#ማንነት_ሲምታታ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤9
#ሂጅ
አታመንች ውዴ ሂጅ ፈቅጃለሁ፤
ያለፈን እያሰብኩ ተክዠ እኖራለሁ፤
ያሳብቅብሻል አስሮሽ ነው ውለታ፤
ፍቅርሽ ካለቀብሽ አያዝሽ ይሉኝታ፤
ሂጅ ግድ የለሽም ልብሽ አያመንታ፤
ኋላ ግን አካሌ......
የሄድሽበት መንገድ እሳት ሆኖ ቢፈጅሽ፤
ፍቅር ተገልብጦ እንቅልፍን ቢነሳሽ፤
አሁን እንደሸሸሽ ቢመለስ ህሊናሽ፤
የት ነው ያለ እንዳትይ ሳጣሽ አብጃለሁ፤ አይኔ ሌላ አላይ ሲል ገደል ገብቻለሁ፤
ፈተናው ሲበዛ እየተንገራደድኩ ወድቄልሻለሁ፤
እናም አትፈልጊኝ በደካሞች መንደር፤
ወደ ላይ ሂጃለሁ አስጠልቶኝ ምድር፤
እዛው እንገናኝ እንዳኝ በፍትህ እንዳኝ በክብር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አታመንች ውዴ ሂጅ ፈቅጃለሁ፤
ያለፈን እያሰብኩ ተክዠ እኖራለሁ፤
ያሳብቅብሻል አስሮሽ ነው ውለታ፤
ፍቅርሽ ካለቀብሽ አያዝሽ ይሉኝታ፤
ሂጅ ግድ የለሽም ልብሽ አያመንታ፤
ኋላ ግን አካሌ......
የሄድሽበት መንገድ እሳት ሆኖ ቢፈጅሽ፤
ፍቅር ተገልብጦ እንቅልፍን ቢነሳሽ፤
አሁን እንደሸሸሽ ቢመለስ ህሊናሽ፤
የት ነው ያለ እንዳትይ ሳጣሽ አብጃለሁ፤ አይኔ ሌላ አላይ ሲል ገደል ገብቻለሁ፤
ፈተናው ሲበዛ እየተንገራደድኩ ወድቄልሻለሁ፤
እናም አትፈልጊኝ በደካሞች መንደር፤
ወደ ላይ ሂጃለሁ አስጠልቶኝ ምድር፤
እዛው እንገናኝ እንዳኝ በፍትህ እንዳኝ በክብር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤12😢4
#እንደምትወዳት_ንገራት
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::
ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::
አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤
ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::
ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::
አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤
ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤11👍5
ህወትን ስረግም በደሏን ስቆጥር
ማማረሬ በዝቶ ስቃዬን ሳበጥር
ሁሌ ጠዋት ማታ ስተኛም ስነሳ
ፊቴ እንደጠቆረ ውስጤም እንደሳሳ።
ባለማስተዋሌ ቀኙ ቢሆን ግራ!
መውደቅ መነሳቴ በሰዎች ቢወራ
ራሴው ከራሴው ስሟገት ከርሜ
ጭንቄ ሲበረታ ሲጠና ህመሜ
ከትዝታ መረብ መውጫ መንገድ ሳጣ
አንዱን ተወጣሁ ስል ሌላኛው ሲመጣ.......
ለጊዜውም ቢሆን ህይወት ብርቱ ሰልፍ ሆና
ልጨብጣት ስጥር ብትመስልም ደመና
ሁሉን ስጋፈጠው በእምነት!ውስጥ ሆኜ
ሁሉን ቻዩን አምላክ ጌታዬን አምኜ
ምን ቢበረታ እንኳን የምድር ፈተና
ለማለፍ ችያለሁ በአንድዬ ስፅናና!
የኃላ ኃላ ግን ሲገባኝ ሚስጥሩ
መኖሬን ወደድኩት
ለካስ...
ሀዘን እና ጭንቄ ሀሴቴን የማግኛ ድልድዮች ነበሩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ማማረሬ በዝቶ ስቃዬን ሳበጥር
ሁሌ ጠዋት ማታ ስተኛም ስነሳ
ፊቴ እንደጠቆረ ውስጤም እንደሳሳ።
ባለማስተዋሌ ቀኙ ቢሆን ግራ!
መውደቅ መነሳቴ በሰዎች ቢወራ
ራሴው ከራሴው ስሟገት ከርሜ
ጭንቄ ሲበረታ ሲጠና ህመሜ
ከትዝታ መረብ መውጫ መንገድ ሳጣ
አንዱን ተወጣሁ ስል ሌላኛው ሲመጣ.......
