#ያኔ_ነው_ምሞተው
ውዴ !!!!!!
እንደ ሁሉም ፍጥረት ህመሜ በርትቶ ፤
ነፍሴን ቢወስድብኝ መልዓከ ሞት መጥቶ ፤
ሐውልት ውስጥ ሆኘ በአበባ ብሸለም ፤
ለኔ ቴአትር ነው እሱ ሞት አይደለም ፤
--- ወይ ደግሞ ---
አካሌ ጎስቁሎ እርጅና ተጭኖኝ ፤
ዳዴ እያልኩ ብሔድ መራመድ ተስኖኝ ፤
አለኝ ያልኩት ሁሉ ሂድልኝ እስኪለኝ ፤
ድህነት ቢወርሰኝ ማጣት ሲያቃጥለኝ፤
የሞትኩ ነኝ ብልም ድንገት ተናድጄ ፤
እሱም ሞት አይደለም እመኝኝ ወዳጄ ፤
--- ንገረኝ ካልሽማ !!!!! ---
የመንፈሴ ምግብ መልክሽ ተለዋውጦ ፤
ተስረቅራቂ ድምፅሽ በሳግ ተቆራርጦ ፤
አይንሽ ዕንባ ቋጥሮ ፈገግታሽ ተውጦ ፤
ከፍቶሽ ያዬሁሽ ለት ዓደይ ፊትሽ ከስሎ ፤
...ያኔ ነው ምሞተው ቅስሜ እንክት ብሎ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ውዴ !!!!!!
እንደ ሁሉም ፍጥረት ህመሜ በርትቶ ፤
ነፍሴን ቢወስድብኝ መልዓከ ሞት መጥቶ ፤
ሐውልት ውስጥ ሆኘ በአበባ ብሸለም ፤
ለኔ ቴአትር ነው እሱ ሞት አይደለም ፤
--- ወይ ደግሞ ---
አካሌ ጎስቁሎ እርጅና ተጭኖኝ ፤
ዳዴ እያልኩ ብሔድ መራመድ ተስኖኝ ፤
አለኝ ያልኩት ሁሉ ሂድልኝ እስኪለኝ ፤
ድህነት ቢወርሰኝ ማጣት ሲያቃጥለኝ፤
የሞትኩ ነኝ ብልም ድንገት ተናድጄ ፤
እሱም ሞት አይደለም እመኝኝ ወዳጄ ፤
--- ንገረኝ ካልሽማ !!!!! ---
የመንፈሴ ምግብ መልክሽ ተለዋውጦ ፤
ተስረቅራቂ ድምፅሽ በሳግ ተቆራርጦ ፤
አይንሽ ዕንባ ቋጥሮ ፈገግታሽ ተውጦ ፤
ከፍቶሽ ያዬሁሽ ለት ዓደይ ፊትሽ ከስሎ ፤
...ያኔ ነው ምሞተው ቅስሜ እንክት ብሎ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤16👍3🥰3
#ልክ_በዛሬው_ቀን
አበባ ባልሰጥሽ ለራት ባልቀጥርሽም
እኔ ወድሻለሁ…
ባለሽበት ሆነሽ ባለሁበት ሆኜ
አብረን እንደሆንን ራሴን አሳምኜ
እራት እበላለሁ እራትሽን ብይ
ስጦታሽን እንቺ አበባሽን እይ
እኔ ወድሻለሁ…
ያለንበት ቦታ ለስላሳ ሙዚቃ
ሰማሽው አይደለ ላንቺ ይሁን በቃ
እወቃለሁ የኔ ሴት አውቃለሁ የኔ ዓለም
ቀይ መጸሀፍ እንጂ ቀይ ልብስ አትወጂም
ለራት የለበስሽው…
ሰማያዊ ቀሚስ ነጭ እስካርፍ ያለበት
ይሁን ደስ ብሎኛል ደምቀሽ እመሪበት
እኔ ወድሻለሁ…
ዘና በይ ፈገግ በይ
ባለሁበት ሆኜ ባለሽበት ሆነሽ
ብቸኝነት የለም የኔ ሆይ ልንገርሽ
ያሳቤን ስጦታ በይ አሁን ክፈቺው
አየሽው…?
ወደድሽው…?
የልቤ ትንፋሽ ነው በልብሽ ተንፍሺው
እኔ ወድሻለሁ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህሌ
አበባ ባልሰጥሽ ለራት ባልቀጥርሽም
እኔ ወድሻለሁ…
ባለሽበት ሆነሽ ባለሁበት ሆኜ
አብረን እንደሆንን ራሴን አሳምኜ
እራት እበላለሁ እራትሽን ብይ
ስጦታሽን እንቺ አበባሽን እይ
እኔ ወድሻለሁ…
ያለንበት ቦታ ለስላሳ ሙዚቃ
ሰማሽው አይደለ ላንቺ ይሁን በቃ
እወቃለሁ የኔ ሴት አውቃለሁ የኔ ዓለም
ቀይ መጸሀፍ እንጂ ቀይ ልብስ አትወጂም
ለራት የለበስሽው…
ሰማያዊ ቀሚስ ነጭ እስካርፍ ያለበት
ይሁን ደስ ብሎኛል ደምቀሽ እመሪበት
እኔ ወድሻለሁ…
ዘና በይ ፈገግ በይ
ባለሁበት ሆኜ ባለሽበት ሆነሽ
ብቸኝነት የለም የኔ ሆይ ልንገርሽ
ያሳቤን ስጦታ በይ አሁን ክፈቺው
አየሽው…?
ወደድሽው…?
