#የፍቅር_ዘመኑ
ወጣቱ .........
አስር – ከሰባቱ
ፀሐይን በጉያህ
ጨረቃን በኪስህ
ዩኒቨርስን ጠቅላዩን
በመዳፍህ ይዘህ
ፍቅርን በቃጠሎ
በትንታግ ታውቃለህ።
ወሬዛው........
ሰላሳ – ካምስቱ
ፀሐይ በቦታዋ
ጠዋት ትወጣና ማታ ትጠልቃለች
ጨረቃም በምሽት
በፀሐይ ዳረጎት በልመና ጨረር
አንሳ ታበራለች።
ፍቅርም እንደልምዱ
ከልቦናህ ያድራል ከተፈጥሮ ግንዱ።
አዛውንቱ .......
ሰባ – ከስምንቱ
ፀሐይ ከቦታዋ
ጥልቁን ትርቃለች
ጨረቃም ተማፅና ጨለማ መግፈፊያ
ብርታቷን ታጣለች።
– በፈንታው –
ትዝታ ክራሩን
ያለፈ ቅኝቱን
ፊትህ ላይ ያከርራል
ዘላለሙን ላይለቅ ፍቅርን ያላዝናል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዮሐንስ ሀብተማሪያም
ወጣቱ .........
አስር – ከሰባቱ
ፀሐይን በጉያህ
ጨረቃን በኪስህ
ዩኒቨርስን ጠቅላዩን
በመዳፍህ ይዘህ
ፍቅርን በቃጠሎ
በትንታግ ታውቃለህ።
ወሬዛው........
ሰላሳ – ካምስቱ
ፀሐይ በቦታዋ
ጠዋት ትወጣና ማታ ትጠልቃለች
ጨረቃም በምሽት
በፀሐይ ዳረጎት በልመና ጨረር
አንሳ ታበራለች።
ፍቅርም እንደልምዱ
ከልቦናህ ያድራል ከተፈጥሮ ግንዱ።
አዛውንቱ .......
ሰባ – ከስምንቱ
ፀሐይ ከቦታዋ
ጥልቁን ትርቃለች
ጨረቃም ተማፅና ጨለማ መግፈፊያ
ብርታቷን ታጣለች።
– በፈንታው –
ትዝታ ክራሩን
ያለፈ ቅኝቱን
ፊትህ ላይ ያከርራል
ዘላለሙን ላይለቅ ፍቅርን ያላዝናል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዮሐንስ ሀብተማሪያም
❤5👍3😁2
#የወንድ_ስንብት
ሊሄድ ያሰበ ሰው — ልቡ የሸፈተ
በ
"ደህና ሁኚ" ብሎ — ዕንባውን ያዘራል
የኀዘኑን ጨሌ — ሙዳይሽ ይሰፍራል
“ቻው” ይላል ዐሥሬ
ያለ ምንም ፍሬ...
ጓዙን ይሸክፋል
ወዲያ ወዲህ ያልፋል...
ይስማል ፍዝ ጉንጭ
ያቅፋል ልዝብ አንገት — እግሩም አይወጣለት
የወንድ ስንብት
“መልሺኝ” መሆኑን — ምነው ብታውቂለት?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሄኖክ በቀለ
ሊሄድ ያሰበ ሰው — ልቡ የሸፈተ
በ
ሌት በጽልመቱ
ምንም ሳይናገር — በር እየከፈተ
እንዳለፈ ክረምት
...እንደ ጠዋት ጤዛ
እንደ ቡና ሐሜት
...እንዲሁ እንደዋዛ
ሄደ ...ሄደ ....ሄደ ...ሄደ ኮበለለ
ይሰጠው ይሆናል — ዕጣው የተሻለ።
እንደኔ ያለው ግን"ደህና ሁኚ" ብሎ — ዕንባውን ያዘራል
የኀዘኑን ጨሌ — ሙዳይሽ ይሰፍራል
“ቻው” ይላል ዐሥሬ
ያለ ምንም ፍሬ...
ጓዙን ይሸክፋል
ወዲያ ወዲህ ያልፋል...
ይስማል ፍዝ ጉንጭ
ያቅፋል ልዝብ አንገት — እግሩም አይወጣለት
የወንድ ስንብት
“መልሺኝ” መሆኑን — ምነው ብታውቂለት?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሄኖክ በቀለ
👍20❤2
"To all my Muslim subscribers, I wish you a very Happy Eid! May this special day be filled with joy, peace, and beautiful moments with your loved ones.”
✨Eid Mubarak!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✨Eid Mubarak!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤6👍4
#ታስፈልጊኛለሽ!
በተለይ በክረምት ፡ ሙቀት ሲያስፈልገኝ
በተለይ በምሽት ፡ የብቻየን ስገኝ !
ብርድና ባዶነት ፡ ተባብረው ሲመጡ
ባንች ተገፍትረው ፡ ፈጥነው እንዲወጡ
ከላየ ቁጭ በይ ፡ ግርማየ ሞገሴ
እቅፍፍፍ ስታደርጊኝ ፡ ትሞቃለች ነፍሴ
ጌጤ ነሽ ለአካሌ ፡ ክብርና ውበቴ
በይ ነይ ልደርብሽ ፡ ከታናሿ ቤቴ
ታ
...ስ
......ፈ
..........ል
..............ጊ
.................ኛ
.....................ለ
.........................ሽ !
ወፍራሟ ጃኬቴ¡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ መላኩ አላምረው
በተለይ በክረምት ፡ ሙቀት ሲያስፈልገኝ
በተለይ በምሽት ፡ የብቻየን ስገኝ !
ብርድና ባዶነት ፡ ተባብረው ሲመጡ
ባንች ተገፍትረው ፡ ፈጥነው እንዲወጡ
ከላየ ቁጭ በይ ፡ ግርማየ ሞገሴ
እቅፍፍፍ ስታደርጊኝ ፡ ትሞቃለች ነፍሴ
ጌጤ ነሽ ለአካሌ ፡ ክብርና ውበቴ
በይ ነይ ልደርብሽ ፡ ከታናሿ ቤቴ
ታ
...ስ
......ፈ
..........ል
..............ጊ
.................ኛ
.....................ለ
.........................ሽ !
