረጡት የዕጣ ቁጥርዎ ላይ ምልክት መደረጉን ያረጋግጡ!

⚠️ ማሳሰቢያ፦ ዕጣው 1️⃣6️⃣ ቱም ሰው እንደተሟላ ወዲያውኑ በቪዲዮ ተደግፎ ይወጣል! ለአሸናፊው ሽልማቱ በ10 ደቂቃዎች ውስጥ ይላካል።

ፈጥነው ይቁረጡ፣ የዛሬው ዕድለኛ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! 🏃‍♂️💨

​[https://t.me/Hammer_Bingo]
7
#ልብ_ተከርችሞ!

ልብ ተቆልፎ ፣ ጥርስ እያገጠጠ፤
በውሸት ፈገግታ ፣ ሰው እያላገጠ፤
ፍቅር አልባ ጉዞ ፣ በከንቱ መዋደድ፤
በማስመሰል ዜማ ፣ የሗሊት መራመድ፤
አብሮ እያሉ አግጥጦ ፣ ሲለያዩ ሀሜት፤
ካለው ጋር መግተልተል ፣ የዘመኑ ቅኝት፤
ከልብ ባልመነጨ ፣ በውሸት ፈገግታ፤
እንዴው ከላይ ከላይ ፣ እየመቱ እስክስታ፤
ፍቅር መቼ ያምርና ፣ ልብ ተከርችሞ፤
በማስመሰል ጉንፋን ፣ አብዛኛው ሰው ታሞ፤
ጥርስማ ያገጣል ፣ የውሸት የውሸት፤
ከልብ ነው እንጂ ፣ የሚነሳው እውነት።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
16👍6💔2🥰1
#መስሎኝ_ነበር_ያኔ

ያላንተ እኔ አልኖርም፤
ህይወትም የለኝም፤
በፍቅርህ ሙቻለሁ፤
ተቀበለኝ አንተም፤
   …ስትይኝማ 'ኔም……
ይህ የዋሁ ልቤ፤
ተቀብሎሽ አንችን፤
ሲናፍቅ ፍቅርሽን፤
አምኖ አንችነትሽን፤
ላያይ ጉዳትሽን፤
ፈልጎ ደስታሽን፤
ሲቀበል ፍቅርሽን፤
    .....አንቺ ግን!
ጥለሽው ሄድሽ ልቤን፤
አውላላ ሜዳ ላይ፤
በድቅድቅ ጨለማ፤
በሌለበት ብርሀን፤
   .....እኔማ
በፍቅር ከኔጋ ልትቆሚ ከጎኔ፤
እኔም ሳስቸልሽ ልክ እንደ ብሌኔ፤
በፍቅር የምንዘልቅ መስሎኝ ነበር ያኔ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
24
#እናትዬ

ምሣሣላት አለች አይቼ ማልጠግባት
አኑርልኝ እያልኩ ዘውትር ማነባላት
ከዕድሜ ግማሹን ተችሎ ብሰጣት
ቢያንስባት እንጂ እሷ አይበዛባት
ደስታዋን እያየሁ ደስታን እንዳገኝበት
ጌታ ሆይ አኑራት...
በመኖሯ ስላለ ..የኔ ሕይወት

እናቴ የኔ እናት.....
የሚገባሽ ነገር ምን ይሆን እላለሁ?
ላረግሽልኝ ሁሉ  ልመልስ እሻለሁ
ከ9ወር ጀምሬ ማብቂያውን አጣለው
ውለታሽ ተቆጥሮ ከቃላት በላይ ነው
ፍቅርሽ እንዳይወዳደር ወደር እንኳ የለው

እና እናትዬ .....እስኪ ምን ላርግልሽ?
እኔ ፈልጌ አጣሁ.. ላንቺ ሚመጥንሽ፣
ወድሻለሁ ማለት መሰለኝ ሚያንስብሽ፣
መውደዴን በምን    ..ልግለፅልሽ?
እናትዬ.....እስኪ ምን ላርግልሽ?

ውብ ቃላቶች ብደረድር...፣
አይችሉም ሊገልፁ ለሆንሽልኝ ነገር፣
እናቴ ምን ልናገር...፣
አጣሁ ቃል ፈልጌ ስላንቺ ልዘረዝር፣
ግን
ወድሻለሁ ማለት ከገለፀ ፍቅር፣
ወድሻለሁ ብዬ በቃል ብቻ አልቅር፣
የሚገባሽን ሁሉ ላሳይሽ በተግባር።
እናትዬ ..እስኪ  ምን ላርግልሽ?
የሚመጥን ካለ.. ለውለታሽ ምላሽ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ብሩክ ፍፁም
መልካም የእናቶች ቀን ❤️
24👍2
#የሰው_ልጅ_ገፅ_ነው!