የልቤ ትንፋሽ ነው በልብሽ ተንፍሺው
እኔ ወድሻለሁ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህሌ
❤21👍7🥰4
#ሳሚኝ_እና_ልንቃ
ነግረውሽ እንደሆን…
መጎዳቴን አይተው ህመሜን በዝርዝር
ጤናዬን እንዳጣው ለክፎኝ ያንቺ ፍቅር
የመኖር አኳኋን ውሉ ተዛብቶብኝ
ቀንና ለሊቱ እንደተምታታብኝ
ሰምተሽ እንደሆነ…
አንቺን ካየሁ ወዲህ ሰላም እንደራቀኝ
ፍቅርሽ ውስጤ ገብቶ እንደሚያስጨንቀኝ
ውበትሽ በልቤ ደምቆ እንደተሳለ
የኔ አካል በሀሳብ ካንቺጋ እንደዋለ
ሰምተሽ እንደሆነ…
ብቻ መዋተቴን
እራሴን ማጣቴን
ውሎ አዳር መተከዝ
አለፍ ሲል መፍዘዝ
ለብቻ መፈገግ
ዝም ብሎ መበርገግ
ሆኗልና ግብሬ ሰርክ የማይቀየር
መጥተሽ አንድ በዪኝ ተይ ነገሩ ሳይከር
ባንቺ እንደታመምኩኝ ባንቺው ልዳን በቃ
በውብ ከንፈሮችሽ ሳሚኝና ልንቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ነግረውሽ እንደሆን…
መጎዳቴን አይተው ህመሜን በዝርዝር
ጤናዬን እንዳጣው ለክፎኝ ያንቺ ፍቅር
የመኖር አኳኋን ውሉ ተዛብቶብኝ
ቀንና ለሊቱ እንደተምታታብኝ
ሰምተሽ እንደሆነ…
አንቺን ካየሁ ወዲህ ሰላም እንደራቀኝ
ፍቅርሽ ውስጤ ገብቶ እንደሚያስጨንቀኝ
ውበትሽ በልቤ ደምቆ እንደተሳለ
የኔ አካል በሀሳብ ካንቺጋ እንደዋለ
ሰምተሽ እንደሆነ…
ብቻ መዋተቴን
እራሴን ማጣቴን
ውሎ አዳር መተከዝ
አለፍ ሲል መፍዘዝ
ለብቻ መፈገግ
ዝም ብሎ መበርገግ
ሆኗልና ግብሬ ሰርክ የማይቀየር
መጥተሽ አንድ በዪኝ ተይ ነገሩ ሳይከር
ባንቺ እንደታመምኩኝ ባንቺው ልዳን በቃ
በውብ ከንፈሮችሽ ሳሚኝና ልንቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤28👏4💯2👍1
#ዋጋዬ_ውድ_ነው!
ክብርህን ለመግዛት ዋጋ የሚያወጡ!
የአንተን ማጣት አይተው በፍጥነት ከመጡ!
እንዲህ ጠይቃቸው?
ምንም ሳትፈራቸው!
ያኔ!! ሳይኖራቸው!ሌሎች ሲገዟቸው!
በሆድ ሲገመቱ ስንት ነው? ዋጋቸው?!
የእኔ ግን ውድ ነው! ዋጋዬ! ተመኑ!
ከሆድ ባሻገር ነው! ጥያቄዬ እመኑ!
ለመኖር ብበላም! ለመብላት አልኖርም!
ሆድ ጎደለ! ብዬ! ክብሬን ግን አልሸጥም!!!
እናም በቃ! ሂዱ! ዋጋዬ ውድ ነው!
የምደራደረው በሰው ልክ ሚዛን ነው!!!
ብለህ ንገራቸው!!!
ድንገት ከገባቸው!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ክብርህን ለመግዛት ዋጋ የሚያወጡ!
የአንተን ማጣት አይተው በፍጥነት ከመጡ!
እንዲህ ጠይቃቸው?
ምንም ሳትፈራቸው!
ያኔ!! ሳይኖራቸው!ሌሎች ሲገዟቸው!
በሆድ ሲገመቱ ስንት ነው? ዋጋቸው?!
የእኔ ግን ውድ ነው! ዋጋዬ! ተመኑ!
ከሆድ ባሻገር ነው! ጥያቄዬ እመኑ!
ለመኖር ብበላም! ለመብላት አልኖርም!
ሆድ ጎደለ! ብዬ! ክብሬን ግን አልሸጥም!!!
እናም በቃ! ሂዱ! ዋጋዬ ውድ ነው!
የምደራደረው በሰው ልክ ሚዛን ነው!!!
ብለህ ንገራቸው!!!
ድንገት ከገባቸው!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤26👍8
#አውቆ_እንዳላወቀ
አንተው እያጠፋህ አንተው ስትወቅሰኝ
ይቅርታ ልሀለሁ እውነቱ እየገባኝ
ሲሻህ ስትቆጣ ሲሻህ ስታኮርፈኝ
ለምኛህም ቢሆን እኔ አወራለሁኝ
ነጩንም ጥቁር ነው እያልክ ስትዋሸኝ
ያንንም አልፋለሁ አይቶ እንዳላየሁኝ
ነገን ተስፋ አድርጌ ዛሬን እያጣሁኝ
አንተ ስቀህ ስቱል እኔ እያለቀስኩኝ
መውደዴ እስኪገባህ እንዳልክ እየሆንኩኝ
ዛሬም ያው አለሁኝ ,,,,,,,
ግን እርፍደህ ነቅተህ ትግስቴ ካለቀ
ሌላ ጋር ብታየው ያ ጥርሴ እየሳቀ
አንተም እንድታልፈኝ አውቆ እንዳለወቀ
አንተው እያጠፋህ አንተው ስትወቅሰኝ
ይቅርታ ልሀለሁ እውነቱ እየገባኝ
ሲሻህ ስትቆጣ ሲሻህ ስታኮርፈኝ
ለምኛህም ቢሆን እኔ አወራለሁኝ
ነጩንም ጥቁር ነው እያልክ ስትዋሸኝ
ያንንም አልፋለሁ አይቶ እንዳላየሁኝ
ነገን ተስፋ አድርጌ ዛሬን እያጣሁኝ
አንተ ስቀህ ስቱል እኔ እያለቀስኩኝ
መውደዴ እስኪገባህ እንዳልክ እየሆንኩኝ
ዛሬም ያው አለሁኝ ,,,,,,,
ግን እርፍደህ ነቅተህ ትግስቴ ካለቀ
ሌላ ጋር ብታየው ያ ጥርሴ እየሳቀ
አንተም እንድታልፈኝ አውቆ እንዳለወቀ
❤32👏4
"እመጣለሁ " ብለሽ ፣ ከቀጠርሽኝ ቦታ
እድሜ እንደ "ቅፅበት" ፣ ዘመን እንደ "አፍታ"
ቆሜ ስጠብቅሽ ፣ ሳላገኝሽ ያልፋል
ስትቀሪ ጊዜ...
