ግጥም
4.26K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ብቸኛ_ነበሩ!

በስህተት ተባብሮ ፣ በደቦ ከሚፈርድ፤
የብቻህን ሃሳብ ፣ ዝምታህን ውደድ፤
አለምን ጠቃሚ ፣ ሆነው የተገኙ፤
በመልካም ስራቸው ፣ አንቱ የተሰኙ፤
ብቸኛ ነበሩ ፣ ሁሉም የተዋቸው፤
በደቦ ተባብሮ በግፍ የጣላቸው፤
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍192
#ምንነት

አብረን በዋልንበት - በሄድንበት ሁሉ
ካንቺ ጋራ ያዩኝ - ያልገባቸው ውሉ
ምኗ ነው እያሉ - ሰው ይጠይቃሉ።

እናምልሽ ውዴ

ምኗ ነው እያሉ - ለሚጠራጠሩ
ስለኔ ምንነት - አውቀው እንዲኖሩ
ከቻልሽ አስረጃቸው - ገልፀሽ በአጭሩ።

እሱ ማለት ለኔ - ገና ከጅምሩ
በሰም የታጠረ - ቅኔ ነው ሚስጥሩ።

ቅኔ ማለት ደግሞ - የማይታይ ጌጡ
ተዘርፎ የማያልቅ - ወርቅ አለ በውስጡ
ለሱ ግን

ከሀብቱ የሚልቅ ሌላ በዚች አለም
ደስታ የሚፈጥር ምንም ይሁን ምንም
ከኔ ሳቅ የሚበልጥ አንዳች ነገር የለም።

መሳቅ ማለት ደስታ - ደስታ ማለት ደሞ
በልቡ ማሳ ላይ - የተዘራው ቀድሞ
የመንፈሱ ችግኝ - ስጋ ያበቀለው
የሚቀጥፈው መውደድ - ጊዜ ያበሰለው
ጣፍጦት የሚበላው የነፍሱ ፍሬ ነው።
ፍሬው ባስተሳሰብ - ዳግም የሚዘራ
የዘሩ ቅርንጫፍ - ከዕምነት የተጋራ
ፍቅር ያዳበረው - ወዳጅ የሚያፈራ
ጥሩ ጓደኛነት - በሚያጠላው ጥላ
እኔ ያስጠለለ - የሆነኝ ከለላ
አፍቅሮኝ የሚኖር - የማይመኝ ሌላ
ታማኝ ወዳጄ ነው - የዕምነቴ ኬላ።
ብለሽ አስረጃቸው
ስለኔ ምንነት - ማወቅ ተስኗቸው
ምኗ ነው ለሚሉ - ፍቅር ላልገባቸው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
8🥰4👏2🔥1
#ከክፋት_ሰውረኝ?!

የእባብ ልብን ይዘው እርግብ ነን ከሚሉ፣
በቀበሮ ተግባር በበግ ስም ከሚምሉ፣
ቃል እየጠቀሱ በክፋት ከራሱ ፣
በተኩላ ስጋ የብግ ለምድ ከለብሱ፣
የአምላክን ስም ጠርተው በቃሉ ከማይኖሩ፣
በእግዚአብሔር ዝማሬ ሰይጣን ከሚያከብሩ፣
እግራቸው ከመቅደስ ልባቸው ከክፋት፣
ቃላቸው የንብ ማር ተግባራቸው እሬት ፣
ከሆነ ሰዎች ዘንድ እግዚአብሔር ነጥለኝ፣
ጻድቅ ባልሆን እንኳን ከክፋት ሰውረኝ?!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍5🥰3👏2🔥1
#ሶሊያና

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ

እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰወች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
(ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም )
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኤፍሬም ስዩም
8👍8
#ተሻለህ_አትበሉኝ!

ያሽለኛል ብዬ የጠጣሁት ኮሶ
ይቆርጠኝ ጀመረ ከበሽታው ብሶ
መድሀኒት ይሆነናል ነበረ ምኞቴ
ሃኪሙን አምኜ በእምነት መጠጣቴ
ለካስ ተመረዟል መድሀኒቱ ዛሬ
ለዚህ ነበር ለካስ ብሶብኝ ማደሬ
ተሻለህ አትበሉኝ እያያችሁ ብሶ
መርዝ ሆኖ አሰቃዬኝ ይሄ የዘር ኮሶ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍104👏3
#እንደገና

እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡
ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡
ሌላም ብዙ ነበር
ሌላም… ደግሞ ሌላ
አለብኝ ትዝታ!
ዘመዶቼ ሳሙኝ
ጓደኞቼም ጋብዙኝ
ሊስትሮ ጨብጠኝ
ባለጋሪ ንዳ መንገዴን አሳየኝ
ያገሬ ልጅ ቆንጆ ‹‹ቤት ለእንግዳ›› በይኝ
አለብኝ ትዝታ…
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገ/ክርስቶስ ደስታ
3
#ውኃ_ማያጠፋው

ውኃ ‚ማያጠፋው ' እሳት ፡ ነው ፡ ፍቅርሽ
ነደድኩኝ "
ቢል ' አልኩኝ "
ተቃጠልኩልሽ ።
ወደድኩሽ "
ወደድኩህ ' በይኝ ፡ እባክሽ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
#ዘመም_ይላል_እንጂ

እንደ ጊዜው  መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ::
የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት
ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር
በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ::
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው ፥
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤
አዎ
ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል ::
ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም ::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
6👍3
#የፍቅር_ፍላፃ

ፈረንሣይ እንግሊዝ ጀርመን ጣልያን
ስትጽፍ ስትናገር አይዛት አፏን
ባርኔጣዋ ሠፌድ በፓሪሱ ቄንጥ
የጫማ ተረከዝ ስንዝር የሚበልጥ
ሥልጡን የተማረች የሠለጠነች
ብለው ሲወድሱሽ ሲሻሙሽ ሰዎች
አንዱ በቢዩክ መጥቶ «እንውጣ» ሲልሽ
በሼቭሮሌት አንዱ ሲያንሸረሽርሽ

መዳብ ያለው ብሩን ወርቅ ያለው ዕንቁን
የራስ አክሊል ያለው ሲሰጥሽ ዘውዱን
ማሞገስ የሚያወቅም ሲዘፍን ያንቺን ስም
ወድሻለሁ ያለሽ ሲሸለም ሲሾም
በፍቅርሽ ፍላፃ ተነድፎ እንዱ ደግሞ
ሚስቱን ያገባትን ምሎ ተፈጥሞ
ሲያባርር ሲፈታ ልጆች እያሉት
ትዳሩን ሲያፈርሰው አንቺን ለማግባት

እንዳላየ ዓይቼ ሰምቼ እንዳልሰማ
በፈላስፋ ትዕግሥት ስቀር ሳልሻማ!
በኒያ ሁሉ ልብሽ ቢጨክን ቢጠም
ከንፈርሽ ከሌላ ሰው ከንፈር ባይገጥም!
ፍቅርሽ ተፈትኖ በገንዘብ በእሳቱ
ታወቀ ማለት ነው ጥሩ ወርቅነቱ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

💓 ራስዬ አላሳዉሪ።: ዛሬ የተጠበቀውን መፅሐፍ ለመምጣት… ዝም ብሎ ቆመ! ቀጥሎ በሚልጠው ቻናል ተጫኑ | InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች
👍1
በዚህ ዓመት መንፈሳዊውን ጉዞ ይቀላቀሉ?
አዲስ የመንፈሳዊ እና የመዝሙር ብቃት ለማግኘት የተዘጋጀ ፕሮግራሞችን በመስመር ላይ ብቻ ይከታተሉ። ተዘጋጅተዋል የማታጣት መዝሙሮችና መልካም መንፈሳዊ ሃይል ከእኛ ጋር!
ይቅረቡ አሁን እና የመንፈሳዊ ህይወትዎን ይወዳድሩ!

#ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች
አዲስ የ4K ጥራት ፎቶ በፍላጎት ትጠብቃለህ?
በቀላሉ ቦታ እና ለsamrt-profile–wallpaper የምታጠቀም ፎቶዎች, የተመረጡ motivational ገጽታዎችና quotes ይፈልጋሉ?
ኢትዮጵያን የመጀመሪያውን እና ብቸኛ የመሆኑን ቻናል አትተዉ፤ አሁኑኑ join በሉ!

#ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች
ያልተሰበሰበው ቀልድ አብሮአችን አይሳካ?

ቀልድ ፣ ሞዝ እና መልካም አዲስ አስቂኝ ቪዲዮዎች በፈን ዞን ይጠበቁ። ሲሳቅ በሚገባ መቀላቀል ይፈልጋሉ? የትኛው መልኩ እንደሚገርም እዚህ ተመልከቱ!

ከመልካም ቀልድ አይተው አትቀሩ! አሁኑኑ ቀልድን ተውዞ ይካፈሉ።

#ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች