#ልቤ_ምን_አጠፋ?
እኔስ መስሎኝ ነበር ካንጀት ያፈቀርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?
ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አርገኸኝ ለማን እሆናለሁ
እንግዲህ ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም አልጠጣም ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣
አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
ጊዜው ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ ይፈርዳል 💔
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እኔስ መስሎኝ ነበር ካንጀት ያፈቀርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?
ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አርገኸኝ ለማን እሆናለሁ
እንግዲህ ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም አልጠጣም ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣
አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
ጊዜው ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ ይፈርዳል 💔
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤9👍2🥰1
#ስሞት_አትቅበረኝ
በህይወት እያለሁ እንባየን ካልጠረግህ
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ
ስታመም ዝም ካልህ
እራቤ ካልገባህ
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ
ደብዛዛው ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ
ተልካሻው ኑሮዬን ካላሰናዳካው
የተደለደለ ቦታ ካላስያዝከው
ማየት የተሳነው ፍቅሬን ካልመራህው
እውነት እልካለሁ ውዴ
ስሞት አትቅበረኝ
እንባም አታንባልኝ
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ
እንደሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ
እጅጉን አምርሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ
ስታመም አስታመኝ
ስከፋ አፅናናኝ
ስወድቅ ደግፈኝ
የጭንቀቴን ብሶት
የውስጤን ተረዳኝ
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ
ተልካሻው ኑሮዬን
ፈጥነህ አሰናዳው
የተደላደለ ቦታውን አሲዘው
ማየት የተሳነው
ልቤን ይዘህ ምራው
ደስታና ፍቅርን
ከልብ አስተምረኝ
ሁልጊዜ ሳቅልኝ
ይኸ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በህይወት እያለሁ እንባየን ካልጠረግህ
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ
ስታመም ዝም ካልህ
እራቤ ካልገባህ
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ
ደብዛዛው ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ
ተልካሻው ኑሮዬን ካላሰናዳካው
የተደለደለ ቦታ ካላስያዝከው
ማየት የተሳነው ፍቅሬን ካልመራህው
እውነት እልካለሁ ውዴ
ስሞት አትቅበረኝ
እንባም አታንባልኝ
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ
እንደሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ
እጅጉን አምርሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ
ስታመም አስታመኝ
ስከፋ አፅናናኝ
ስወድቅ ደግፈኝ
የጭንቀቴን ብሶት
የውስጤን ተረዳኝ
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ
ተልካሻው ኑሮዬን
ፈጥነህ አሰናዳው
የተደላደለ ቦታውን አሲዘው
ማየት የተሳነው
ልቤን ይዘህ ምራው
ደስታና ፍቅርን
ከልብ አስተምረኝ
ሁልጊዜ ሳቅልኝ
ይኸ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍18❤12
#ከአበባ_ተማሪ
አንዲት ፅጌሬዳ አንዲት እምቡጥ አበባ
አይን የምትሰርቅ ሆድ የምታባባ
አንዲት ፅጌሬዳ ሰፈሬ ነበረች
አልፈነዳም ብላ ብዙ አመት የኖረች
ግና ምን ያረጋል
ይህን ውበት አይቶ የአዳም ልጅ ቢከባት
እየኮተኮተ ውሀ እየመገበ ሰው ቢንከባከባት
ለሷ አሽከር የሆነ አፍቃሪ መሰላት
እናም
የልብልብ ተሰምቷት ድንገት ብትፈነዳ
ያ ሞትኩልሽ ያላት ሊያርዳት ተሰናዳ
እባክሽ ውዴ ሆይ ከአበባ ተማሪ ከእምቡጧ
ተረጂ
አብበሽ አብበሽ ድንገት ስትፈነጂ
አፍቃሪ አታገኚም በላተኛን እንጂ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አንዲት ፅጌሬዳ አንዲት እምቡጥ አበባ
አይን የምትሰርቅ ሆድ የምታባባ
አንዲት ፅጌሬዳ ሰፈሬ ነበረች
አልፈነዳም ብላ ብዙ አመት የኖረች
ግና ምን ያረጋል
ይህን ውበት አይቶ የአዳም ልጅ ቢከባት
እየኮተኮተ ውሀ እየመገበ ሰው ቢንከባከባት
ለሷ አሽከር የሆነ አፍቃሪ መሰላት
እናም
የልብልብ ተሰምቷት ድንገት ብትፈነዳ
ያ ሞትኩልሽ ያላት ሊያርዳት ተሰናዳ
እባክሽ ውዴ ሆይ ከአበባ ተማሪ ከእምቡጧ
ተረጂ
አብበሽ አብበሽ ድንገት ስትፈነጂ
አፍቃሪ አታገኚም በላተኛን እንጂ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍14❤5🥰3👌3
ባይኖራት ቢከፋት
ምንም ቢቸግራት
ምን ብትጎሳቆል
መከራ ቢከባት
ለልጆቼ የምትል
እሷን እየራባት
ምንም ግዜም ቢሆን
እናት ያው እናት ናት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መልካም የእናቶቾ ቀን
እማ እወድሻለሁ
ምንም ቢቸግራት
ምን ብትጎሳቆል
መከራ ቢከባት
ለልጆቼ የምትል
እሷን እየራባት
ምንም ግዜም ቢሆን
እናት ያው እናት ናት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መልካም የእናቶቾ ቀን
❤49👍6🔥3
#ፈልጌሽ_ብመጣ
እንደወፍ በርሬ
ጫካው ተሻግሬ
ማንም እንዳይቀርበኝ ዙርያዬን አጥሬ
ከወንዙ ዳር ቆሜ
ልቤን አስታምሜ
ከተራሮች ጀርባ በለሷን አልሜ
አጠገቤ ካለው
ከሚንፎለፎለው
ከድንጋይ ጋ ሲጋጭ ከሚንቦጫረቀው
ልብስ አወላልቄ
በምዕናብ ጠልቄ
ሀጥያተኛ ልቤን በፍቅርሽ አጥምቄ
ከፍሳሽ ጅረቱ
ከድንጋይ ባልጩቱ
ግንባሬን ሳጋጨው ቁልቁል ስወረወር
በዛ ፈታኝ ሰዐት ስቃዬ ላይ ሳይቀር
ስለኔ ረስቼ እያሰብኩሽ ነበር
ካፈር ብስባሹ
ከማሳ ፍሳሹ
የማጀት እልፍኙ ደራሽ ተቀላቅሎ
የጣባው ጠብታ ውቅያኖስ አክሎ
ከመነጨሁበት ከቀዬው ኮብልሎ
ከተራሮች መሀል እያቆራረጠ
ቁልቁለት ሸለቆ ሜዳ እየመረጠ
ገጠሩን ጨርሶ ከተማ ዘለቀ
ደለልም አጋጥሞት ለሁለት ሲከፈል
እኔ ያለሁበቱ በናንተ ቤት በኩል
ከበራቹ ደጃፍ ለመፍሰስ ስሞክር
ሽታና ጠረንሽ ላጣጥመው ስጥር
ያልታደልኩ አፍቃሪ ዉዴ ምን ያደርጋል?
ደረቱን ታቅፈሽ
ከላይ ምታሻሽው ሌላ ወንድ ይሸታል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እንደወፍ በርሬ
ጫካው ተሻግሬ
ማንም እንዳይቀርበኝ ዙርያዬን አጥሬ
ከወንዙ ዳር ቆሜ
ልቤን አስታምሜ
ከተራሮች ጀርባ በለሷን አልሜ
አጠገቤ ካለው
ከሚንፎለፎለው
ከድንጋይ ጋ ሲጋጭ ከሚንቦጫረቀው
ልብስ አወላልቄ
በምዕናብ ጠልቄ
ሀጥያተኛ ልቤን በፍቅርሽ አጥምቄ
ከፍሳሽ ጅረቱ
ከድንጋይ ባልጩቱ
ግንባሬን ሳጋጨው ቁልቁል ስወረወር
በዛ ፈታኝ ሰዐት ስቃዬ ላይ ሳይቀር
ስለኔ ረስቼ እያሰብኩሽ ነበር
ካፈር ብስባሹ
ከማሳ ፍሳሹ
የማጀት እልፍኙ ደራሽ ተቀላቅሎ
የጣባው ጠብታ ውቅያኖስ አክሎ
ከመነጨሁበት ከቀዬው ኮብልሎ
ከተራሮች መሀል እያቆራረጠ
ቁልቁለት ሸለቆ ሜዳ እየመረጠ
ገጠሩን ጨርሶ ከተማ ዘለቀ
ደለልም አጋጥሞት ለሁለት ሲከፈል
እኔ ያለሁበቱ በናንተ ቤት በኩል
ከበራቹ ደጃፍ ለመፍሰስ ስሞክር
ሽታና ጠረንሽ ላጣጥመው ስጥር
ያልታደልኩ አፍቃሪ ዉዴ ምን ያደርጋል?