ለጊዜውም ቢሆን ህይወት ብርቱ ሰልፍ ሆና
ልጨብጣት ስጥር ብትመስልም ደመና
ሁሉን ስጋፈጠው በእምነት!ውስጥ ሆኜ
ሁሉን ቻዩን አምላክ ጌታዬን አምኜ
ምን ቢበረታ እንኳን የምድር ፈተና
ለማለፍ ችያለሁ በአንድዬ ስፅናና!
የኃላ ኃላ ግን ሲገባኝ ሚስጥሩ
መኖሬን ወደድኩት
ለካስ...
ሀዘን እና ጭንቄ ሀሴቴን የማግኛ ድልድዮች ነበሩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤13👍3🔥2
#የአምላክ_ስጋን_ትቶ!
በኮንትራት ዓለም በሞት ለሚገታ
ይህ ሁሉ ግርግር ይህ ሁሉ ግንባታ
የሰማዩን ትቶ ሰው ለምድር ሲያዋጣ
ስጋችን ደልቦ ነፍሳችን ዋጋ አጣ!!!
በስብሶ ለሚቀር ስጋውን አፍቅሮ
የግፍ ማስፈፀሚያ ገንዝብን አክብሮ
መጠራቱ ላይቀር በተራ በተራ
ከምድሩ ቀንሶ ለሰማይ ሳይሰራ
ከማር የሚጣፍጥ የአምላክ ስጋን ትቶ
እሬትን ይመርጣል ዘወትር ሀሜት በልቶ
ነፍሱን ችላ ብሎ ለስጋ እያዳላ
በድንገት ይጠራል ያለውን ሳይበላ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
በኮንትራት ዓለም በሞት ለሚገታ
ይህ ሁሉ ግርግር ይህ ሁሉ ግንባታ
የሰማዩን ትቶ ሰው ለምድር ሲያዋጣ
ስጋችን ደልቦ ነፍሳችን ዋጋ አጣ!!!
በስብሶ ለሚቀር ስጋውን አፍቅሮ
የግፍ ማስፈፀሚያ ገንዝብን አክብሮ
መጠራቱ ላይቀር በተራ በተራ
ከምድሩ ቀንሶ ለሰማይ ሳይሰራ
ከማር የሚጣፍጥ የአምላክ ስጋን ትቶ
እሬትን ይመርጣል ዘወትር ሀሜት በልቶ
ነፍሱን ችላ ብሎ ለስጋ እያዳላ
በድንገት ይጠራል ያለውን ሳይበላ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤20🔥4
#አልተውሽም
የልጅነት ፍቅሬ
የተስፋዬ ፍሬ
የእድሜ ልክ ማገሬ
አልተውሽም ፍቅሬ
ከሜዳ ላይ ጥዬሽ
እንዲበላሽ አውሬ
አላደርግም ማሬ
አንቺ ማለት ለኔ..............
የልጅነት ውበት
የድካሜ ብርታት
የናፍቆቴ ጥማት
.......ባለቤቴ እኮ ነሽ........
አልተውሽም ፍቅሬ
አንቺን ይዤ ስሄድ...........
ተራራው ሜዳ ነው
ፀሀዩ ብርታት ነው
እርጅናው ምርኩዝ ነው
አንቺን ከተውኩ ግን.......
ሜዳውም ይሆናል ተራራ
እኔም እደክማለው በፀሀይ ጠራራ
እርጅናውም ቢሆን ሬት ነው መራራ
አልተውሽም ፍቅሬ.........
የጥንቱ ቃላችን ላልተውሽ ላተይኝ
የተማማልንበት መቼ ተዘነጋኝ
ልክ እጅሽን ስይዝ..........
ብርሀን ይታየኛል
ጉልበት ይኖረኛል
ማርጀቴ ይጠፋኛል
....እናም አልተውሽም.......
ገላችን ቢያረጅም
ፍቅር አያረጅም
አንቺም እንዳተይኝ
እኔም አልተውሽም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የልጅነት ፍቅሬ
የተስፋዬ ፍሬ
የእድሜ ልክ ማገሬ
አልተውሽም ፍቅሬ
ከሜዳ ላይ ጥዬሽ
እንዲበላሽ አውሬ
አላደርግም ማሬ
አንቺ ማለት ለኔ..............
የልጅነት ውበት
የድካሜ ብርታት
የናፍቆቴ ጥማት
.......ባለቤቴ እኮ ነሽ........
