#የኑሮ_ኳስ_ሜዳ
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ተጫዋች ነው እንጂ መሀል ዳኛ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ይሯሯጣል
ይራሱን ጎል ሰርቶ
የራሱን ያገባል የራሱን ይስታል
ሁሉም በጨዋታው ራሱ ተጠምዶ
አንዱ ያንዱን ላይዳኝ በኑሮ ተገዶ
ሁሉም ይራገጣል
እውነትን ጠልዞ ሀሰትን ይገባል
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ቢደክሙ ቢጎዱ ተቀያሪ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ሰው የራሱን 90 ደቂቃ
ተጫውቶ ሲያበቃ
ትንፋሹን ጨርሶ ድካሙን ተቋቁሞ
ሜዳውን ይለቃል በራሱ ሜዳ ላይ ራሱን ሰይሞ
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
መሸናነፍ እንጂ አቻ ውጤት የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም....
የዚህ ሁሉ ልፋት ፍሬ የሚያገኘው
የሜዳ አሯሯጡ ብቃት ሚመዘነው
ሀሰት አሽሞንሙኖ እውነት ማስመሰል ነው
በዚህች ከንቱ ዓለም....
ውሸት እውነት እንጂ እውነት ውሸት የለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ልዑል ሀይሌ
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ተጫዋች ነው እንጂ መሀል ዳኛ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ይሯሯጣል
ይራሱን ጎል ሰርቶ
የራሱን ያገባል የራሱን ይስታል
ሁሉም በጨዋታው ራሱ ተጠምዶ
አንዱ ያንዱን ላይዳኝ በኑሮ ተገዶ
ሁሉም ይራገጣል
እውነትን ጠልዞ ሀሰትን ይገባል
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ቢደክሙ ቢጎዱ ተቀያሪ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ሰው የራሱን 90 ደቂቃ
ተጫውቶ ሲያበቃ
ትንፋሹን ጨርሶ ድካሙን ተቋቁሞ
ሜዳውን ይለቃል በራሱ ሜዳ ላይ ራሱን ሰይሞ
በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
መሸናነፍ እንጂ አቻ ውጤት የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም....
የዚህ ሁሉ ልፋት ፍሬ የሚያገኘው
የሜዳ አሯሯጡ ብቃት ሚመዘነው
ሀሰት አሽሞንሙኖ እውነት ማስመሰል ነው
በዚህች ከንቱ ዓለም....
ውሸት እውነት እንጂ እውነት ውሸት የለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ልዑል ሀይሌ
👍14❤4
#መለየት
የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
🥰10👍7💔3
#ሰው_መስለሺኝ_ነበር
እስኪ ስሚኝ ውዴ
ልጠይቅሽ አንዴ
ላንቺ የሰው ልጅ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?
ፍቅርና ክብር ተስፋስ ምን ማለት ነው?
ስላንቺ ሳወራ ስላንቺ ስናገር
ለካስ አላውቅሽም ሰው መስለሺኝ ነበር
ለኔ እንኳን ግድ የለም ኃላ እንዳትጎጂ
መናቁን ተይና ሰው ማክበር ልመጂ
ለኔ ሲሆን ጊዜ ስጠራሽ ብውልም
እየቻልሽ አትችዪም እያለሽ የለሽም
ከቻልሽ አገናዝቢ ካልገባሽ ጠይቂ
ትንሽ የሚባል ሰው እንደሌለ እወቂ
ህሊና ላለው ሰው ትርግሙ ለገባው
እሺ ብሎ መቅረት እምቢ እንደማለት ነው
እኔ እኮ የሚገርመኝ ታሪክ እንደሰራ
አላፊ በሆነው በመልኳ ስትኮራ
ትመጪያለሽ እያልኩ በተስፋ ብኖርም
ባትመጪም ቅጠሪኝ ማለት ግን አልችልም
እናም አንዴ ስሚኝ ይጠቅምሻልና
ማስመሰሉን ትተሽ ሰው ሁኚ እንደገና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጉልላት አበበ
እስኪ ስሚኝ ውዴ
ልጠይቅሽ አንዴ
ላንቺ የሰው ልጅ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?
ፍቅርና ክብር ተስፋስ ምን ማለት ነው?
ስላንቺ ሳወራ ስላንቺ ስናገር
ለካስ አላውቅሽም ሰው መስለሺኝ ነበር
ለኔ እንኳን ግድ የለም ኃላ እንዳትጎጂ
መናቁን ተይና ሰው ማክበር ልመጂ
ለኔ ሲሆን ጊዜ ስጠራሽ ብውልም
እየቻልሽ አትችዪም እያለሽ የለሽም
ከቻልሽ አገናዝቢ ካልገባሽ ጠይቂ
ትንሽ የሚባል ሰው እንደሌለ እወቂ
ህሊና ላለው ሰው ትርግሙ ለገባው
እሺ ብሎ መቅረት እምቢ እንደማለት ነው
እኔ እኮ የሚገርመኝ ታሪክ እንደሰራ
አላፊ በሆነው በመልኳ ስትኮራ
ትመጪያለሽ እያልኩ በተስፋ ብኖርም
ባትመጪም ቅጠሪኝ ማለት ግን አልችልም
እናም አንዴ ስሚኝ ይጠቅምሻልና
ማስመሰሉን ትተሽ ሰው ሁኚ እንደገና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጉልላት አበበ
👍21❤7👏2
#ልቤን_ባታደምጪው
ላዩ ዘፈን መስሎ ፣ ውስጡ ከሚያስጨንቅ
ጆሮን ከሚያደማ ፣ባዶ ጩኸት ይልቅ
ምቱ ያልከረረውን...
ዘፈን ልስጥሽ ብዬ ፣ ከልቤ ላይ ዜማ
ያላዛኞች ብዛት...
ላዋከቡት ጆሮሽ ፣ ሳይጎል እንዲሰማ
ከልቤ ላስጠጋሽ
ደረቴ ላይ ጣልኩሽ ፤
አደመጥሽው ብዬም ፣ ደስ አለኝ አመንኩሽ፡፡
ግን ለካስ
የከፈትኩልሽ
የልቤ ውብ ዜማ ፣ በደሬቴ ሚፈስ
ለካ
ጥሞሻል ብዬ ስል ፣ እኔን እንደጣመኝ
ከሩቅ የሚሰማው...
የጎረቤት ዘፈን ሲያጓጓሽ አመመኝ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ኢዛና መስፍን
ላዩ ዘፈን መስሎ ፣ ውስጡ ከሚያስጨንቅ
ጆሮን ከሚያደማ ፣ባዶ ጩኸት ይልቅ
ምቱ ያልከረረውን...
ዘፈን ልስጥሽ ብዬ ፣ ከልቤ ላይ ዜማ
ያላዛኞች ብዛት...
ላዋከቡት ጆሮሽ ፣ ሳይጎል እንዲሰማ
ከልቤ ላስጠጋሽ
ደረቴ ላይ ጣልኩሽ ፤
አደመጥሽው ብዬም ፣ ደስ አለኝ አመንኩሽ፡፡
ግን ለካስ
የከፈትኩልሽ
የልቤ ውብ ዜማ ፣ በደሬቴ ሚፈስ
ለካ
ጥሞሻል ብዬ ስል ፣ እኔን እንደጣመኝ
ከሩቅ የሚሰማው...
የጎረቤት ዘፈን ሲያጓጓሽ አመመኝ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ኢዛና መስፍን
👍16❤4👏1
#አልነግርሽም
ሰው አያውቅም እንጂ ፊደል እንደ ዓዳኝ ጥይት ይታጠቃል፤
ገዳይ ይመስለኛል ከቃላት መካከል "ወድሻለው" 'ሚል ቃል፤
አልነግርሽም ውዴ
ለመኖር ስታገል ዘባራቂ አፌ ሀቁን ከከፈተው፤
ድንገት ወለም አርጎት ወድሻለሁ ብሎ ምላሴ ከሳተው፤
አትጠራጠሪ……
አንቺ የሰማሽ ቀን ነው እኔ የምሞተው፤
ያጠመዱ ይመስል
ምላሴ ጫፉ ላይ እንዳኖሩ ፈንጂ፤
ገና ልንገርሽ ስል
ቃሉ ይበትነኛል አልነግርሽም እንጂ፤
አልነግርሽም ውዴ
እንደ ሻማ እንደ ጧፍ ያለሽበት ሁሉ ብርሃን ካረበበ፤
እንኳን'ና ገፅሽ……
ከጥፍርሽ እንኳ' ውበት ከታለበ፤
ይህንን እያዬ መኖር የፈለገ የተፈጥሮ ደባል፤
"ወድሻለሁ" ብሎ በራሱ ጭንቅላት እንዴት ቃታ ይስባል?፤
አልነግርሽም ውዴ
ሰው አያውቅም እንጂ ፊደል እንደ አዳኝ ሊገል ይታጠቃል፤
ገዳይ ይመስለኛል ከቃላት መካከል "ወድሻለው" ሚል ቃል፤
ምናልባት ምናልባት እንዲህ አስባለሁ፤
ኑሮ ያስጠላኝ ጊዜ……
የታከተኝ ጊዜ……
ራሴን ለማጥፋት የወሰንኩኝ ጊዜ ልነግርሽ መጣለሁ፤
ምክንያት……
መርዝና መኪና ከልብ ያፈቀረ ሰው ስለማይገሉ፤
ዓይንሽን እያየሁ "ወድሻለሁ" ስልሽ ይገለኛል ቃሉ፤
እስከዛ ኣልነግርሽም……
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ምስክር ይብራ
ሰው አያውቅም እንጂ ፊደል እንደ ዓዳኝ ጥይት ይታጠቃል፤
ገዳይ ይመስለኛል ከቃላት መካከል "ወድሻለው" 'ሚል ቃል፤
አልነግርሽም ውዴ
ለመኖር ስታገል ዘባራቂ አፌ ሀቁን ከከፈተው፤
ድንገት ወለም አርጎት ወድሻለሁ ብሎ ምላሴ ከሳተው፤
አትጠራጠሪ……
አንቺ የሰማሽ ቀን ነው እኔ የምሞተው፤
ያጠመዱ ይመስል
ምላሴ ጫፉ ላይ እንዳኖሩ ፈንጂ፤
ገና ልንገርሽ ስል
ቃሉ ይበትነኛል አልነግርሽም እንጂ፤
አልነግርሽም ውዴ
እንደ ሻማ እንደ ጧፍ ያለሽበት ሁሉ ብርሃን ካረበበ፤
እንኳን'ና ገፅሽ……
ከጥፍርሽ እንኳ' ውበት ከታለበ፤
ይህንን እያዬ መኖር የፈለገ የተፈጥሮ ደባል፤
"ወድሻለሁ" ብሎ በራሱ ጭንቅላት እንዴት ቃታ ይስባል?፤
አልነግርሽም ውዴ
ሰው አያውቅም እንጂ ፊደል እንደ አዳኝ ሊገል ይታጠቃል፤
ገዳይ ይመስለኛል ከቃላት መካከል "ወድሻለው" ሚል ቃል፤
ምናልባት ምናልባት እንዲህ አስባለሁ፤
ኑሮ ያስጠላኝ ጊዜ……
የታከተኝ ጊዜ……
ራሴን ለማጥፋት የወሰንኩኝ ጊዜ ልነግርሽ መጣለሁ፤
ምክንያት……
መርዝና መኪና ከልብ ያፈቀረ ሰው ስለማይገሉ፤
ዓይንሽን እያየሁ "ወድሻለሁ" ስልሽ ይገለኛል ቃሉ፤
እስከዛ ኣልነግርሽም……
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ምስክር ይብራ
👍14❤7👏2🥰1
#ኑዛዜ
ማን ነበር እንደኔ
ከየፅዋው ቀማሽ
ከጭን ሸለቆ ስር፣ የገነት ምንጭ ማሽ
አሁን እዚህ ሆኜ
ከኪሴ እያወጣሁ፣ ዘመኔን ስደምር
ከመኖር አርፌ፣ ማስታወስ ስጀምር
ከጣፋጩ ብትይ፣ ወይም ከሚመረው
ያንቺ ጣም ብቻ ነው፣ አፌ ላይ የቀረው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
ማን ነበር እንደኔ
ከየፅዋው ቀማሽ
ከጭን ሸለቆ ስር፣ የገነት ምንጭ ማሽ
አሁን እዚህ ሆኜ
ከኪሴ እያወጣሁ፣ ዘመኔን ስደምር
ከመኖር አርፌ፣ ማስታወስ ስጀምር
ከጣፋጩ ብትይ፣ ወይም ከሚመረው
ያንቺ ጣም ብቻ ነው፣ አፌ ላይ የቀረው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
❤11👍8
#ነግሬሽ_ከበረ!
ሴት ክብሯን ረስታ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ፣ የሁሉም የሆነው!!!
ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም-ግባትሽ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅ አይን...
ከተበተነበት፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ
ትንሽ ስትዘነጊኝ፣ ብዙ እንደማስብ!!!
ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ፣ ለ'ራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም፣ የሚኮነው እናት።
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ-ቢስ ህይወቶች፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ፣ ከልጇ እንዳልወጣ
ወልዳም ምንም ነች፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
ነግሬሽ ነበረ
ሴት ክብሯን ስትጥል፣ እድሜዋ ይሄዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴት ልጅ ውበት ነው፣ ካየበት ይለምዳል።
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ጭንቅላቴን፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሽት ፊት፣ ስድብ ይመስላሉ።
ግን እነግርሻለሁ፣ ዛሬም ሳልታበይ
ነግሪያት ነበር ስል፣ አንቺ "ሰደበኝ" በይ።
ግን እነግርሻለሁ...
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ያፈቅራታል፣ አንዱም ጋር የለችም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በላይ በቀለ ወያ
ሴት ክብሯን ረስታ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ፣ የሁሉም የሆነው!!!
ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም-ግባትሽ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅ አይን...
ከተበተነበት፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ
ትንሽ ስትዘነጊኝ፣ ብዙ እንደማስብ!!!
ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ፣ ለ'ራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም፣ የሚኮነው እናት።
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ-ቢስ ህይወቶች፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ፣ ከልጇ እንዳልወጣ
ወልዳም ምንም ነች፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
ነግሬሽ ነበረ
ሴት ክብሯን ስትጥል፣ እድሜዋ ይሄዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴት ልጅ ውበት ነው፣ ካየበት ይለምዳል።
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ጭንቅላቴን፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሽት ፊት፣ ስድብ ይመስላሉ።
ግን እነግርሻለሁ፣ ዛሬም ሳልታበይ
ነግሪያት ነበር ስል፣ አንቺ "ሰደበኝ" በይ።
ግን እነግርሻለሁ...
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ያፈቅራታል፣ አንዱም ጋር የለችም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በላይ በቀለ ወያ
👍19❤7👏4🔥2
#ሶስቱ_ፍሬ_ቢሶች
የተማረ ሆኖ ዕውቀቱን የማይገልጥ
ባለጠጋ ሆኖ ለደሀ የማይሰጥ
ደሀ ሆኖ መስራት የሚጠላ ልቡ
ሶስቱ ፍሬ ቢሶች ለምንም አይረቡ !
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ከበደ ሚካኤል
የተማረ ሆኖ ዕውቀቱን የማይገልጥ
ባለጠጋ ሆኖ ለደሀ የማይሰጥ
ደሀ ሆኖ መስራት የሚጠላ ልቡ
ሶስቱ ፍሬ ቢሶች ለምንም አይረቡ !
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ከበደ ሚካኤል
👍22❤6💯4
#ያማል!
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶብሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ
እና እንደ ነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑችኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከ
የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት
እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደ ነገርኩሽ
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረ መጣ
ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት
እ. . . .ና. . . .ቷን !
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ
ግን አንቺን ስወድሽ
ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል !!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህሌ
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶብሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ
እና እንደ ነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑችኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከ
ጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕልየ`ጭቃ እሾህ ወግቶት
እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደ ነገርኩሽ
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረ መጣ
ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት
እ. . . .ና. . . .ቷን !
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ
ግን አንቺን ስወድሽ
ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል !!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህሌ
🥰12❤8👍4👏2
#እንባዬን_የት_ላርገው
ቀና በል ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ
በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ
ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው
ወዴት ልሸሽገው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ቀና በል ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ
በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ
ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው
ወዴት ልሸሽገው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤6👍6🥰2😢2🔥1
#ጸሎቴ_ስለቴ
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ለአንድ ጊዜ ብቻ፣ የለሊት ወፍን ክንፍ፤
የጨለመን ዘመን፣ ሰንጥቆ ʽሚያሳልፍ፡፡
እንደየኖህ መርከብ፣ እንደሙሴ በትር፤
ከዘመን ደንቃራ፣
ከገዢ ፉከራ፣
ከመንጋ ገጀራ፣
ፍጡራንን ሁሉ፣ ጠብቆ ʽሚያሻግር፡፡
የሆነ ምትሀት!
የሆነ ብልሀት!
. . . . . . ፈጣሪ ቢያድለኝ!
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
እንደህጻን ትንፋሽ፣ ሳያነቃ ከእንቅልፍ፤
እንደንጋት ዝናብ፣ ህልም ሳያዛንፍ፤
በዛሬዬ ስፍር - ለነገ እንድበቃ፤
ሽንቁሬን ደፍኜ - ሰው ሆኜ እንድነቃ፤
የሆነ ምትሀት፡፡
የሆነ ብልሀት፡፡
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ከታሪክ አለት ላይ፣
በጥላቻ ትርክት፣
በቂም በቀል መሮ የተፈለፈሉ፤
በየእድሩ ደጃፍ፣
በየተራራው ጫፍ፣
. . . . . . . . . . እንዳሸን የፈሉ፤
የጥፋት ርችት፣ አዳፍኔ ሀውልቶች፤
የአብሮነት ፍልፈል፣ አይጠ መጎጦች፤
እንደቅቤ ቀልጠው፣
እመቀመቅ ወርደው፣
በቆሙበት ቦታ፤
ለትውልድ የሚተርፍ፣ ጊዜን የሚረታ፤
የፍትህ፣ የፍቅር፣ የአብሮነት ቁርባን፤
ለልጅ ልጅ የሚቆይ፣ትርጉም ያለው ድርሳን፤
. . . . . . አሻራ እንዲኖረኝ፤
ፈጣሪ ቢያድለን፣
. . . . . . ፈጣሪ ቢያድለኝ!
መቼም መላ የለን፣
. . . . . መቼም መላ የለኝ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በድሉ ዋቅጅራ
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ለአንድ ጊዜ ብቻ፣ የለሊት ወፍን ክንፍ፤
የጨለመን ዘመን፣ ሰንጥቆ ʽሚያሳልፍ፡፡
እንደየኖህ መርከብ፣ እንደሙሴ በትር፤
ከዘመን ደንቃራ፣
ከገዢ ፉከራ፣
ከመንጋ ገጀራ፣
ፍጡራንን ሁሉ፣ ጠብቆ ʽሚያሻግር፡፡
የሆነ ምትሀት!
የሆነ ብልሀት!
. . . . . . ፈጣሪ ቢያድለኝ!
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
እንደህጻን ትንፋሽ፣ ሳያነቃ ከእንቅልፍ፤
እንደንጋት ዝናብ፣ ህልም ሳያዛንፍ፤
በዛሬዬ ስፍር - ለነገ እንድበቃ፤
ሽንቁሬን ደፍኜ - ሰው ሆኜ እንድነቃ፤
የሆነ ምትሀት፡፡
የሆነ ብልሀት፡፡
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ከታሪክ አለት ላይ፣
በጥላቻ ትርክት፣
በቂም በቀል መሮ የተፈለፈሉ፤
በየእድሩ ደጃፍ፣
በየተራራው ጫፍ፣
. . . . . . . . . . እንዳሸን የፈሉ፤
የጥፋት ርችት፣ አዳፍኔ ሀውልቶች፤
የአብሮነት ፍልፈል፣ አይጠ መጎጦች፤
እንደቅቤ ቀልጠው፣
እመቀመቅ ወርደው፣
በቆሙበት ቦታ፤
ለትውልድ የሚተርፍ፣ ጊዜን የሚረታ፤
የፍትህ፣ የፍቅር፣ የአብሮነት ቁርባን፤
ለልጅ ልጅ የሚቆይ፣ትርጉም ያለው ድርሳን፤
. . . . . . አሻራ እንዲኖረኝ፤
ፈጣሪ ቢያድለን፣
. . . . . . ፈጣሪ ቢያድለኝ!
መቼም መላ የለን፣
. . . . . መቼም መላ የለኝ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በድሉ ዋቅጅራ
❤2👍2🥰2
#ምስጢር
ሁሉም እንደዘበት፣
ሁሉም በዘልማድ፤
ሁሉም እንዲያው፣ እንዲያው፣
የሚሆን መስሎሃል …
ጉንዳንን ተመልከት፣
የወፍ ቤትን አጥና፣
ንቦችን አስተውል
አንድ የውሻ ጩኸት፣
ሙዚቃ እየሆነ
ዓለምን ያነጋል፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገብረክርስቶስ ደስታ
ሁሉም እንደዘበት፣
ሁሉም በዘልማድ፤
ሁሉም እንዲያው፣ እንዲያው፣
የሚሆን መስሎሃል …
ጉንዳንን ተመልከት፣
የወፍ ቤትን አጥና፣
ንቦችን አስተውል
አንድ የውሻ ጩኸት፣
ሙዚቃ እየሆነ
ዓለምን ያነጋል፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገብረክርስቶስ ደስታ
👍5⚡3❤1🔥1
#ይሄን_ቃል_ፍቺልኝ ?
ምን ያደርግልሻል ስለኔ ጥሩነት እየተናገሩ
ጥሎ መኮብለሉ
በማይሆን ሽንገላ በማይዋጥ ቋንቋ
እኔን ማባበሉ
ምናለበት ብትሄጅ ጥፋቴን ተናግረሽ
ለበደልከው በደል ቅጣት ይሁን ብለሽ
ቅስሜም ቢሰባበር ፀፀቱም ቢገለኝ
እራሴን ብኮንን የጄን ስለሰጠኝ
እባክሽ የኔ ሆድ ባክሽ ስለ ፍቅር
ጥሩ ነህ ተብሎ እንዴት ይተዋል ሰው
እኔን አልገባኝም ፍቺው ይሄን ምስጢር
እውነቱን ንገሪኝ ግዴለም አትስጊ
ልስማሽ በጥሞና
ከተዋበ ውሸት የሚያስጠላ እውነት
ይሻለኛልና
ባክሽ በፈጠረሽ! ባክሽ ባርባ'ራቱ
መልስ አምጣ እያለኝ ነው አፍ አውጥቶ ቤቱ
ምን ልመልሰለት ጥላኝ ሄደች ልበል
ስለሆንኩኝ ጥሩ
አምኖስ ይቀበላል ጣራና ግድግዳው
የቤቴ ማገሩ
አያሻኝም እቴ አንቺ አበሽ ብዬ
አብሬ ማበዱ
ምን ይሉታል ይሄን ለወዳጅ ዘመዱ
መኖር አልፈልግም የማይመስል ነገር
እየዘላበዱ
ዳግመኛ አይለምደኝም አላስቸግርሽም
መልሽ ይቺን ብቻ ?
አንቺው ጋር ነው ያለው እንዲህ ያስጨከነሽ
የሚስጥሩ መፍቻ
እኔም ክፉ አልሁን በቀሪው ህይወቴ
ጥሩነቴም አይሁን ምክንያት የሆነኝ
አንቺን ለማጣቴ
ጨካኝ ያረገሽ ሚስጥሩን ፍቺልኝ
በሞቴ በሞቴ
__በሞቴ በሞቴ !!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
ምን ያደርግልሻል ስለኔ ጥሩነት እየተናገሩ
ጥሎ መኮብለሉ
በማይሆን ሽንገላ በማይዋጥ ቋንቋ
እኔን ማባበሉ
ምናለበት ብትሄጅ ጥፋቴን ተናግረሽ
ለበደልከው በደል ቅጣት ይሁን ብለሽ
ቅስሜም ቢሰባበር ፀፀቱም ቢገለኝ
እራሴን ብኮንን የጄን ስለሰጠኝ
እባክሽ የኔ ሆድ ባክሽ ስለ ፍቅር
ጥሩ ነህ ተብሎ እንዴት ይተዋል ሰው
እኔን አልገባኝም ፍቺው ይሄን ምስጢር
እውነቱን ንገሪኝ ግዴለም አትስጊ
ልስማሽ በጥሞና
ከተዋበ ውሸት የሚያስጠላ እውነት
ይሻለኛልና
ባክሽ በፈጠረሽ! ባክሽ ባርባ'ራቱ
መልስ አምጣ እያለኝ ነው አፍ አውጥቶ ቤቱ
ምን ልመልሰለት ጥላኝ ሄደች ልበል
ስለሆንኩኝ ጥሩ
አምኖስ ይቀበላል ጣራና ግድግዳው
የቤቴ ማገሩ
አያሻኝም እቴ አንቺ አበሽ ብዬ
አብሬ ማበዱ
ምን ይሉታል ይሄን ለወዳጅ ዘመዱ
መኖር አልፈልግም የማይመስል ነገር
እየዘላበዱ
ዳግመኛ አይለምደኝም አላስቸግርሽም
መልሽ ይቺን ብቻ ?
አንቺው ጋር ነው ያለው እንዲህ ያስጨከነሽ
የሚስጥሩ መፍቻ
እኔም ክፉ አልሁን በቀሪው ህይወቴ
ጥሩነቴም አይሁን ምክንያት የሆነኝ
አንቺን ለማጣቴ
ጨካኝ ያረገሽ ሚስጥሩን ፍቺልኝ
በሞቴ በሞቴ
__በሞቴ በሞቴ !!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
👍6❤3🥰1👏1
#አድዋ
ታሪክ በሰራ ተራራሽ ፣ በኮረብታና ተረተሩ
በሸለቆና በጋራሽ ፣በሰማይና በምድሩ
በአምባላጌ በእንጢቾ ፣ በአባ ዳዕሮ ጉብታ
በእንዳ ኪዳነምሕረት ፣ በኣዲ አቡን ምከታ
በማርያም ሸዊት ሸለቆ ፣ በአዲፍቼና ሰማያታ
በመቀሌው ምሽግ ድርሳን ፣ በእንዳየሱስ ኮረብታ
በአባ ገሪማ ፍልሚያሽ ፣ በዓድዋ እቶን ወላፈን
በሶሎዳ ተራራ ክንድሽ ፣ ግብርሽ ዛሬም ይትረፈን
የሚያሳድደን መከራ ፣ በድልሽ መጀን ይለፈን
ያስተባበርሽው ሕብረት ፣
አንድ ያደረግሽው አንድነት ፣ በጽኑ ክንዱ ይቀፈን
ባንቺ መድኃኒት እንዳን ፣ እናትነትሽ ያትርፈን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ አበባው መላኩ
ታሪክ በሰራ ተራራሽ ፣ በኮረብታና ተረተሩ
በሸለቆና በጋራሽ ፣በሰማይና በምድሩ
በአምባላጌ በእንጢቾ ፣ በአባ ዳዕሮ ጉብታ
በእንዳ ኪዳነምሕረት ፣ በኣዲ አቡን ምከታ
በማርያም ሸዊት ሸለቆ ፣ በአዲፍቼና ሰማያታ
በመቀሌው ምሽግ ድርሳን ፣ በእንዳየሱስ ኮረብታ
በአባ ገሪማ ፍልሚያሽ ፣ በዓድዋ እቶን ወላፈን
በሶሎዳ ተራራ ክንድሽ ፣ ግብርሽ ዛሬም ይትረፈን
የሚያሳድደን መከራ ፣ በድልሽ መጀን ይለፈን
ያስተባበርሽው ሕብረት ፣
አንድ ያደረግሽው አንድነት ፣ በጽኑ ክንዱ ይቀፈን
ባንቺ መድኃኒት እንዳን ፣ እናትነትሽ ያትርፈን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ አበባው መላኩ
🔥6👍4❤2
#ባክህ_ቶሎ_አትምጣ...
ጥሩ እንዳደረጉ እንደሰሩ ደህና
ብለው ይፀልያሉ ጌታ ሆይ ቶሎ ና፣
እኔ ግን ምስኪኑ ሀጢያተኛ ልጅህ
ይችን ፀሎት ፀለይኩ ወድቄ ከደጀህ፣
አምላኬ...
ካለሁበት ሀጢያት ነብሴን ሳላወጣ
በንስሀ ፀፀት እራሴን ሳልቀጣ
ባክህ ቶሎ አትምጣ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ እዮብ ዘ-ማርያም
ጥሩ እንዳደረጉ እንደሰሩ ደህና
ብለው ይፀልያሉ ጌታ ሆይ ቶሎ ና፣
እኔ ግን ምስኪኑ ሀጢያተኛ ልጅህ
ይችን ፀሎት ፀለይኩ ወድቄ ከደጀህ፣
አምላኬ...
ካለሁበት ሀጢያት ነብሴን ሳላወጣ
በንስሀ ፀፀት እራሴን ሳልቀጣ
ባክህ ቶሎ አትምጣ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ እዮብ ዘ-ማርያም
👍17❤5😭5👏4😢2
#በመንገዴ
ሁሉም ሲተራመስ……
በመታየት ዘመን ~ ሲሯሯጥ ለታይታ፤
ነብሴ ስትደበቅ……
ካንቺ ብሌን ውጪ ~ መታየቷን ፈርታ፤
ሰ'ው ስጋን ያያል ~ ነብስ ተደብቃ፤
በዚህ ሁሉ መሀል……
ነብሴን ነው 'ምታየው~ነብስሽ አጮልቃ፤
እንዲህ በመንገዴ
የዘነጠ ወጣት ~ መልካም የለበሰ፤
ጎጆ በሌለበት ~ ጎጆ የቀለሰ፤
ወዘናው ያማረ ~ ዓማርጦ የጎረሰ፤
እንዲህ በመንገዴ
ዓይናማ ሚመራ ~ የታወረ መሪ፤
አስራ አራቱ ሀብታም……
መሆኛ መንገዶች~ሚናገር መካሪ፤
እንዲህ በመንገዴ፤
በህዝብ ላቦት ላይ~ሀብቱን የዘረጋ~የሰባ ነጋዴ፤
ሁሉም ኣይኖቼ ላይ~ትምክህቱን ይሰራል፤
ቀኔን ለማጨለም………
ጉድለቴን አግዝፎ ~ ሊያሳየኝ ይጥራል፤
እግዚኦ! ላንቺ መውደድ
ይህን ሁሉ እንዳላይ……
የፍቅርሽ ግድግዳ ~ ሆኖልኛል ተገን፤
ኣቤት! ስትጋርጂኝ…………
ስቄ ነው ማልፋቸው~እግዚሃብሄር ይመስገን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ምስክር ይብራ
ሁሉም ሲተራመስ……
በመታየት ዘመን ~ ሲሯሯጥ ለታይታ፤
ነብሴ ስትደበቅ……
ካንቺ ብሌን ውጪ ~ መታየቷን ፈርታ፤
ሰ'ው ስጋን ያያል ~ ነብስ ተደብቃ፤
በዚህ ሁሉ መሀል……
ነብሴን ነው 'ምታየው~ነብስሽ አጮልቃ፤
እንዲህ በመንገዴ
የዘነጠ ወጣት ~ መልካም የለበሰ፤
ጎጆ በሌለበት ~ ጎጆ የቀለሰ፤
ወዘናው ያማረ ~ ዓማርጦ የጎረሰ፤
እንዲህ በመንገዴ
ዓይናማ ሚመራ ~ የታወረ መሪ፤
አስራ አራቱ ሀብታም……
መሆኛ መንገዶች~ሚናገር መካሪ፤
እንዲህ በመንገዴ፤
በህዝብ ላቦት ላይ~ሀብቱን የዘረጋ~የሰባ ነጋዴ፤
ሁሉም ኣይኖቼ ላይ~ትምክህቱን ይሰራል፤
ቀኔን ለማጨለም………
ጉድለቴን አግዝፎ ~ ሊያሳየኝ ይጥራል፤
እግዚኦ! ላንቺ መውደድ
ይህን ሁሉ እንዳላይ……
የፍቅርሽ ግድግዳ ~ ሆኖልኛል ተገን፤
ኣቤት! ስትጋርጂኝ…………
ስቄ ነው ማልፋቸው~እግዚሃብሄር ይመስገን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ምስክር ይብራ
🔥9👍6❤1
#የፍቅር_ሞረድ
ብእረኛ ባሎችሽ፣ አግብተው የፈቱሽ፣ ፈትተው ያላገቡሽ
ርእስ እየሰጡ፣ አሽቀንጥረው ጣሉሽ
ያገኘሁት ልብሽ፣ ከሰውዳር ተጥሎ
ተፅፎበት ነበር -ነዝናዛ -ጨቅጫቃ-ሻካራ ነሽ ተብሎ
ነዝናዛ-ጨቅጫቃ ሻካራ ነሽ ተብሎ።
ይነዝንዘኝ እቱ፣
ይጨቅጭቀኝ እቱ፣
ሽክረትሽ ጣፋጩ።
መሸረፍ መሳሉን፣ ተዪው ለጨባጩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በረከት በላይነህ
ብእረኛ ባሎችሽ፣ አግብተው የፈቱሽ፣ ፈትተው ያላገቡሽ
ርእስ እየሰጡ፣ አሽቀንጥረው ጣሉሽ
ያገኘሁት ልብሽ፣ ከሰውዳር ተጥሎ
ተፅፎበት ነበር -ነዝናዛ -ጨቅጫቃ-ሻካራ ነሽ ተብሎ
ነዝናዛ-ጨቅጫቃ ሻካራ ነሽ ተብሎ።
ይነዝንዘኝ እቱ፣
ይጨቅጭቀኝ እቱ፣
ሽክረትሽ ጣፋጩ።
መሸረፍ መሳሉን፣ ተዪው ለጨባጩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በረከት በላይነህ
👍7❤3
#ይናገራል_ፎቶ
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳሙኤል አለሙ
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳሙኤል አለሙ
👍10❤4🔥4
#ጠብቂኝ_አልልም
አንድ ቀን
መጣለው ያልሽው ቃል ልቤ ከተዋህደ፥
ዘመን ጉድፉ አርጎኝ ስንቴ ጥሎኝ ሄደ፥
ስንት ዜ የጣፍኩት መናኛ ኑሮዬ ስንቴ ተቀደደ፥
በእምነት የካብኩት የልቤ የተስፋ ካብ ስንት ዜ ተናደ፥
በቀን መፈራረቅ የፀና ጉልበቴ ስንት ጊዜ ራደ፥
እኮ
ስንቴ?
ስንቴ?
ግዴለም፦
አትደንግጭ የኔ አለም፥
ይህንን ስትሰሚ አትራጅ የኔ ውድ፥
ወትሮም ዘመን ሯጭ ነው ተይው ጥሎኝ ይሂድ፥
ብቻ፦
የመምጣትሽ ወራት ከእድሜዬ ድር ረዝሞ፥
ጠባቂሽ የኔ ልብ እንዳይጎድል ታሞ፥
ናፋቂሽ የኔ አካል እንዳይጫጭ ዘሞ፥
ብዬ የሰጋሁ እለት፦
ከመጠበቅ ይልቅ መፈለግ ሲቀለው አካሌ በተራው፥
ከቤቴ የመጣሽ ለት ከቤትሽ መጥቼ እንዳላጣሽ ፈራው፥
ብቻ ያኔም ቢሆን፦
ልፈልግሽ እንጂ ጠብቂኝ አልልም፥
ልቤ ይህን ያውቃል
የመቅጠርን ያህል መጠበቅ አይቀልም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ቢንያም በሀይሉ
አንድ ቀን
መጣለው ያልሽው ቃል ልቤ ከተዋህደ፥
ዘመን ጉድፉ አርጎኝ ስንቴ ጥሎኝ ሄደ፥
ስንት ዜ የጣፍኩት መናኛ ኑሮዬ ስንቴ ተቀደደ፥
በእምነት የካብኩት የልቤ የተስፋ ካብ ስንት ዜ ተናደ፥
በቀን መፈራረቅ የፀና ጉልበቴ ስንት ጊዜ ራደ፥
እኮ
ስንቴ?
ስንቴ?
ግዴለም፦
አትደንግጭ የኔ አለም፥
ይህንን ስትሰሚ አትራጅ የኔ ውድ፥
ወትሮም ዘመን ሯጭ ነው ተይው ጥሎኝ ይሂድ፥
ብቻ፦
የመምጣትሽ ወራት ከእድሜዬ ድር ረዝሞ፥
ጠባቂሽ የኔ ልብ እንዳይጎድል ታሞ፥
ናፋቂሽ የኔ አካል እንዳይጫጭ ዘሞ፥
ብዬ የሰጋሁ እለት፦
ከመጠበቅ ይልቅ መፈለግ ሲቀለው አካሌ በተራው፥
ከቤቴ የመጣሽ ለት ከቤትሽ መጥቼ እንዳላጣሽ ፈራው፥
ብቻ ያኔም ቢሆን፦
ልፈልግሽ እንጂ ጠብቂኝ አልልም፥
ልቤ ይህን ያውቃል
የመቅጠርን ያህል መጠበቅ አይቀልም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ቢንያም በሀይሉ
👍5❤2🔥1