ወፍራሟ ጃኬቴ¡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ መላኩ አላምረው
😁24❤10👍6🔥2
#ረስተሽ_ካልሆነ
ነግሬሽ ነበረ ነገሬ በዝቶብሽ ረሳሽው እንጂ
አንቺም ነግረሽኛል ዛሬ ብረሳውም ረስተሽኝ ስትሄጂ
ስላንቺ የፃፍኩት ያሰብኩት በሞላ
የተኮረጀ ነው ካለም የተቀዳ ገና ያልተብላላ
ረስተሸ ካልሆነ አዝማሪ ወዳለሁ
በማሲንቆ ቅኝት ነፍሴን አደምጣለሁ
አናልሽ በቀደም አዝማሪ ቤት ሆኜ
የጠጁን ብርሌ አፌ ላይ ደቅኜ
ከኔ ባርጩማ ጎን አንድ ድንክ ቁጭ ብሏል
መላጣውን ሲያዩት ዲያስፖራ ይመስላል
አዝማሪው ይዘፍናል ለድንኩ ሰውየ
አዲስ ዜማ ፈጥሮ ከባቲ ዋሆየ
‹‹የጎፈሬህ ጫካ መሸፈት ያሰኛል››
‹‹መለሎው ቁመትህ አክሱምን ያስንቃል››
ድንኩ ወዳጃችን በጎፈሬው ፋንታ መላጣው ያበራል
በርጩማ ላይ ቆሞ አዝማሪው ግምባር ላይ መቶ ብር ይመርጋል
ከኔ አለፍ ብለው ኣናረጅም ያሉ ሁለት አሮጊቶች
ይፍለቀለቃሉ ባዝማሪው ቃላቶች
‹‹ጡትሽ ማለት ሎሚ አንገትሽ ብርሌ››
‹‹ስከተልሽ ልኑር አርጊኝና ሎሌ››
ነገርና ብቅል ናላውን ያዞረው
አንዱ ስክር ያለ ላዝማሪው ጠየቀው
‹‹ጡትሽ ማለት ሎሚ ብለህ የገጠምከው››
‹ጡትሽ ሀምሳ ሎሚ ልትል ፈልገህ ነው?››
ሁለቱ አሮጊቶች ሁለት ነገር ሰሩ
ሰካራሙን ጠጪ ከቤት አስባረሩ
አዝማሪው ግምባር ላይ ረብጣ ጋገሩ
ህይወትን ስንፈታው መንታ ትርም አዝሏል
እውነትን መናገር ከደጃፍ ያስጥላል
በውሸት ማሞገስ ሽልማት ያዘንባል
‹‹ አንቺ ማለት ለኔ የምስራቅ ፀሀይ ነሽ ››
‹‹ንጋት እና ምሽት ቀን የምቆጥርብሽ››
ብየ የጻፍኩልሽ ያንድ ቀኑ ግጥም
እርሽው አታስታውሽው ለኔም አልገባኝም
አንቺ ማለት ለኔ በቃ አንቺ ማለት ነሽ
በልቤ ጎዳና ወክ አድርገሽ ያለፍሽ
የሆነ ቀን መጣሽ በሆነ ምሽት ሄድሽ
ስትመጪ ግቢ አልኩሽ ስትሄጂ ረሳሁሽ
መርሳት በሽታየ መርሳት መዳኒቴ
በመርሳት ታምሜ ዳንኩኝ በመርሳቴ
አንድ ሰው ነበረ እንደኔ ሚረሳ
ሲተኛ ይፅፋል እቃዎቹን ሁሉ የት እንዳኖራቸው
‹‹ጫማየ ቴብል ስር ካልሲዎቼ ደግሞ ጫማ ውስጥ ናቸው››
‹‹ሸሚዜ ሻንጣ ውስጥ ሱሪየ ወንበር ላይ››
‹‹ሞባይሌ መሬት እኔ ደሞ አልጋ ላይ ››
በጠዋት ይነሳና ደብተሩን ይገልጣል
ሱሪና ሸሚዙን ሞባይል ሰአቱን ካሉበት ያነሳል
አንድ ነገር ብቻ ከፃፈበት ያጣል
አልጋው ባዶ ሆኗል
እናም እንዳልረሳሽ ልፅፍሽ ስሞክር
አንቺን ከሌላዋ ለይቼ ማሰፍረው አጣሁ ልዩ ነገር
ተመሳሳይ ሀሳብ ባዲስ ገፅ መፃፍ
ደብተር መጨረስ ነው ብእርን ማንጠፍጠፍ
ይህ የፃፍኩት ግጥም ሀሳብና ቋንቋው ለዛና ፍሰቱ እንዳይሆን የሆነው
ላንቺ መታሰቢያ አንቺን እንዲመስል የሳልኩት ስዕል ነው፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዘላለም ምህረቱ
ነግሬሽ ነበረ ነገሬ በዝቶብሽ ረሳሽው እንጂ
አንቺም ነግረሽኛል ዛሬ ብረሳውም ረስተሽኝ ስትሄጂ
ስላንቺ የፃፍኩት ያሰብኩት በሞላ
የተኮረጀ ነው ካለም የተቀዳ ገና ያልተብላላ
ረስተሸ ካልሆነ አዝማሪ ወዳለሁ
በማሲንቆ ቅኝት ነፍሴን አደምጣለሁ
አናልሽ በቀደም አዝማሪ ቤት ሆኜ
የጠጁን ብርሌ አፌ ላይ ደቅኜ
ከኔ ባርጩማ ጎን አንድ ድንክ ቁጭ ብሏል
መላጣውን ሲያዩት ዲያስፖራ ይመስላል
አዝማሪው ይዘፍናል ለድንኩ ሰውየ
አዲስ ዜማ ፈጥሮ ከባቲ ዋሆየ
‹‹የጎፈሬህ ጫካ መሸፈት ያሰኛል››
‹‹መለሎው ቁመትህ አክሱምን ያስንቃል››