አልተውሽም ፍቅሬ
አንቺን ይዤ ስሄድ...........
ተራራው ሜዳ ነው
ፀሀዩ ብርታት ነው
እርጅናው ምርኩዝ ነው
አንቺን ከተውኩ ግን.......
ሜዳውም ይሆናል ተራራ
እኔም እደክማለው በፀሀይ ጠራራ
እርጅናውም ቢሆን ሬት ነው መራራ
አልተውሽም ፍቅሬ.........
የጥንቱ ቃላችን ላልተውሽ ላተይኝ
የተማማልንበት መቼ ተዘነጋኝ
ልክ እጅሽን ስይዝ..........
ብርሀን ይታየኛል
ጉልበት ይኖረኛል
ማርጀቴ ይጠፋኛል
....እናም አልተውሽም.......
ገላችን ቢያረጅም
ፍቅር አያረጅም
አንቺም እንዳተይኝ
እኔም አልተውሽም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤18🔥1
"#አንተ_ብቻ_ሙት"
የሚያኗኑር እንጂ የሌለው ዘንድሮ ፤
ቀባሪማ ሞልቷል በነፍስ ይማር ንፍሮ ፤
ብቻ አንተ ሙት እንጂ አታጣም ቀባሪ ፤
ሞልቷል አፈር መላሽ እልፍ አስተባባሪ ፤
ስትኖር ፊት አክብዶ ስትሞት ደረት ደቂ ፤
አንተን አያሳስብህ ለቅሶህን አድማቂ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
የሚያኗኑር እንጂ የሌለው ዘንድሮ ፤
ቀባሪማ ሞልቷል በነፍስ ይማር ንፍሮ ፤
ብቻ አንተ ሙት እንጂ አታጣም ቀባሪ ፤
ሞልቷል አፈር መላሽ እልፍ አስተባባሪ ፤
ስትኖር ፊት አክብዶ ስትሞት ደረት ደቂ ፤
አንተን አያሳስብህ ለቅሶህን አድማቂ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤13👍10
#የዕንቁዎች_ሰሌዳ
ከተፃፈው ግጥም ከስንኞች ሐረግ
ከሆሄያት መንደር ከተረት የሚሰርግ
ፊደላት ላይ ነግሶ የኔ ልብ አንበሳ
ውበቷን ሊናገር ስለሷ ሊያወሳ
ቃላትን መረጠ ቅኝትን አገሳ
ተውኔቶችን ሊፅፍ ብዕሩን አነሳ
ቀጠለ እንዲህ ሲል የፍቅሩን አበሳ
አይኗ ክብልል የሚል በቀይ የተሳለች
መልከ ፀዳል ብሩህ ግርማን የተመላች
ጉንጯ ብር ሐመልማል ላያት ያስገረመች
ከንፈሯ መንደሪን
ጉንጯ እንደ ብርትኳን
እያልኩ የሰየምኳት እንቡጥ ፅጌረዳ
ያቺ ድንቅ ፍጥረት የዕንቊዎች ሰሌዳ
ምን ልበል ስለሷ ሆናብኝ እንግዳ
ወርቅና አልማዝ ሆና ለስሜ ለክብሬ
ጠልቃ የጠለቀች እንደ ውቅያኖስ የፍቅር ባህሬ
ገፀ ለምለም ሰናይ ጥዑም ወይነ ፍሬ
ገልጬ አልጨርሳት አላብዛ ፍካሬ
አንቺን አልጨርስሽ ቃላትን ደርድሬ
ባበቃ ይሻላል ይህን ተናግሬ
የፃፍኩት ውዳሴ ለውስጥሽ ባይጥሙሽ
ትርጉም የሌላቸው ሆሄ ቢበዙብሽ
የደረስኩት ድርሰት ውሸት እንዳይመስልሽ
ግጥሜ ቢያወድስሽ ልቤ ቢያዜምልሽ
ቃላት አጥሮኝ እንጂ በጣም ነው ምወድሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ከተፃፈው ግጥም ከስንኞች ሐረግ
ከሆሄያት መንደር ከተረት የሚሰርግ
ፊደላት ላይ ነግሶ የኔ ልብ አንበሳ
ውበቷን ሊናገር ስለሷ ሊያወሳ
ቃላትን መረጠ ቅኝትን አገሳ
ተውኔቶችን ሊፅፍ ብዕሩን አነሳ
ቀጠለ እንዲህ ሲል የፍቅሩን አበሳ
አይኗ ክብልል የሚል በቀይ የተሳለች