ህይወት እንቆቅልሽ ? ምን አውቅልህ? በይኝ
በለቅሶ ጀምሮ በለቅሶ ሚያበቃ ? እስኪ መልሽልኝ?
ይኼማ ቀላል ነው ሀገርም አልሰጥህ፣
የሰው ልጅ እኮ ነው ይኸው መለስኩልህ!
ሲወለድ አልቅሱ ሲሞት አስለቅሶ፣
መኖሩን ያበቃል አፈር ከላይ ለብሶ!
በእኔ ተፈትኖ ሳቅ ሀዘንን አይቶ፣
ይለቀስለታል በእድሜ ገደብ ሞቶ፣
ምስጢሩ ሲፈታ ቅኔው ሲፈለቅቅ፣
በለቅሶ ተወልዶ አስለቅሶ የሚያልቅ ፣
የሰው ልጅ ገጽ ነው ከአፈር የተገኘ፣
ትቢያነቱን ሳያውቅ በጉራ የናኘ!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
👍1412
#እኔና_ጨረቃ

አመሻሽ ላይ ሆኜ ሳስብሽ ሳስብሽ
በረንዳ ላይ ሆኜ አንቺኑ ስስልሽ
ስላንቺ የሚያወራ ግጥም ስፅፍልሽ
አንባ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ እያሉ
አይኔና ጉንጮቼ በእንባ ሲሞሉ
ከሰማይ ላይ ሆና ትታዘበኛለች
አጇን በአፏ አርጋ ታፈጥብኛለች
ደንገጥ አልኩኝና እንባዬን ጠረኩኝ
እሷም ቀስ በቀስ እኔን ቀረበችኝ
ብርሀኗ ልዩ ነው ሁሉን የሚያስረሳ
ፈዝዤ ቀረሁኝ ፎቶ እንደሚነሳ
አኔ ጋር ደረሰች ከዋክብት አጅቧት
መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ እኔም በፍርሀት
ጠጋ አለችና አይዞህ ጨረቃ ነኝ
አትፍራ አትሽሽ ብላ አቀፈችኝ
ኮከብ እንዳጀባት እየነገርችኝ
እንባዬን ጠራርጋ አይኖቼን እያየች
በሹክሹክታ መንፈስ ማውራት ጀመረች
አይዞህ ጠንከር በል ምንም አትሆንም
እውነት ካፈቀርቃት የትም አትሄድም
ለፍቅርክ ምስክር እሆንልካለው
ካለችበት ሄጄ እነግርልሀለው፡፡
ያቺ ውብ ጨረቃ ቀርባ አፅናናችኝ
ለተከፋው ልቤ ደስታን ሰጠችልኝ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
23👍6🤣1
#ምን_እየሆንኩ_ልጠብቅሽ?

ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ?
እራስ ዳሽንን እየገፋሁ?
ወይስ እየሰራሁ የኖህ መርከብ?
ሳፈላልግ የሰው ኮከብ?
ምን እየሆንኩ  ልጠብቅሽ..???!

እየዘመርኩ?
እየዘፈንኩ?
እያረመምኩ?
ግራ ገባኝ እኮ 
ያለየለት ድል ነው
ያለየለት  ምርኮ! 

ምን ስሆን ልጠብቅሽ..???!
አባይን ስጠልቀው?
ኤርታሌን ስሞቀው?
ቆዳየን እንደ ጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው
ተዋነይ' ጋ ልሃድ ዕፁን እዲምሰው?

ምን ስሆን ልጠብቅሽ...???!
በጌታዬ ግራ? በጌታዬ ቀኙ?
በየት ትመጫለሽ? ወይ አፍቃሪ ሞኙ?
በአብርሃም ቤት አጋር?
ወይስ ባቢሎን ግንብ ጋር?

የት' ጋ ተመጫለሽ..???!
ከዘመን በየትዘመን?
ከንጉስ ማን ንጉስ?
ከባህር የት ባህር?  
ከደብር የት ደብር?
ከጫካ የት ጫካ? 
ከሰዓት ምን ሰዓት?

ምን እያረኩ ልጠብቅሽ...???!
ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ? 
የዛፍ ቆዳ ስልጥ!
ግዙፍ ሁኜ  ወይ እረቂቅ?
ንፋስ ሆኜ  ወይስ  ደቂቅ?  
ደስታ ሁኜ ወይስ  ሀዘን?
ፀሐይ ግርጌ ወይ ጨረቃ?
ግጥም ሁኜ ወይ ሙዚቃ?

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ..???!
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ኤልያስ ሽታሁን
31
#ስውር_ኃይል

ውሎ-ገባው መንገድ ፥ ልስልሱ ጎዳና
ቀናት ሲፈጅብኝ ፥ አይቶ ታዘበና ፣
የት ይወለድ እንጃ ፥ ከየትኛው ነገድ
ስንቅ አትያዝ አለኝ፥ አስበህ ለመንገድ።

እውነትም .... እውነትም
......... . ሐሰት የለበትም።
በጊዜ ደረስኹኝ ፥ ዘንድሮ ከአምና
እረሃብና ጥም ፥ ጊዜ አይሰጡምና።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     በርናባስ ከበደ
👍115
#በምላሴ_ገደፍኩ!!

