ግጥም
4.77K subscribers
23 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#አርፎ_አይቀመጥም

ሰው መንገደኛ ነው ተጓዥ በየዕለቱ
ባአቀበት ቁልቁለት የተሰራ ቤቱ
ሲወጣ ሲወርድ ይነጋል ለሊቱ
ካአፈር የተገኘ ሸክላ  አከላቱ
መቸ ያስችለዋል ልተወው ቢልኳ
ደርሶ እየተናደ የካበው ሲንኳኳ
መስመሯን ስቀይር ህይወት ለታሪኳ
ልቡ ባህር ገብቶ ሲቀዘፍ በታንኳ
ግር ይለዋልና እስኪለምደው ድረስ
ሲቀኘው ይውላል ትዝታን ሲደርስ
ሽው ሽው እያለ  እንደቀኑ ንፋስ
ወስዶ እስኪመልሰው  የሀሰቡ ፈርስ
አርፎ አይቀመጥም ከመሬቱ ጎኑ
እስኪሸልብ ድርስ እስካለ በውኑ
ኮሽ ባለቁጥር ይገለጣል አይኑ
ትንፍሹ እንድሰማ እንደሸት ጠረኑ!!
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ሊድያ ማሞ
👍157
#እቴዋ_ልምከርሽ !

ማሬ ማሬ እያለ የሚነጠፍልሽ፣
እኔን እኔን ብሎ ድንግጥ የሚልልሽ፣
ከአንቺ ሌላ እያለ በስምሽ የሚምል፣
ስርስርሽን በዝቶ ሲከብሽ የሚውል፣
ማርሽን ፍለጋ መሆኑን አትርሽ፣
በጥርስሽ እየሳቅሽ ልብሽን አሽሽ!
እውነተኛ አፍቃሪ ላንች የተፈጠረ፣
አይቀርም መምጣቱ የተመረመረ፣
እቴዋ ልምከርሽ በስንኝ ቋጠሮ
መኖርን ከፈለግሽ ሴትነትሽ ከብሮ
ውበትሽን አርግፎ ልብሽን ለሚሰብር፣
አትስጭ ቸኩለሽ ክብርሽ ነው ብር አንባር !
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
26👍11🥰2
#ጆሮዬን_መልሽ!

ይመስለኝ ነበረ ...
ልቤን የሰወርሽው ፥ እንዳያስብ ሌላ
ዓይኔን የጋረድሽው ፥ በመውደድሽ ጥላ፣...

ይመስለኝ ነበረ ...
ከንፈሬን ያሸግሽው ፥ የሰው እንዳይነካ
አሁን ሳስተውለው ...
ጆሮዬን ጨምረሽ ፥ ወስደሽዋል ለካ!

ዘፈን እንዴት ላድምጥ? ...
ፍቅርን አስቀይሜ ፥ ቃል ኪዳኔን ጥዬ
አምባሰል ነሽ ባቲ ፥ ኧረግ አንቺ ሆዬ!

ክራር ጤና ነሳኝ ...
መሰንቆና ዋሽንት ፥  ከበሮ ድለቃ ...
እንዳውም ይቅርብኝ!  ኃጢኣት ነው ሙዚቃ።

ለደስታ ካልሆነኝ
                 ዝንቱ ከንቱ ውእቱ
ጥርቅም!  ....  ኤ--ታ--ባ--ቱ!!

ዋ! ሞኙ!
ዋ!  እኔ!
ያበጀሁኝ መስሎኝ ፥ ያቀናሁ በቤቴ
ባሳብ ለሚዋልል ፥ ርብሽብሽ ስሜቴ
ፀጥታን ላጣጥም ፥ እፎይ ከማለቴ፣ ...

