ግጥም
4.79K subscribers
23 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ቢታነፅ_ቢወቀር!

እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!

ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ

ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!

ለካስ...

ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     በእውቀቱ ስዩም
16🥰6🔥1👏1
#ስጠብቅሽ_ልኑር!

ቀናቶች ቢረዝሙ ቢቆጠሩ አመታት
ግዜ ቢለያየን ቢያልፉብን ዘመናት
ከልብሽ ባልጠፋም ከትዉስታሽ ጓዳ
በስቃይ ታስሬ በናፍቆት ጎዳና
ህልሜም ባይሳካ የሆዴን ባላገኝ
በደስታየ ዘመን ባይተዋር ቢያረገኝ
ግዴለም ችላለሁ ሁሉን ነገር ችዬ
እጠብቅሻለሁ ልቤን አባብየ
የሀሳብ በረዶ ይጥለቅ በአናቴ
ይደንዝዝ አካሌ ይድከሙ ጉልበቴ
አንገናኛለን እያልኩ በተስፋ ልጠብቅ
እልፍ ግዜ ይለፍ ወዜ ሁሉ ይድቀቅ
ምን ያደርግልኛል ካንች ወድያ ንሮ
ፍቅርሽ ይበቃኛል የስንቅሽ ቋጠሮ
በትዝታሽ ዋሻ እራሴን ደብቄ
በምናቤ ስየ ፍቅርሽን ሰንቄ
እጠብቅሻለሁ በተሰጠኝ እድሜ
ባንች ናፍቆት ፍቅር ካልሞትኩኝ ታምሜ
አዎ...ስጠብቅሽ ልኑር ሳለሁ በህይዎቴ
ፍቅርም ባንች ይብቃኝ ይምከን ፍላጎቴ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
16👍1
#መጪውን_ማን_አውቆ?!

የኖረውን እንጂ ፣ የፊቱን ማን? አውቆ?
እድሜው ላይ፣ ጨመር አብዝቶ ተጨንቆ?
በአለፍነው ካልሆነ ፣ ህይወት የሚለካ፤
የመጪው ባለቤት ፣ እግዚአብሔር ነው ለካ፤
ትላንትን ተሻግሮ ፣ ዛሬን በእጁ ይዞ፤
የእርሱ ባልሆነ ነገ ፣ ያለቅጥ ተክዞ፤
የሚጨናነቀው ፣ ሰው በከንቱ እርቆ ፣
ያለፈውን እንጂ ፤ መጪውን ማን አውቆ?
እንኳንስ ዓመታት ፣ አልፎ ለመገመት ፤
የፈት ለፊት ነገ ፣ የእኛ አይደለም ህይወት ፤
እናም ልቤ አስተውል ፣ በዛሬ ላይ ትጋ፤
ከትላንት ተምረህ ፣ በአምላክ ሀሳብ እርጋ፤
ነገማ ማን አውቆ ፣ መድረሻውን ቆጥሮ፤
ከአምላኩ በስተቀር ፣ ዛሬውን ተሻግሮ ?
እንኳን ዓመታቱን ፣ እሩቅ! ቀድሞ ማየት ፤
በእግዚአብሔር እጅ ነው ፣ የዛሬው ሰአታት!
በከንቱ መጨነቅ ፣ ልባችን ታውሮ ፤
ዛሬያችን ከነፈ ፣ ትላንት ሆኖ በሮ!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
14👍2
#አድገናል ¡

የዘንድሮ ኑሮ ውሉም አልተያዘኝ፤
እንዴት እንዳደግነ መለኪያው አልገባኝ፤

ብቻ ግን አድገናል፤
በሁለት ዲጅት ወደ ላይ መጥቀናል¡፤

እቤታችን ድረስ ትቦ ተዘርግቷል፤
መብራት ገብቶልናል፤
ሲምም ተሰጦናል፤

ግና ውሀ የለም አንፖሉም አልበራ፤
ባዶ "ሲም" ነው እንጅ "ኔትወርኩም" አልሰራ፤
ብቻ ግን አድገናል፤
በሁለት "ዲጅት" ወደላይ መጥቀናል፤
አፍ ቀላጤ ፈርተን ሳናምነው አምነናል፤

ይህ ነው እድገታችን?፤
በሁለት ዲጅት ላይ ላይ መውጣታችን?፤

እኛም እንጮሀለን፤
እናስተጋባለን፤
ሀሰት እየሰማን አሜን እንላለን፤

እኔን እንደገባኝ....
ወደላይ ወደላይ ወደላይ መለፈፍ፤
ፍሬ ማያፈራው አበባው እስኪረግፍ፤
መና ካምላካችን ወድቆ እስኪዘረገፍ፤
ዝም አለማለት ነው መጮህ ነው ወደላይ፤
መብራቱ፣ ኔትወርኩ ውሃው የሞላላት ኢትዬጵያን እስክናይ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍127
#ተመልሼ_አልመጣም

ከወንጌል ቃል ሁሉ እግዜር ካስተማረው
ነብስያዬን ገዝቶ ቀልቤን የማረከው
ከልቡ የሆነ ይድናል የሚለው !!

ምክንያቱም አለሜ ምክንያቱም ህመሜ
የእውነትን ካልኖርኩ እኔ አልድንም ፆሜ
ፀሎትም አይሰምር አይፈይድም ስግደት
ሰደቃም አያርግ ይስሙላ ካለበት

እናልሽ አለሜ
ከወንጌል ቃል ሁሉ እግዜር ካስተማረው
ነብስያዬን ገዝቶ ቀልቤን የማረከው
ከልቡ የሆነ ይድናል የሚለው!!!

ስለዚህ መሻትሽ ከልብሽ ከሆነ
በፍቅራችን ቅጠል አንቺም ትድኛለሽ የኔም ነብስ ዳነ!!
ግና ነብስያዬን ፍፁም ካልወደድሻት
ውዴ ቀረሽብኝ አንቺም ቀረሽባት!

ደግሞ ካንቺ  እርቄ ከሸሸሁኝ በጣም
ውዴ ካለሽበት ተመልሼ  አልመጣም።
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ዳዊት ጥዑማይ
6🥰4👍2
ያለቀኔ አፍቅሬሽ፥ ገፍተሽኝ ሄደሻል፣
አቻሽን ፍለጋ፥ ብዙ ተጉዘሻል፤
መቼም አይሰምርልሽ፥ልብ ሰብረሽ ሄደሽ፣
ምንጊዜ ቢረዝም፥ አይቀር መመለስሽ፣
ብዬሽ እንደነበር፥ ቆየሁ ስጠብቅሽ።
ባ'ይኔ ላይ ተስለሽ፥ ዓመታት አልፈዋል፣
በልቤ እንደታተምሽ፥ ልጅነት ኰብልሏል።
ባልተሳካው መሻት፥ በዛለው መንፈስሽ፣
ዓይንሽን ስትገልጪ፥ እርቃን ቀርታ ነፍስሽ፤
ክፍቱን እንደተውሽው፥ ቤቴን አግኝተሻል፣
ስጠብቅሽ ነበር፥ ለ'ኔ ግን ረፍዷል።
መምጫ መንገድሽን ሲያይ፥ ሲባጅ የከረመው፣
በሰለለ ተስፋ፥ ታስሮልሽ የኖረው፤
ማፍቀሩን ሳይቀንስ፥ አንቺን በጠበቀ፣
ናፍቆትሽ ያሳሳው፥ የኔ ገላ አለቀ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍91
#መንደር_ላይ_አትከክ!!!