መልከ ፀዳል ብሩህ ግርማን የተመላች
ጉንጯ ብር ሐመልማል ላያት ያስገረመች
ከንፈሯ መንደሪን
ጉንጯ እንደ ብርትኳን
እያልኩ የሰየምኳት እንቡጥ ፅጌረዳ
ያቺ ድንቅ ፍጥረት የዕንቊዎች ሰሌዳ
ምን ልበል ስለሷ ሆናብኝ እንግዳ
ወርቅና አልማዝ ሆና ለስሜ ለክብሬ
ጠልቃ የጠለቀች እንደ ውቅያኖስ የፍቅር ባህሬ
ገፀ ለምለም ሰናይ ጥዑም ወይነ ፍሬ
ገልጬ አልጨርሳት አላብዛ ፍካሬ
አንቺን አልጨርስሽ ቃላትን ደርድሬ
ባበቃ ይሻላል ይህን ተናግሬ
የፃፍኩት ውዳሴ ለውስጥሽ ባይጥሙሽ
ትርጉም የሌላቸው ሆሄ ቢበዙብሽ
የደረስኩት ድርሰት ውሸት እንዳይመስልሽ
ግጥሜ ቢያወድስሽ ልቤ ቢያዜምልሽ
ቃላት አጥሮኝ እንጂ በጣም ነው ምወድሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤7👍1
#የሰው_የእውነት_ሀቁ
ግዜ ባይጣደፍ ዘመን ባይገሰግስ
ምን ነበር ለጥቂት ልጅነት ቢታገስ
እድሜ በቀን ቀመር በዓመታት ሲሰላ
የሰው የእውነት ሀቁ ልጅነት ነው ጥላ
ክፋት ያልበረዘው ጭንቀት ያልከሰሰው
ማስመሰል የራቀው እምነት ያልጎደለው
ከሁላችን እድሜ አምላክ ቢመዝነው
ልጅነት ብቻ ነው የእውነት የተኖረው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ግዜ ባይጣደፍ ዘመን ባይገሰግስ
ምን ነበር ለጥቂት ልጅነት ቢታገስ
እድሜ በቀን ቀመር በዓመታት ሲሰላ
የሰው የእውነት ሀቁ ልጅነት ነው ጥላ
ክፋት ያልበረዘው ጭንቀት ያልከሰሰው
ማስመሰል የራቀው እምነት ያልጎደለው
ከሁላችን እድሜ አምላክ ቢመዝነው
ልጅነት ብቻ ነው የእውነት የተኖረው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤16👏1
#ፍቅር_አለቀሰ
ፍቅርን ስፈልገው ቀናቶች አለፉ
ፈለኩት ፈለኩት ድካም ሆነ ትርፉ
አጋጣሚ ሆኖ ተደብቆ አየሁት
አላምን ስላልኩኝ ምክንያቱን ጠየኩት!
ፍቅር አንተ ነህ ወይ? ብየ ብጠይቀው
ምንም መልስ ሳይመልስ እንባ ተናነቀው
ግራ ገባኝና ባግራሞት አየሁት
ቆይ! ፍቅር ደስታ ነው ሲባል ሰምቻለሁ
ታድያ ያንተ ለቅሶ ከየት የመጣ ነው?
ፍቅርም መለሰልኝ አይኑን መሬት ተክሎ
መናገር ጀመረ ቃላትን ቀጣጥሎ
ደስታማ ደስታ ነኝ ላወቀው ሚስጥሬን
ከደስታም በላይ ነኝ ከተረዱኝ እኔን
ያስለቀሰኝ ነገር ሆድ ሆዴን ያባሰው
በኔ ስም መነገድ መች አቆመ ሰው
አፈቀርኩሺ ብሎ ሲዋሻት በኔ ስም
ማሬ ውዴ ብላ ከድታው ስቴድ እሷም
በኔ ሲጫወቱ የሀሰት ጨዋታ
በኔ ሲባልጉ በኔ ስም ሲምታታ
በውሼት አለም ሆነው በኔ ስም ሲጠሩ
እንደት አላነባ? ካልረባ ነገሩ!
ብሎ መለሰልኝ ፍቅር በቀስታ
አንገቱን ቢያስደፋው የሀሰት ጨዋታ!
በፍቅር አስኪ አሁን መቀለድ ይብቃ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ፍቅርን ስፈልገው ቀናቶች አለፉ
ፈለኩት ፈለኩት ድካም ሆነ ትርፉ
አጋጣሚ ሆኖ ተደብቆ አየሁት
አላምን ስላልኩኝ ምክንያቱን ጠየኩት!