ናፍቆትን ቀስቅሶ ፥ በንፋስ ጣት ንዝረት
በሽንቁር ሾላኪ ፥ ፉጨት - ርግብግቢት፣...
ጥሩሩን አጥልቆ
ስውር ሰይፉን ታጥቆ፣ ...
ዜመኛው ዝምታሽ ፥ ሊሸርፈኝ ይከንፋል
ትዝታ እንደ ዘፈን ፥ ተጫውቶ መች ያልፋል?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
12🔥3💔1
#ምትወደኝ_ከሆነ

ምትወደኝ ከሆነ ከምር ምትሳሳልኝ
ገፆቼን አንብበህ ትርጉሙን ፍታልኝ
የእውነት ካነበብከው ምንድነው የሚሉት
ጥቂት ከተፃፉት ገፆቼ ላይ ካሉት
...ብዬ ስጠይቅህ አንተ ምንም ያልከኝ
በአፌ ባልነግርህም በጣም አሳዘንከኝ
ታውቀኛለህ ብዬ አንተ ላይ ስመካ
አጠገቤ ሁነህ አታውቀኝም ለካ
በል ስማኝ የኔ አለም እንዲዚ ነው ሚሉት
በጉልህ ሚታዩት ከፊቴ ላይ ያሉት
እነዚ አይኖቼ አንዳች ነገር ሆነው
ፍቅርን ተርበው ፍቅርህን ተጠምተው
እንደዚ ሁኛለሁ እንደዚም ባይሉ
ዝምታዬ መሃል ቃላቶችም አሉ
ዳሩ ግን ሌላ ነው አንተ አይገባህም
ከኔ ጋ ቆምክ እንጂ ከኔ ጋ አይደለህም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
         ነጋሲ ግደይ
13👍9👏3
#ሱሰኛ_ነኝ

አዎ ሱሰኛ ነኝ ሱሴ እልፍ የበዛ፣
አንድ ሁለት ካላልኩ ፊቴ የማይወዛ፣
ቀኔ የማይበራ ሚጨልም ደንጋዛ፣
አይኔ ማይከፈት እንዲሁ በዋዛ፣

አጨሳለሁ ገና መቼ ተጨሰና፣
የፊደል ጭራሮ መች ተለኮሰና፣
የቃላት ቅርንጫፍ መች ተማገደና፣

በጭሱ ናውዤ በዜማው ሰክሬ፣
አልችልም ልላቀቅ ክፉኛ ታስሬ፣
አዎ ሱሰኛ ነኝ ውስጡ ተነክሬ፣
ድንገት ያጣው ጊዜ አልችልም ዳክሬ፣
ምርኩዝ አያነሳኝ ምቀር ተሰብሬ፣
አዎ ሱሴ በዝቷል ጠልቆ ከደም ስሬ፣

ቃል ከቃል ሲጋጠም በሚፈጥረው ግለት፣
ስቃጠል ኖራለሁ ካጣው ስለምሞት፣

የፊደል ስደራ የወግ አቀማመጥ፣
የቃሎቹ ጉልበት ሲጮሁ ብለው ፀጥ፣
ወኔ ቢስ ሲሰማው የሚያረገው ሸነጥ፣
የሀረግ ሹል ስለት የብዕር ረመጥ፣
ያቅበዘብዘኛል ብሎኝ አላስቀምጥ፣

አዎ ሱሰኛ ነኝ የቃላት ግጥምጥም፣
የቤት መቺዎቹ እኛ ያሉት ፍርጥም፣
ጊዜ ማይሽራቸው ስንቱን ቢሽሩትም፣
አዎ ሱሰኛ ነኝ እኔማ የግጥም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
14👍2
Channel photo removed
'' እኔ ምን አገባኝ ! ''  ~ የምንላት ሐረግ ፥
እርሱ ነው ሀገሬን ~ ያረዳት እንደ - በግ ፥
የሚል ግጥም ልፅፍ ~ ተነሳሁኝና ፥
ምናገባኝ ብዬ ~ ተዉኩት እንደገና ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
  ኑረዲን_ኢሳ
26🤣12👍6😁1
#አትምጭ_በህልሜ
  
