#እጠብቅሻለሁ!!
ሰኞ ለት ቀጥረሺኝ የምን ቀን ነው ብለሽ
ቀረሽ ሳትመጪ
ማክሰኞ ቀጥረሺኝ ታምሚያለሁ ብለሽ ከቤት ሳትወጪ
በረቡዕ ተስማምተን በጊዜ ወጥቼ
ስጠብቅሽ ቆሜ
ደውለሽ ይቅርታ ፆም ነው ለካ ዛሬ በፍስግ ይሻላል ሃሙስ
ወይ ቅዳሜ
ያልሺኝን አመኜ ሃሙስን መርጬ
አንቺን ለማማለል ብወጣም ዘንጬ
ወይ በረሽ አልመጣሽ ወይ ስልክሽ አይሰራ
ምን አገኛት እያልኩ እያሰላሰልኩኝ
ለብቻ ሳወራ
ድንገት ስልኬ ጠራ
"መቼም አታምነኝም ያጎቴ ልጅ ሞቶ
ለቅሶ ቤት ሄጄ ነው
እንዳትቀየመኝ ምንም ይሁን ምንም ነገ ግን ግድ ነው"
ብለሽ አምኛለሁ
ግን ግን ግዴለሽም !
አርብን እንዝለለው ላንቺም ይሻልሻል
በአፍቃሪ እይታ መጠራጠር የለም ሁሉም ይታመናል
ወይ ፆሙን አስታከሽ ወይ በልጁ ቀብር አትመጪም ይሆናል
ስለዚህ ቅዳሜ በተወደደው ቀን
ውጪ ዘንጪና
እኔም ልጠብቅሽ በጊዜ ወጥቼ አይንሽን ለማየት ጓጉቻለሁና
ቅዳሜንስ ለኔ ማነው የፈቀደው
ለመታመን ያህል በትመጪ ተስፋ ከመንገድ ቆሚያለሁ
ይኸው ቀኑም መሸ
የናፈቀው አይኔ ሳያይሽ ሟሸሸ
ካሁን በኋላ ግን እየወጡ መግባት እየገቡ መውጣት ስልችት ስላለኝ
እሁድን እዚያው ነኝ
ሰኞና ማክሰኞ እረቡም አለሁኝ
ሀሙስና አርብን ቅዳሜም አታጪኝ
ጎዳና አጎሳቁሎኝ ገፅታዬ ጠፍቶሽ
አይተሽ ካላለፍሺኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
ሰኞ ለት ቀጥረሺኝ የምን ቀን ነው ብለሽ
ቀረሽ ሳትመጪ
ማክሰኞ ቀጥረሺኝ ታምሚያለሁ ብለሽ ከቤት ሳትወጪ
በረቡዕ ተስማምተን በጊዜ ወጥቼ
ስጠብቅሽ ቆሜ
ደውለሽ ይቅርታ ፆም ነው ለካ ዛሬ በፍስግ ይሻላል ሃሙስ
ወይ ቅዳሜ
ያልሺኝን አመኜ ሃሙስን መርጬ
አንቺን ለማማለል ብወጣም ዘንጬ
ወይ በረሽ አልመጣሽ ወይ ስልክሽ አይሰራ
ምን አገኛት እያልኩ እያሰላሰልኩኝ
ለብቻ ሳወራ
ድንገት ስልኬ ጠራ
"መቼም አታምነኝም ያጎቴ ልጅ ሞቶ
ለቅሶ ቤት ሄጄ ነው
እንዳትቀየመኝ ምንም ይሁን ምንም ነገ ግን ግድ ነው"
ብለሽ አምኛለሁ
ግን ግን ግዴለሽም !