ደረቱን ታቅፈሽ
ከላይ ምታሻሽው ሌላ ወንድ ይሸታል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍12👏4❤3
#ዛሬም_ወድሻለው
ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ
በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ
የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ
ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስከምቀር እስከለተ ሞቴ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ
በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ
የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ
ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስከምቀር እስከለተ ሞቴ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🥰11❤10👍10👏1
#ነይልኝ
ሜክሲኮ ጎዳና ወክ የበላንበት
ከዓመታት በኋላ ብቻዬን ሄድኩበት
ለካ ሰፊው መንገድ ልብ ሚመስጠው
ካንቺ ጋር አብሬ በፍቅር ስጓዝ ነው
አሁን ገና ገባኝ
የሜክሲኮ ምድር እንደሾህ ሲወጋኝ
በጥንዶች ጋጋታ በወያላው ጩኸት
መካከል እያለን በብቻችን አለም ምንደማመጠው ዛሬ ትዝ ብሎኝ መንፈሴን ጨነቀው
በክረምት ዝናብ ሁሉም ሰው ሲጠለል
እኔና አንቺ ብቻ ያለምንም ጥላ ስንቦርቅ ስንዘል ያሳለፍነው ሁሉ አሁን ሊያስታውሰኝ
ይኸው ዝናብ መጣ ዳግም ሊመልሰኝ
ከሰማይ ሚፈሰው የዝናብ ጠብታ
ያንቺን ትዝታዎች ይዞብኝ ቢመጣ
ባዶነት ተሰማኝ መፈጠሬን ጠላሁ
ነይልኝ አለሜ ለብቻዬ ፈራሁ
ያኔ ስንፋቀር ያስተዋሉን ሁሉ
ብቻዬን ሲያዩኝ ያንሾካሹካሉ
ዝናቡ ያወራል
ያሳለፍነው ሁሉ መልሶይነግረኛል
ወያላው ይጣራል
ፒያሳ! ፒያሳ! “ና ግባ!” ይለኛል
የፒያሳን ምሽት ደግሞ ያስታውሰኛል
ታክሲው ውስጥ ገብቼ ወንበር ላይ ስቀመጥ ወንበሩ አቃጠለኝ ፈጀኝ እንደረመጥ
እሱም ላይ ትዝታ ናፍቆት ትተሸበት
አላስቀምጥ አለኝ አንቺ ስትቀሪበት
መስኮቱን ከፍቼ አሻግሬ ሳየው
ጎዳናው በሙሉ ያንቺ ትዝታ ነው
ከታክሲ እየወረድኩ ታክሲ ብቀይርም
ብሬን ከሰርኩ እንጂ ትዝታሽ አይቀርም
ነይልኝ አለሜ ጎዳናው ሃገሩ ካላንቺ አያምርም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሜክሲኮ ጎዳና ወክ የበላንበት
ከዓመታት በኋላ ብቻዬን ሄድኩበት
ለካ ሰፊው መንገድ ልብ ሚመስጠው
ካንቺ ጋር አብሬ በፍቅር ስጓዝ ነው
አሁን ገና ገባኝ
የሜክሲኮ ምድር እንደሾህ ሲወጋኝ
በጥንዶች ጋጋታ በወያላው ጩኸት
መካከል እያለን በብቻችን አለም ምንደማመጠው ዛሬ ትዝ ብሎኝ መንፈሴን ጨነቀው
በክረምት ዝናብ ሁሉም ሰው ሲጠለል
እኔና አንቺ ብቻ ያለምንም ጥላ ስንቦርቅ ስንዘል ያሳለፍነው ሁሉ አሁን ሊያስታውሰኝ
ይኸው ዝናብ መጣ ዳግም ሊመልሰኝ
ከሰማይ ሚፈሰው የዝናብ ጠብታ
ያንቺን ትዝታዎች ይዞብኝ ቢመጣ
ባዶነት ተሰማኝ መፈጠሬን ጠላሁ
ነይልኝ አለሜ ለብቻዬ ፈራሁ
ያኔ ስንፋቀር ያስተዋሉን ሁሉ
ብቻዬን ሲያዩኝ ያንሾካሹካሉ
ዝናቡ ያወራል
ያሳለፍነው ሁሉ መልሶይነግረኛል
ወያላው ይጣራል
ፒያሳ! ፒያሳ! “ና ግባ!” ይለኛል
የፒያሳን ምሽት ደግሞ ያስታውሰኛል
ታክሲው ውስጥ ገብቼ ወንበር ላይ ስቀመጥ ወንበሩ አቃጠለኝ ፈጀኝ እንደረመጥ
እሱም ላይ ትዝታ ናፍቆት ትተሸበት
አላስቀምጥ አለኝ አንቺ ስትቀሪበት
መስኮቱን ከፍቼ አሻግሬ ሳየው
ጎዳናው በሙሉ ያንቺ ትዝታ ነው
ከታክሲ እየወረድኩ ታክሲ ብቀይርም
ብሬን ከሰርኩ እንጂ ትዝታሽ አይቀርም
ነይልኝ አለሜ ጎዳናው ሃገሩ ካላንቺ አያምርም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍11❤7👏3
#አንችን_ትቼ ...