ኸረ ምኑን ትቼ ምኑን ልንገርሽ፡
እንቅልፍ አላስተኛ ብሎኛል ፍቅርሽ፡፡
ጣራውን እያየሁ ከአልጋው ተጋድሜ፡
ሌት ሳልተኛ አድራለሁ ቀኑን ሙሉ ቁሜ፡፡
በሀሳብ ዋልሁና ቀኑን ስንገላታ፡
ተኝቼ በህልሜ አየሁሽ በማታ፡፡
ወይ ዛሬ ወይ ነገ አገኝሻለሁ ስል፡
ጥለሽብኝ ቀረሽ የህሌና ቁስል፡፡
በንፁሁ ልቤ በደማቁ ፅፌሽ፡
ሌሊቱን በህልሜ አደርሁኝ አቅፌሽ፡፡
እያሽለበለበኝ ከአልጋው ተጋድሜ፡
ስትፍነከነኪ አየሁሽ በህልሜ፡፡
ቀን አልበቃኝ ብሎ አንቺን መመልከቱ፡
ስጨነቅ አድራለሁ ሳይሽ በሌሊቱ፡፡
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
21👍1
#በሆድ_ጉርምርምታ

ስጠግብ ከጻፍኩት ስሜት አልባ ቅኝት
ቤት ካልመታ ስንኝ ትርጉም አልባ ስሜት
ሲርበኝ የጻፍኩት በዜማ ታጅቦ በሆድ ጉርምርምታ
ባልበላሁት ምግብ ባይኔ በሚዞረው የውብ ጠረን ሽታ
ይሻላል አስር እጅ ጠንካራ ነው ቃሉ ቅኔ ነው ትርጉሙ
ከውስጥ የመነጨ የስቃይ ደም እንባ ጥልቅ ነው ህመሙ
ስሜት ከማይሰጠው ጠግቤ ከጻፍኩት ከቃላት ጋጋታ
ከላይ ከላይ ስሜት የውሸት ፈገግታ እቃቃ ጨዋታ
እርቦኝ የፃፍኩት ትርጉም አለው ለኔ ጥልቅ ነው ስሜቱ
ከባህር የሰፋ ከየብስም የሚበልጥ ሰፊ ነው እውነቱ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
  ስንታየሁ ሀብታሙ
21🔥2👍1
#አፍቃሪ_ያሳጣሽ

ካለሽ ውበት በላይ አምረሽ ተኳኩለሽ
ከቤት ስትወጪ እንደ ፀሀይ ደመቀሽ

በምቴጂው መንገድ..
ከአንድ አንቺ በስተቀር ሰዎች አይኑሩበት
አንቺን የማይነካም ወጥመድ ይዙርበት።

ተወለጋገጂ ስተሄጅ በመንገዱ
ማንም አይመኝሽ ለወዳጅ ዘመዱ።

ያርግሽ ነገረኛ ከሰው አትስማሚ
ለሚመለከትሽ መሳይ ሁኝ ታማሚ።

ብቻ...
የኔ ሰሞነኛ የዘወትር ፀሎቴ
ይህ ነው አለሜ ውዳሴ ዳዊቴ።

ምክኒያቱም አለሜ ስስቴ ሁነሻል
በልቤ ማሳ ላይ ውብ ፍቅርን ዘርተሻል።

እናም..
በይ እስኪ እወቂ የልቤን ውስጥ እውነት
በፍቅርሽ ደክሜ እንዳጣሁኝ ገሉበት
አንቺን ለማግኘት ስል እንደገባሁ ስለት

አንቺን እያሰብኩም ከቤተ መቅደሱ
አሀዱ እንዳሉ መስቀል ይዘው ቄሱ።

ብቻ...
የዘወትር ፀሎቴ  ውዳሴ  ዳዊቴ
አፍቃሪ ያሳጣሽ የሚል ነው ስስቴ።

አዎ አለሜዋ የኔ ሁሉ ነገር
አፍቃሪ ያሳጣሽ ከአንድ እኔ በስተቀር።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
25😁14
#ለሰው_የሚታየው!

