ግጥም
4.19K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ባዶ_ቤት_በክረምት

አንች የሌለሽበት
ዝም ጸጥ ብቻ
ጣሪያ መጫወቻ፡፡

አመሻሽ
ኦና ቤት
አንች የሌለሽበት
ፀጥ -ረጭ፣ ብቻ
ወለል መጫወቻ፡፡

ጠረጴዛ፣
ወንበር፣
አንድ አልጋ፣
አንድ በር፣
አንድ እኔ፣
አንድ መስኮት፣
ባዶ ቤ . . . ት በክረምት
አንች የሌለሽበት፣
ፀጥ-ረጭ ብቻ
እም መጫወቻ
ዝም መደሰቻ
ዝም ዝም
ዝም ዝም
ዝም ዝም ለብቻ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ጌትነት እንየው
17👍2
#ጎረቤት_እንደ_እሳት

ሰው ወዳጁን መምረጥ የሚችል ቢሆንም
ጎረቤት መምረጡ ማዳገቱ አይቀርም

ከጎረቤት መኖር ሐቁ ይህ ከሆነ
ጎረቤትን አምኖ እሱም ከታመነ

ጎረቤትን መጉዳት አራስን መጉዳት
መሆኑን ይረዳል ያውቀዋል በእውነት

ሰውን ካጋጠመው የጎረቤት ጥሩ
ለችግሩ እሚደርስ ከዘመድ ከእድሩ

ጎረቤትን በክብር በፍቅር መያዝ
ከመጥቀም በስተቀር የለውም መዘዝ

ይህን የተረዳ ምሥጢሩን ያወቀ
የስጋቱ አግረ ሙቅ ተፈታ ወለቀ

ጎረቤት እንደሳት ሊጠቅምም ሊጎዳ
የሚችል መሆ ኑን ሰው በውል ይረዳ

የጎረቤት ኑሮ ደንቡን ያላወቁ
ጉዳቱ ከጥቅሙ አይባስ ይጠንቀቁ!

ድንገት በአጋጣሚ አሳት እንደሚፋጅ
ለሰው ጎረቤቱ ካልሆነው የሚበጅ

ከነገር ለመራቅ አጥር ይለያቸው
አስታራቂ ዳኛ እንዲሆንላቸው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11🔥1
#ይበቃል

መንገዱም ቆሽሿል ደፍርሷል ባህሩ፡
ወጣቱም ተሰዷል ወጥቷል ከሀገሩ ፡
የተራበች ሀገር መዋደድ የራቃት፡
ዚፕ እንደሌለው ኪስ በዝቷል የሚሰርቃት፡
ወንበር ላይ ተቀምጦ በተናገረው ቃል፡
በማያውቀው ነገር የድሀ ልጅ ያልቃል፡
እርሜን አውጥቻለሁ ሰላም እንደራቀኝ፡
ከወንድሜ ሰርቆ ይለኛል ደብቀኝ፡
በቃኝ ሰልችቶኛል ከንቱ ነች ይቺ ዓለም፡
ላመነችው እንጂ ላመናት አትሆንም፡

ድንገት ምህረት ቢልክ የአምላክ ፍቃድ ቢሆን፡
ያኔ እመለሳለሁ ሰውነት ሰው ሲሆን።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ሀሽ ማል (ብቸኛው)
19👏1
#ልጫር_ልሞጫጭረው!

ቃላት አሽሞንሙኖ በፊደላት ደምቆ
በምሁር ቃል ጠቀስ ቢመጥቅ ተራቆ
ቅኔው ቢወሳሰብ አንባቢ ካልፈታው
ጠቢባዊው ሁሉ ለማነው የሚጽፈው ?
ህግጋት ጠብቆ ቀለማትን ቆጥሮ
ምጣኔን መጥኖ ሀረጋትን ቋጥሮ
ምሁሩ ወንድሜ ቅኝት ተከትሎ
እኔን ፊደላዊ ከጥበብ ነጥሎ
እርሱ ባወቀው ልክ መብቴን ከልሎ
ሲከሰኝ ይውላል እንዳትገጥም ብሎ
አንተሙ ለተማሩት ለተመራመሩት
እኔም ለቢጤየ ፊደል ለሚገድፉት
በተሰጠን ድንበር እውቀታዊ ልኬት
አንተም እንዳዋቂ ሳድስን ዝለላት
እኔ ግን ስወዳት ስን እንዴት ልጣላት?
ለስሜ መጠሪያ ሁልጊዜም ከፊት ናት
አንተም ለተማሩት ለተመራመሩት
ስንቴም እጭራለሁ ፊደል ለሚገድፉት
ግን ማወቅ ጥሩ ነው አለማወቅ ክፉ
ሳያውቁ አውቂያለሁ እረዘመ ሰልፉ
አንተ አስተምረኸኝ ለእውቀት እስከበቃ
ልጫር ልሞጫጭረው አትከልክለኝ በቃ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
8👏1
Forwarded from PHOTO STYLE
#Ad