ዘላለሜ ባክኖ ፣ ናፍቆትሽ ይገዝፋል፡፡"
ምናምን እያለ...
በቃል አሳምሮ ፣ የሚፅፍ ብሶቱን
የደሀ ግጥም ነው ፣ ልንገርሽ እውነቱን ።
.............................................
አናልሽ የኔ ውብ...
ደሀ "ውድ" ያለውን ፣
"ርካሽ ነው" ብሎ ፣ ሀብታም እየገዛው
ለምን ይመስልሻል...
"ውዴ" የሚለው ቃል ፣ ግጥም ላይ የበዛው?
እውነቱን ልንገርሽ...
ደሀ አፍቃሪ ነው ፣
ግጥምን እየፃፈ ፣ "ውዴ"ን ያጠነዛው ።
............................... ..... .......
እናልሽ የኔ ውብ ...
በፍቅርሽ ተቃጥላ ፣ ነፍሴ ብትቀልጥም
ቆሜ ስጠብቅሽ....
እድሜዬ አያልፍም ፣ ዘመኔ አያመልጥም
ባለሽበት ቦታ ...
"ሳልቀጥርሽ ላግኝሽ" ፣ ሚል ነው የኔ ግጥም።
..........................................
ሳልቀጥርሽ ላግኝሽ (ርዕስ)
ደሀ አፍቃሪ ሁሉ...
"በዱር በገደሉ
በፀሃይ በጠሉ
አንቺን በመጠበቅ ፣ተቃጠልን" ሲሉ
"ስፈልግሽ ሳድር ፣ ስፈልግሽ ውዬ
ጎንደር ላይ ሳስፈልግ፣ "ጎጃም" ናት ተብዬ
ጎጃም ላይ ሳስጠይቅ ፣ "ትግራይ" ናት ተብዬ
ትግራይ ላይ ሳስፈልግ ፣ "ወለጋ" ነች ሲሉኝ
ወለጋ ሳስፈልግ ፣ "ሸገር ገባች"ሲሉኝ"
ምናምን እያሉኝ....
ልቤን ከሚያደክመው ፣ በዙረታም ግጥም
"አለች" ባሉት ቦታ....
ሲደርስ ከሄደች፣
"ጠልታኛለች" ብሎ ፣ ለምን ልቡ አይቆርጥም ?!
እናልሽየኔ ውብ ....
ደሀ ነው 'ሚፅፈው ፣እንዲህ አይነት ግጥም ።
............................................
እናልሽ የኔ ውብ....
አንድ የቤት መኪና ፣
ካንድ ቪላ ቤት ጋር ፣ ብሰጥሽ ገዝቼ
ደሀ ቀጥሮ ሲያጣሽ....
እኔ አገኝሻለሁ ፣ሳልቀጥርሽ መጥቼ።
እንጂ አልጠብቅሽም!
"ትመጣለች" እያልኩ እድሜዬን ሸኝቼ፡፡
............................................
እናልሽ የኔ ውብ ....
በፍቅርሽ የምትነድ ፣ ነብሴ ብትቀልጥም
ቆሜ እየጠበኩሽ...
ዘመኔ አያልፍም ፣ እድሜዬ አያመልጥም
መምጣት የማይችል ነው!
"ትመጫለሽ "ብሎ የሚፅፈው ግጥም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በላይ በቀለ ወያ
እድሜ እንደ "ቅፅበት" ፣ ዘመን እንደ "አፍታ"
ቆሜ ስጠብቅሽ ፣ ሳላገኝሽ ያልፋል
ስትቀሪ ጊዜ...
ዘላለሜ ባክኖ ፣ ናፍቆትሽ ይገዝፋል፡፡"
ምናምን እያለ...
በቃል አሳምሮ ፣ የሚፅፍ ብሶቱን
የደሀ ግጥም ነው ፣ ልንገርሽ እውነቱን ።
.............................................
አናልሽ የኔ ውብ...
ደሀ "ውድ" ያለውን ፣
"ርካሽ ነው" ብሎ ፣ ሀብታም እየገዛው
ለምን ይመስልሻል...
"ውዴ" የሚለው ቃል ፣ ግጥም ላይ የበዛው?
እውነቱን ልንገርሽ...
ደሀ አፍቃሪ ነው ፣
ግጥምን እየፃፈ ፣ "ውዴ"ን ያጠነዛው ።
............................... ..... .......
እናልሽ የኔ ውብ ...
በፍቅርሽ ተቃጥላ ፣ ነፍሴ ብትቀልጥም
ቆሜ ስጠብቅሽ....
እድሜዬ አያልፍም ፣ ዘመኔ አያመልጥም
ባለሽበት ቦታ ...
"ሳልቀጥርሽ ላግኝሽ" ፣ ሚል ነው የኔ ግጥም።
..........................................
ሳልቀጥርሽ ላግኝሽ (ርዕስ)
ደሀ አፍቃሪ ሁሉ...
"በዱር በገደሉ
በፀሃይ በጠሉ
አንቺን በመጠበቅ ፣ተቃጠልን" ሲሉ
"ስፈልግሽ ሳድር ፣ ስፈልግሽ ውዬ
ጎንደር ላይ ሳስፈልግ፣ "ጎጃም" ናት ተብዬ
ጎጃም ላይ ሳስጠይቅ ፣ "ትግራይ" ናት ተብዬ
ትግራይ ላይ ሳስፈልግ ፣ "ወለጋ" ነች ሲሉኝ
ወለጋ ሳስፈልግ ፣ "ሸገር ገባች"ሲሉኝ"
ምናምን እያሉኝ....
ልቤን ከሚያደክመው ፣ በዙረታም ግጥም
"አለች" ባሉት ቦታ....