አርብን እንዝለለው ላንቺም ይሻልሻል
በአፍቃሪ እይታ መጠራጠር የለም ሁሉም ይታመናል
ወይ ፆሙን አስታከሽ ወይ በልጁ ቀብር አትመጪም ይሆናል
ስለዚህ ቅዳሜ በተወደደው ቀን
ውጪ ዘንጪና
እኔም ልጠብቅሽ በጊዜ ወጥቼ አይንሽን ለማየት ጓጉቻለሁና
ቅዳሜንስ ለኔ ማነው የፈቀደው
ለመታመን ያህል በትመጪ ተስፋ ከመንገድ ቆሚያለሁ
ይኸው ቀኑም መሸ
የናፈቀው አይኔ ሳያይሽ ሟሸሸ
ካሁን በኋላ ግን እየወጡ መግባት እየገቡ መውጣት ስልችት ስላለኝ
እሁድን እዚያው ነኝ
ሰኞና ማክሰኞ እረቡም አለሁኝ
ሀሙስና አርብን ቅዳሜም አታጪኝ
ጎዳና አጎሳቁሎኝ ገፅታዬ ጠፍቶሽ
አይተሽ ካላለፍሺኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
👍24❤14🔥10👏4
#በፀሀይ_ቅጠሪኝ
በዝናብ ስነግርሽ በርትቶብኝ ፍቅሬ
ሳይገባሽ ብታልፊ ዘንግተሽኝ ዛሬ
ብርሀን ሲፈካ ሲፈነጥቅ ጮራ
ጭጋጉ ሲበተን ዝናቡ ሲያባራ
ይሰማሽ ይሆናል እንባዬ ሲያወራ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በዝናብ ስነግርሽ በርትቶብኝ ፍቅሬ
ሳይገባሽ ብታልፊ ዘንግተሽኝ ዛሬ
ብርሀን ሲፈካ ሲፈነጥቅ ጮራ
ጭጋጉ ሲበተን ዝናቡ ሲያባራ
ይሰማሽ ይሆናል እንባዬ ሲያወራ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍13❤3👏2🔥1
#ጌታዬ_አቅቶኛል !
ፍቅርና ምህረትህ አልፎብኝ ከልኬ
መሸከም አቃተኝ ከበደኝ አምላኬ!
በየቱ ስራዬ በየቱ ትህትና
ችዬ ልሸከመው ደካማ ነኝና
አንተ ሁሌም ስትምር እኔ ሁሌም በዳይ
ጌታዬ አቅቶኛል ፍቅርህ ከብዶኝ ከላይ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ፍቅርና ምህረትህ አልፎብኝ ከልኬ
መሸከም አቃተኝ ከበደኝ አምላኬ!
በየቱ ስራዬ በየቱ ትህትና
ችዬ ልሸከመው ደካማ ነኝና
አንተ ሁሌም ስትምር እኔ ሁሌም በዳይ
ጌታዬ አቅቶኛል ፍቅርህ ከብዶኝ ከላይ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
❤24👍9🔥2
ያን ጠይሙን ዘመን ...
ያንን ገራም ወራት ...
ያን የጊዜ መቅኔ ያን የዘመን ኣስኳል ፤
በምን ወዜ ላስጊጥ በምን እጄ ልኳል?!
ያ ዘመን ገራሙ ...
ያ ዘመን ህያው ቃል ፤
ነገሩን በሙሉ የቀመሰው ያውቃል።
ብዬ ልተው ይሆን ...
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
የተቃኙበትን የነፍስያ ኣውታር ለዛ ስልቱን ሲያጡት ፤
የሚፈጥሩት ዜማ ፣
ከራስ ነፍስ ፈልቆ ለራስ የሚሰማ ፤
የሞት ጠረን ያለው ኑሮ ኑሮ 'ሚሸት ፤
ስሙኝ ስሙኝ የሚል የደናግል ዜማ
ቃሙኝ ቃሙኝ የሚል የማሽላ እሸት ።
( ትዝታ ግን ማለት ... )
ትዝታ ይጥላል ...
ትዝታ ያነሳል ፤
ትዝታ ይቸራል ...
ትዝታ ይነሳል ፤
ትዝታ ሆሄ ነው የተበታተነ የፈራረሰ ቃል ፤
ሲያሻው ያስከብራል በል ሲለው ያስንቃል ፤
ህልም እየነጠቀ ይተናል እንደጉም ፤
ትርጉም ማሳጣት ነው የትዝታ ትርጉም ።
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
እንኳን ባ'ይነ ስጋ ኣሻራውን ሲያጡት ፤
የሚደነግጡት ...
የሰቀቀን ሆሳ ።
ከገዛ ቅዠት ጋር በገሃድ የሚያብር ፤
ከንቱ ትላንት ነው ነገን የሚያሸብር ።
እውነት ነው ትዝታ
ከቅዠት ያብራል ፤
እውነት ነው ትዝታ
ነገን ያሸብራል ።
እንደውም ...