በአይናችን ቦይ መስመር የሚንዠቀዠቀው
የሚታየው እንባ ጎርፍ ሆኖ የሚወርደው
የብዙ አመት ህመም የስቃይ ምንጭ ነው
በልባችን ኩሬ በግድ ተገድቦ ታፍኖ የኖረው
በጉንጫችን ዳገት ቁልቁል መስመር ሰርቶ
በሐይል አስገድዶ ሁለት ቅንድብ ገፍቶ
የአንድ ቀን አይደለም ድንገት የሚመጣ
በጥቂት ሀዘን ቁልፍ ተከፍቶ የሚወጣ
የከራረመ ነው የዘለላ ድምር
ከልባችን ሳሎን ቀድሞ የሚቋጠር
ሲሞላ ግድቡ የሚወርደው ጥሶ
ከታቻምናው አምና ዘንድሮን ቀንሶ
ከገደብ ያለፈው የተራረፈው ነው
ቅጥሩን እየጣሰ ለሰው የሚታየው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
      ስንታየሁ ሀብታሙ
14👍7
#ቀን_ቀን_አትሳቂ

ቀን ቀን አትሳቂ የማታው ይበቃል
ፉጡር ሞኝ አይደለ
ፈገግታሽን ብሎ ከፊጣሪ ይርቃል
ይህ ሁሉ ከሚሆን
ሰሪ እየተናቀ ስሬት ከሚወደስ
ልክ ስለሆነ
ነገር እና ግብሩን አንዳንዴ መቀነስ
ጨረቃ ብቻዋን
ፅልመትን ለመግፈፍ አቅሟ ስላነሰ
ማታ ማታ ሳቂ
ፈገግታሽ ያድናት ሳቅ እየፀነሰ
እርግጥ
ልክ እንደቀን ሁሉ
ማታውም ማታ ነው በእሱ የተሰራ
ግን ደግሞ
የሰው ልጅ በሙሉ
የጠቆረን ሁሉ ሴጣን ነው እያለ ሰርክ ከተጣራ
ባይገናኝ እንኳን ነገር እና  ውሉ
ሰው ብሎ ከጠራሽ ሰዋሰው በሙሉ
ነጭን ነፁ አድርገሽ ሁኚ ልክ እደሰው
ጠቁሩን አሳንሶ ነጭ እንደቀደሰው

አይጭነቅሽ ከቶ
ደግሞ እንዳታስቢ
ያለሽበት ሀገር ይሄንን አይፈቅድም
አድዋ ለጥቁር ነው ለነጮች አይሰግድም
ምክንያቱም
ታሪክ ተረት ተረት ሆኖ ቢፀና እንኳን
ነጭ ሆኖ መድመቅ ነው በጥቁርነት ድንኳን
ከጠቆረ ሰማይ ፊቱ አለች ጨረቃ
ፅልመት ለመጋፈፍ አርፍዳ ምትነቃ
ደግሞም እንደውነታው ደግሞም እንደሀቁ
ጨላማ ሲኖር ነው ንጋት መታወቁ
የፅልመት አድማቂ የንጋት ምልክት
እስቲ ፈገግ በይ አብሪ እንደከዋክብት
እ...........ሰ.....ይ !
አሁን ደግ አደረግሽ
ብርሃንሽ ወጣ ፅልመት እየቸረሽ
እ...........ሰ.....ይ !
አሁን ገና አበጀሽ
ጥቅሩን ተንተርሰሽ ነጭ ነጩን ፈጀሽ
አየሽ
አሁን ተረዳሽኝ
ስቀሽ አነጋሽኝ
ስጣጣር ብውልም ለሞት ተሰይሜ
ፈገግ ያልሽ ለታ
ኖሪያለሁ እላለው መቃብር ላይ ቆሜ
እ ...............ሰ...................ይ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   በእውቀቱ ስዩም
12👏4👍3🔥3
#ተባብለን_ባይ_ባይ

ደህና ሁን ደህና ሁኚ ተባብለን ነበር
ያለቀ ሲመስለን የጀመርነው ፍቅር
አሁን ምን አመጣው የትዝታን ፈረስ
ከአንቺ ከእኔ እያለ ናፍቆት ሊያመላልስ
ሰው አላለያየን በፍቅራችን ገብቶ
ሰበቡ የእኛው ነው የገመድነው ላልቶ
አሁን ከረፈደ ከሌላ ተላምደን
ትዝታችን መጥቶ ምን ፍጠሩ ሚለን?
አንቺም የሌላ ነሽ እኔም የሌላ ሰው
ትዝታሽ ከእኔ ቤት ምን አመላለሰው
አርፎ መኖር እንጂ ችሎ እንደነገሩ
በክራሩ ቅኝት እያንጎራጎሩ!!!
እህል ውሃ እንዲህ ነው አገናኝቶ ነጣይ
ሳንጀምር ቋጨነው ተባብለን ባይ ባይ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
💔166😱4👍2👌2
#ነይ_ግጥም_እናንብብ

ውደጅኝ አልልም
ፍቅር እረቂቅ ነው…
ሚስጥሩ ውስብስብ፤
ይልቅ ጠጋ በይኝ !?
ክንዴን አንተርሼሽ…
ውብ ግጥም እናንብብ።

ታምሪያለሽ የኔ ዓ'ለም
ከ'ዓይኖችሽ ቅፅበት
ምትሀት ይዘንባል፤
ሳቅሽ ፏፏቴ ነው፣
እንደመላክ ቀለም 
ከውበት ይጠራል።

ነይ ግጥም እናንብብ
ነይ ውበት እንሳል
ነይ ዜማ እንቀምር፤
እንቆቅልሽ አይደል
ግዜ ይፈታዋል
የኔ'ና አንቺን ነገር

ድምፅሽ እረቂቅ ስልት
የቤትሆቨን ጣዕም
የሞዛርት ቅማሬ፤
ወደድኩሽ የኔ ዓለም
የፍቅርሽን ቅኔ
እንደአዲስ ተምሬ።

ውደጅኝ አልልም
የመውደድ ሚዛኑ
ስለሆነ  መውደድ፣
ነይ ግጥም እናንብብ?
ይቺን ምድር ለቀን፣
እኔና አንቺ እንበድ ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
17👍5🥰4🔥1
#አገር_በሚያልፍበት_ባዘቦት_መንገዱ

አገር በሚያልፍበት ፥ ባዘቦት ጎዳና
በሁሉም ሰው ፊት ላይ ፥ትካዜ ተስሎ
ሲመስል  ደመና
ማን ከማን ተሽሎ
ማን ማንን ሊያጽናና?
በዕንባ  ስፍር  እንጂ የምንለያየው
ክንብንቡን ገልጦ፥ ቀረብ ብሎ ላየው
ሁሉም ልቅሶ ላይ ነው ::
በየትኛው ዘመን  ፥ይፈርሳል ድንኳኑ
የምስራች መምጫው መቼ ይሆን ቀኑ?
ብየ ብጠይቅም
መልሱን ግን አላውቅም::
አገር በሚያልፍበት፥  ባዘቦት መንገዱ
ባስፋልት  በሐዲዱ
መርዶ እየዘለለ
ብስራት ግን ይድሀል
በዚህ ሁሉ መሀል
እኔን ስታስቢ
ፈገግታሽ ፤ ከናደው   
ፊትሽ አካባቢ
ያንዣበበውን ጉም
በሕይወት መኖሬ፥  አለው ትልቅ  ትርጉም::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
12
#ልንገርሽ_ጨረቃ