LUCKY HABESHA 🎯
ወረቀት ድሮ ቀረ | ቀጥታ አሸንፎ ብር መውሰድ!

የሚያሸንፉት እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ!
💰 በእያንዳንዱ ጨዋታ አዲስ አሸናፊዎች! 
ፈጣን ክፍያ | 📲 ቀላል ጨዋታ 

አሁን ይቀላቀሉ

https://t.me/Lucky_Habesha

🔥 አሁን ይጫወቱ! - እድልዎን ይሞክሩ 
#LuckyHabesha #አሸናፊ_ይሁኑ
1👍1
#ገጣሚና_ግጥም!

ገጣሚ ለጋስ ነው
ከሰማይ እጆች ላይ ጨረቃዋን ነጥቆ
በጠቢብ ምናቡ
በብዕሩ ቀለም ቃላቶች አርቅቆ
የልቡን ለመግለፅ
በሃሳብ ጎዳና ይወርዳል ይወጣል
ከስንኝ ቀምሮ
የጨረቃን ውበት ላንዲት ሴት ይሰጣል፡፡

ገጣሚ የዋህ ነው
ቃላትን ፍለጋ ውቅያኖስን ቀዝፎ
ከምድር አሸዋ
ከማይቆጠረው ስሜቱን አግዝፎ
የውስጡን ሊከትብ
በማይታክት ሀሳብ አድማሳትን ያልፋል
ከልቡ ቁስል ላይ
ደም እያጠቀሰ ላንዲት ሴት ይፅፋል

ገጣሚ ጀግና ነው
በጦርነት አለም መኖሩ ሳይደንቀው
ዘውትር የሚሰማው
የሙታኖች መርዶ ስሜቱን ሳይሰርቀው
የልቡን ትርታ
ብቻ እያዳመጠ ካ'ሳብ ይሟገታል
በምናብ ጦርነት
ስለ ፍቅሯ ታግሎ ላንዲት ሴት ይሞታል፡፡

ገጣሚ ምስኪን ነው
ከብዙሀን መሀል አንዲቷን አብልጦ
ጠቢብ ማንቱን
በማይመጥን ዋጋ ስለ ፍቅሯ ሽጦ
በብቻነት አለም
ሁሉን እየረሳ እርሷን ያስታውሳል
በትዝታ ታስሮ
በብዕር አይኖቹ ላንዲት ሴት ያለቅሳል፡፡

እንዲህ ነው ገጣሚ
ለሄደች ሄዋኑ ቃላት እያማጠ የሚቀበጣጥር
ከዚህ ሁሉ ታግሎ
ስላንዲት ሴት ገድል ስንኝ የሚቋጥር፡፡

ይሄ ነው ገጣሚ
ከጥበቡ ጋራ
አፍቃሪ ልቦናን አብሮ የታደለ
ባልጎደለ ፀጋው
ስላንዲት ሴት ብሎ ክብሩን የገደለ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰ
13👌5👍1
#ትንሽ_ቦታ

በዚህ ዓመት፣
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ትንሸ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ቦታ መሠደጃ፡፡
ምናለበት፣
ለምናልባት ብንተውለት
ፍፁም መሆን ስለማንችል
ትንሽ ቦታ እንዋዋል፣በልባችን ደግ እንሁን፡፡
በአንጎላችን መላወሻ፣
ትንሽ ቦታ እንተውለት
‹‹ምናልባት›› የምንልበት!!
ልክ እንደአምና ለዚህ ዓመት
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሠር ይቅር ማያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ስራ፣ጥግ ድረስ የለም ፋታ፡፡
በልባችን ደግ በኩል፣ እንፈልግ ባዶ ቦታ፣
የጳጉሜ አይነት ትንሽ ቦታ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ነብዩ መኮንን
8🔥3👏1
#አንዴ_ብትሰጠኝ