አንተ ብቻ ጽና ፣ በሀገር ውሃ ልክ፤
ወርደህ በዝቅታ፣ መንደር ላይ አትከክ!
በሰውኛ ሚዛን ፣ በእውነት ስሌት ትጋ!
ሀገር ከማይጠቅም ፣ በደቦ አትንጋጋ!
ሰፋ! ብለህ ብረር ! በከፍታ! ሀሳብ ፤
በግፊያው መሀከል ገብተህ አትጣበብ!
በዛሬ ግርግር ፣ ነገን አታበላሽ ፤
በሰውኛ ፈረስ ፣ ሁን ለብቻ ገስጋሽ!
ትውልዱ ሲነቃ ፣ በእውነት ተቀስቅሶ፤
መጠየቅ ሲጀምር ፣ ታሪክን አጣቅሶ፤
ያኔ! አንተ ኮራ በል ፣ ሌላው ሲሸማቀቅ፤
በሀገርህ ምድር ፣ ሰንደቅ ሆነህ ድመቅ!
ከፍ! በል! ለነገ ፣ በአዲስ ህብረ ቅኔ!
ይኸን ነው ዛሬ ላይ ፣ የምመክርህ እኔ!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
12👏2🔥1
#በቃልሽ_ታስሬ

የልቤ ላይ ንግስት አንቺ ውቧ ፍቅሬ
ቀናትን በመቁጠር ወራትን ደምሬ
ከጎንሽ ባልሆንም ከአንቺው ጋር አብሬ
በፍቅርሽ ሰንሰለት በፅናት ታስሬ
አሜን ይሁን ብዬ ቃልሽን አክብሬ
ለልቤ ትርታ ለደም ዝውውሬ
ለመንፈሴ እርካታ ብታመም ዶክተሬ
ደስታን ለማጣጣም ፍቅርሽን ዘምሬ
እስትንፋሴ ነብሴ ሆነሽ ለእኔ ጤና
ለመኖሬ ትርጉም የሂወቴ ቃና
አዛኝ እንደ ሄዋን ሩህሩህ ነሽና
አለም አስር ትሙላ ከቤቴ ግቢና
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
21
#ምኞትሽ_ላይ_በርቺ!

አንፖልን ለማብራት ይቃጣሉ ጣቶች
ጨለማ ም ነበረ
ፋኖስ የሚያደምቁ ... ባይኖሩ ለኳሾች ።
እመኚኝ እታለም!
በምታይው ዓለም.. .
አምፖልም ፋኖስም ድምቀቶች አይደሉም
ብርሀን ለማፍለቅ እንደሚገለጥ ህልም
ፈፅሞ አይፈኩም!
መፍካት በመሻት ነው  በምኞት ነው መንቃት
ጨለማን ለመስበር ...
ከፋኖሱ ቀድመሽ... ልብሽን ነው ማብራት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ሚካኤል አስጨናቂ
11🥰3👏3👎1🔥1
#የእብደቴ_መነሻ

       ፀሐይን አግብቼ ጨረቃን ስወሽም፣
       "ይኼ ሰው ምን ነካው?" ትያለሽ ሁልሽም፤
                  በተስፈኛ ምድር......
       ደራሲ ገጣሚ አድርጎ ሲፈጥረኝ፣
       በዚያች ዕለት ነበር እብደት የጀመረኝ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👏2116🥰3
https://rdr.one/9NicSbj

ቤተሰብ አንድ ነገር ላስቸግራችሁ እኔን ለማገዝ ፍቃደኛ የሆናችሁ 700 ሰዎች ይኸን የቴሌግራም ቻናል join እያደረጋችሁ screenshot ላኩልኝ የ5 ቀን ቻሌንጅ ሰተውኝ ነው ስለትብብራችሁ ከወዲሁ ከልብ አመሰግናለሁ 🙏
8
#የመሸበት_የለም

የመሸ ቢመስለኝ የጨለመ በእኔ
ነገ ጤዛ ሆኖ ይረግፋል ሀዘኔ
በእኔ የምትሰራው ገና ሆኖ ግዜው
አንተ እኮ ጌታዬ መምጫህ በድንገት ነው
የተውከኝ ቢመስለኝ የረሳኸኝ ዛሬ
ነገም ያንተ ቀን ነው ይመለሳል ክብሬ
እጠብቅሃለሁ በተስፋ ቃል ኪዳን
አንተን ተስፋ አድርጎ የመሸበት የለም
ወድቆ ቀረው ሲሉ አንሳኝና ልቁም
አምላክ ባንተ ስራ ጠላትም ይደመም።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
15👍2
#ሳብድ_ለምን_መጣሽ?

ከሄድሽ ጀምሮ •••
ትዝታና ናፍቆት አቅም እያሳጡ
ሲጥሉ ሲያነሱኝ ወራቶች ሲሮጡ
በሞት መኖር መሀል ጎኔ ተሰንቅሮ
በምኞት  በማየት  ስለነገ  አሻግሮ
በግድ ስላለፍኩት ወራት አመታቱ
ብታውቂም አልመጣሽ ተይዤ በብርቱ
           እሺ ይሄም ይቅር
ዕልፍ የሆኑ ወቅቶች በተስፋ ማለሙ
የመጠበቅ ደዌ ጠንቶብኝ ህመሙ
እድሜን ያህል ነገር ስላንቺ መስጠቴ
የዘመኔን ክፋይ ላንቺው መሰዋቴ
ስሜቱ እየገባሽ ከእንቅልፍ መኳረፍ
ገላን ብቻ አንጋሎ በሀሳብ መንሳፈፍ
እንደው እንዴት ሆነ ብለሽ ሳጠይቂ
ዕልፍ አሳልፈሻል ለብቻሽ ስትስቂ
                   
ከአይኖቼ በመፍለቅ ትራሴን ያራሱት
ዘለላ እምባዎቼ ስላንቺ ያነቡት
በዋዛ ተቆጥረው ሁነውብሽ ተራ
እንዲያ በመሆኔም ልብሽም ሳይራራ
            ቀርተሻል በዘበት
እግርሽ አረገጠም እኔም ካለሁበት
                   
የሳቅ ደስታ ትርጉም እስኪጠፋኝ ድረስ
ሌተቀን በማዘን እድሌንም ስወቅስ
ትመጫለሽ በሚል ሰርክ በመጠበቅ
ደጁን እያማተርኩ ሳጣሽም ስሳቀቅ
ብስቁልቁል ብዬ ስላዩ ባክኜ
ባላፊው አግዳሚው በሰው ተኮንኜ
እኔው በታመምኩት እኔው ብንገላታ
አላስቀምጥ ብሎኝ የሰው አሉባልታ
ማንም ከማያቀኝ ከአዲስ ቦታ መንደር
ከሰው ተገልዬ ሁኜ እንደ ባይተዋር
በጣር ስለኖርኩት ስላለፍኩት ስቃይ
እያወቀሽ ሁሉንም መጥተሽ አይኔን ሳታይ
እኔን ለኔው ትተሽ ስላንቺው ኑረሻል
መቼም አትክጂውም ሁሉን ልብሽ ያውቃል
                 ታዲያ •
                              •
                                ለምን
                                •
                              •
                       ይሆን ?
             ዛሬ ሁሉ ረፍዶ
ጎኔ እንደናፈቀሽ ግዜው ሄዶ ሄዶ
ከለየልኝ   ዃላ  ጨርቄ   ተቀዳዶ
ሰዎች ሲያወሩልሽ የማበዴን መርዶ
ልታዪኝ  መምጣትሽ ካለሽበት ማዶ
አዝነሽ ነው ፀፅቶሽ ፣ ወይስ ደስ ብሎሽ ?
ንገሪኝ  እውነቱን ሳብድ ለምን  መጣሽ ?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
13💔11👍7
#አርፎ_አይቀመጥም