የተለየሽኝ ቀን ......
ለምን ተለየሽው?
ብሎ ለጠየቀሽ
ታሚኛለሽ አሉ
ብር የለውም ብለሽ!
ፍቅሬ ትርጉም ካጣ
ካስወደደኝ ብሬ
ሳገኝ ትመጫለሽ
ስታይኝ ከብሬ
ያኔ ስትመጭ ......
ድል ነስቼ ህልሜን
እንዳትሄጅብኝ ....
ላላ አድርጌ ፍቅሬን
እንከባከባለሁ .....
አንችን ትቼ ብሬን!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የተለየሽኝ ቀን ......
ለምን ተለየሽው?
ብሎ ለጠየቀሽ
ታሚኛለሽ አሉ
ብር የለውም ብለሽ!
ፍቅሬ ትርጉም ካጣ
ካስወደደኝ ብሬ
ሳገኝ ትመጫለሽ
ስታይኝ ከብሬ
ያኔ ስትመጭ ......
ድል ነስቼ ህልሜን
እንዳትሄጅብኝ ....
ላላ አድርጌ ፍቅሬን
እንከባከባለሁ .....
አንችን ትቼ ብሬን!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍18😡4❤2🥰1🤝1
#መልስልኝ
ያኔ ካንተ ጋራ፤
ፍቅርን ስንጋራ፤
መውደድን ስንቅም፤
ሀዘንኮ አናውቅም።
በሳቅ ተሸፍነን፤
በደስታ ታጅበን፤
ፍቅርን ስናዜማት፤
እንደ ንብ ስንቀስማት፤
በጨረቃ ብርሀን በወፎች ዝማሬ፤
በደስታ ባህር ውስጥ ካንተ ጋር አብሬ፤
ባዜምልህ ፍቅርን ብቀኝልህ ቅኔ፤
አልሰለችም ነበር አንተ ካለህ ጎኔ።
እንዲ ነበርኩ ያኔ
የወደደ አበደ በሚሉት አምኜ፤
በልብህ ገዳም ውስጥ ለፍቅርህ መንኜ፤
ልቤም በሙሉ እምነት ባንተ ተደግፎ፤
ድንገት ሸርተት ብትል ማገሩ ተዛንፎ፤
ላይነቃ አሸለበ ላይሳሳ አመረረ፤
ላይድን ቆሰለብህ ላይነጣ ጠቆረ፤
እንዲያ እንዳልሆነልህ እንዳላፈቀረ፤
በክህደትህ ዱላ በ'ጅህ ተሰበረ።
ውስጠቴ አዘነብህ ጠላኸው አፍቅረህ፤
ሳቄንም ወሰድከው በለቅሶ ቀይረህ።
እናም ስማኝ ውዴ፤
ላስቸግርህ አንዴ፤
ቀርቶብኛል ፍቅርህ ይቅርብህ መውደዴ፤
ግና ተለመነኝ እሺ በል ወዳጄ፤
ሳቄን መልስልኝ
መኖር እንዲያስችለኝ ከሰው ተላምጄ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ያኔ ካንተ ጋራ፤
ፍቅርን ስንጋራ፤
መውደድን ስንቅም፤
ሀዘንኮ አናውቅም።
በሳቅ ተሸፍነን፤
በደስታ ታጅበን፤
ፍቅርን ስናዜማት፤
እንደ ንብ ስንቀስማት፤
በጨረቃ ብርሀን በወፎች ዝማሬ፤
በደስታ ባህር ውስጥ ካንተ ጋር አብሬ፤
ባዜምልህ ፍቅርን ብቀኝልህ ቅኔ፤
አልሰለችም ነበር አንተ ካለህ ጎኔ።
እንዲ ነበርኩ ያኔ
የወደደ አበደ በሚሉት አምኜ፤
በልብህ ገዳም ውስጥ ለፍቅርህ መንኜ፤
ልቤም በሙሉ እምነት ባንተ ተደግፎ፤
ድንገት ሸርተት ብትል ማገሩ ተዛንፎ፤
ላይነቃ አሸለበ ላይሳሳ አመረረ፤
ላይድን ቆሰለብህ ላይነጣ ጠቆረ፤
እንዲያ እንዳልሆነልህ እንዳላፈቀረ፤
በክህደትህ ዱላ በ'ጅህ ተሰበረ።
ውስጠቴ አዘነብህ ጠላኸው አፍቅረህ፤
ሳቄንም ወሰድከው በለቅሶ ቀይረህ።
እናም ስማኝ ውዴ፤
ላስቸግርህ አንዴ፤
ቀርቶብኛል ፍቅርህ ይቅርብህ መውደዴ፤