ፍቅር አንተ ነህ ወይ? ብየ ብጠይቀው
ምንም መልስ ሳይመልስ እንባ ተናነቀው
ግራ ገባኝና ባግራሞት አየሁት
ቆይ! ፍቅር ደስታ ነው ሲባል ሰምቻለሁ
ታድያ ያንተ ለቅሶ ከየት የመጣ ነው?
ፍቅርም መለሰልኝ አይኑን መሬት ተክሎ
መናገር ጀመረ ቃላትን ቀጣጥሎ
ደስታማ ደስታ ነኝ ላወቀው ሚስጥሬን
ከደስታም በላይ ነኝ ከተረዱኝ እኔን
ያስለቀሰኝ ነገር ሆድ ሆዴን ያባሰው
በኔ ስም መነገድ መች አቆመ ሰው
አፈቀርኩሺ ብሎ ሲዋሻት በኔ ስም
ማሬ ውዴ ብላ ከድታው ስቴድ እሷም
በኔ ሲጫወቱ የሀሰት ጨዋታ
በኔ ሲባልጉ በኔ ስም ሲምታታ
በውሼት አለም ሆነው በኔ ስም ሲጠሩ
እንደት አላነባ? ካልረባ ነገሩ!
ብሎ መለሰልኝ ፍቅር በቀስታ
አንገቱን ቢያስደፋው የሀሰት ጨዋታ!
በፍቅር አስኪ አሁን መቀለድ ይብቃ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤13👍2
#መልክአ_ሕይወት
ቧልትን ከፈገግታ
ሳቅን ከፌዝ ጋራ
ባንድ ላይ ቀይጠን፥
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን ባሕር ላይ ፥ ብናንቆረቁርም
ባሕሩ ሰፊ ነው፤ መልኩን አይቀይርም::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ቧልትን ከፈገግታ
ሳቅን ከፌዝ ጋራ
ባንድ ላይ ቀይጠን፥
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን ባሕር ላይ ፥ ብናንቆረቁርም
ባሕሩ ሰፊ ነው፤ መልኩን አይቀይርም::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
👍13❤6🔥1
#እንዴት_ይሆን_ፍርድሽ?
ጥቂት ታገሽ ሆዴ መንገዱን አሳብረሽ
ማዶ ማዶ እያየሽ
ብቻ ተስፋ አትቁረጭ ቁጭብለሽ ጠብቂኝ
እንዳትሄጅ ተናደሽ
እርሜን አረፈድኩኝ አንድ መሪ መ'ቶ
መንገድ ተዘጋግቶ
ወደዚ ሂድ ሲሉት ወደዛ ተመለስ
ህዝቤ ተሰላችቶ
ተስፋ ቆርጦ ሳለ
እኔ ግን የኔ ማር ካንቺ ተቃጥሬ
እንዴት እቀራለው ልሂድ ብዬ በግሬ
እየመጣሁኝ ነው ፍቅርሽ ጉልበት ሆኖኝ
ለመድረስ አንቺጋ
አይንሽን ካላየሁ ነብሴም እረፍት የላት
መንፈሴም አትረጋ
አይዞሽ የኔ ቆንጆ አልቀርም አልቀርም
ጥቂት እንደሮጥኩኝ
ቁሙ ባላቹበት ተብለን ብንቆምም
ልቤ እየሮጠች ነው በፍፁም አታርፍም
አቤት ክፉ ጊዜ አይ የቀን ጎዶሎ
ባልጠበቅነው መንገድ ባላሰብነው ውሎ
ደውዬ እንዳልነግርሽ ተዘግቷል ኔትዎርኩ
አልበር እንዳሞራ ለዚህ አልታደልኩ
አወይ የኔ ፍቅር ለጠባቂ ሴኮንድ
ከሰአት በላይ ነው ይህንን አውቃለው
ደቂቃ ዘግይተሽ በቀናት አስልቼም
ተቆጥቼሻለው
ብቻ የኔ አበባ
ምን አሰበ ይሆን ምን ወሰነ ልብሽ ?
ለጠዋት ቀጠሮ ማታም ሳልደርስልሽ
በቃሽ የኔ ነገር ? ጠላሺኝ ወዳጄ
እንዴት ይሆን ፍርድሽ
ለቀረሁ ታግጄ ???