ሰው መንገደኛ ነው ተጓዥ በየዕለቱ
ባአቀበት ቁልቁለት የተሰራ ቤቱ
ሲወጣ ሲወርድ ይነጋል ለሊቱ
ካአፈር የተገኘ ሸክላ  አከላቱ
መቸ ያስችለዋል ልተወው ቢልኳ
ደርሶ እየተናደ የካበው ሲንኳኳ
መስመሯን ስቀይር ህይወት ለታሪኳ
ልቡ ባህር ገብቶ ሲቀዘፍ በታንኳ
ግር ይለዋልና እስኪለምደው ድረስ
ሲቀኘው ይውላል ትዝታን ሲደርስ
ሽው ሽው እያለ  እንደቀኑ ንፋስ
ወስዶ እስኪመልሰው  የሀሰቡ ፈርስ
አርፎ አይቀመጥም ከመሬቱ ጎኑ
እስኪሸልብ ድርስ እስካለ በውኑ
ኮሽ ባለቁጥር ይገለጣል አይኑ
ትንፍሹ እንድሰማ እንደሸት ጠረኑ!!
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ሊድያ ማሞ
👍157
#እቴዋ_ልምከርሽ !

ማሬ ማሬ እያለ የሚነጠፍልሽ፣
እኔን እኔን ብሎ ድንግጥ የሚልልሽ፣
ከአንቺ ሌላ እያለ በስምሽ የሚምል፣
ስርስርሽን በዝቶ ሲከብሽ የሚውል፣
ማርሽን ፍለጋ መሆኑን አትርሽ፣
በጥርስሽ እየሳቅሽ ልብሽን አሽሽ!
እውነተኛ አፍቃሪ ላንች የተፈጠረ፣
አይቀርም መምጣቱ የተመረመረ፣
እቴዋ ልምከርሽ በስንኝ ቋጠሮ
መኖርን ከፈለግሽ ሴትነትሽ ከብሮ
ውበትሽን አርግፎ ልብሽን ለሚሰብር፣
አትስጭ ቸኩለሽ ክብርሽ ነው ብር አንባር !
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
26👍11🥰2
#ጆሮዬን_መልሽ!

ይመስለኝ ነበረ ...
ልቤን የሰወርሽው ፥ እንዳያስብ ሌላ
ዓይኔን የጋረድሽው ፥ በመውደድሽ ጥላ፣...

ይመስለኝ ነበረ ...
ከንፈሬን ያሸግሽው ፥ የሰው እንዳይነካ
አሁን ሳስተውለው ...
ጆሮዬን ጨምረሽ ፥ ወስደሽዋል ለካ!

ዘፈን እንዴት ላድምጥ? ...
ፍቅርን አስቀይሜ ፥ ቃል ኪዳኔን ጥዬ
አምባሰል ነሽ ባቲ ፥ ኧረግ አንቺ ሆዬ!

ክራር ጤና ነሳኝ ...
መሰንቆና ዋሽንት ፥  ከበሮ ድለቃ ...
እንዳውም ይቅርብኝ!  ኃጢኣት ነው ሙዚቃ።

ለደስታ ካልሆነኝ
                 ዝንቱ ከንቱ ውእቱ
ጥርቅም!  ....  ኤ--ታ--ባ--ቱ!!

ዋ! ሞኙ!
ዋ!  እኔ!
ያበጀሁኝ መስሎኝ ፥ ያቀናሁ በቤቴ
ባሳብ ለሚዋልል ፥ ርብሽብሽ ስሜቴ
ፀጥታን ላጣጥም ፥ እፎይ ከማለቴ፣ ...