ግና ተለመነኝ እሺ በል ወዳጄ፤
ሳቄን መልስልኝ
መኖር እንዲያስችለኝ ከሰው ተላምጄ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍15❤6👌3
#የት_ነበርክ
ፍሬያቸው ሲረግፍ አበቦች ሲደርቁ፥
ጨረቃም ደም መስላ ኮከቦች ሲወድቁ፥
የወፎች ዝማሬ እንደ እንጀራ ርቦኝ፥
ሰላም ደስታን ሳጣ ሀዘን ፅልመት ከቦኝ፥
መኖሬን ሳማርር ለመኖርህ ብዬ፥
ለደስታህ ስለፋ የኔን ቀን ገድዬ፥
አለሁኝ 'ምትለኝ ድንገት ደርሰህ ማታ፥
ሰው ሲጠማ ልቤ የት ነበርክ ያን ለታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ፍሬያቸው ሲረግፍ አበቦች ሲደርቁ፥
ጨረቃም ደም መስላ ኮከቦች ሲወድቁ፥
የወፎች ዝማሬ እንደ እንጀራ ርቦኝ፥
ሰላም ደስታን ሳጣ ሀዘን ፅልመት ከቦኝ፥
መኖሬን ሳማርር ለመኖርህ ብዬ፥
ለደስታህ ስለፋ የኔን ቀን ገድዬ፥
አለሁኝ 'ምትለኝ ድንገት ደርሰህ ማታ፥
ሰው ሲጠማ ልቤ የት ነበርክ ያን ለታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍9❤7🏆4🥰2
#ኢትዮጵያዊ_ነኝ!
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣
እንደ አክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣
የጊዜ ሞገድ ያልነቀነቀኝ፣
የመከራ ዶፍ ያላደቀቀኝ፣
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣
ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣
በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣
ራስምታቴን በዳማከሴ፣
ነቅዬ 'ምጥል፣
አገር በነገር የማብጠለጥል፣
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣
በዘብ በኬላ የማልገታ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣
እንደ አክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣
የጊዜ ሞገድ ያልነቀነቀኝ፣
የመከራ ዶፍ ያላደቀቀኝ፣
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣
ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣
በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣
ራስምታቴን በዳማከሴ፣
ነቅዬ 'ምጥል፣
አገር በነገር የማብጠለጥል፣
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣
በዘብ በኬላ የማልገታ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
👍11❤2
#ትንሽ_ነበር_ለካ!!