ድንኩ ወዳጃችን በጎፈሬው ፋንታ መላጣው ያበራል
በርጩማ ላይ ቆሞ አዝማሪው ግምባር ላይ መቶ ብር ይመርጋል
ከኔ አለፍ ብለው ኣናረጅም ያሉ ሁለት አሮጊቶች
ይፍለቀለቃሉ ባዝማሪው ቃላቶች
‹‹ጡትሽ ማለት ሎሚ አንገትሽ ብርሌ››
‹‹ስከተልሽ ልኑር አርጊኝና ሎሌ››
ነገርና ብቅል ናላውን ያዞረው
አንዱ ስክር ያለ ላዝማሪው ጠየቀው
‹‹ጡትሽ ማለት ሎሚ ብለህ የገጠምከው››
‹ጡትሽ ሀምሳ ሎሚ ልትል ፈልገህ ነው?››
ሁለቱ አሮጊቶች ሁለት ነገር ሰሩ
ሰካራሙን ጠጪ ከቤት አስባረሩ
አዝማሪው ግምባር ላይ ረብጣ ጋገሩ
ህይወትን ስንፈታው መንታ ትርም አዝሏል
እውነትን መናገር ከደጃፍ ያስጥላል
በውሸት ማሞገስ ሽልማት ያዘንባል
‹‹ አንቺ ማለት ለኔ የምስራቅ ፀሀይ ነሽ ››
‹‹ንጋት እና ምሽት ቀን የምቆጥርብሽ››
ብየ የጻፍኩልሽ ያንድ ቀኑ ግጥም
እርሽው አታስታውሽው ለኔም አልገባኝም
አንቺ ማለት ለኔ በቃ አንቺ ማለት ነሽ
በልቤ ጎዳና ወክ አድርገሽ ያለፍሽ
የሆነ ቀን መጣሽ በሆነ ምሽት ሄድሽ
ስትመጪ ግቢ አልኩሽ ስትሄጂ ረሳሁሽ
መርሳት በሽታየ መርሳት መዳኒቴ
በመርሳት ታምሜ ዳንኩኝ በመርሳቴ
አንድ ሰው ነበረ እንደኔ ሚረሳ
ሲተኛ ይፅፋል እቃዎቹን ሁሉ የት እንዳኖራቸው
‹‹ጫማየ ቴብል ስር ካልሲዎቼ ደግሞ ጫማ ውስጥ ናቸው››
‹‹ሸሚዜ ሻንጣ ውስጥ ሱሪየ ወንበር ላይ››
‹‹ሞባይሌ መሬት እኔ ደሞ አልጋ ላይ ››
በጠዋት ይነሳና ደብተሩን ይገልጣል
ሱሪና ሸሚዙን ሞባይል ሰአቱን ካሉበት ያነሳል
አንድ ነገር ብቻ ከፃፈበት ያጣል
አልጋው ባዶ ሆኗል
እናም እንዳልረሳሽ ልፅፍሽ ስሞክር
አንቺን ከሌላዋ ለይቼ ማሰፍረው አጣሁ ልዩ ነገር
ተመሳሳይ ሀሳብ ባዲስ ገፅ መፃፍ
ደብተር መጨረስ ነው ብእርን ማንጠፍጠፍ
ይህ የፃፍኩት ግጥም ሀሳብና ቋንቋው ለዛና ፍሰቱ እንዳይሆን የሆነው
ላንቺ መታሰቢያ አንቺን እንዲመስል የሳልኩት ስዕል ነው፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዘላለም ምህረቱ
👍10👏7❤6
#ሰውና_ምላሱ
አምሮብኝ አጊጬ፥
ቢያዩኝ ተለውጬ፥
ሀብት ንብረት ኖሮኝ ከማጣት አምልጬ፥
..........ቀን ከሌት ብለፋ፥
..........ኑሮዬን ላፋፋ፥
ጥርሴ ሲስቅ ሲያዩኝ ጭንቀቴ ሲጠፋ፥
ሰርቼ በበላሁ ፀዳል ፊቴ ፈክቶ፥
ለፍቼ ባገኘሁ ቤት ማጀቴ ሞልቶ፥
ብኖር ሁለን ችዬ ከሰው ተስማምቼ፥
የግር እሳት ሆነ ይህ ለጠላቶቼ።
"እሷማ ሰላቢ ሌባ ናት ሟርተኛ፥
ሳትሰራ የምታገኝ ጠንቋይ መተተኛ፥
ገንዘብና ንብረት፥
ሰው አቀራት ውበት ፥
ሁሉን ከኛ ሰልባ ክብሯን ሾመችበት።"
.........ስትሉኝ ሰምቼ
..........በጣም ተከፍቼ
ሀብትና ውበቴን ሁሉን ነገር ትቼ፥
ለናንተው አድልቼ ከሰዎች ሸሽቼ፥
ብኖር ሁሉን ጥዬ በሬን ዘጋግቼ፥
በዚህስ መች ተዉኝ
"ጭራሽ ይባስ ብላ ንብረቷን አምክና፥
ገንዘቧን ለሰዎች ለወንዶች በትና፥
ይኸው ባዶ እጆቿን ቀረች በጎዳና፥"
ስትሉኝ ስማሁኝ ወይ የኔ ፈተና።
ቦርጭ አውጥቶ ሆዴ ቢወፍር አካሌ፥
አረገዘች አሉኝ አወየው እድሌ።
እሱንም ሰምቼ
በጣም ተከፍቼ
አካሌን ባከሳ ፍዳዬን በልቼ፥
አስወረደች ሲሉኝ ሰማሁ በጆሮቼ።
አረዲያ እስከመቼ.....
ኤጭ አሁንስ በቃኝ አስጠላኝ መኖሩ፥
ሰለቸኝ እናንተን ማለት እሹሩሩ።
የምላሳችሁ መርዝ ወደማይደርስበት፥
ከሀሜት አምልጬ እፎይይይ የምልበት፥
እናንተም አርፋችሁ እኔም ልረፍበት፥
..........አሁን እኳን ተዉኝ..........