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ጥቂት ታገሽ ሆዴ መንገዱን አሳብረሽ
ማዶ ማዶ እያየሽ
ብቻ ተስፋ አትቁረጭ ቁጭብለሽ ጠብቂኝ
እንዳትሄጅ ተናደሽ
እርሜን አረፈድኩኝ አንድ መሪ መ'ቶ
መንገድ ተዘጋግቶ
ወደዚ ሂድ ሲሉት ወደዛ ተመለስ
ህዝቤ ተሰላችቶ
ተስፋ ቆርጦ ሳለ
እኔ ግን የኔ ማር ካንቺ ተቃጥሬ
እንዴት እቀራለው ልሂድ ብዬ በግሬ
እየመጣሁኝ ነው ፍቅርሽ ጉልበት ሆኖኝ
ለመድረስ አንቺጋ
አይንሽን ካላየሁ ነብሴም እረፍት የላት
መንፈሴም አትረጋ
አይዞሽ የኔ ቆንጆ አልቀርም አልቀርም
ጥቂት እንደሮጥኩኝ
ቁሙ ባላቹበት ተብለን ብንቆምም
ልቤ እየሮጠች ነው በፍፁም አታርፍም
አቤት ክፉ ጊዜ አይ የቀን ጎዶሎ
ባልጠበቅነው መንገድ ባላሰብነው ውሎ
ደውዬ እንዳልነግርሽ ተዘግቷል ኔትዎርኩ
አልበር እንዳሞራ ለዚህ አልታደልኩ
አወይ የኔ ፍቅር ለጠባቂ ሴኮንድ
ከሰአት በላይ ነው ይህንን አውቃለው
ደቂቃ ዘግይተሽ በቀናት አስልቼም
ተቆጥቼሻለው
ብቻ የኔ አበባ
ምን አሰበ ይሆን ምን ወሰነ ልብሽ ?
ለጠዋት ቀጠሮ ማታም ሳልደርስልሽ
በቃሽ የኔ ነገር ? ጠላሺኝ ወዳጄ
እንዴት ይሆን ፍርድሽ
ለቀረሁ ታግጄ ???
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤13😢7👍3
#አንድ_እንባ_ለሁለት_ስሜት
ለሀዘን ለደስታ
የእንባ ቋጠሮ ሲፈታ
ከሁለት አይኖች ለሁለት ስሜት
ለማዘን ወይ ለመደሰት
በሳቅ ታጅቦ ወይም በለቅሶ
በመንታ ጉንጮች ቁልቁል ፈስሶ
ለመለያየት
ለመገናኘት
ብሶት ለመግለጽ ወይ ደስታ
በሁለት ስሜት የሚምታታ
እንባ አንድ ነው ግን ሁለት ስሜት
በሀዘንም በደስታም " ና " ብለው የሚጠሩት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ለሀዘን ለደስታ
የእንባ ቋጠሮ ሲፈታ
ከሁለት አይኖች ለሁለት ስሜት
ለማዘን ወይ ለመደሰት
በሳቅ ታጅቦ ወይም በለቅሶ
በመንታ ጉንጮች ቁልቁል ፈስሶ
ለመለያየት
ለመገናኘት
ብሶት ለመግለጽ ወይ ደስታ
በሁለት ስሜት የሚምታታ
እንባ አንድ ነው ግን ሁለት ስሜት
በሀዘንም በደስታም " ና " ብለው የሚጠሩት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
👍11❤9
በሔድክበት መንገድ
አይኔን ጣል አድርጌ
በትዝታ መርከብ
በሀሳብ ቀዝፌ
አተን እያሰብኩኝ ጉጬን ተደግፌ
እየጠበኩህ ነው
ትዛለህ ?
ትተኸኝ ስትሔድ
እዳትከተይኝ
ደግመሽ እዳትመጪ በሔድኩበት መንገድ
ብለኸኝ ስትሔድ
ስላስጠነከከኝ እዳልከተልህ
አሳስቶኝ እኳን ዞሬም እዳላይህ
ቃልህን አክብሬ አልተከተልኩህም
ባለህበት ቦታ ፍፁም አልመጣሁም
ነገር ግን እጠብቅሀለሁ
አለሁኝ እዛው ነኝ
እጠብቅሀለሁ ሳልሆን እራስ ወዳድ
ምናልባት ከመጣህ በሔድክበት መንገድ
አይኔን ጣል አድርጌ
በትዝታ መርከብ
በሀሳብ ቀዝፌ
አተን እያሰብኩኝ ጉጬን ተደግፌ
እጠብቅሀለሁ
በትዝታ መርከብ በሀሳብ ቀዝፌ
እየጠበኩህ ነው ጉጬን ተደግፌ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አይኔን ጣል አድርጌ
በትዝታ መርከብ
በሀሳብ ቀዝፌ
አተን እያሰብኩኝ ጉጬን ተደግፌ
እየጠበኩህ ነው
ትዛለህ ?