ቀምሼው አላውቅም
እያልኳት አትስጭኝ
ልብሱን ገለጥ አርጋ
መልኩን ብታሳየኝ
እኔው ሰፍ ብዬ
አልኳት ስጭኝ ስጭኝ
እርሷም ሳትሳሳ
አንድ ጊዜ ብትሰጠኝ
ሁሌም ስጭኝ አልኳት
በጣም ነው የጣመኝ
ስሙንም ስትነግረኝ
እንዳይጠፋኝ ብላ
ለካስ የማውቀው ነው
ደስታ ከረሚላ!!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
🥰13😁12👍87👏2
#ቢጥፉት_ቢጥፉት

የተላበሱትን
ላይጥሉት አውልቀው
ቢጥፉት፣ቢጥፉት
መቀደዱን ዓይተው
      ዲሪቶን ቢደርቱት
ደጋግመው ቢጥፉት
አጋልጦ ይሰጣል
በአዲስ ካልቀየሩት
       እንደው ላይከርሙበት
      በመጣፌያ ጥፎ
     ገበና ላይሸፍን
      ሊሰጥ  አሳልፎ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ           
    ግዛቸው ማሞ
8🔥5👏1
#የሰሞኑን_እንጃ

ጋቢዬን ደርቤ
      ውስጤን ይበርደኛል
ከእሳቱም ቀርቤ
         ያንቀጠቅጠኛል
ሰው መሀልም ሆኜ
         ሰው ይናፍቀኛል
ከራሴው ዝምታ
         ጩኸት ይሰማኛል
ለወትሮ የወደድኩት
          ዛሬ አስጠልቶኛል
የሰሞኑን እንጃ
          ፍርሀት ያርደኛል
ልቤ ሁሉን ጠልቶ
          አንቺን ብቻ ይለኛል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
17🥰10👍1
#ቅበጭ_እንደ_ልብሽ

በጫንቃዬ ለዋልሽ ሸክሙ ላልከበደኝ፣
ቅብጠትሽ የመጨ እኔን ከተመቸኝ፣
ምን አርጊ ይሉሻል? ቢሉሽም ተያቸው፣
በእራሴ ትክሻ ምን ቁርጥ አርጓቸው?
ቅበጭ እንደ ልብሽ ደስ ይበልሽ በርቺ፣
ተከፍተሽ ሳይሽ ነው የሚጨንቀኝ ላንቺ፣
ምን ይሉኝ አትበይ ካሉሽም ተያቸው፣
እነርሱን ካልነካሽ ምን ጥልቅ አርጓቸው?
እንኳንስ ጫንቃዬን ልቤንም ወስደሻል፣
ገና እጨምራለሁ ላንቺ እኮ ያንስሻል፣
ብቻ አደራ ውዴ ከሌላ አትቅበጭ፣
በእኔ ሰውነት ላይ ሰክነሽ ተቀመጭ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👏139👍2
#እንደዚም_አለንዴ?

ምን ልበል ስላንቺ ቃላቶቼም ፈሩ፡
አንደበቴም ሞተ ሳይገባ ካፈሩ፡
አይኔም አላይ አለ ግርማሽ አሳውሮት፡
እግሬም አልፀናልኝ ክብርሽ አሸብሮት፡
እጄም ከፍ አለብኝ ድንቅ ውበትሽ ማርኮት፡
እንደዚም አለንዴ ማማር በተፈጥሮ፡
ሰዓሊ ማይስለው ቀለምን አጣምሮ፡
ፀሀፊ ማይገልፀው በብዕር ሞንጭሮ፡
ዘፋኝ የማይዘፍነው ድምፁን አሳምሮ፡
ምሁር ማይደርስበት ዝንት ተመራምሮ፡
ጨረቃን ሰማሗት እሪ ወየው ስትል፡
ፀሀይም በንዴት ፍጥረትን ስታግል፡
ኮከቧም አዝና ወዲያ ስትኮበልል፡
ደመናም ተከፍቶ ዞር ሲል ገለል፡
እንዲ ብስጭት ያሉት ዳሩ ባንቺ ላይ ነው፡
የጨረቃን ድምቀት ለራስሽ አርገሽው፡
የከዋክብትን ውበት በድፍረት ዘርፈሽው፡
የፀሀይን ሙቀት ይዘሽ አፍነሽው፡
የደመናን ግርማ በሀይል ነጥቀሽው፡
አኖረብሽ እንደው ያን ፀዳል ጥበቡን፡
ውበቱን ደፋብሽ ከሱ የሆነውን፡
እኔም ተገርሜ በውበትሽ ውዴ፡
ብዬ ትቼዋለው እንደዚም አለንዴ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍125🔥1🥰1
#በመኖር_አጸድ_ውስጥ

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::
እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤
ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
12🔥3👏2🥰1
ንገሪኝ ካልክማ •••••••
ትተኸው የሄድከው ያ የዋሁ ልቤ

በመቆየትህ ልክ መቅረትህን አምኖ
ያንተን ትውስታዎች  በሌላ  ሸፍኖ 

ከትዝታህ ባህር ከናፍቆትህ ሞገድ  
ከብቸኝነት ጥግ  ከረጂሙ  መንገድ
ሊወጣ አሰበና  ከሌላው ሊላመድ

መግባባት ጀምሮ መተዋወቅ ጣረ
አንዱ አልሆንህ ሲለው ሌላ እየሞከረ
ብዙ  በጋ  ክረምት  በመሀል በረረ

   ግና ምን ዋጋ  አለው  •••
የየዋህ ልቤ ልክ  ባንተ ተመጥኖ
ላንዱ  እየጠበበ  ላንዱ ሰፊ  ሁኖ 
          ካብሮነት ተቃርኖ•••

ዛሬም ለብቻው ነው ከፍቅር  እርቆ
መርሳት ያልቻለውን  ትዝታህን አንቆ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
20👏6👍2💔2🔥1
#ለከርሞ_ልጠብቅ!

ክሴን የሚሰማ አድማጭ ዳኛ ጠፍቶ
ይግባኝ በል ይሉኛል የቀደመው ቀርቶ
ቀድሞ ፍትህ ጎድሎ ሚዛኑ በገንዘብ
ሰሚ ጆሮ የለም ይግባኝ ቢደራረብ
ችሎት ቢለዋወጥ ፍትህ ካልነገሰ
አውነት እንደጥንቱ በገንዘብ ካነሰ
እንዳምና ታቻምናው ድሐ ካለቀሰ
ጥጋበኛ በዝቶ ወንበር ከረከሰ
አቤት ቢባል ያው ነው የጅብ ቆዳ ክራር
እንብላው ነው ዜማው የት ሊገባው ፍቅር
እባብ እያራቡ የእርግም ጫጩት የለም
ይግባኝ በል አትበሉኝ በቃ ችየው ልክረም
አምና ከፈረደው የዘንድሮው ብሶ
ሲረክስ እያየሁ እውነት ዛሬም አንሶ
ስንት ዶሴ ቀርቷል አቧራውን ለብሶ
ላይረታ በከንቱ ድሐ ሀብታም ከሶ
ገና ከጅምሩ ፍርድ ሚዛን ከሳተ
ዋናው ጉዳይ ቀሎ እየተጓተተ
በይግባኝ አልረታም ልተወው ዘንድሮ
ለከርሞ ልጠብቅ  ድሐ ሰሚ ጆሮ!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
10👍4🔥2
#ሳይኖር_አለቀ!

ከአለማነው ይልቅ የአጠፋነው በዝቶ
የቃረምነው እውቀት በዜሮ ተባዝቶ
ቁሳቁስ ተከብሮ ሰውነት ተናቀ
ኖርነው ያልነው ህይወት ሳይኖር አለቀ
የጋራነት ቀርቶ የግል ያልነው በዝቶ
ጥሎ ማለፍ ሆነ እርስ በእርስ ተጋፍቶ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
👍134🔥1
#እጠብቅሻለሁ

     እጠብቅሻለሁ ካለሁበት ቆሜ
     ሀሳብና ናፍቆት ፍቅርን ተሸክሜ
     እዛው ቦታ አለው እኔን ከተውሽበት
     እኔንም ፍቅርሽን ጥለሽ ከሄድሽበት
    
      እጠብቅሻለሁ ደቂቃም ሳላጎል
     ምንስ ደህና ባልሆን ሰላሜ ቢታጎል
      እዛው አለው ፍቅሬ ያኔ ከቆምንበት
      ትተሺኝ መሄድሽን ምንስ ባላምንበት
     ቆሜ ስጠብቅሽ ጭራሽ ቀን                   አልመርጥም እሁድ አልል ሰንበት
  
     እጠብቅሻለሁ ፍቅሬ እዛው ሰፈር
   ጥለሽኝ ከሄድሽበት ብለሽ አይንህ ላፈር
    እጠብቅሻለሁ ዳግም መምጣትሽን
    ምን ልቤ ቢሰጋ፤እንዲያበቃን በማሰብ
                  ዳግም ለአይነ ስጋ
   