ሞታቹን አልነካሁ ሞቴን ልሙትበት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አምሮብኝ አጊጬ፥
ቢያዩኝ ተለውጬ፥
ሀብት ንብረት ኖሮኝ ከማጣት አምልጬ፥
..........ቀን ከሌት ብለፋ፥
..........ኑሮዬን ላፋፋ፥
ጥርሴ ሲስቅ ሲያዩኝ ጭንቀቴ ሲጠፋ፥
ሰርቼ በበላሁ ፀዳል ፊቴ ፈክቶ፥
ለፍቼ ባገኘሁ ቤት ማጀቴ ሞልቶ፥
ብኖር ሁለን ችዬ ከሰው ተስማምቼ፥
የግር እሳት ሆነ ይህ ለጠላቶቼ።
"እሷማ ሰላቢ ሌባ ናት ሟርተኛ፥
ሳትሰራ የምታገኝ ጠንቋይ መተተኛ፥
ገንዘብና ንብረት፥
ሰው አቀራት ውበት ፥
ሁሉን ከኛ ሰልባ ክብሯን ሾመችበት።"
.........ስትሉኝ ሰምቼ
..........በጣም ተከፍቼ
ሀብትና ውበቴን ሁሉን ነገር ትቼ፥
ለናንተው አድልቼ ከሰዎች ሸሽቼ፥
ብኖር ሁሉን ጥዬ በሬን ዘጋግቼ፥
በዚህስ መች ተዉኝ
"ጭራሽ ይባስ ብላ ንብረቷን አምክና፥
ገንዘቧን ለሰዎች ለወንዶች በትና፥
ይኸው ባዶ እጆቿን ቀረች በጎዳና፥"
ስትሉኝ ስማሁኝ ወይ የኔ ፈተና።
ቦርጭ አውጥቶ ሆዴ ቢወፍር አካሌ፥
አረገዘች አሉኝ አወየው እድሌ።
እሱንም ሰምቼ
በጣም ተከፍቼ
አካሌን ባከሳ ፍዳዬን በልቼ፥
አስወረደች ሲሉኝ ሰማሁ በጆሮቼ።
አረዲያ እስከመቼ.....
ኤጭ አሁንስ በቃኝ አስጠላኝ መኖሩ፥
ሰለቸኝ እናንተን ማለት እሹሩሩ።
የምላሳችሁ መርዝ ወደማይደርስበት፥
ከሀሜት አምልጬ እፎይይይ የምልበት፥
እናንተም አርፋችሁ እኔም ልረፍበት፥
..........አሁን እኳን ተዉኝ..........
ሞታቹን አልነካሁ ሞቴን ልሙትበት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤10😢4👍3👎1
#ዕድሌ_ነው....
በሚስት ልወሰን እኔ ትዳር ሲያምረኝ
ሳታገባ ምትቆይ አንድም ሴት አትገኝ
እኔ ዲግሪ ስይዝ ዲግሪ ዋጋ ያጣል
ገንዘብ ያለው ሁሉ ዶክትሬት ያመጣል
እኔ መድረክ ስይዝ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ ይሆናል ትንሣኤ
በቁርባን ለመኖር ንሰሐ ስገባ
አቁራቢው ፖትልኮ ቤተመንግሥት ገባ
እኔ ኳስ ስገዛ ሜዳው ይታረሳል
እኔ ቤት ሲኖረኝ ሰፈሬ ይፈርሳል
ለተሾመ ሁሉ እንዳልኖርሁ ስለፋ
እኔ አለቃ ስሆን የሚታዘዝ ጠፋ
ዕድሌ ነውና...
ከዕለታት አንድ ቀን መንገሤ ባይቀርም
እኔ ንጉስ ስሆን ሀገሪቶ አትኖርም፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በሚስት ልወሰን እኔ ትዳር ሲያምረኝ
ሳታገባ ምትቆይ አንድም ሴት አትገኝ
እኔ ዲግሪ ስይዝ ዲግሪ ዋጋ ያጣል
ገንዘብ ያለው ሁሉ ዶክትሬት ያመጣል
እኔ መድረክ ስይዝ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ ይሆናል ትንሣኤ
በቁርባን ለመኖር ንሰሐ ስገባ
አቁራቢው ፖትልኮ ቤተመንግሥት ገባ
እኔ ኳስ ስገዛ ሜዳው ይታረሳል
እኔ ቤት ሲኖረኝ ሰፈሬ ይፈርሳል
ለተሾመ ሁሉ እንዳልኖርሁ ስለፋ
እኔ አለቃ ስሆን የሚታዘዝ ጠፋ
ዕድሌ ነውና...
ከዕለታት አንድ ቀን መንገሤ ባይቀርም
እኔ ንጉስ ስሆን ሀገሪቶ አትኖርም፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍35❤6✍4
#እኔ_አንተን_ከማጣ
...እኔ አንተን ከማጣ....
ደመናው ይቆጣ ያዝንብ ፡ ሚስማር ከላይ
ሲፈልግ ደጎራ ፡ ሲያሻው ጥርብ ድንጋይ
ፀሃይ ብርሃን ታቁም ፡ ስትፈልግ ትበተን
ምድር ዱቄት ትሁን ፡ ሲያሻት ከስላ ትብነን
ጨረቃም ትሠወር ፡ አትውጣ እድሜ ልኳን ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ስትፈልግ የሎጥ ሚስት ፡ ጎጃምኛ ትምታ
የፈርኦን ሠራዊት ፡ እስራኤልን ይቅጣ
የኤርትራም ባህር ፡ ይኑር በከፍታ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
እፅዋት ይድረቁ ፡ እንስሳት ይለቁ
ፕላኔቶች ሁሉ : ምድር ላይ ይውደቁ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ዳይኖሠር ተነስቶ ፡ በምድር እሣት ይትፋ
ምፃት ነገ ይሁን : አለም ካለም ትጥፋ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ምድረበዳው ያዝንብ : ኤርታሌም ይወርዛ
ኢህአዴግ አስር ሺህ ፡ አመታትን ይግዛ
ሲፈልግ ተሻግሮ ፡ አለማትን ይንዳ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ማወቅ ድብን ይበል : ባፍ ጢሙ ይደፋ
ክፉወች ወፍረው : መልካም አንገት ይድፋ ።
እኔ አንተን ከማጣ....
ፈጣሪ አሲድ ይርጭ : ምድሪቱን ያጉርፋት
ቁጣውን ያበርታ : አይዳኑ ፍጥረታት ።
እኔ አንተን ከማጣ.....
ማንም ምንም ይምጣ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
...እኔ አንተን ከማጣ....
ደመናው ይቆጣ ያዝንብ ፡ ሚስማር ከላይ
ሲፈልግ ደጎራ ፡ ሲያሻው ጥርብ ድንጋይ
ፀሃይ ብርሃን ታቁም ፡ ስትፈልግ ትበተን
ምድር ዱቄት ትሁን ፡ ሲያሻት ከስላ ትብነን
ጨረቃም ትሠወር ፡ አትውጣ እድሜ ልኳን ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ስትፈልግ የሎጥ ሚስት ፡ ጎጃምኛ ትምታ
የፈርኦን ሠራዊት ፡ እስራኤልን ይቅጣ
የኤርትራም ባህር ፡ ይኑር በከፍታ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
እፅዋት ይድረቁ ፡ እንስሳት ይለቁ
ፕላኔቶች ሁሉ : ምድር ላይ ይውደቁ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ዳይኖሠር ተነስቶ ፡ በምድር እሣት ይትፋ
ምፃት ነገ ይሁን : አለም ካለም ትጥፋ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ምድረበዳው ያዝንብ : ኤርታሌም ይወርዛ
ኢህአዴግ አስር ሺህ ፡ አመታትን ይግዛ
ሲፈልግ ተሻግሮ ፡ አለማትን ይንዳ ።
እኔ አንተን ከማጣ...
ማወቅ ድብን ይበል : ባፍ ጢሙ ይደፋ
ክፉወች ወፍረው : መልካም አንገት ይድፋ ።
እኔ አንተን ከማጣ....
ፈጣሪ አሲድ ይርጭ : ምድሪቱን ያጉርፋት
ቁጣውን ያበርታ : አይዳኑ ፍጥረታት ።
እኔ አንተን ከማጣ.....
ማንም ምንም ይምጣ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍15❤9😁4🥰2👏1😢1🙉1
#ሕልሜን_አደራ
ባይመረመሬ ጥበብ ተሽቀርቅሮ
ከወርቃማ ብርሃን፤ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ፥ ከህልሞቼ በቀር ፡፡
የኔ ውድ እንግዲህ
ሕልሜን እግሮችሽ ስር፥ ከዘረጋሁ ወዲህ፥
ቀስ ብለሽ ርገጪ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና የምትራመጂ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
ባይመረመሬ ጥበብ ተሽቀርቅሮ
ከወርቃማ ብርሃን፤ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ፥ ከህልሞቼ በቀር ፡፡
የኔ ውድ እንግዲህ
ሕልሜን እግሮችሽ ስር፥ ከዘረጋሁ ወዲህ፥
ቀስ ብለሽ ርገጪ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና የምትራመጂ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
👍18❤1🥰1
#እጠብቅሻለሁ!!
ሰኞ ለት ቀጥረሺኝ የምን ቀን ነው ብለሽ
ቀረሽ ሳትመጪ
ማክሰኞ ቀጥረሺኝ ታምሚያለሁ ብለሽ ከቤት ሳትወጪ
በረቡዕ ተስማምተን በጊዜ ወጥቼ
ስጠብቅሽ ቆሜ
ደውለሽ ይቅርታ ፆም ነው ለካ ዛሬ በፍስግ ይሻላል ሃሙስ
ወይ ቅዳሜ
ያልሺኝን አመኜ ሃሙስን መርጬ
አንቺን ለማማለል ብወጣም ዘንጬ
ወይ በረሽ አልመጣሽ ወይ ስልክሽ አይሰራ
ምን አገኛት እያልኩ እያሰላሰልኩኝ
ለብቻ ሳወራ
ድንገት ስልኬ ጠራ
"መቼም አታምነኝም ያጎቴ ልጅ ሞቶ
ለቅሶ ቤት ሄጄ ነው
እንዳትቀየመኝ ምንም ይሁን ምንም ነገ ግን ግድ ነው"
ብለሽ አምኛለሁ
ግን ግን ግዴለሽም !
አርብን እንዝለለው ላንቺም ይሻልሻል
በአፍቃሪ እይታ መጠራጠር የለም ሁሉም ይታመናል
ወይ ፆሙን አስታከሽ ወይ በልጁ ቀብር አትመጪም ይሆናል
ስለዚህ ቅዳሜ በተወደደው ቀን
ውጪ ዘንጪና
እኔም ልጠብቅሽ በጊዜ ወጥቼ አይንሽን ለማየት ጓጉቻለሁና
ቅዳሜንስ ለኔ ማነው የፈቀደው
ለመታመን ያህል በትመጪ ተስፋ ከመንገድ ቆሚያለሁ
ይኸው ቀኑም መሸ
የናፈቀው አይኔ ሳያይሽ ሟሸሸ
ካሁን በኋላ ግን እየወጡ መግባት እየገቡ መውጣት ስልችት ስላለኝ
እሁድን እዚያው ነኝ
ሰኞና ማክሰኞ እረቡም አለሁኝ
ሀሙስና አርብን ቅዳሜም አታጪኝ
ጎዳና አጎሳቁሎኝ ገፅታዬ ጠፍቶሽ
አይተሽ ካላለፍሺኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
ሰኞ ለት ቀጥረሺኝ የምን ቀን ነው ብለሽ
ቀረሽ ሳትመጪ
ማክሰኞ ቀጥረሺኝ ታምሚያለሁ ብለሽ ከቤት ሳትወጪ
በረቡዕ ተስማምተን በጊዜ ወጥቼ
ስጠብቅሽ ቆሜ
ደውለሽ ይቅርታ ፆም ነው ለካ ዛሬ በፍስግ ይሻላል ሃሙስ
ወይ ቅዳሜ
ያልሺኝን አመኜ ሃሙስን መርጬ
አንቺን ለማማለል ብወጣም ዘንጬ
ወይ በረሽ አልመጣሽ ወይ ስልክሽ አይሰራ
ምን አገኛት እያልኩ እያሰላሰልኩኝ
ለብቻ ሳወራ
ድንገት ስልኬ ጠራ
"መቼም አታምነኝም ያጎቴ ልጅ ሞቶ
ለቅሶ ቤት ሄጄ ነው
እንዳትቀየመኝ ምንም ይሁን ምንም ነገ ግን ግድ ነው"
ብለሽ አምኛለሁ
ግን ግን ግዴለሽም !