እንደውም ...
በዘመን ተብላልቶ የደቀቀ ቅስሙ ፤
እንደውም ትዝታ አሸብር ነው ስሙ ...
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሙሀመድ
ያንን ገራም ወራት ...
ያን የጊዜ መቅኔ ያን የዘመን ኣስኳል ፤
በምን ወዜ ላስጊጥ በምን እጄ ልኳል?!
ያ ዘመን ገራሙ ...
ያ ዘመን ህያው ቃል ፤
ነገሩን በሙሉ የቀመሰው ያውቃል።
ብዬ ልተው ይሆን ...
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
የተቃኙበትን የነፍስያ ኣውታር ለዛ ስልቱን ሲያጡት ፤
የሚፈጥሩት ዜማ ፣
ከራስ ነፍስ ፈልቆ ለራስ የሚሰማ ፤
የሞት ጠረን ያለው ኑሮ ኑሮ 'ሚሸት ፤
ስሙኝ ስሙኝ የሚል የደናግል ዜማ
ቃሙኝ ቃሙኝ የሚል የማሽላ እሸት ።
( ትዝታ ግን ማለት ... )
ትዝታ ይጥላል ...
ትዝታ ያነሳል ፤
ትዝታ ይቸራል ...
ትዝታ ይነሳል ፤
ትዝታ ሆሄ ነው የተበታተነ የፈራረሰ ቃል ፤
ሲያሻው ያስከብራል በል ሲለው ያስንቃል ፤
ህልም እየነጠቀ ይተናል እንደጉም ፤
ትርጉም ማሳጣት ነው የትዝታ ትርጉም ።
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
እንኳን ባ'ይነ ስጋ ኣሻራውን ሲያጡት ፤
የሚደነግጡት ...
የሰቀቀን ሆሳ ።
ከገዛ ቅዠት ጋር በገሃድ የሚያብር ፤
ከንቱ ትላንት ነው ነገን የሚያሸብር ።
እውነት ነው ትዝታ
ከቅዠት ያብራል ፤
እውነት ነው ትዝታ
ነገን ያሸብራል ።
እንደውም ...
እንደውም ...
በዘመን ተብላልቶ የደቀቀ ቅስሙ ፤
እንደውም ትዝታ አሸብር ነው ስሙ ...
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሙሀመድ
❤6👍2🥰2
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''
''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''
ውድ የግጥም ቻናል የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''
ውድ የግጥም ቻናል የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤9👍4🙏2
#እውነቱን_ልንገርህ?
እንደ ሙሴ በትር ተአምር ብትሰራ፥
እንደ ንጉስ ዳዊት አለምን ብትመራ፥
እንደ አብረሀም የዋህ ለሰው የምትራራ፥
ብትሆን በስራህ ሁሉን ምታኮራ፥
እውነቱን ልንገርህ አንዳችም ሳልደብቅ የውስጤን አሻራ...
እንደ እያሪኮ ግንብ አለም ብትፈራርስ፥
ምድር ብትደፋ ሰማዩ ቢታረስ፥
ጨረቃና ፀሀይ ወድቀው ቢሰበሩ፥
ከዋክብት እንደ ጉም በነው ቢሰወሩ፥
በጥፋት ውሀ ዳግም ምድር ተጥለቅልቃ፥
ነፍሴ ከፍም እሳት ከነበልባል ጠልቃ፥
የዚ አለም መከራ ቢጫን በኔ ጫንቃ፥
ሞት ቢፈረድብኝ መኖሬ ቢያበቃ፥
እውነቱን ልንገርህ?
ዳግም ተመልሼ እኔስ ያንተ እልሆንም አከተመ በቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እንደ ሙሴ በትር ተአምር ብትሰራ፥
እንደ ንጉስ ዳዊት አለምን ብትመራ፥
እንደ አብረሀም የዋህ ለሰው የምትራራ፥
ብትሆን በስራህ ሁሉን ምታኮራ፥
እውነቱን ልንገርህ አንዳችም ሳልደብቅ የውስጤን አሻራ...
እንደ እያሪኮ ግንብ አለም ብትፈራርስ፥
ምድር ብትደፋ ሰማዩ ቢታረስ፥
ጨረቃና ፀሀይ ወድቀው ቢሰበሩ፥
ከዋክብት እንደ ጉም በነው ቢሰወሩ፥
በጥፋት ውሀ ዳግም ምድር ተጥለቅልቃ፥
ነፍሴ ከፍም እሳት ከነበልባል ጠልቃ፥
የዚ አለም መከራ ቢጫን በኔ ጫንቃ፥
ሞት ቢፈረድብኝ መኖሬ ቢያበቃ፥
እውነቱን ልንገርህ?
ዳግም ተመልሼ እኔስ ያንተ እልሆንም አከተመ በቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍16👏5❤2
#አንደኛው_ሰው_ላንዱ
በቀን ወይ በሌሊት
በጾም በቅበላ
የበላ ይኖራል፥ ይብላኝ ለተበላ
ጋጋሪው ቢራቀቅ፥ ቢሰወር ምጣዱ
የለት እንጀራ ነው፤ አንደኛው ሰው ላንዱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
በቀን ወይ በሌሊት
በጾም በቅበላ
የበላ ይኖራል፥ ይብላኝ ለተበላ
ጋጋሪው ቢራቀቅ፥ ቢሰወር ምጣዱ
የለት እንጀራ ነው፤ አንደኛው ሰው ላንዱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
👍13❤2🔥2
#ቃል…
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል
ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል
እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል
ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’
የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ
ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ
ልበ ገራገሩን…
ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህለ
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል
ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል
እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል
ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’
የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ
ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ
ልበ ገራገሩን…
ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህለ
❤14👍7
#ፈጥረህኝ_እያለህ
ፈጥረህኝ እያለ አሟልተህ በጤና
ማመስገን የማልችል ደካማ ነኝና
ለስጋዬ ማሰብ አድርጎኛል መና
ቪላ አልሰጠህኝ እንዲሁም መኪና
አልማዝ ወርቅም የለኝ እያለኝ ግን ጤና
እያልኩኝ ሳማርር አልገባኝምና
ለዚህ ለብልጭልጭ ለብስባሽ ገላ
ዛሬን አምሮ ታይቶ ነገን ለሚገማ
ሁሉስ መች አወቀው ነገ እንደሚቀማ
አምላክ ግን ሲጠራን ወርቄን ማቄን የለ
አልማዙም መኪናው ሁሉም የኛ አይደለ
ባንዲት አቡጀዲ ከነ ሀጢያታችን ከጉድጓድ አይደለ?
ታድያ ምን አለበት ተመስገን እያልን ከተሰጠን በልተን ካለንም ተቃምሰን
ይችን ብርቅርቅ አለም ወደ ኃላ ትተን
የሰይጣንን ሥራ ለሰይጣኑ ሰጥተን
የኛ የሆነውን አመስግነን ይዘን
ተመስገን ተመስገን በቃሉም ተገዝተን
እንኑር በፍቅር ባንድነት ተስማምተን::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ፈጥረህኝ እያለ አሟልተህ በጤና
ማመስገን የማልችል ደካማ ነኝና
ለስጋዬ ማሰብ አድርጎኛል መና
ቪላ አልሰጠህኝ እንዲሁም መኪና
አልማዝ ወርቅም የለኝ እያለኝ ግን ጤና
እያልኩኝ ሳማርር አልገባኝምና
ለዚህ ለብልጭልጭ ለብስባሽ ገላ
ዛሬን አምሮ ታይቶ ነገን ለሚገማ
ሁሉስ መች አወቀው ነገ እንደሚቀማ
አምላክ ግን ሲጠራን ወርቄን ማቄን የለ
አልማዙም መኪናው ሁሉም የኛ አይደለ
ባንዲት አቡጀዲ ከነ ሀጢያታችን ከጉድጓድ አይደለ?