ለሚሻግት ምግብ አድሮ ላይበላ
እምነቱን ይሸጣል ሰው ሆዱን ሊሞላ
ከሰው በተረፈ በተናቀ እንጀራ
እምነቱን የሚሸጥ እየበላ አደራ
የልብ ድሃ ነው አዕምሮ የሌለው
ስልጣንን ፍለጋ በሆድ የተገዛው
በይሁዳ ሚዛን እራሱን የለካ
ትልቅ ያልነው ሁሉ ትንሽ ነበር ለካ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ብታሙ
ለሚሻግት ምግብ አድሮ ላይበላ
እምነቱን ይሸጣል ሰው ሆዱን ሊሞላ
ከሰው በተረፈ በተናቀ እንጀራ
እምነቱን የሚሸጥ እየበላ አደራ
የልብ ድሃ ነው አዕምሮ የሌለው
ስልጣንን ፍለጋ በሆድ የተገዛው
በይሁዳ ሚዛን እራሱን የለካ
ትልቅ ያልነው ሁሉ ትንሽ ነበር ለካ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ብታሙ
👍21👏8❤4🥰1
#ናፈከኝ
ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ፤
ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ፤
ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ፤
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ፤
የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው፤
ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው፤
በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት፤
ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት።
ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር፥
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር፥
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር፥
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር።
ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ ባስተውለ፥
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ፥
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ፥
አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ፥
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ፥
የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ፥
ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ፤
ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ፤
ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ፤
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ፤
የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው፤
ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው፤
በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት፤
ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት።
ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር፥
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር፥
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር፥
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር።
ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ ባስተውለ፥
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ፥
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ፥
አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ፥
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ፥
የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ፥
ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤11👍11
#እንዳማኝ_በተስፋ_እንደ_ቆቅ_በስጋት
በቀን ተግቶ ሰርቶ ፤ በሌት ተግቶ ማሰብ
ለማይወዛ ግንባር፤ ለማይሞላ ሞሰብ::
ከቅድሟ ጀንበር፥ እስከ መጪው ንጋት
እንዳማኝ በተስፋ፥ እንደ ቆቅ በስጋት::
በወፍጮው ላይ ዱቄት
በዱቄት ላይ አፈር
በመጁ ላይ ሞፈር
ከሞፈሩ ጋራ
ደም የለበሰ ጦር
ከጦሩ ጋር ጋሻው
የማይችለው የለም፤ ያገር ሰው ትከሻው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
በቀን ተግቶ ሰርቶ ፤ በሌት ተግቶ ማሰብ
ለማይወዛ ግንባር፤ ለማይሞላ ሞሰብ::
ከቅድሟ ጀንበር፥ እስከ መጪው ንጋት