ሲደርስ ከሄደች፣
"ጠልታኛለች" ብሎ ፣ ለምን ልቡ አይቆርጥም ?!
እናልሽየኔ ውብ ....
ደሀ ነው 'ሚፅፈው ፣እንዲህ አይነት ግጥም ።
............................................
እናልሽ የኔ ውብ....
አንድ የቤት መኪና ፣
ካንድ ቪላ ቤት ጋር ፣ ብሰጥሽ ገዝቼ
ደሀ ቀጥሮ ሲያጣሽ....
እኔ አገኝሻለሁ ፣ሳልቀጥርሽ መጥቼ።
እንጂ አልጠብቅሽም!
"ትመጣለች" እያልኩ እድሜዬን ሸኝቼ፡፡
............................................
እናልሽ የኔ ውብ ....
በፍቅርሽ የምትነድ ፣ ነብሴ ብትቀልጥም
ቆሜ እየጠበኩሽ...
ዘመኔ አያልፍም ፣ እድሜዬ አያመልጥም
መምጣት የማይችል ነው!
"ትመጫለሽ "ብሎ የሚፅፈው ግጥም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በላይ በቀለ ወያ
❤23👍4
#ማነው?
እስኪ ማነው ውዴ ከቶ 'ሚዳፈረው?
ካንበሳ መንጋጋ ስጋን ለመናጠቅ የሚንደረደረው?
እኮ መልስልኝ?
ንጉስ አስወጥቶ ከቤተ መቅደሱ፣
ዙፋን አስለቅቆ ሚሾምበት እሱ፣
የልዑልን ዋንጫ ፅዋ መጠጫውን፣
ካባውንስ ቢሆን ክብሩን መግለጫውን፣
አዳራሹን ሳይከፍት ወይ ቁልፉን ሰባብሮ፣
ማነው ከዙፋኑ የሚያወርደው ደፍሮ?
እእ???
እንግዲያውስ ስማኝ ልናገር ሚስጥሩን፣
እንኳንስ ዙፋኑን ከደጅ ሆኖ ቅጥሩን፣
ማንም ደፋር ነኝ ባይ አይረግጥም ድንበሩን።
ስልጣን ለማስለቀቅ አዳራሼን ከፍቶ፣
ከቤተ መንግስትህ ተንደርድሮ ገብቶ፣
ካባህን አውልቆ ዋንጫህን ቀምቶ፣
ክብርህን 'ሚገፈው ፅዋህን ጠጥቶ፣
አትጠራጠረኝ እመነኝ የኔ አለም፣
መቼም ቢሆን መቼ ከልቤ ዙፋን ላይ የሚያወርድህ የለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እስኪ ማነው ውዴ ከቶ 'ሚዳፈረው?
ካንበሳ መንጋጋ ስጋን ለመናጠቅ የሚንደረደረው?
እኮ መልስልኝ?
ንጉስ አስወጥቶ ከቤተ መቅደሱ፣
ዙፋን አስለቅቆ ሚሾምበት እሱ፣
የልዑልን ዋንጫ ፅዋ መጠጫውን፣
ካባውንስ ቢሆን ክብሩን መግለጫውን፣
አዳራሹን ሳይከፍት ወይ ቁልፉን ሰባብሮ፣
ማነው ከዙፋኑ የሚያወርደው ደፍሮ?
እእ???
እንግዲያውስ ስማኝ ልናገር ሚስጥሩን፣
እንኳንስ ዙፋኑን ከደጅ ሆኖ ቅጥሩን፣
ማንም ደፋር ነኝ ባይ አይረግጥም ድንበሩን።
ስልጣን ለማስለቀቅ አዳራሼን ከፍቶ፣
ከቤተ መንግስትህ ተንደርድሮ ገብቶ፣
ካባህን አውልቆ ዋንጫህን ቀምቶ፣
ክብርህን 'ሚገፈው ፅዋህን ጠጥቶ፣
አትጠራጠረኝ እመነኝ የኔ አለም፣
መቼም ቢሆን መቼ ከልቤ ዙፋን ላይ የሚያወርድህ የለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤13👍6
❤19👍3😢3
#ያንች_ሁኜ_ልቅር
ከይቅርታ በላይ?፤
ከመፀፀት በላይ?፤
ምንድን ነገር አለ በምረት የሚታይ?፤
እስኪ ጀሮ ስጭኝ አንድ ታሪክ ልንገርሽ፤
ጌታ ባካል ሳለ ምን ሆነ መሰለሽ፤
በፈጣሪ ጥበብ በውበቷ ኮርታ፤
የሰማዩን ሳይሆን የታች ቤቷን አይታ፤
አዳምን አማላ አዳምን እረታ፤
በሀጽያት ተዘፍቃ ዝሙትን አስፋፍታ፤
ትኖር ነበር አሉ በዚህ በኛ ምድር፤
መቅደላዊት ሚሏት ወጣ የምታድር፤
እናም የኔ እመቤት....
ያች ሀጽያተኛ በሰው የተገፋች፤
በርሱ ህግ ሳይሆን በርሷ ህግ የኖረች፤
ጥፋቷ ሲገባት ኳላ ተፀፀተች፤
እንባዋን አዝርታ አምላኳን ለመነች፤
ይቅርታ፣ ይቅርታ፣ ይቅርታ እያለች፤
እናም ይቅር አላት፤
ፍቅርና ምህረት ደርቦ አስተማራት፤
ውዴ....
በጅ የያዙት ወርቅ... ሆነና ተረቴ፤
አንችን ቤት አኑሬ ከሌሎቹ ጋራ እያወቅሁ መውጣቴ፤
አሁን ነው የገባኝ ወርቅ ቁጭ ብሎ መዳብ መመኘቴ።
እናልሽ አካሌ....
አይኔን በጨው አጥቤ ጥፋት አጥፍቻለሁ፤
ላንች ባልኩት አይኔ ሌላ አይቻለሁ፤
ውበት አሳስቶኝ እኔም ወስልቻለሁ፤
ዛሬ ግን.....