በገጣሚ ብዕር በስንኝ ቋጠሮ
በዜማ ቀማሪ በድምጽ እንጉርጉሮ
እየተሞላቀቅሽ በአፍቃሪ ደብዳቤ
በሰአሊ ቀለም በሸራ ላይ ድቤ
አሞጋሽ ሲበዛ በስምሽ ዘማሪ
ፀሀይ ልሁን አትበይ ጨረቃ ተይ ፍሪ
ደራሲ ነው እንጂ ብዕር አንጠፍጥፎ
በሰው ህሊና ላይ ያተመሽ አግዝፎ
ሰአሊው ነው እንጂ ውበትሽን አድምቆ
የሌለሽ ማንነት ከፀሀይ ላይ ሰርቆ
ገጣሚ ነው እንጂ በስንኝ ቋጠሮ
ዜመኛው በዋሽንት በድምጽ እንጉርጉሮ
አንቺን ያገዘፉሽ በሌለሽ ከፍታ
በምናብ አስውበው በፍቅረኞች ኩታ
የተራ ተራ ነሽ ልንገርሽ ጨረቃ
ፀሀይ ትበልጣለች እጅግ ብዙ ልቃ
በአሞጋሽ ግርግር በዘፋኝ እስክስታ
በጨለማ አድናቂ ሲሰጥሽ ከፍታ
ፀሀይ ነኝ አትበይ አቅምሽን እወቂ
በሰው ህሊና ላይ ገዝፈሽ አትድመቂ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
7👍5👏3
​በቀን ውስጥ ለምናባክነው ጊዜ ትርጉም የሚሰጥ፣ አእምሮን የሚያድስ እና የነገ ማንነታችንን የሚቀርጽ አንድ ምርጥ ቻናል ልጋብዛቹ

⭕️በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኟቸው፦

📜 የታዋቂ ሰዎች የሕይወት ጉዞ፦ ከውድቀት እስከ ስኬት ማማ ያደረሳቸው እውነተኛ ታሪኮች!

📚 ከመጽሐፍት ዓለም፦ የሺህ ገጽ መጽሐፍትን ጭማቂ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ!

🎭 Dark Psychology፦ የሰውን አእምሮ የማንበብ እና የማሳመን ጥበብ (ሚስጥራዊ ጥቆማዎች)!

📖 ቁልፍ ትምህርቶች፦ ለስኬትዎ አቋራጭ የሚሆኑ የጥበብ መንገዶች!

💥 አነቃቂ ጥቅሶች፦ ሞራልዎ ሲወድቅ ስንቅ የሚሆኑ ብርቱ ቃላት!

አልማዝን ለማግኘት መቆፈር ያስፈልጋል፤ ጥበብን ለማግኘት ግን "Join" ማለት ብቻ በቂ ነው! 😉

​አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇👇👇

🔗 https://t.me/BIOGRAPHY_TEACH
🔗 https://t.me/BIOGRAPHY_TEACH
🔗 https://t.me/BIOGRAPHY_TEACH

👍21
#ዋ!... ያቺ አድዋ

ዋ!...
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…
ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብጽዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና…
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ!... ዓድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው፣ በለው- በለው!
ዋ! … ዓድዋ …
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እደገና፡፡
… ዋ! … ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የዐለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…🇪🇹
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን
7🥰1😱1
#ይድረስ_ለናፈቅሽኝ