ታድያ ምን አለበት ተመስገን እያልን ከተሰጠን በልተን ካለንም ተቃምሰን
ይችን ብርቅርቅ አለም ወደ ኃላ ትተን
የሰይጣንን ሥራ ለሰይጣኑ ሰጥተን
የኛ የሆነውን አመስግነን ይዘን
ተመስገን ተመስገን በቃሉም ተገዝተን
እንኑር በፍቅር ባንድነት ተስማምተን::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👌14❤10👍5💯3👏1
#ዝምታየን_አድምጥ
እየውልህ ፍቅሬ እኔም እንደ ሌላ፣
የሌለን ለመግለፅ ቃል እንደሚያሰላ፣
ካንገት በላይ ወዳጅ እንደግዜው ኗሪ ፣
አለ ሲሉት የለም የይምሰል አፍቃሪ ፣
ወሬ ቀባጥሬ ባልዋልክብት ውየ ፣
ከልቤ ያልታየን ሰው ስላለ ብየ፣
እንዲህ ነው በማለት ባፌ ባልነግርህም
በቃ ዝም ብለህ ዝምታየን አድምጥ
ያኔ ትሰማለህ ጥልቅ የመውደድ ህመም
ጥልቅ የማፍቀር ጩኸት የመሰለ እንደ ጥም
እየውልህ ፍቅሬ እኔም እንደ ሌላ፣
የሌለን ለመግለፅ ቃል እንደሚያሰላ፣
ካንገት በላይ ወዳጅ እንደግዜው ኗሪ ፣
አለ ሲሉት የለም የይምሰል አፍቃሪ ፣
ወሬ ቀባጥሬ ባልዋልክብት ውየ ፣
ከልቤ ያልታየን ሰው ስላለ ብየ፣
እንዲህ ነው በማለት ባፌ ባልነግርህም
በቃ ዝም ብለህ ዝምታየን አድምጥ
ያኔ ትሰማለህ ጥልቅ የመውደድ ህመም
ጥልቅ የማፍቀር ጩኸት የመሰለ እንደ ጥም
👍14🥰3❤2
#የሄድኩበት_መንገድ
እርሳኝ ያልሽኝ ጊዜ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
ከሰይጣን ታርቄ
በብቸኝነት ጥግ
በቅጠል ታሰሬ
በጭስ ተደብቄ!
ያንን ውብ ቁንጅና
ያንን ወብ ትዝታ
ክብርሽን አውርጄ
ልረሳሽ ታገልኩኝ
ከራሴ ተሟገትኩ
አመታት ወስጄ!
እናም ረሳሁሽ
መልክሽም ጠፋብኝ
ላስታውስሽ ሞከርኩ
ጭራሽ አልመጣ አልሽኝ
ይገርማል!
ውሎ አደሮ ሲገባኝ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
የሄድኩበት መንገድ
አንቺን አስረስቶ
ዛሬ እኔን አሳጣኝ
አንድ አስታዋሽ ዘመድ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እርሳኝ ያልሽኝ ጊዜ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
ከሰይጣን ታርቄ
በብቸኝነት ጥግ
በቅጠል ታሰሬ
በጭስ ተደብቄ!
ያንን ውብ ቁንጅና
ያንን ወብ ትዝታ
ክብርሽን አውርጄ
ልረሳሽ ታገልኩኝ
ከራሴ ተሟገትኩ
አመታት ወስጄ!
እናም ረሳሁሽ
መልክሽም ጠፋብኝ
ላስታውስሽ ሞከርኩ
ጭራሽ አልመጣ አልሽኝ
ይገርማል!
ውሎ አደሮ ሲገባኝ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
የሄድኩበት መንገድ
አንቺን አስረስቶ
ዛሬ እኔን አሳጣኝ
አንድ አስታዋሽ ዘመድ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍12❤5👏4
#ማህሌተ_ገንቦ
ባጭር ቀረን ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
ፊታችንን ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ-
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዪም
ባጭር ቀረን ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
ፊታችንን ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ-
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዪም
👍14🍾4❤2👏2
#መጣለሁ_ጠብቂኝ
አንቺ.......
የአባይ ዳር አፈር
የአውራጃ ምስለኔ
አለም አሳች ፍጥረት
አደይ መሳይ ቅኔ
ድጉስ አልባ መፅሐፍ
ርዕስ የለሽ ዳራ
የመሰንበት ትንፋሽ
የህብረ ቀለም ጎራ
አንቺ የሀቅ አለም
የአለም ህብረ ቀለም
በይ ቃሌን ተቀበይ ቃልሽን ላኪልኝ
የልብሽ ልባችን ፍቅራችን እንዲናኝ
ከራዕማው ከፍታ ከሰማየ ሰማይ
ተቀምጠሽ አያለሁ...ሆነሽ አልማለሁ
ከእግዜሩ መንበር ላይ
ሀሳቤ እንዲሰምር ተቀምጠሽም እንዳይ
ቀን ሌት አስሳለሁ የመላውን ጉሬ
አንድ ቀን ሰምሮልኝ ሆኖልኝ ነገሬ
አመጣልሻለው ከእግዜር ተበድሬ
ከደጅሽ ጠብቂኝ ቀን በመሸ ጊዜ
አላበድር ቢለኝ ቢበዛ መዘዜ
ከእግዜራችን ሀገር ትዝብትን አርግዤ
ድንገት እመጣለሁ አንድ እራሴን ይዤ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሲራክ
አንቺ.......
የአባይ ዳር አፈር
የአውራጃ ምስለኔ
አለም አሳች ፍጥረት
አደይ መሳይ ቅኔ
ድጉስ አልባ መፅሐፍ
ርዕስ የለሽ ዳራ
የመሰንበት ትንፋሽ
የህብረ ቀለም ጎራ
አንቺ የሀቅ አለም
የአለም ህብረ ቀለም
በይ ቃሌን ተቀበይ ቃልሽን ላኪልኝ
የልብሽ ልባችን ፍቅራችን እንዲናኝ
ከራዕማው ከፍታ ከሰማየ ሰማይ
ተቀምጠሽ አያለሁ...ሆነሽ አልማለሁ
ከእግዜሩ መንበር ላይ
ሀሳቤ እንዲሰምር ተቀምጠሽም እንዳይ
ቀን ሌት አስሳለሁ የመላውን ጉሬ
አንድ ቀን ሰምሮልኝ ሆኖልኝ ነገሬ
አመጣልሻለው ከእግዜር ተበድሬ
ከደጅሽ ጠብቂኝ ቀን በመሸ ጊዜ
አላበድር ቢለኝ ቢበዛ መዘዜ
ከእግዜራችን ሀገር ትዝብትን አርግዤ
ድንገት እመጣለሁ አንድ እራሴን ይዤ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሲራክ
👍7❤2
#ይድረስ_ለሄዋኔ
ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ
ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለኔ
..............ይልቅስ ሄዋኔ
ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ
ከቻልሽ ነይልኝ ካልሆነ እኔ ልምጣ
ግን ልትመጪ ከሆነ መንገድ ሳትጀምሪ
ማንነቴን ሰምተሽ ከቀረሽም ቅሪ
ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ
የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ
ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ
ቤት ማጀቴ ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ
ልብሴም ድሪቶ ነው ፊቴም ውበት የለው
ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ያቆሰለው
ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ ሳይረታሽ
ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ወደ እኔ ከመጣሽ
እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ................
በደስታ ፈንጥዤ
በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ
ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለኔ
..............ይልቅስ ሄዋኔ
ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ
ከቻልሽ ነይልኝ ካልሆነ እኔ ልምጣ
ግን ልትመጪ ከሆነ መንገድ ሳትጀምሪ
ማንነቴን ሰምተሽ ከቀረሽም ቅሪ
ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ
የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ
ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ
ቤት ማጀቴ ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ
ልብሴም ድሪቶ ነው ፊቴም ውበት የለው
ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ያቆሰለው
ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ ሳይረታሽ
ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ወደ እኔ ከመጣሽ
እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ................
በደስታ ፈንጥዤ
በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍20❤6👏4🥰1
#ልቤ_ምን_አጠፋ?
እኔስ መስሎኝ ነበር ካንጀት ያፈቀርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?
ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አርገኸኝ ለማን እሆናለሁ
እንግዲህ ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም አልጠጣም ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣
አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
ጊዜው ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ ይፈርዳል 💔
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እኔስ መስሎኝ ነበር ካንጀት ያፈቀርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?
ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አርገኸኝ ለማን እሆናለሁ
እንግዲህ ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም አልጠጣም ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣
አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
ጊዜው ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ ይፈርዳል 💔
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤9👍2🥰1
#ስሞት_አትቅበረኝ
በህይወት እያለሁ እንባየን ካልጠረግህ
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ
ስታመም ዝም ካልህ
እራቤ ካልገባህ
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ
ደብዛዛው ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ
ተልካሻው ኑሮዬን ካላሰናዳካው
የተደለደለ ቦታ ካላስያዝከው
ማየት የተሳነው ፍቅሬን ካልመራህው
እውነት እልካለሁ ውዴ
ስሞት አትቅበረኝ
እንባም አታንባልኝ
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ
እንደሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ
እጅጉን አምርሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ
ስታመም አስታመኝ
ስከፋ አፅናናኝ
ስወድቅ ደግፈኝ
የጭንቀቴን ብሶት
የውስጤን ተረዳኝ
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ
ተልካሻው ኑሮዬን
ፈጥነህ አሰናዳው
የተደላደለ ቦታውን አሲዘው
ማየት የተሳነው
ልቤን ይዘህ ምራው
ደስታና ፍቅርን
ከልብ አስተምረኝ
ሁልጊዜ ሳቅልኝ
ይኸ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በህይወት እያለሁ እንባየን ካልጠረግህ
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ
ስታመም ዝም ካልህ
እራቤ ካልገባህ
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ
ደብዛዛው ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ
ተልካሻው ኑሮዬን ካላሰናዳካው
የተደለደለ ቦታ ካላስያዝከው
ማየት የተሳነው ፍቅሬን ካልመራህው
እውነት እልካለሁ ውዴ
ስሞት አትቅበረኝ
እንባም አታንባልኝ
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ
እንደሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ
እጅጉን አምርሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ
ስታመም አስታመኝ
ስከፋ አፅናናኝ
ስወድቅ ደግፈኝ
የጭንቀቴን ብሶት
የውስጤን ተረዳኝ
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ
ተልካሻው ኑሮዬን
ፈጥነህ አሰናዳው
የተደላደለ ቦታውን አሲዘው
ማየት የተሳነው
ልቤን ይዘህ ምራው
ደስታና ፍቅርን
ከልብ አስተምረኝ
ሁልጊዜ ሳቅልኝ
ይኸ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍18❤12
#ከአበባ_ተማሪ
አንዲት ፅጌሬዳ አንዲት እምቡጥ አበባ
አይን የምትሰርቅ ሆድ የምታባባ
አንዲት ፅጌሬዳ ሰፈሬ ነበረች
አልፈነዳም ብላ ብዙ አመት የኖረች
ግና ምን ያረጋል
ይህን ውበት አይቶ የአዳም ልጅ ቢከባት
እየኮተኮተ ውሀ እየመገበ ሰው ቢንከባከባት
ለሷ አሽከር የሆነ አፍቃሪ መሰላት
እናም
የልብልብ ተሰምቷት ድንገት ብትፈነዳ
ያ ሞትኩልሽ ያላት ሊያርዳት ተሰናዳ
እባክሽ ውዴ ሆይ ከአበባ ተማሪ ከእምቡጧ
ተረጂ
አብበሽ አብበሽ ድንገት ስትፈነጂ
አፍቃሪ አታገኚም በላተኛን እንጂ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አንዲት ፅጌሬዳ አንዲት እምቡጥ አበባ
አይን የምትሰርቅ ሆድ የምታባባ
አንዲት ፅጌሬዳ ሰፈሬ ነበረች
አልፈነዳም ብላ ብዙ አመት የኖረች
ግና ምን ያረጋል
ይህን ውበት አይቶ የአዳም ልጅ ቢከባት
እየኮተኮተ ውሀ እየመገበ ሰው ቢንከባከባት
ለሷ አሽከር የሆነ አፍቃሪ መሰላት
እናም
የልብልብ ተሰምቷት ድንገት ብትፈነዳ
ያ ሞትኩልሽ ያላት ሊያርዳት ተሰናዳ
እባክሽ ውዴ ሆይ ከአበባ ተማሪ ከእምቡጧ
ተረጂ
አብበሽ አብበሽ ድንገት ስትፈነጂ
አፍቃሪ አታገኚም በላተኛን እንጂ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍14❤5🥰3👌3
ባይኖራት ቢከፋት
ምንም ቢቸግራት
ምን ብትጎሳቆል
መከራ ቢከባት
ለልጆቼ የምትል
እሷን እየራባት
ምንም ግዜም ቢሆን
እናት ያው እናት ናት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መልካም የእናቶቾ ቀን
እማ እወድሻለሁ
ምንም ቢቸግራት
ምን ብትጎሳቆል
መከራ ቢከባት
ለልጆቼ የምትል
እሷን እየራባት
ምንም ግዜም ቢሆን
እናት ያው እናት ናት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መልካም የእናቶቾ ቀን
❤49👍6🔥3
#ፈልጌሽ_ብመጣ
እንደወፍ በርሬ
ጫካው ተሻግሬ
ማንም እንዳይቀርበኝ ዙርያዬን አጥሬ
ከወንዙ ዳር ቆሜ
ልቤን አስታምሜ
ከተራሮች ጀርባ በለሷን አልሜ
አጠገቤ ካለው
ከሚንፎለፎለው
ከድንጋይ ጋ ሲጋጭ ከሚንቦጫረቀው
ልብስ አወላልቄ
በምዕናብ ጠልቄ
ሀጥያተኛ ልቤን በፍቅርሽ አጥምቄ
ከፍሳሽ ጅረቱ
ከድንጋይ ባልጩቱ
ግንባሬን ሳጋጨው ቁልቁል ስወረወር
በዛ ፈታኝ ሰዐት ስቃዬ ላይ ሳይቀር
ስለኔ ረስቼ እያሰብኩሽ ነበር
ካፈር ብስባሹ
ከማሳ ፍሳሹ
የማጀት እልፍኙ ደራሽ ተቀላቅሎ
የጣባው ጠብታ ውቅያኖስ አክሎ
ከመነጨሁበት ከቀዬው ኮብልሎ
ከተራሮች መሀል እያቆራረጠ
ቁልቁለት ሸለቆ ሜዳ እየመረጠ
ገጠሩን ጨርሶ ከተማ ዘለቀ
ደለልም አጋጥሞት ለሁለት ሲከፈል
እኔ ያለሁበቱ በናንተ ቤት በኩል
ከበራቹ ደጃፍ ለመፍሰስ ስሞክር
ሽታና ጠረንሽ ላጣጥመው ስጥር
ያልታደልኩ አፍቃሪ ዉዴ ምን ያደርጋል?
ደረቱን ታቅፈሽ
ከላይ ምታሻሽው ሌላ ወንድ ይሸታል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እንደወፍ በርሬ
ጫካው ተሻግሬ
ማንም እንዳይቀርበኝ ዙርያዬን አጥሬ
ከወንዙ ዳር ቆሜ
ልቤን አስታምሜ
ከተራሮች ጀርባ በለሷን አልሜ
አጠገቤ ካለው
ከሚንፎለፎለው
ከድንጋይ ጋ ሲጋጭ ከሚንቦጫረቀው
ልብስ አወላልቄ
በምዕናብ ጠልቄ
ሀጥያተኛ ልቤን በፍቅርሽ አጥምቄ
ከፍሳሽ ጅረቱ
ከድንጋይ ባልጩቱ
ግንባሬን ሳጋጨው ቁልቁል ስወረወር
በዛ ፈታኝ ሰዐት ስቃዬ ላይ ሳይቀር
ስለኔ ረስቼ እያሰብኩሽ ነበር
ካፈር ብስባሹ
ከማሳ ፍሳሹ
የማጀት እልፍኙ ደራሽ ተቀላቅሎ
የጣባው ጠብታ ውቅያኖስ አክሎ
ከመነጨሁበት ከቀዬው ኮብልሎ
ከተራሮች መሀል እያቆራረጠ
ቁልቁለት ሸለቆ ሜዳ እየመረጠ
ገጠሩን ጨርሶ ከተማ ዘለቀ
ደለልም አጋጥሞት ለሁለት ሲከፈል
እኔ ያለሁበቱ በናንተ ቤት በኩል
ከበራቹ ደጃፍ ለመፍሰስ ስሞክር
ሽታና ጠረንሽ ላጣጥመው ስጥር
ያልታደልኩ አፍቃሪ ዉዴ ምን ያደርጋል?
ደረቱን ታቅፈሽ
ከላይ ምታሻሽው ሌላ ወንድ ይሸታል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍12👏4❤3
#ዛሬም_ወድሻለው
ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ
በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ
የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ
ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስከምቀር እስከለተ ሞቴ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ
በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ
የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ
ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስከምቀር እስከለተ ሞቴ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🥰11❤10👍10👏1