ትተኸኝ ስትሔድ
እዳትከተይኝ
ደግመሽ እዳትመጪ በሔድኩበት መንገድ
ብለኸኝ ስትሔድ
ስላስጠነከከኝ እዳልከተልህ
አሳስቶኝ እኳን ዞሬም እዳላይህ
ቃልህን አክብሬ አልተከተልኩህም
ባለህበት ቦታ ፍፁም አልመጣሁም
ነገር ግን እጠብቅሀለሁ
አለሁኝ እዛው ነኝ
እጠብቅሀለሁ ሳልሆን እራስ ወዳድ
ምናልባት ከመጣህ በሔድክበት መንገድ
አይኔን ጣል አድርጌ
በትዝታ መርከብ
በሀሳብ ቀዝፌ
አተን እያሰብኩኝ ጉጬን ተደግፌ
እጠብቅሀለሁ
በትዝታ መርከብ በሀሳብ ቀዝፌ
እየጠበኩህ ነው ጉጬን ተደግፌ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍14❤5
#ሀዘኑ_መች_ጠፋ!!!
ማልቀስ አምሮኝ ነበር እንባ ከየት መጥቶ
ሐዘን በልቤ ውስጥ ተርፎ ተከማችቶ
ከዚህ ሁሉ ሀዘን በዝቶ ከተረፈው
አንዲት ጠብታ እንባ ይቸግረዋል ሰው
እባክህ እንባዬ መንታ ሆነህ ፍሰስ
የታመቀው ውስጤ በጥቂት ይተንፍስ
ሀዘኑ መች ጠፋ ከልባችን ጓዳ
የራቀን ዘንድሮ እንባችን ነው ባዳ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ማልቀስ አምሮኝ ነበር እንባ ከየት መጥቶ
ሐዘን በልቤ ውስጥ ተርፎ ተከማችቶ
ከዚህ ሁሉ ሀዘን በዝቶ ከተረፈው
አንዲት ጠብታ እንባ ይቸግረዋል ሰው
እባክህ እንባዬ መንታ ሆነህ ፍሰስ
የታመቀው ውስጤ በጥቂት ይተንፍስ
ሀዘኑ መች ጠፋ ከልባችን ጓዳ
የራቀን ዘንድሮ እንባችን ነው ባዳ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤19💔10👍1
#ውሻ_ነበር_ያልሽኝ?
ቃል ኪዳን ጠብቄ ለእምነቴ መኖሬን፣
ከራሴ ሰስቼ ላንች መታመኔን፣
ስትመሰክሪልኝ......!
አቻ በሌላቸው በሁለት ቃላቶች፣
ስሜን ከፍ አ'ረግሽው ውሻ ብለሽ ጠርተሽ።
ላንች ውሻ ማለት ስድብ ቢመስልሽም፣
ማክበር እንደሆነ ፈፅሞ አልገባሽም።
አዎ እኔ ውሻ ነኝ........!
ጊዜ አይቼ ምቀርብ ድመት አይደለሁም፣
ለመጣ ለሄደው ጅራቴን አልቆላም።
ቀዘቀዘ ብዬ ቤቴን አልቀይርም፣
ሲሰጡኝ ወድጄ ሲነሱኝ አልጠላም።
አዎ እኔ ውሻ ነኝ...........።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ቃል ኪዳን ጠብቄ ለእምነቴ መኖሬን፣
ከራሴ ሰስቼ ላንች መታመኔን፣
ስትመሰክሪልኝ......!
አቻ በሌላቸው በሁለት ቃላቶች፣
ስሜን ከፍ አ'ረግሽው ውሻ ብለሽ ጠርተሽ።
ላንች ውሻ ማለት ስድብ ቢመስልሽም፣
ማክበር እንደሆነ ፈፅሞ አልገባሽም።
አዎ እኔ ውሻ ነኝ........!
ጊዜ አይቼ ምቀርብ ድመት አይደለሁም፣
ለመጣ ለሄደው ጅራቴን አልቆላም።
ቀዘቀዘ ብዬ ቤቴን አልቀይርም፣
ሲሰጡኝ ወድጄ ሲነሱኝ አልጠላም።
አዎ እኔ ውሻ ነኝ...........።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤11👏9🥰2
#ወዴት_ተሰወሩ?