እንዳማኝ በተስፋ፥ እንደ ቆቅ በስጋት::
በወፍጮው ላይ ዱቄት
በዱቄት ላይ አፈር
በመጁ ላይ ሞፈር
ከሞፈሩ ጋራ
ደም የለበሰ ጦር
ከጦሩ ጋር ጋሻው
የማይችለው የለም፤ ያገር ሰው ትከሻው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤16👏3
#ናፍቆት
የልቤ ቅኝቱ አንቺ ሆየም አይደል
ከባቲም አይገጥም ይለያል ካምባሰል
የመናፈቅ ቅኝት የእፍቅሮ ማጣት ምት
በነጠላ አመት ውስጥ ማሳለፍ እልፍ አመት
ይከብዳል ሊገለፅ በባቲ አንቺ ሆየ
ደስታን ለረሳ ልብ ከሳቅ ለተለየ
ውዴ ሆይ ልንገርሽ ዛሬስ ተስኖኛል
መጠበቄ በዝቶ መረሳት ወርሶኛል
የሀዘኔ ጫፉ ከራስ ዳሽን ገዝፏል
የመከፋቴ ጥግ ቀይ ባህር ተሻግሯል
ትመጫለሽ ብየ በመናፈቅ ጠኔ
እኔው በራሴ ውስጥ ገብቼ ምናኔ
በእምባ በታነፀ የሀዘን ተራራ
ሰው ከማይደርስበት ከህልም አለም ስፍራ
ሀረግ የወረሳት ጎጆየን ዘግቼ
ባሮጌው ኮቴ ስር ሀብታም ልብ አንግቼ
ስንት ዘመን ኖርኩኝ መኖርን ዘንግቼ
ዛሬ…ከጎጆየ በላይ እኔ ዘምሜያለሁ
የኔ የነበረን ሁሉን ..አጥቻለሁ
ምናልባት አንድ ቀን ስታልፊ በደጄ
ከእርጅና ቡሃላ መቶ አመት ያረጄ
የህይወት ጥላሸት ገፁን የወረሰው
በድንገት ካየሽኝ እኔ ነኝ እሱ ሰው፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዘላለም ምህረቱ
የልቤ ቅኝቱ አንቺ ሆየም አይደል
ከባቲም አይገጥም ይለያል ካምባሰል
የመናፈቅ ቅኝት የእፍቅሮ ማጣት ምት
በነጠላ አመት ውስጥ ማሳለፍ እልፍ አመት
ይከብዳል ሊገለፅ በባቲ አንቺ ሆየ
ደስታን ለረሳ ልብ ከሳቅ ለተለየ
ውዴ ሆይ ልንገርሽ ዛሬስ ተስኖኛል
መጠበቄ በዝቶ መረሳት ወርሶኛል
የሀዘኔ ጫፉ ከራስ ዳሽን ገዝፏል
የመከፋቴ ጥግ ቀይ ባህር ተሻግሯል
ትመጫለሽ ብየ በመናፈቅ ጠኔ
እኔው በራሴ ውስጥ ገብቼ ምናኔ
በእምባ በታነፀ የሀዘን ተራራ
ሰው ከማይደርስበት ከህልም አለም ስፍራ
ሀረግ የወረሳት ጎጆየን ዘግቼ
ባሮጌው ኮቴ ስር ሀብታም ልብ አንግቼ
ስንት ዘመን ኖርኩኝ መኖርን ዘንግቼ
ዛሬ…ከጎጆየ በላይ እኔ ዘምሜያለሁ
የኔ የነበረን ሁሉን ..አጥቻለሁ
ምናልባት አንድ ቀን ስታልፊ በደጄ
ከእርጅና ቡሃላ መቶ አመት ያረጄ
የህይወት ጥላሸት ገፁን የወረሰው
በድንገት ካየሽኝ እኔ ነኝ እሱ ሰው፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዘላለም ምህረቱ
❤21🥰4
#ዝምተኛ_ልቦች
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው
ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጌትነት እንየው
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው
ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጌትነት እንየው
👍22❤12🥰5🤷♀2🔥1😢1
#አፈቅርሽ_ነበረ
በነበር የሚነግስ ባይኖርም በዚ አለም ፣
መለየትን ሚገልፅ ከነበር ውጭ የለም ፣
መለያየት ሳይሆን ያስታቀፈን እዳ ፣
አለመፋቀር ነው የኔናንቺ ፍዳ ።
ቃል ባጡ ሀረጎች ባልገልፅልሽ ፍቅሬን ፣
የሩቅ ሲሆን ፍቅር ቢጎዳውም ልቤን ፣
ይህን ሁሉ ችዬ እኔ ባፈቅርሽም ፣
ያንቺ ጉዳት እንጂ የኔ አይታይሽም ።
ናፍቆት እንዴት ያማል ትዝታም ያደማል ፣
ከዚሁሉ በላይ
አትወደኝም መባል እንዴት ልብ ይሰብራል ፣
ብወድሽአይደለ በሀሳቤመሀል ምትመላለሺ ፣
ችኩልአይምሮዬን በናፍቆትሽውሀ ምታረሰርሺ ።
እንዴት አልወድሽም ?
በሀገር በምድሩ ያልታየውን ሴራ ፣
ባንቺ መሄድ ልቤ ነበር ቤት ሲሰራ ፣
ነበር ቤት ይሰራል
ግድግዳውን ናፍቆት ጣራውን ትዝታ ፣
ልብ እያፈቀረ አይምሮ አሸንፎ የተለዩ ለታ ።
ወንበዴ ነው ፍቅርሽ አይረጋም ጨርሶ ፣
መታጠፊያ ሲያገኝ ሄደ ተቀይሶ ፣
የቱጋ ነው ፍቅርሽ ፍቅር ትግስት ሲሻ ፣
የፍቅር ክፍያ መታገስ ነበረ እስከ መጨረሻ ።
ብቻ ግን እወቂ
አፈቅርሽ ነበረ !!!
መንገድሽ ጨርቅ ይሁን እንዳትመለሺ ፣
እኔም አንቺን ላስታውስ አንቺም እኔን እርሺ ፣
እጅሽን አልይዝም መንገድሽን አልሰርቀው ፣
ያምኮ ፍቅር ነው
የሚወዱትን ሰው ለሚወደው መተው ።
በይ እንዳይረፍድብሽ ......
ቢያቅትሽ መታገስ የፍቅር ህመሙን ፣
ሲያወራርድብሽ ትዝታ ናፍቆቱን ፣
እኔም ጋ ነበረ ያንቺ አይነት መከራ ፣
ግን አንቺ አስቀመጥው ከስሜትሽ ጋራ ፣
ፍቅርሽ ግብዝ ሆኖ ምላሽ ከጠበቀ ፣
እንለያይ በቃ ማፍቀርሽ ካለቀ ፣
መለየት ወግ አለው አብረው ለነበሩ ፣
እኔ አብሬሽ ነበርኩ
ከ እኔጋ አልነበርሽም እንዲያ ነው ነገሩ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በነበር የሚነግስ ባይኖርም በዚ አለም ፣
መለየትን ሚገልፅ ከነበር ውጭ የለም ፣
መለያየት ሳይሆን ያስታቀፈን እዳ ፣
አለመፋቀር ነው የኔናንቺ ፍዳ ።
ቃል ባጡ ሀረጎች ባልገልፅልሽ ፍቅሬን ፣
የሩቅ ሲሆን ፍቅር ቢጎዳውም ልቤን ፣
ይህን ሁሉ ችዬ እኔ ባፈቅርሽም ፣
ያንቺ ጉዳት እንጂ የኔ አይታይሽም ።
ናፍቆት እንዴት ያማል ትዝታም ያደማል ፣
ከዚሁሉ በላይ
አትወደኝም መባል እንዴት ልብ ይሰብራል ፣
ብወድሽአይደለ በሀሳቤመሀል ምትመላለሺ ፣
ችኩልአይምሮዬን በናፍቆትሽውሀ ምታረሰርሺ ።
እንዴት አልወድሽም ?