የናፈቅሽኝ ለታ
ሀሳቤ ሲምታታ
ስትናፍቂኝ ጊዜ
ሲጫነኝ ትካዜ
ያስታወስኩሽ ለታ ያሰላሰልኩሽ ለት
በተቃርኖ አለም ውስጥ መንፈሴ ሲዋትት
አንቺ ትዝ ያልሽኝ ቀን
በቁሜ ስባንን
ጠራራ ላይ ቁሜ ብርዱ ውስጤ ገብቶ
በጨረቃ ብርሀን ላበቴ በርክቶ
ጠጠር ላይ አንጥፌ ደልቶኝ እተኛለሁ
ፍራሽ ብርድልብሱ ሲያቃዠኝ አድራለሁ
ትውስ ያልሽኝ ጊዜ
በምድረ በዳው ላይ በሰው ተከብቤ
በሁካታው መሀል ሰላሜን ደርቤ
ሲርበኝ ጠጥቼ ሲጠማኝ በላለሁ
ቀን ተኝቼ ውየ ሌሊት ቁሜ አድራለሁ
ስትናፍቂኝ ጊዜ እንዲህ ያደርገኛል
በሌለው አለም ውስጥ ያለሁ ይመስለኛል
ወደሗላ እያየሁ ወደፊት መራመድ
ከሰው ተለይቼ ከአራዊት የምለምድ
በረሀ ወጥቼ በጫካው ውስጥ ኗሪ
የምትመጪበትን እልፍ ቀን ቆጣሪ
ትውስታየን ሁሉ ትውስታሽ አዝሎ
በመናፈቅ ብዛት አካሌ ጎስቁሎ
ደሞስ ስትናፍቂኝ ምናለ ያልሆንኩት
ያንቺን ቀን ስቆጥር የኔን ቀን ዘለልኩት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
21👍5
#Ads
🔨 ሀመር ፈጣን ዕጣ  🔨
"ዕድልዎን በሀመር ይቅረጹ!"

​የመጀመሪያው ዙር ፈጣን ዕጣ ተጀምሯል! አነስተኛ ብር ከፍለው ትልቅ ሽልማት የሚያሸንፉበት ዕድል እንዳያመልጥዎ።

🎁 የዚህ ዙር ሽልማት፦ [1ኛ ዕጣ 2,000 ብር, 2ኛ ዕጣ 600 ብር እና 3ኛ ዕጣ 200 ብር]

🎟️ የአንድ ዕጣ ዋጋ፦ [200 ብር ብቻ]

👥 አጠቃላይ የሰው ብዛት፦ [16 ሰው ብቻ]

እንዴት መሳተፍ ይቻላል?

1️⃣ ያልተያዘ ቁጥር በመምረጥ ግሩፕ ላይ የመረጡትን ቁጥር ይፃፉ።

2️⃣  [በንግድ ባንክ ወይም በቴሌ ብር ወይም በሲቢኢ ብር ወይም በMPESSA] ክፍያውን ይፈጽሙ።

3️⃣ የከፈሉበትን ደረሰኝ (Screenshot ወይም message) ግሩፕ ላይ ይላኩ።

4️⃣ የመረጡት የዕጣ ቁጥርዎ ላይ ምልክት መደረጉን ያረጋግጡ!

⚠️ ማሳሰቢያ፦ ዕጣው 1️⃣6️⃣ ቱም ሰው እንደተሟላ ወዲያውኑ በቪዲዮ ተደግፎ ይወጣል! ለአሸናፊው ሽልማቱ በ10 ደቂቃዎች ውስጥ ይላካል።

ፈጥነው ይቁረጡ፣ የዛሬው ዕድለኛ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! 🏃‍♂️💨

​[https://t.me/Hammer_Bingo]
7
#ልብ_ተከርችሞ!

ልብ ተቆልፎ ፣ ጥርስ እያገጠጠ፤
በውሸት ፈገግታ ፣ ሰው እያላገጠ፤
ፍቅር አልባ ጉዞ ፣ በከንቱ መዋደድ፤
በማስመሰል ዜማ ፣ የሗሊት መራመድ፤
አብሮ እያሉ አግጥጦ ፣ ሲለያዩ ሀሜት፤
ካለው ጋር መግተልተል ፣ የዘመኑ ቅኝት፤
ከልብ ባልመነጨ ፣ በውሸት ፈገግታ፤
እንዴው ከላይ ከላይ ፣ እየመቱ እስክስታ፤
ፍቅር መቼ ያምርና ፣ ልብ ተከርችሞ፤
በማስመሰል ጉንፋን ፣ አብዛኛው ሰው ታሞ፤
ጥርስማ ያገጣል ፣ የውሸት የውሸት፤
ከልብ ነው እንጂ ፣ የሚነሳው እውነት።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
16👍6💔2🥰1