እንደ መቅደላዊት ዳግም ላላጠፋ ምህረት ጠይቄያለሁ፤
እግርሽ ስር ወድቄ እለምንሻለሁ፤
ውዷ የኔ እመቤት አንች የኔ ፍቅር፤
ምህረት አድርጊና ያንች ሁኘ ልቅር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ከይቅርታ በላይ?፤
ከመፀፀት በላይ?፤
ምንድን ነገር አለ በምረት የሚታይ?፤
እስኪ ጀሮ ስጭኝ አንድ ታሪክ ልንገርሽ፤
ጌታ ባካል ሳለ ምን ሆነ መሰለሽ፤
በፈጣሪ ጥበብ በውበቷ ኮርታ፤
የሰማዩን ሳይሆን የታች ቤቷን አይታ፤
አዳምን አማላ አዳምን እረታ፤
በሀጽያት ተዘፍቃ ዝሙትን አስፋፍታ፤
ትኖር ነበር አሉ በዚህ በኛ ምድር፤
መቅደላዊት ሚሏት ወጣ የምታድር፤
እናም የኔ እመቤት....
ያች ሀጽያተኛ በሰው የተገፋች፤
በርሱ ህግ ሳይሆን በርሷ ህግ የኖረች፤
ጥፋቷ ሲገባት ኳላ ተፀፀተች፤
እንባዋን አዝርታ አምላኳን ለመነች፤
ይቅርታ፣ ይቅርታ፣ ይቅርታ እያለች፤
እናም ይቅር አላት፤
ፍቅርና ምህረት ደርቦ አስተማራት፤
ውዴ....
በጅ የያዙት ወርቅ... ሆነና ተረቴ፤
አንችን ቤት አኑሬ ከሌሎቹ ጋራ እያወቅሁ መውጣቴ፤
አሁን ነው የገባኝ ወርቅ ቁጭ ብሎ መዳብ መመኘቴ።
እናልሽ አካሌ....
አይኔን በጨው አጥቤ ጥፋት አጥፍቻለሁ፤
ላንች ባልኩት አይኔ ሌላ አይቻለሁ፤
ውበት አሳስቶኝ እኔም ወስልቻለሁ፤
ዛሬ ግን.....
እንደ መቅደላዊት ዳግም ላላጠፋ ምህረት ጠይቄያለሁ፤
እግርሽ ስር ወድቄ እለምንሻለሁ፤
ውዷ የኔ እመቤት አንች የኔ ፍቅር፤
ምህረት አድርጊና ያንች ሁኘ ልቅር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤21👍4😢3
#ተአምር_ፈልቋል_በየመንገዱ
ዐይኔን ጨፍኜ -እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ - ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጉዋሮ ገብቷል- መርዶ ነጋሪ ::
እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
ርግብ መሬት ላይ -ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ሞልቷል- በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል- በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሰይጣን
ለመደነቂያ፥ ጊዜ ነው ያጣን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ዐይኔን ጨፍኜ -እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ - ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጉዋሮ ገብቷል- መርዶ ነጋሪ ::
እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
ርግብ መሬት ላይ -ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ሞልቷል- በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል- በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሰይጣን
ለመደነቂያ፥ ጊዜ ነው ያጣን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤18👍3
#በአንተ
በምወድድህ ፊት
ተመልከተዉ ዳንሴን
እግር አያያዜን
ወገብ አያያዜን
ያይን አወራወሬን
ቃላት አጣጣሌን ...
ተመልከት ዉበቴን
ተመልከተዉ ፊቴን
አስተዉል ሀሳቤን ፣ ጣዕምና ምሬቴን ።
ድካሜን
እረፍቴን
ድልና ሽንፈቴን
ተመልከተዉ ኩሌን
የአይኔን ልቦናዬን
ቅንድቤን ፣ ከንፈሬን ፣ ልቤን ፣ ኩላሊቴን
" ተመልከተኝ እኔን
ገላዉ የረገፈ አበባ መሆኔን "
ተመልከተዉ ሀሬን
ቀሚሴን ጥምጣሜን
ማማሩ
ማማሩ
ማነዉ የሚባሉት ደህነኞች ሲሰክሩ !?
ፍቅር ባፍቃሪዉ ፡ ፊት እንደምን ይሳሳል
የአፍቃሪስ ልብ ሲፈስ በምን ይታፈሳል ።
በምን ይከተታል፣
አፍቃሪ የዘራዉ የቀን ሌቱ ግጥም
ከልብ በቀረ እሳት ማን ይችላል ቢሰጠዉስ አቅም ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በምወድድህ ፊት
ተመልከተዉ ዳንሴን
እግር አያያዜን
ወገብ አያያዜን
ያይን አወራወሬን
ቃላት አጣጣሌን ...
ተመልከት ዉበቴን
ተመልከተዉ ፊቴን
አስተዉል ሀሳቤን ፣ ጣዕምና ምሬቴን ።
ድካሜን
እረፍቴን
ድልና ሽንፈቴን
ተመልከተዉ ኩሌን
የአይኔን ልቦናዬን
ቅንድቤን ፣ ከንፈሬን ፣ ልቤን ፣ ኩላሊቴን
" ተመልከተኝ እኔን
ገላዉ የረገፈ አበባ መሆኔን "
ተመልከተዉ ሀሬን
ቀሚሴን ጥምጣሜን
ማማሩ
ማማሩ
ማነዉ የሚባሉት ደህነኞች ሲሰክሩ !?
ፍቅር ባፍቃሪዉ ፡ ፊት እንደምን ይሳሳል
የአፍቃሪስ ልብ ሲፈስ በምን ይታፈሳል ።
በምን ይከተታል፣
አፍቃሪ የዘራዉ የቀን ሌቱ ግጥም
ከልብ በቀረ እሳት ማን ይችላል ቢሰጠዉስ አቅም ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤18
መነሻ ስእል
ኣያልቅም ይህ ጉዞ...
ማስመሰል-መተርጎም
በቀለም መዋኘት
በመስመር መዋኘት
ክብርሃን መጋጨት
ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት።
መፈለግ....... መፈለግ......