ለመፆም አስቤ ሁለት ወር ሁዳዴ፣
የከብት ስጋ ትቶ የሰው ለምዶ ሆዴ፣
እንዳልተው ጀምሬ እንዳልበላ ፈራሁ፣
ምላሴን ለጉሜ ሱባኤን ካልገባሁ!
ወተትን ሳልጠጣ ለመክረም አስቤ፣
መፆም ጀመርኩና ጋቢየን ደርቤ፣
በምላሴ ገደፍኩ ቀርቶ ዶሮ ወጡ፣
እንደኔ እንዳትረክሱ ሐሜት አታላምጡ።
የከብት ፁማቸሁ የሰው ስጋ አትብሉ፣
ፍቅርን ስበኩና ሐሜትን ዝለሉ፣
ወተት እየፆሙ የሰው ደም መጠጣት፣
ዶሮ ወጥን ዘሎ የሰው ስጋ መብላት፣
ፍቅር እያፈረሱ ጥላቻን መገንባት፣
ስጋ ባለመብላት እጸድቃለሁ ማለት፣
በርግጥ ፆም ጥሩ ነው ስጋን ያሸንፋል፣
ካልተጠነቀቁ ሐሜት ግን ያረክሳል፣
ጮማውን ለመቁረጥ ልባችን ከፈራ፣
ምነው አንደነግጥ ሐሰት ስናወራ?!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
20👍11😢1
ለመላው የቻናላችን እስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ 1447ተኛው የ ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❤️

🔆 Eid Mubarek  ኢድ ሙባረክ 🌙
👍113
#የኗሪ_ታዛቢ!

ተይ በሏት ይችን ሰው፥ ምከሯት ትታረም
አጀብ አያሰኝም ፥ጅብ ካህያ መክረም!¡
ታግሼው ነው እንጂ!
እስስት አመልሽን ፥ ስታግለበልቢኝ
ፈርቼሽ አይደለም ፥ እንዳሻሽ ስትገልቢኝ።
ተቻችሎ መክረም!
አንቺ ትብሺ አንተ ፥
በሚል የጋራ ሀሳብ ፥ ፍቅር ካላሰረን
ቤታችን ፈረሰ፥ አውላላ ላይ ቀረን።
እወቂበት በቃ!
ማን የገነባውን ፥ ማን አፍርሶ ያልፋል
በመቻቻል ሲሆን ፥ የኔም ልብ ይሰፋል።
መቼስ ምን ይደረግ!
ጊዜ ላይቀይርሽ !
ታጥቦ ጭቃ አመልሽ ፥ ቀኔን እያስረጀው
(ትኖሪያለሽ እንጂ)
ባኗኗሪነት ነው ፥ እድሜዬን ምፈጀው።
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
17👍6👏3🤯2
#ግማሽ_ቅጠል

አበባ ነኝ እኔ ፥ የአበባ ዛፍ ቅጠል
ማማር ነው ስራዬ ፥ ራስን ሆኖ መብቀል።

አንገቴን አልደፋም ፥ ቢጨፈን ዓይን ሁሉ
የትም እፈካለሁ ፥ በዱር በገደሉ።

እንዲያ ሆኜ ስኖር ...
ከውበታት አንድ ቀን፣ ...

በመስመር ከፈኩት ፥ ከሆኑት ሰልፈኛ
ወጣ ብዬ ቢያየኝ ፥ አንድ አትክልተኛ፣...
የአካሌ ክፋይ ፥ ድንገት ተቀነሰ
ክርክም ለማሳመር ፥ በመቀስ ተላሰ!!

ግማሽ ቅጠል ሆንኩኝ።

የቀረው ግማሼ
እየተንሳፈፈ ... ወደቀ ከአፈር፣
....... እኔን ልንፈራፈር!!!

ቆየና ....
ቀናት አለፉና፣ ...

ያ የኔው እኔነት
ያ የኔው ማንነት፣...
ለምለም የነበረው ፥ ደርቆና በስብሶ
መብል ሆኖ መጣ ፥ ለኔው ተመልሶ።

ተቆርጦ የወደቀው ፥ የአካሌ ቅንጣት
የሞትን መዓዛ ፥ በደም ስሬ አመጣት።

ኦውው!
ለካስ እረባለሁ ፥ ከማማር ባሻገር
ቀስሞ ይወስደኛል ፥ የሌላ አበባ ስር።

እግዚአብሔር ይመስገን!
ሕይወቴን ወደድኩት ፥ አሁን በተለየ
አኗኗር አይከብድም ፥ አሟሟቱን ላዬ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     በርናባስ ከበደ
11👍3🔥2