ናፍቆትን ቀስቅሶ ፥ በንፋስ ጣት ንዝረት
በሽንቁር ሾላኪ ፥ ፉጨት - ርግብግቢት፣...
ጥሩሩን አጥልቆ
ስውር ሰይፉን ታጥቆ፣ ...
ዜመኛው ዝምታሽ ፥ ሊሸርፈኝ ይከንፋል
ትዝታ እንደ ዘፈን ፥ ተጫውቶ መች ያልፋል?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
12🔥3💔1
#ምትወደኝ_ከሆነ

ምትወደኝ ከሆነ ከምር ምትሳሳልኝ
ገፆቼን አንብበህ ትርጉሙን ፍታልኝ
የእውነት ካነበብከው ምንድነው የሚሉት
ጥቂት ከተፃፉት ገፆቼ ላይ ካሉት
...ብዬ ስጠይቅህ አንተ ምንም ያልከኝ
በአፌ ባልነግርህም በጣም አሳዘንከኝ
ታውቀኛለህ ብዬ አንተ ላይ ስመካ
አጠገቤ ሁነህ አታውቀኝም ለካ
በል ስማኝ የኔ አለም እንዲዚ ነው ሚሉት
በጉልህ ሚታዩት ከፊቴ ላይ ያሉት
እነዚ አይኖቼ አንዳች ነገር ሆነው
ፍቅርን ተርበው ፍቅርህን ተጠምተው
እንደዚ ሁኛለሁ እንደዚም ባይሉ
ዝምታዬ መሃል ቃላቶችም አሉ
ዳሩ ግን ሌላ ነው አንተ አይገባህም
ከኔ ጋ ቆምክ እንጂ ከኔ ጋ አይደለህም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
         ነጋሲ ግደይ
13👍9👏3
#ሱሰኛ_ነኝ

አዎ ሱሰኛ ነኝ ሱሴ እልፍ የበዛ፣
አንድ ሁለት ካላልኩ ፊቴ የማይወዛ፣
ቀኔ የማይበራ ሚጨልም ደንጋዛ፣
አይኔ ማይከፈት እንዲሁ በዋዛ፣

አጨሳለሁ ገና መቼ ተጨሰና፣
የፊደል ጭራሮ መች ተለኮሰና፣
የቃላት ቅርንጫፍ መች ተማገደና፣

በጭሱ ናውዤ በዜማው ሰክሬ፣
አልችልም ልላቀቅ ክፉኛ ታስሬ፣
አዎ ሱሰኛ ነኝ ውስጡ ተነክሬ፣
ድንገት ያጣው ጊዜ አልችልም ዳክሬ፣
ምርኩዝ አያነሳኝ ምቀር ተሰብሬ፣
አዎ ሱሴ በዝቷል ጠልቆ ከደም ስሬ፣

ቃል ከቃል ሲጋጠም በሚፈጥረው ግለት፣
ስቃጠል ኖራለሁ ካጣው ስለምሞት፣

የፊደል ስደራ የወግ አቀማመጥ፣
የቃሎቹ ጉልበት ሲጮሁ ብለው ፀጥ፣
ወኔ ቢስ ሲሰማው የሚያረገው ሸነጥ፣
የሀረግ ሹል ስለት የብዕር ረመጥ፣
ያቅበዘብዘኛል ብሎኝ አላስቀምጥ፣

አዎ ሱሰኛ ነኝ የቃላት ግጥምጥም፣
የቤት መቺዎቹ እኛ ያሉት ፍርጥም፣
ጊዜ ማይሽራቸው ስንቱን ቢሽሩትም፣
አዎ ሱሰኛ ነኝ እኔማ የግጥም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
14👍2
Channel photo removed
'' እኔ ምን አገባኝ ! ''  ~ የምንላት ሐረግ ፥
እርሱ ነው ሀገሬን ~ ያረዳት እንደ - በግ ፥
የሚል ግጥም ልፅፍ ~ ተነሳሁኝና ፥
ምናገባኝ ብዬ ~ ተዉኩት እንደገና ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
  ኑረዲን_ኢሳ
26🤣12👍6😁1