በሳቃችን ዘመን አብረውን የሳቁ፣
ከእናንተ ውጪ ብለው ትላንት ያደነቁ፣
ሳቃችን ሲጠፋ መከራችን ነግሶ፣
በእህ! እህ! ሲተካ በሀዘን በለቅሶ፣
ወዴት ተሰወሩ? ምንስ ከለላቸው?
የትኛው ተራራ የትኛውስ እርቀት
ገዝፎ ጋረዳቸው ?
በዙሪያችን ከበው በክብር ሸልመው፣
በንግግራችን ፣ በማያስቅ ስቀው!
ለጥቅማቸው ሲሉ ትላንት ያገጠጡ
መካራ ሲገጥመን ወዴት? ፈረጠጡ?!
የሉም፣ አይታዩም! ምን ጉድጓድ ዋጣቸው?!
የትኛውስ እርቀት ከእኛ ሰውራቸው?
የሉም! የሉም! በቃ ዛሬ የሉም!
ሳቃችን ከጠፋ ከቶ አይመለሱም!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
በሳቃችን ዘመን አብረውን የሳቁ፣
ከእናንተ ውጪ ብለው ትላንት ያደነቁ፣
ሳቃችን ሲጠፋ መከራችን ነግሶ፣
በእህ! እህ! ሲተካ በሀዘን በለቅሶ፣
ወዴት ተሰወሩ? ምንስ ከለላቸው?
የትኛው ተራራ የትኛውስ እርቀት
ገዝፎ ጋረዳቸው ?
በዙሪያችን ከበው በክብር ሸልመው፣
በንግግራችን ፣ በማያስቅ ስቀው!
ለጥቅማቸው ሲሉ ትላንት ያገጠጡ
መካራ ሲገጥመን ወዴት? ፈረጠጡ?!
የሉም፣ አይታዩም! ምን ጉድጓድ ዋጣቸው?!
የትኛውስ እርቀት ከእኛ ሰውራቸው?
የሉም! የሉም! በቃ ዛሬ የሉም!
ሳቃችን ከጠፋ ከቶ አይመለሱም!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤10👍9💔4
#ልቤን_መልስልኝ
ልትሄድ ከሆነ ላይቀር መለየቱ
ቢበቃኝ ይሻላል ባንተ መጎዳቱ።
ቀልብህ ካላረፈ እግረኛ ሆነህ
መጓዝህ ካልቀረ ከእኔ መራቅህ
ለምን አስፈለገ ልቤን መስረቅህ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ልትሄድ ከሆነ ላይቀር መለየቱ
ቢበቃኝ ይሻላል ባንተ መጎዳቱ።
ቀልብህ ካላረፈ እግረኛ ሆነህ
መጓዝህ ካልቀረ ከእኔ መራቅህ
ለምን አስፈለገ ልቤን መስረቅህ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🔥14❤9
#አንተም_እኔም_ተጓዥ
አትግፋኝ ወንድሜ ፣ በከንቱ ጥላቻ፤
ለየትኛው እድሜ ? እንኑር በጡንቻ?
ለኮንትራት ዓለም ፣ ባለቤት ለሌላት፤
ከፍቅር ቀንሰን የምን? መገፋፋት ?
አንተም እኔም ተጓዥ ፣ በተራ ለጣቂ፤
ማን እንደሚቀድም ፣ አምላክ ነው አዋቂ ።
ስትገፋኝ ስገፋህ ፣ አንዱ ላያሸንፍ፤
መጓተት ብቻ ነው ፣ ሌላ የለንም ትርፍ ።
ለፍቅርም አይበቃ ፣ የተሰጠን አድሜ፤
እኔም ነኝ ወንድምህ ፣ አንተም ነህ ወንድሜ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
አትግፋኝ ወንድሜ ፣ በከንቱ ጥላቻ፤
ለየትኛው እድሜ ? እንኑር በጡንቻ?
ለኮንትራት ዓለም ፣ ባለቤት ለሌላት፤
ከፍቅር ቀንሰን የምን? መገፋፋት ?
አንተም እኔም ተጓዥ ፣ በተራ ለጣቂ፤
ማን እንደሚቀድም ፣ አምላክ ነው አዋቂ ።
ስትገፋኝ ስገፋህ ፣ አንዱ ላያሸንፍ፤
መጓተት ብቻ ነው ፣ ሌላ የለንም ትርፍ ።
ለፍቅርም አይበቃ ፣ የተሰጠን አድሜ፤
እኔም ነኝ ወንድምህ ፣ አንተም ነህ ወንድሜ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
👍14❤8