አርብን እንዝለለው ላንቺም ይሻልሻል
በአፍቃሪ እይታ መጠራጠር የለም ሁሉም ይታመናል
ወይ ፆሙን አስታከሽ ወይ በልጁ ቀብር አትመጪም ይሆናል
ስለዚህ ቅዳሜ በተወደደው ቀን
ውጪ ዘንጪና
እኔም ልጠብቅሽ በጊዜ ወጥቼ አይንሽን ለማየት ጓጉቻለሁና
ቅዳሜንስ ለኔ ማነው የፈቀደው
ለመታመን ያህል በትመጪ ተስፋ ከመንገድ ቆሚያለሁ
ይኸው ቀኑም መሸ
የናፈቀው አይኔ ሳያይሽ ሟሸሸ
ካሁን በኋላ ግን እየወጡ መግባት እየገቡ መውጣት ስልችት ስላለኝ
እሁድን እዚያው ነኝ
ሰኞና ማክሰኞ እረቡም አለሁኝ
ሀሙስና አርብን ቅዳሜም አታጪኝ
ጎዳና አጎሳቁሎኝ ገፅታዬ ጠፍቶሽ
አይተሽ ካላለፍሺኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
👍24❤14🔥10👏4
#በፀሀይ_ቅጠሪኝ
በዝናብ ስነግርሽ በርትቶብኝ ፍቅሬ
ሳይገባሽ ብታልፊ ዘንግተሽኝ ዛሬ
ብርሀን ሲፈካ ሲፈነጥቅ ጮራ
ጭጋጉ ሲበተን ዝናቡ ሲያባራ
ይሰማሽ ይሆናል እንባዬ ሲያወራ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በዝናብ ስነግርሽ በርትቶብኝ ፍቅሬ
ሳይገባሽ ብታልፊ ዘንግተሽኝ ዛሬ
ብርሀን ሲፈካ ሲፈነጥቅ ጮራ
ጭጋጉ ሲበተን ዝናቡ ሲያባራ
ይሰማሽ ይሆናል እንባዬ ሲያወራ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍13❤3👏2🔥1
#ጌታዬ_አቅቶኛል !
ፍቅርና ምህረትህ አልፎብኝ ከልኬ
መሸከም አቃተኝ ከበደኝ አምላኬ!
በየቱ ስራዬ በየቱ ትህትና
ችዬ ልሸከመው ደካማ ነኝና
አንተ ሁሌም ስትምር እኔ ሁሌም በዳይ
ጌታዬ አቅቶኛል ፍቅርህ ከብዶኝ ከላይ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ፍቅርና ምህረትህ አልፎብኝ ከልኬ
መሸከም አቃተኝ ከበደኝ አምላኬ!
በየቱ ስራዬ በየቱ ትህትና
ችዬ ልሸከመው ደካማ ነኝና
አንተ ሁሌም ስትምር እኔ ሁሌም በዳይ
ጌታዬ አቅቶኛል ፍቅርህ ከብዶኝ ከላይ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
❤24👍9🔥2
ያን ጠይሙን ዘመን ...
ያንን ገራም ወራት ...
ያን የጊዜ መቅኔ ያን የዘመን ኣስኳል ፤
በምን ወዜ ላስጊጥ በምን እጄ ልኳል?!
ያ ዘመን ገራሙ ...
ያ ዘመን ህያው ቃል ፤
ነገሩን በሙሉ የቀመሰው ያውቃል።
ብዬ ልተው ይሆን ...
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
የተቃኙበትን የነፍስያ ኣውታር ለዛ ስልቱን ሲያጡት ፤
የሚፈጥሩት ዜማ ፣
ከራስ ነፍስ ፈልቆ ለራስ የሚሰማ ፤
የሞት ጠረን ያለው ኑሮ ኑሮ 'ሚሸት ፤
ስሙኝ ስሙኝ የሚል የደናግል ዜማ
ቃሙኝ ቃሙኝ የሚል የማሽላ እሸት ።
( ትዝታ ግን ማለት ... )
ትዝታ ይጥላል ...
ትዝታ ያነሳል ፤
ትዝታ ይቸራል ...
ትዝታ ይነሳል ፤
ትዝታ ሆሄ ነው የተበታተነ የፈራረሰ ቃል ፤
ሲያሻው ያስከብራል በል ሲለው ያስንቃል ፤
ህልም እየነጠቀ ይተናል እንደጉም ፤
ትርጉም ማሳጣት ነው የትዝታ ትርጉም ።
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
እንኳን ባ'ይነ ስጋ ኣሻራውን ሲያጡት ፤
የሚደነግጡት ...
የሰቀቀን ሆሳ ።
ከገዛ ቅዠት ጋር በገሃድ የሚያብር ፤
ከንቱ ትላንት ነው ነገን የሚያሸብር ።
እውነት ነው ትዝታ
ከቅዠት ያብራል ፤
እውነት ነው ትዝታ
ነገን ያሸብራል ።
እንደውም ...
እንደውም ...
በዘመን ተብላልቶ የደቀቀ ቅስሙ ፤
እንደውም ትዝታ አሸብር ነው ስሙ ...
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሙሀመድ
ያንን ገራም ወራት ...
ያን የጊዜ መቅኔ ያን የዘመን ኣስኳል ፤
በምን ወዜ ላስጊጥ በምን እጄ ልኳል?!
ያ ዘመን ገራሙ ...
ያ ዘመን ህያው ቃል ፤
ነገሩን በሙሉ የቀመሰው ያውቃል።
ብዬ ልተው ይሆን ...
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
የተቃኙበትን የነፍስያ ኣውታር ለዛ ስልቱን ሲያጡት ፤
የሚፈጥሩት ዜማ ፣
ከራስ ነፍስ ፈልቆ ለራስ የሚሰማ ፤
የሞት ጠረን ያለው ኑሮ ኑሮ 'ሚሸት ፤
ስሙኝ ስሙኝ የሚል የደናግል ዜማ
ቃሙኝ ቃሙኝ የሚል የማሽላ እሸት ።
( ትዝታ ግን ማለት ... )
ትዝታ ይጥላል ...
ትዝታ ያነሳል ፤
ትዝታ ይቸራል ...
ትዝታ ይነሳል ፤
ትዝታ ሆሄ ነው የተበታተነ የፈራረሰ ቃል ፤
ሲያሻው ያስከብራል በል ሲለው ያስንቃል ፤
ህልም እየነጠቀ ይተናል እንደጉም ፤
ትርጉም ማሳጣት ነው የትዝታ ትርጉም ።
መቼም ይህ ትዝታ ...
የሳሙትን ከንፈር የዳበሱትን ጡት ፤
እንኳን ባ'ይነ ስጋ ኣሻራውን ሲያጡት ፤
የሚደነግጡት ...
የሰቀቀን ሆሳ ።
ከገዛ ቅዠት ጋር በገሃድ የሚያብር ፤
ከንቱ ትላንት ነው ነገን የሚያሸብር ።
እውነት ነው ትዝታ
ከቅዠት ያብራል ፤
እውነት ነው ትዝታ
ነገን ያሸብራል ።
እንደውም ...
እንደውም ...
በዘመን ተብላልቶ የደቀቀ ቅስሙ ፤
እንደውም ትዝታ አሸብር ነው ስሙ ...
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሙሀመድ
❤6👍2🥰2
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''
''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''
ውድ የግጥም ቻናል የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''
ውድ የግጥም ቻናል የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤9👍4🙏2
#እውነቱን_ልንገርህ?
እንደ ሙሴ በትር ተአምር ብትሰራ፥
እንደ ንጉስ ዳዊት አለምን ብትመራ፥
እንደ አብረሀም የዋህ ለሰው የምትራራ፥
ብትሆን በስራህ ሁሉን ምታኮራ፥
እውነቱን ልንገርህ አንዳችም ሳልደብቅ የውስጤን አሻራ...
እንደ እያሪኮ ግንብ አለም ብትፈራርስ፥
ምድር ብትደፋ ሰማዩ ቢታረስ፥
ጨረቃና ፀሀይ ወድቀው ቢሰበሩ፥
ከዋክብት እንደ ጉም በነው ቢሰወሩ፥
በጥፋት ውሀ ዳግም ምድር ተጥለቅልቃ፥
ነፍሴ ከፍም እሳት ከነበልባል ጠልቃ፥
የዚ አለም መከራ ቢጫን በኔ ጫንቃ፥
ሞት ቢፈረድብኝ መኖሬ ቢያበቃ፥
እውነቱን ልንገርህ?
ዳግም ተመልሼ እኔስ ያንተ እልሆንም አከተመ በቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እንደ ሙሴ በትር ተአምር ብትሰራ፥
እንደ ንጉስ ዳዊት አለምን ብትመራ፥
እንደ አብረሀም የዋህ ለሰው የምትራራ፥
ብትሆን በስራህ ሁሉን ምታኮራ፥
እውነቱን ልንገርህ አንዳችም ሳልደብቅ የውስጤን አሻራ...
እንደ እያሪኮ ግንብ አለም ብትፈራርስ፥
ምድር ብትደፋ ሰማዩ ቢታረስ፥
ጨረቃና ፀሀይ ወድቀው ቢሰበሩ፥
ከዋክብት እንደ ጉም በነው ቢሰወሩ፥
በጥፋት ውሀ ዳግም ምድር ተጥለቅልቃ፥
ነፍሴ ከፍም እሳት ከነበልባል ጠልቃ፥
የዚ አለም መከራ ቢጫን በኔ ጫንቃ፥
ሞት ቢፈረድብኝ መኖሬ ቢያበቃ፥
እውነቱን ልንገርህ?
ዳግም ተመልሼ እኔስ ያንተ እልሆንም አከተመ በቃ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍16👏5❤2
#አንደኛው_ሰው_ላንዱ
በቀን ወይ በሌሊት
በጾም በቅበላ
የበላ ይኖራል፥ ይብላኝ ለተበላ
ጋጋሪው ቢራቀቅ፥ ቢሰወር ምጣዱ
የለት እንጀራ ነው፤ አንደኛው ሰው ላንዱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
በቀን ወይ በሌሊት
በጾም በቅበላ
የበላ ይኖራል፥ ይብላኝ ለተበላ
ጋጋሪው ቢራቀቅ፥ ቢሰወር ምጣዱ
የለት እንጀራ ነው፤ አንደኛው ሰው ላንዱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
👍13❤2🔥2
#ቃል…
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል
ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል
እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል
ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’
የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ
ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ
ልበ ገራገሩን…
ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህለ
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀጣዩ ሲቀጥል
ስጠብቅሽ ነበር ከእስትንፋሴ እኩል
እዛው ነሽ አውቃለሁ እዚህ ነሽ መጥተሻል
ልቤ ገራገር ነው እስከዚህ ያምንሻል!’’
የሚለውን መዝጊያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ፎቶ ደብዳቤውን አንድላይ ሰብስባ
ፍቅር የሰጣትን በፍቅር አስባ
ልበ ገራገሩን…
ልቡን እንዳደማች ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህለ
❤14👍7
#ፈጥረህኝ_እያለህ
ፈጥረህኝ እያለ አሟልተህ በጤና
ማመስገን የማልችል ደካማ ነኝና
ለስጋዬ ማሰብ አድርጎኛል መና
ቪላ አልሰጠህኝ እንዲሁም መኪና
አልማዝ ወርቅም የለኝ እያለኝ ግን ጤና
እያልኩኝ ሳማርር አልገባኝምና
ለዚህ ለብልጭልጭ ለብስባሽ ገላ
ዛሬን አምሮ ታይቶ ነገን ለሚገማ
ሁሉስ መች አወቀው ነገ እንደሚቀማ
አምላክ ግን ሲጠራን ወርቄን ማቄን የለ
አልማዙም መኪናው ሁሉም የኛ አይደለ
ባንዲት አቡጀዲ ከነ ሀጢያታችን ከጉድጓድ አይደለ?
ታድያ ምን አለበት ተመስገን እያልን ከተሰጠን በልተን ካለንም ተቃምሰን
ይችን ብርቅርቅ አለም ወደ ኃላ ትተን
የሰይጣንን ሥራ ለሰይጣኑ ሰጥተን
የኛ የሆነውን አመስግነን ይዘን
ተመስገን ተመስገን በቃሉም ተገዝተን
እንኑር በፍቅር ባንድነት ተስማምተን::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ፈጥረህኝ እያለ አሟልተህ በጤና
ማመስገን የማልችል ደካማ ነኝና
ለስጋዬ ማሰብ አድርጎኛል መና
ቪላ አልሰጠህኝ እንዲሁም መኪና
አልማዝ ወርቅም የለኝ እያለኝ ግን ጤና
እያልኩኝ ሳማርር አልገባኝምና
ለዚህ ለብልጭልጭ ለብስባሽ ገላ
ዛሬን አምሮ ታይቶ ነገን ለሚገማ
ሁሉስ መች አወቀው ነገ እንደሚቀማ
አምላክ ግን ሲጠራን ወርቄን ማቄን የለ
አልማዙም መኪናው ሁሉም የኛ አይደለ
ባንዲት አቡጀዲ ከነ ሀጢያታችን ከጉድጓድ አይደለ?
ታድያ ምን አለበት ተመስገን እያልን ከተሰጠን በልተን ካለንም ተቃምሰን
ይችን ብርቅርቅ አለም ወደ ኃላ ትተን
የሰይጣንን ሥራ ለሰይጣኑ ሰጥተን
የኛ የሆነውን አመስግነን ይዘን
ተመስገን ተመስገን በቃሉም ተገዝተን
እንኑር በፍቅር ባንድነት ተስማምተን::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👌14❤10👍5💯3👏1
#ዝምታየን_አድምጥ
እየውልህ ፍቅሬ እኔም እንደ ሌላ፣
የሌለን ለመግለፅ ቃል እንደሚያሰላ፣
ካንገት በላይ ወዳጅ እንደግዜው ኗሪ ፣
አለ ሲሉት የለም የይምሰል አፍቃሪ ፣
ወሬ ቀባጥሬ ባልዋልክብት ውየ ፣
ከልቤ ያልታየን ሰው ስላለ ብየ፣
እንዲህ ነው በማለት ባፌ ባልነግርህም
በቃ ዝም ብለህ ዝምታየን አድምጥ
ያኔ ትሰማለህ ጥልቅ የመውደድ ህመም
ጥልቅ የማፍቀር ጩኸት የመሰለ እንደ ጥም
እየውልህ ፍቅሬ እኔም እንደ ሌላ፣
የሌለን ለመግለፅ ቃል እንደሚያሰላ፣
ካንገት በላይ ወዳጅ እንደግዜው ኗሪ ፣
አለ ሲሉት የለም የይምሰል አፍቃሪ ፣
ወሬ ቀባጥሬ ባልዋልክብት ውየ ፣
ከልቤ ያልታየን ሰው ስላለ ብየ፣
እንዲህ ነው በማለት ባፌ ባልነግርህም
በቃ ዝም ብለህ ዝምታየን አድምጥ
ያኔ ትሰማለህ ጥልቅ የመውደድ ህመም
ጥልቅ የማፍቀር ጩኸት የመሰለ እንደ ጥም
👍14🥰3❤2
#የሄድኩበት_መንገድ
እርሳኝ ያልሽኝ ጊዜ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
ከሰይጣን ታርቄ
በብቸኝነት ጥግ
በቅጠል ታሰሬ
በጭስ ተደብቄ!
ያንን ውብ ቁንጅና
ያንን ወብ ትዝታ
ክብርሽን አውርጄ
ልረሳሽ ታገልኩኝ
ከራሴ ተሟገትኩ
አመታት ወስጄ!
እናም ረሳሁሽ
መልክሽም ጠፋብኝ
ላስታውስሽ ሞከርኩ
ጭራሽ አልመጣ አልሽኝ
ይገርማል!
ውሎ አደሮ ሲገባኝ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
የሄድኩበት መንገድ
አንቺን አስረስቶ
ዛሬ እኔን አሳጣኝ
አንድ አስታዋሽ ዘመድ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እርሳኝ ያልሽኝ ጊዜ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
ከሰይጣን ታርቄ
በብቸኝነት ጥግ
በቅጠል ታሰሬ
በጭስ ተደብቄ!
ያንን ውብ ቁንጅና
ያንን ወብ ትዝታ
ክብርሽን አውርጄ
ልረሳሽ ታገልኩኝ
ከራሴ ተሟገትኩ
አመታት ወስጄ!
እናም ረሳሁሽ
መልክሽም ጠፋብኝ
ላስታውስሽ ሞከርኩ
ጭራሽ አልመጣ አልሽኝ
ይገርማል!
ውሎ አደሮ ሲገባኝ
ውዴ አንቺን ለመርሳት
የሄድኩበት መንገድ
አንቺን አስረስቶ
ዛሬ እኔን አሳጣኝ
አንድ አስታዋሽ ዘመድ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍12❤5👏4
#ማህሌተ_ገንቦ
ባጭር ቀረን ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
ፊታችንን ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ-
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዪም
ባጭር ቀረን ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
ፊታችንን ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ-
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዪም
👍14🍾4❤2👏2