    እዛው አለው ፍቅሬ ያኔ ከቆምንበት
    ከፍቅራችን አልፎ ትዳር ካሰብንበት
    አዬ ትዳር እቴ እንኳን ትዳር ቀርቶ
    ዛሬ አንቺም ሄደሽ ደስታው ተቀይሯል
               ወደ ሀዘን ቀረርቶ
    
   እኔ ግን የኔ ውድ ዛሬም ወድሻለሁ
   አንቺ ያፈራረስሽው ፍቅሬን አድሻለሁ
   ዳግም ካንቺ መሆን መጫወት እሻለሁ
    ጊዜ አስተምሮሽ አንቺም እኔን ካሻሽ
    ፍቅሬን ይዤ አለሁህኝ ለጥላቻሽ ምላሽ
    ፍቅሬ ካንቺ በላይ ጠንቅቄ አውቅሻለሁ
     መቅረትሽን ባምንም አንቺ የተውሽውን
          ለተረኛ ይዤ እጠብቅሻለሁ
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
6👍6🔥2👏2
#የታል_ፈገግታዬ

ያንን ጣፋጭ ጊዜ፣ምን ዋጠው ደስታየን
የታል ፈገግታየ፣ምን ወሰደው ሳቄን
እንቅልፌስ የት ሄደ፣ቅዠት የሌለበት
አይኖቼ ለ እረፍት፣የተከደኑበት
ከቶ ወዴት ገባ፣የመስኩ ቡረቃ
ስዘል የዋልኩበት፣እያቦካሁ ጭቃ
ዛሬማ ጭንቅ ነው፣ኑሮ በሰቆቃ
መልኬም ይናገራል፣ምቾት እንደሌለኝ
ሀሳቤ ተሰርቆ፣ለተመለከተኝ
ድሮን በመለስኩት፣የልጅነት ወዜን
ድሎት የሞላውን፣ያቺን ነፃነቴን
ጊዜው ተሰደደ፣ሂዷል አሁንማ
በእናት ነበር ኩራት፣ከሷ ወዲህማ
ሳቄም አይበረክት፣ድምፄም አይሰማ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ፋሲል ብስራት
12🔥1
#አበባና_ውበት

የአበባ ውበቱ
ሳቢ ደም ግባቱ
የሚታይ ድምቀቱ
የማር መስሪያነቱ
እሰከሚከስም ነው
ሁሉም የሚከበው
ፍቅረኞች ለፍቅር
አልቃሾች ለቀብር
ንቦች ደግማ ለማር
ለአበባ የሚዘመር
የሚንከባከቡት
አለውህ የሚሉት
ውበቱ እስካለ ነው
ከዚያ ወዳቂ ነው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
11🥰10🔥4👍1😢1
#ከንፈርሽን_ስስመው 💋

ከንፈርሽን ስስመው
የአለም ጨለማ በፍቅራችን በርቶ
በአብርሃም በሳራ መመሠሉ ቀርቶ
ከምድር 'ርቆ በገነት እንዳለ
ፍቅር በ'ኔና አንቺ እየተመሠለ
...መስሎ ይታየኛል...

ከንፈርሽን ስስመው
አባይ ተገድቦ ሲፈስ ወደ አገሩ
ፅጌረዳ አበቦች በመስመር ሲዘሩ
ባ'በቦቹ መሀል እየተሯሯጥን
ከፅጌረዳው ስር ፍለጋ ስኳትን

ከንፈርሽን ስስመው
ምድርን የሞሏት አበቦቹ ሁሉ
ጣፋጭ ከንፈርሽን መስለው የበቀሉ
ወደ ገነት ደሴት ሲወስደን ባቡሩ
ወፎች ለ'ኔና አንቺ ፍቅር እየዘመሩ
...መስሎ ይታየኛል...

ከንፈርሽን ስስመው
አለም ለ'ኔና አንቺ ግብር እየከፈለ
ለሁሉ 'ሚበቃ ፍቅር እየታደለ
ሠማይን የሞሉት ከዋክብቱ ሁሉ
ውበትሽን ለማድመቅ የሚንቀለቀሉ
...መስሎ ይታየኛል...

ከንፈርሽን ስስመው
ውዴ ይሄን ሁሉ አየሁኝ ብልሽም
አይኖቼ ተከድነው አንቺን አላዩሽም::
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
14👏3🥰2