ኣዲስ ነገር መፍጠር
ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር።
ህይወትን መጠየቅ
ሃሳብን መጠየቅ
ኣለምን መጠየቅ
መሄድ መሄድ መሄድ....
ከጨረቃ በላይ
ከኮከቦች በላይ
ከሰማዩ በላይ።
መጉዋዝ ወደሌላ - ባዶ ቦታ መግባት
በሃሳብ መደበቅ፥
መፈለግ ማስገኘት።
ኣያልቅም ይህ ጉዞ....
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረክርስቶስ ደሰታ
ኣያልቅም ይህ ጉዞ...
ማስመሰል-መተርጎም
በቀለም መዋኘት
በመስመር መዋኘት
ክብርሃን መጋጨት
ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት።
መፈለግ....... መፈለግ......
ኣዲስ ነገር መፍጠር
ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር።
ህይወትን መጠየቅ
ሃሳብን መጠየቅ
ኣለምን መጠየቅ
መሄድ መሄድ መሄድ....
ከጨረቃ በላይ
ከኮከቦች በላይ
ከሰማዩ በላይ።
መጉዋዝ ወደሌላ - ባዶ ቦታ መግባት
በሃሳብ መደበቅ፥
መፈለግ ማስገኘት።
ኣያልቅም ይህ ጉዞ....
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረክርስቶስ ደሰታ
❤12👍1
የስጦታ ፈረስ ባይታይም ጥርሱ
መቼ ሆነ ከቶ መወደድ መርከሱ
ለነገር ነው እንጂ ህሊናችን አብዶ
ምን ይሰራለታል ለመላጣ ሚዶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መቼ ሆነ ከቶ መወደድ መርከሱ
ለነገር ነው እንጂ ህሊናችን አብዶ
ምን ይሰራለታል ለመላጣ ሚዶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🔥11🥰6
#ሹም_ሽር
አንቺ እቴ ፔንዱለም
ፌዝና የምርሽ የተደቃቀለ፤
እዚህ ሲሉሽ እዛ
ነፍስሽና ስጋሽ ሁሌ እየዋለለ፤
በውበትሽ ግርማ
አፍቃሪ ከጉያሽ ሲገባ እየዋለ፤
ልቡ እየቀለለ፥
ሰርክ እየማለለ...
በሀሰት ግብርሽ ላይ
ሀቂቃዊ ፍቅሩን ገምዶና ጠቅልሎ፤
ስንቱ አዳም መሰለሽ
በዥዋዥዌሽ ክር የሞተው ተሰቅሎ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ አብርሃም ፍቅሬ
አንቺ እቴ ፔንዱለም
ፌዝና የምርሽ የተደቃቀለ፤
እዚህ ሲሉሽ እዛ
ነፍስሽና ስጋሽ ሁሌ እየዋለለ፤
በውበትሽ ግርማ
አፍቃሪ ከጉያሽ ሲገባ እየዋለ፤
ልቡ እየቀለለ፥
ሰርክ እየማለለ...
በሀሰት ግብርሽ ላይ
ሀቂቃዊ ፍቅሩን ገምዶና ጠቅልሎ፤
ስንቱ አዳም መሰለሽ
በዥዋዥዌሽ ክር የሞተው ተሰቅሎ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ አብርሃም ፍቅሬ
❤6
#የተሸነፈ_ኩራት!!
በቃኝ!!! ያልሽኝ ዕለት መገፋቴ አሞኝ
እልህ ጉልበት ሆኖኝ
ካንቺ ሌላ ብዬ
ከጣልኩዋቸው መሀል አንዱዋን አሳምኜ
አንቺን እንዳቄልኩሽ እሱዋንም እንዳንቺው ካንቺ ሌላ ብዬ
ቂ…..ቂ….ቂ…..ቂ..
የመጣሌን ህመም የግፊሽን ጉዳት
በእሱዋ እቅፍ ለመርሳት
የሌለኝን መውደድ ያልነካኝን ፍቅር
ሰርክ ስዘረዝር
ስሜቴ ከእምነቴ እየተጣረሰ
እውነቴም ከሐሰቴ እየተካሰሰ፡፡
ይበለኝ!!..
በማስመሰል ብቻ
በመዋሸት ብቻ
ከንፈር ተሳልሜ ትከሻ ታቅፌ
ንጹህ ገላዋ ላይ ሙት ገላ አሳርፌ
ወይኔ..
ልቤ አንቺን እያለኝ
እኔ ኩራት አስሮኝ
በጸጸት ስመግል በቁጭት ስነፍር
እውነቴን ቀበርኩዋት ከሀሰት እግር ስር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በቃኝ!!! ያልሽኝ ዕለት መገፋቴ አሞኝ
እልህ ጉልበት ሆኖኝ
ካንቺ ሌላ ብዬ
ከጣልኩዋቸው መሀል አንዱዋን አሳምኜ
አንቺን እንዳቄልኩሽ እሱዋንም እንዳንቺው ካንቺ ሌላ ብዬ
ቂ…..ቂ….ቂ…..ቂ..
የመጣሌን ህመም የግፊሽን ጉዳት
በእሱዋ እቅፍ ለመርሳት
የሌለኝን መውደድ ያልነካኝን ፍቅር
ሰርክ ስዘረዝር
ስሜቴ ከእምነቴ እየተጣረሰ
እውነቴም ከሐሰቴ እየተካሰሰ፡፡
ይበለኝ!!..
በማስመሰል ብቻ
በመዋሸት ብቻ
ከንፈር ተሳልሜ ትከሻ ታቅፌ
ንጹህ ገላዋ ላይ ሙት ገላ አሳርፌ
ወይኔ..
ልቤ አንቺን እያለኝ
እኔ ኩራት አስሮኝ
በጸጸት ስመግል በቁጭት ስነፍር
እውነቴን ቀበርኩዋት ከሀሰት እግር ስር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤14🔥1👏1
#ኑረሽ_እይው_በቃ
ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ
ዘለሽ አትጠግቢ፥ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሃ ፅጌ ነው ፤አመት ሙሉ ላንቺ
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
(የፍጥረት ሰቆቃ)
ለጋ ነው ላ'እምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኖረሽ እይው በቃ ፤
በየጎዳናሽ ላይ ፥አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፥ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ፥ፈልቶልሽ ፥አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፥ የብቻነት ሸክሙን
አዎ!
መፈቀር ፥ መታጀብ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ነፋስ ማቀፍ፥
አንዳንዴም ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት ፥የማይልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኑረሽ እይው በቃ፤
አንቺ ደስታ ወዳጅ
በለምለም አፀድ ውስጥ፥ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፤ እንደ ጣኦስ ቀልማ
እንዳትሸወጂ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ህይወትም እንደ ጃርት፥የሾህ ቀሚስ አላት፤
ተድላም ከሃዘን ፣ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሳቅ በስተጀርባ፥ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላ ምን ልበልሽ ፥
ኑረሽ እይው በቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍በዕውቀቱ ስዩም
ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ
ዘለሽ አትጠግቢ፥ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሃ ፅጌ ነው ፤አመት ሙሉ ላንቺ
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
(የፍጥረት ሰቆቃ)
ለጋ ነው ላ'እምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኖረሽ እይው በቃ ፤
በየጎዳናሽ ላይ ፥አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፥ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ፥ፈልቶልሽ ፥አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፥ የብቻነት ሸክሙን
አዎ!
መፈቀር ፥ መታጀብ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ነፋስ ማቀፍ፥
አንዳንዴም ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት ፥የማይልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኑረሽ እይው በቃ፤
አንቺ ደስታ ወዳጅ
በለምለም አፀድ ውስጥ፥ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፤ እንደ ጣኦስ ቀልማ
እንዳትሸወጂ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ህይወትም እንደ ጃርት፥የሾህ ቀሚስ አላት፤
ተድላም ከሃዘን ፣ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሳቅ በስተጀርባ፥ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላ ምን ልበልሽ ፥
ኑረሽ እይው በቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍በዕውቀቱ ስዩም
❤13👍8🔥1
#አትገረም
አይክፋህ አትዘን ወንድሜ!
ነግሬህ ነበር እኮ ድሮ አስቀድሜ
አደናቅፎህ ብትወድቅ፥ቧጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን ማንንም አትማ
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጂ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አይክፋህ አትዘን ወንድሜ!
ነግሬህ ነበር እኮ ድሮ አስቀድሜ
አደናቅፎህ ብትወድቅ፥ቧጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን ማንንም አትማ
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጂ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤24👍10👏2
#ባዶ_ቤት_በክረምት
አንች የሌለሽበት
ዝም ጸጥ ብቻ
ጣሪያ መጫወቻ፡፡
አመሻሽ
ኦና ቤት
አንች የሌለሽበት
ፀጥ -ረጭ፣ ብቻ
ወለል መጫወቻ፡፡
ጠረጴዛ፣
ወንበር፣
አንድ አልጋ፣
አንድ በር፣
አንድ እኔ፣
አንድ መስኮት፣
ባዶ ቤ . . . ት በክረምት
አንች የሌለሽበት፣
ፀጥ-ረጭ ብቻ
እም መጫወቻ
ዝም መደሰቻ
ዝም ዝም
ዝም ዝም
ዝም ዝም ለብቻ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጌትነት እንየው
አንች የሌለሽበት
ዝም ጸጥ ብቻ
ጣሪያ መጫወቻ፡፡
አመሻሽ
ኦና ቤት
አንች የሌለሽበት
ፀጥ -ረጭ፣ ብቻ
ወለል መጫወቻ፡፡
ጠረጴዛ፣
ወንበር፣
አንድ አልጋ፣
አንድ በር፣
አንድ እኔ፣
አንድ መስኮት፣
ባዶ ቤ . . . ት በክረምት
አንች የሌለሽበት፣
ፀጥ-ረጭ ብቻ
እም መጫወቻ
ዝም መደሰቻ
ዝም ዝም
ዝም ዝም
ዝም ዝም ለብቻ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጌትነት እንየው
❤17👍2
#ጎረቤት_እንደ_እሳት
ሰው ወዳጁን መምረጥ የሚችል ቢሆንም
ጎረቤት መምረጡ ማዳገቱ አይቀርም
ከጎረቤት መኖር ሐቁ ይህ ከሆነ
ጎረቤትን አምኖ እሱም ከታመነ
ጎረቤትን መጉዳት አራስን መጉዳት
መሆኑን ይረዳል ያውቀዋል በእውነት
ሰውን ካጋጠመው የጎረቤት ጥሩ
ለችግሩ እሚደርስ ከዘመድ ከእድሩ
ጎረቤትን በክብር በፍቅር መያዝ
ከመጥቀም በስተቀር የለውም መዘዝ
ይህን የተረዳ ምሥጢሩን ያወቀ
የስጋቱ አግረ ሙቅ ተፈታ ወለቀ
ጎረቤት እንደሳት ሊጠቅምም ሊጎዳ
የሚችል መሆ ኑን ሰው በውል ይረዳ
የጎረቤት ኑሮ ደንቡን ያላወቁ
ጉዳቱ ከጥቅሙ አይባስ ይጠንቀቁ!
ድንገት በአጋጣሚ አሳት እንደሚፋጅ
ለሰው ጎረቤቱ ካልሆነው የሚበጅ
ከነገር ለመራቅ አጥር ይለያቸው
አስታራቂ ዳኛ እንዲሆንላቸው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሰው ወዳጁን መምረጥ የሚችል ቢሆንም
ጎረቤት መምረጡ ማዳገቱ አይቀርም
ከጎረቤት መኖር ሐቁ ይህ ከሆነ
ጎረቤትን አምኖ እሱም ከታመነ
ጎረቤትን መጉዳት አራስን መጉዳት
መሆኑን ይረዳል ያውቀዋል በእውነት
ሰውን ካጋጠመው የጎረቤት ጥሩ
ለችግሩ እሚደርስ ከዘመድ ከእድሩ
ጎረቤትን በክብር በፍቅር መያዝ
ከመጥቀም በስተቀር የለውም መዘዝ
ይህን የተረዳ ምሥጢሩን ያወቀ
የስጋቱ አግረ ሙቅ ተፈታ ወለቀ
ጎረቤት እንደሳት ሊጠቅምም ሊጎዳ
የሚችል መሆ ኑን ሰው በውል ይረዳ
የጎረቤት ኑሮ ደንቡን ያላወቁ
ጉዳቱ ከጥቅሙ አይባስ ይጠንቀቁ!
ድንገት በአጋጣሚ አሳት እንደሚፋጅ
ለሰው ጎረቤቱ ካልሆነው የሚበጅ
ከነገር ለመራቅ አጥር ይለያቸው
አስታራቂ ዳኛ እንዲሆንላቸው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤11🔥1
#ይበቃል
መንገዱም ቆሽሿል ደፍርሷል ባህሩ፡
ወጣቱም ተሰዷል ወጥቷል ከሀገሩ ፡
የተራበች ሀገር መዋደድ የራቃት፡
ዚፕ እንደሌለው ኪስ በዝቷል የሚሰርቃት፡
ወንበር ላይ ተቀምጦ በተናገረው ቃል፡
በማያውቀው ነገር የድሀ ልጅ ያልቃል፡
እርሜን አውጥቻለሁ ሰላም እንደራቀኝ፡
ከወንድሜ ሰርቆ ይለኛል ደብቀኝ፡
በቃኝ ሰልችቶኛል ከንቱ ነች ይቺ ዓለም፡
ላመነችው እንጂ ላመናት አትሆንም፡
ድንገት ምህረት ቢልክ የአምላክ ፍቃድ ቢሆን፡
ያኔ እመለሳለሁ ሰውነት ሰው ሲሆን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሀሽ ማል (ብቸኛው)
መንገዱም ቆሽሿል ደፍርሷል ባህሩ፡
ወጣቱም ተሰዷል ወጥቷል ከሀገሩ ፡
የተራበች ሀገር መዋደድ የራቃት፡
ዚፕ እንደሌለው ኪስ በዝቷል የሚሰርቃት፡
ወንበር ላይ ተቀምጦ በተናገረው ቃል፡
በማያውቀው ነገር የድሀ ልጅ ያልቃል፡
እርሜን አውጥቻለሁ ሰላም እንደራቀኝ፡
ከወንድሜ ሰርቆ ይለኛል ደብቀኝ፡
በቃኝ ሰልችቶኛል ከንቱ ነች ይቺ ዓለም፡
ላመነችው እንጂ ላመናት አትሆንም፡
ድንገት ምህረት ቢልክ የአምላክ ፍቃድ ቢሆን፡
ያኔ እመለሳለሁ ሰውነት ሰው ሲሆን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሀሽ ማል (ብቸኛው)
❤19👏1
#ልጫር_ልሞጫጭረው!
ቃላት አሽሞንሙኖ በፊደላት ደምቆ
በምሁር ቃል ጠቀስ ቢመጥቅ ተራቆ
ቅኔው ቢወሳሰብ አንባቢ ካልፈታው
ጠቢባዊው ሁሉ ለማነው የሚጽፈው ?
ህግጋት ጠብቆ ቀለማትን ቆጥሮ
ምጣኔን መጥኖ ሀረጋትን ቋጥሮ
ምሁሩ ወንድሜ ቅኝት ተከትሎ
እኔን ፊደላዊ ከጥበብ ነጥሎ
እርሱ ባወቀው ልክ መብቴን ከልሎ
ሲከሰኝ ይውላል እንዳትገጥም ብሎ
አንተሙ ለተማሩት ለተመራመሩት
እኔም ለቢጤየ ፊደል ለሚገድፉት
በተሰጠን ድንበር እውቀታዊ ልኬት
አንተም እንዳዋቂ ሳድስን ዝለላት
እኔ ግን ስወዳት ስን እንዴት ልጣላት?
ለስሜ መጠሪያ ሁልጊዜም ከፊት ናት
አንተም ለተማሩት ለተመራመሩት
ስንቴም እጭራለሁ ፊደል ለሚገድፉት
ግን ማወቅ ጥሩ ነው አለማወቅ ክፉ
ሳያውቁ አውቂያለሁ እረዘመ ሰልፉ
አንተ አስተምረኸኝ ለእውቀት እስከበቃ
ልጫር ልሞጫጭረው አትከልክለኝ በቃ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ቃላት አሽሞንሙኖ በፊደላት ደምቆ
በምሁር ቃል ጠቀስ ቢመጥቅ ተራቆ
ቅኔው ቢወሳሰብ አንባቢ ካልፈታው
ጠቢባዊው ሁሉ ለማነው የሚጽፈው ?
ህግጋት ጠብቆ ቀለማትን ቆጥሮ
ምጣኔን መጥኖ ሀረጋትን ቋጥሮ
ምሁሩ ወንድሜ ቅኝት ተከትሎ
እኔን ፊደላዊ ከጥበብ ነጥሎ
እርሱ ባወቀው ልክ መብቴን ከልሎ
ሲከሰኝ ይውላል እንዳትገጥም ብሎ
አንተሙ ለተማሩት ለተመራመሩት
እኔም ለቢጤየ ፊደል ለሚገድፉት
በተሰጠን ድንበር እውቀታዊ ልኬት
አንተም እንዳዋቂ ሳድስን ዝለላት
እኔ ግን ስወዳት ስን እንዴት ልጣላት?
ለስሜ መጠሪያ ሁልጊዜም ከፊት ናት
አንተም ለተማሩት ለተመራመሩት
ስንቴም እጭራለሁ ፊደል ለሚገድፉት
ግን ማወቅ ጥሩ ነው አለማወቅ ክፉ
ሳያውቁ አውቂያለሁ እረዘመ ሰልፉ
አንተ አስተምረኸኝ ለእውቀት እስከበቃ
ልጫር ልሞጫጭረው አትከልክለኝ በቃ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤8👏1