በሀገር በምድሩ ያልታየውን ሴራ ፣
ባንቺ መሄድ ልቤ ነበር ቤት ሲሰራ ፣
ነበር ቤት ይሰራል
ግድግዳውን ናፍቆት ጣራውን ትዝታ ፣
ልብ እያፈቀረ አይምሮ አሸንፎ የተለዩ ለታ ።
ወንበዴ ነው ፍቅርሽ አይረጋም ጨርሶ ፣
መታጠፊያ ሲያገኝ ሄደ ተቀይሶ ፣
የቱጋ ነው ፍቅርሽ ፍቅር ትግስት ሲሻ ፣
የፍቅር ክፍያ መታገስ ነበረ እስከ መጨረሻ ።
ብቻ ግን እወቂ
አፈቅርሽ ነበረ !!!
መንገድሽ ጨርቅ ይሁን እንዳትመለሺ ፣
እኔም አንቺን ላስታውስ አንቺም እኔን እርሺ ፣
እጅሽን አልይዝም መንገድሽን አልሰርቀው ፣
ያምኮ ፍቅር ነው
የሚወዱትን ሰው ለሚወደው መተው ።
በይ እንዳይረፍድብሽ ......
ቢያቅትሽ መታገስ የፍቅር ህመሙን ፣
ሲያወራርድብሽ ትዝታ ናፍቆቱን ፣
እኔም ጋ ነበረ ያንቺ አይነት መከራ ፣
ግን አንቺ አስቀመጥው ከስሜትሽ ጋራ ፣
ፍቅርሽ ግብዝ ሆኖ ምላሽ ከጠበቀ ፣
እንለያይ በቃ ማፍቀርሽ ካለቀ ፣
መለየት ወግ አለው አብረው ለነበሩ ፣
እኔ አብሬሽ ነበርኩ
ከ እኔጋ አልነበርሽም እንዲያ ነው ነገሩ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤26👍4
#ይሄ_ሁሉ_ጣዖት
እናት ያበጀችው ከስጋዋ ከፍላ
ያንን ሁሉ ወጣት ፤ ያንን ጅምር አፍላ
በውነት በፍትህ ስም ፥ እየማሉ ከዱት
እንደ ፋሲካ በግ ፥ወደ ካራው ነዱት::
የቀኑ ቀውስነት፤ የሌለው አምሳያ
ዝናብ እንደፈታው ፥ የገጠር ገበያ
ዘመን ተዘባርቆ፥
አገር በግራጁ ፥ ከቀኝ ኪሱ ሰርቆ
ጉዳችን መች አልቆ!
ትናንት አለም አቀፍ ወዛደራዊነት
ዛሬ በየፈርጁ ፥ዘርማንዘራዊነት
ደሞ ያርማው ብዛት፥ የባንዲራው አይነት
ቢያመልኩት አይራራም፥ እጣን እያጨሱ
ሻማ እየለኮሱ
ይሄ ሁሉ ጣኦት፥ የሰው ደም ነው ምሱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
እናት ያበጀችው ከስጋዋ ከፍላ
ያንን ሁሉ ወጣት ፤ ያንን ጅምር አፍላ
በውነት በፍትህ ስም ፥ እየማሉ ከዱት
እንደ ፋሲካ በግ ፥ወደ ካራው ነዱት::
የቀኑ ቀውስነት፤ የሌለው አምሳያ
ዝናብ እንደፈታው ፥ የገጠር ገበያ
ዘመን ተዘባርቆ፥
አገር በግራጁ ፥ ከቀኝ ኪሱ ሰርቆ
ጉዳችን መች አልቆ!
ትናንት አለም አቀፍ ወዛደራዊነት
ዛሬ በየፈርጁ ፥ዘርማንዘራዊነት
ደሞ ያርማው ብዛት፥ የባንዲራው አይነት
ቢያመልኩት አይራራም፥ እጣን እያጨሱ
ሻማ እየለኮሱ
ይሄ ሁሉ ጣኦት፥ የሰው ደም ነው ምሱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤10👍5👏5
#ማነው_የተረዳኝ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤26