ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ሰላም Family እንዴት ናችሁ? የግጥም ፖስት ላሻሽል አስቤ ነበር እስኪ VOTE አድርጉ
Anonymous Poll
16%
በሳምንት 2 ፖስት
48%
በሳምንት 3 ፖስት
4%
በሳምንት 1 ፖስት
32%
በእስከዛሬው ይቀጥል
👍81
#ያልታደለች_እናት

ሳቋን ለገሰችው
መልኳን አተመችው
ሳጠግብ አጉርሳ ከዚህ አደረሰችው
አደገልኝ አለች ጦሮ ሊያሳርፈኝ
የልፋቴን ዋጋ ፈጣሪ ሊክሰኝ

ግና መቼ ሊሆን ከልቧ ያለመችው
በእርሱ ስትሰቃይ ዕድሜዋን ፈጀችው
ዕድሜዋን ፈጀችው!
ውጥኗን ቀጨችው!
መኖር እንዳልጓጓች ሞቷን ናፈቀችው
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኪሩቤል አሰፋ
😢185🥰3👏1
#አፋልጉኝ
💚💚💚💛💛💛
ስህተቱን አራሚ
ሌሎችንም ሰሚ
ፍፁም ነኝ የማይል በእብሪት ተወጥሮ
በሀሳብ ልእልና የሚያከብር ተከብሮ
ሲሰራ የሚሳሳት ፍጥኖ ደግሞ አራሚ
የእርሱን ብቻ ሳይሆን የሰው ሀሳብ ሰሜ
በሰውነት ሚዛን እራሱን የለካ
የግል አቋም ያለው የሌላ ሳይነካ
አፋልጉኝ ጠፋብኝ
ካያችሁ ንገሩኝ
ወረታ ከፋይ ነኝ
ይህን ሰው ላሳዬኝ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
11👍8👏4
#ጊዜ_በረርክ_በረርክ

ጊዜ በረርክ በረርክ
ጊዜ በረርክ በረርክ
ግና ምን አተረፍክ
ግና ምን አጎደልክ?
ሞትን አላሸነፍክ
ሕይወትን አልገደልክ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍103🔥2
#ይድረስ_ለእናቴ_ልጅ

ደምህ እና ደሜ
ከገነቱ ጠበል ከጊዮን ተቀድቶ
ስጋዬ እና ስጋህ
ከበረከት አፈር ከኤደን ተቦክቶ
ያውም በእግዜር ቃል
በተስፋዋ ምድር ሰው ሆኖ እነዳልኖረ
ያ ሁሉ ፍቅራችን
በትንሽ የዘር ክር ስለምን ታሰረ?

አንተ'ኮ ክብሬ ነህ
የመጎሴ ሚስጥር ህመሜን ታማሚ
እኔ'ኮ ደስታህ ነኝ
ከባድ ሀዘንህን ቀሎኝ ተሸካሚ፡፡

ያ'ንተ ዘር የኔ ዘር
ትሁፊቴ ትሁፍትህ ባህልህ ባህሌ
ዘመናት ስንኖር
ሳቄ ሳቅህ ነበር በደልህ በደሌ፡፡

ግሸን ስታስቀድስ
ለዱኒያ ዱአ ነጃሽ ካድሜአለሁ
እዛ'ና እዚህ ሆነን
በቁልቢ ስትምል በፂሆን ምያለሁ፡፡

ባ'ክሱም ስመፃደቅ
በ'ላሊበላ አለት ኩራት ተሰምቶሀል
በጀጎል ሳቅራራ
በፋሲለደስ ጌጥ አምረህ ሸልለሀል፡፡

ታዲያ ምነው ዛሬ
ዘመን ባጎደፈው በማይድን ነቀርሳ
በዘር አቅላሚዎች
አንድነትን ጠልተን ተለየን በጎሳ?

እባክህ ወንድሜ
ለባለቀን ብለህ ከፍቶህ አታስከፋኝ
አንተ ነህ ደስታዬ
ሲረግጡን ተረግጠህ ሲገፉን አትግፋኝ፡፡

ባይሆን ከረገጠን
ከገፋን ባለቀን ደም እየጨለጠ ከሰከረ ነፍሱ
በአንድነት ጠበል
ተጠምቀን እንዳን
ለለከፈን ሴጣን ፋቅራችን ነው ምሱ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11👍5👏2
መኖር በሰው ፍቃድ ሆነና ዘንድሮ
ማስተዋል ተሳነን ልባችን ታውሮ።
ጌታ የሰጠውን ፍጡር ከነጠቀ
አትጠራጠሩ ይህ ዘመን አለቀ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍236🥰1
ግጥም
ሰላም Family እንዴት ናችሁ? የግጥም ፖስት ላሻሽል አስቤ ነበር እስኪ VOTE አድርጉ
1 ሺ ሰው አይቶታል VOTE ያደረገ ሰው ግን 111 ሰው ነው 🤔
🥰10
#ወህኒ

ካቻምና በመስቀል ድፎ ባርኬአለሁ።
ዘንድሮ በጩቤ አጥንት ወግቻለሁ።

          ለምን እንዳትሉ፤
           በቃ ሆነ በሉ፤
           የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አምና ደግ ነበርኩ ፣ ክፉ ሰው ዘንድሮ
ትናንትና ምሁር ፣ ዛሬ ግን ደንቆሮ ።

            ለምን እንዳትሉ ፤
            በቃ ሆነ በሉ ፤
            የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

መሆን አምሮኝ ያውቃል፤ ፖለቲከኛ ሰው ፣ ኃያል የጦር መሪ ፤
ተመኝቼም ነበር ለመሆን አዝማሪ ፤
ገጣሚ ለመሆን ስንኝ ቋጥሬአለሁ ፤
ደራሲ ለመሆን ተስዬም አውቃለሁ ፤
ሞዴል አርሶአደርም ለመሆን ፈልጌ ፣
አስጠምጄ ነበር ከ 4 ኪሎ ግርጌ ።
ኢንጂነር ዶክተርም ልሆን ነበር እኮ ፤
እንደዚህ ሆንኩ እንጂ ነገር ሌላ ታኮ ።

            ለምን እንዳትሉ፤
            በቃ ሆነ በሉ ፤
            የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አንድ ሰው አንድ ነው ከንግዲህ አትበሉ ፤
            የሰው ልጅ ወህኒ ነው ፤
እልፍ አዕላፍ ሰዎች ታስረው የተጣሉ ፣
መውጫ አጥተው ነው እንጂ፣አንድ ሰው ውስጥ አሉ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ይስማዕከ ወርቁ
👏11👍81
#እቅፍ_አርጎ_የሚይዝ

ቢኒያም በለጠ ና ጀግናው ና ወንዱ ፡
አላስኬድም አለ ችግር በመንገዱ ፤
ውሀ ሆነው ቀርተው ሀገር የሚንዱ ፡
ምነው እንደ ቢኒ ሺዎች ቢወለዱ ፤

በምድር እየኖረ በሰማይ ቤት ሰሪ ፡
ማንአለ እንደቢኒ ለነፍሱ አዳሪ ፤
ዛሬም እንደ ቢኒ ሳይል ቤት ትዳሬ ፡
እቅፍ አርጎ የሚይዝ ትሻለች ሀገሬ ፡
በተግባር የሆነ ያይደለ በወሬ ፤

በስምንተኛው ሺህ ሰዉ በከፋበት ፡
ቢኒያም በለጠ ተከሰተ ድንገት ፤
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ክንፈ ጀማነህ
👍13👏4
አውቆ እንዳላወቀ ሰምቶ እንዳልሰማ ሰው
ያረገኝን ሁሉ በደሉን ስረሳው
እሱው ይከሰኛል እሱው ይወቅሰኛል
በኔ ችሎ ማለፍ ሞኝ ነህ ይለኛል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
15
#የኑሮ_ኳስ_ሜዳ

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ተጫዋች ነው እንጂ መሀል ዳኛ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ይሯሯጣል
ይራሱን ጎል ሰርቶ
የራሱን ያገባል የራሱን ይስታል
ሁሉም በጨዋታው ራሱ ተጠምዶ
አንዱ ያንዱን ላይዳኝ በኑሮ ተገዶ
ሁሉም ይራገጣል
እውነትን ጠልዞ ሀሰትን ይገባል

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ቢደክሙ ቢጎዱ ተቀያሪ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ሰው የራሱን 90 ደቂቃ
ተጫውቶ ሲያበቃ
ትንፋሹን ጨርሶ ድካሙን ተቋቁሞ
ሜዳውን ይለቃል በራሱ ሜዳ ላይ ራሱን ሰይሞ

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
መሸናነፍ እንጂ አቻ ውጤት የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም....
የዚህ ሁሉ ልፋት ፍሬ የሚያገኘው
የሜዳ አሯሯጡ ብቃት ሚመዘነው
ሀሰት አሽሞንሙኖ እውነት ማስመሰል ነው
በዚህች ከንቱ ዓለም....
ውሸት እውነት እንጂ እውነት ውሸት የለም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ልዑል ሀይሌ
👍144
#መለየት

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   በእውቀቱ ስዩም
🥰10👍7💔3
#ሰው_መስለሺኝ_ነበር

እስኪ ስሚኝ ውዴ
ልጠይቅሽ አንዴ
ላንቺ የሰው ልጅ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?
ፍቅርና ክብር ተስፋስ ምን ማለት ነው?
ስላንቺ ሳወራ ስላንቺ ስናገር
ለካስ አላውቅሽም ሰው መስለሺኝ ነበር
ለኔ እንኳን ግድ የለም ኃላ እንዳትጎጂ
መናቁን ተይና ሰው ማክበር ልመጂ
ለኔ ሲሆን ጊዜ ስጠራሽ ብውልም
እየቻልሽ አትችዪም እያለሽ የለሽም
ከቻልሽ አገናዝቢ ካልገባሽ ጠይቂ
ትንሽ የሚባል ሰው እንደሌለ እወቂ
ህሊና ላለው ሰው ትርግሙ ለገባው
እሺ ብሎ መቅረት እምቢ እንደማለት ነው
እኔ እኮ የሚገርመኝ ታሪክ እንደሰራ
አላፊ በሆነው በመልኳ ስትኮራ
ትመጪያለሽ እያልኩ በተስፋ ብኖርም
ባትመጪም ቅጠሪኝ ማለት ግን አልችልም
እናም አንዴ ስሚኝ ይጠቅምሻልና
ማስመሰሉን ትተሽ ሰው ሁኚ እንደገና።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ጉልላት አበበ
👍217👏2
#ልቤን_ባታደምጪው

ላዩ ዘፈን መስሎ ፣ ውስጡ ከሚያስጨንቅ
ጆሮን ከሚያደማ ፣ባዶ ጩኸት ይልቅ
ምቱ ያልከረረውን...
ዘፈን ልስጥሽ ብዬ ፣ ከልቤ ላይ ዜማ
ያላዛኞች ብዛት...
ላዋከቡት ጆሮሽ ፣ ሳይጎል እንዲሰማ
ከልቤ ላስጠጋሽ
ደረቴ ላይ ጣልኩሽ ፤
አደመጥሽው ብዬም ፣ ደስ አለኝ አመንኩሽ፡፡

ግን ለካስ
የከፈትኩልሽ
የልቤ ውብ ዜማ ፣ በደሬቴ ሚፈስ
ለካ
ጥሞሻል ብዬ ስል ፣ እኔን እንደጣመኝ
ከሩቅ የሚሰማው...
የጎረቤት ዘፈን ሲያጓጓሽ አመመኝ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኢዛና መስፍን
👍164👏1
#አልነግርሽም

ሰው አያውቅም እንጂ ፊደል እንደ ዓዳኝ ጥይት ይታጠቃል፤
ገዳይ ይመስለኛል ከቃላት መካከል "ወድሻለው" 'ሚል ቃል፤

አልነግርሽም ውዴ

ለመኖር ስታገል ዘባራቂ አፌ ሀቁን ከከፈተው፤
ድንገት ወለም አርጎት ወድሻለሁ ብሎ ምላሴ ከሳተው፤
አትጠራጠሪ……
አንቺ የሰማሽ ቀን ነው እኔ የምሞተው፤

ያጠመዱ ይመስል
ምላሴ ጫፉ ላይ እንዳኖሩ ፈንጂ፤
ገና ልንገርሽ ስል
ቃሉ ይበትነኛል አልነግርሽም እንጂ፤

አልነግርሽም ውዴ

እንደ ሻማ እንደ ጧፍ ያለሽበት ሁሉ ብርሃን ካረበበ፤
እንኳን'ና ገፅሽ……
ከጥፍርሽ እንኳ' ውበት ከታለበ፤

ይህንን እያዬ መኖር የፈለገ የተፈጥሮ ደባል፤
"ወድሻለሁ" ብሎ በራሱ ጭንቅላት እንዴት ቃታ ይስባል?፤

አልነግርሽም ውዴ

ሰው አያውቅም እንጂ ፊደል እንደ አዳኝ ሊገል ይታጠቃል፤
ገዳይ ይመስለኛል ከቃላት መካከል "ወድሻለው" ሚል ቃል፤

ምናልባት ምናልባት እንዲህ አስባለሁ፤
ኑሮ ያስጠላኝ ጊዜ……
የታከተኝ ጊዜ……
ራሴን ለማጥፋት የወሰንኩኝ ጊዜ ልነግርሽ መጣለሁ፤

ምክንያት……

መርዝና መኪና ከልብ ያፈቀረ ሰው ስለማይገሉ፤
ዓይንሽን እያየሁ "ወድሻለሁ" ስልሽ ይገለኛል ቃሉ፤

እስከዛ ኣልነግርሽም……
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ምስክር ይብራ
👍147👏2🥰1
#ኑዛዜ

ማን ነበር እንደኔ
ከየፅዋው ቀማሽ
ከጭን ሸለቆ ስር፣ የገነት ምንጭ ማሽ
አሁን እዚህ ሆኜ
ከኪሴ እያወጣሁ፣ ዘመኔን ስደምር
ከመኖር አርፌ፣ ማስታወስ ስጀምር

ከጣፋጩ ብትይ፣ ወይም ከሚመረው
ያንቺ ጣም ብቻ ነው፣ አፌ ላይ የቀረው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በዕውቀቱ ስዩም
11👍8
#ነግሬሽ_ከበረ!

ሴት ክብሯን ረስታ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ፣ የሁሉም የሆነው!!!

ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም-ግባትሽ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅ አይን...
ከተበተነበት፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ
ትንሽ ስትዘነጊኝ፣ ብዙ እንደማስብ!!!

ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!

ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ፣ ለ'ራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም፣ የሚኮነው እናት።
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ-ቢስ ህይወቶች፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ፣ ከልጇ እንዳልወጣ
ወልዳም ምንም ነች፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።

ነግሬሽ ነበረ
ሴት ክብሯን ስትጥል፣ እድሜዋ ይሄዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴት ልጅ ውበት ነው፣ ካየበት ይለምዳል።

ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ጭንቅላቴን፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር፣ ሁሉም ከመረጠው!

ብነግርሽ ብነግርሽ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሽት ፊት፣ ስድብ ይመስላሉ።
ግን እነግርሻለሁ፣ ዛሬም ሳልታበይ
ነግሪያት ነበር ስል፣ አንቺ "ሰደበኝ" በይ።

ግን እነግርሻለሁ...
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ያፈቅራታል፣ አንዱም ጋር የለችም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
  በላይ በቀለ ወያ
👍197👏4🔥2
#ሶስቱ_ፍሬ_ቢሶች

         የተማረ ሆኖ ዕውቀቱን የማይገልጥ
         ባለጠጋ ሆኖ ለደሀ የማይሰጥ
         ደሀ ሆኖ መስራት የሚጠላ ልቡ
         ሶስቱ ፍሬ ቢሶች ለምንም አይረቡ !
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
        ከበደ ሚካኤል
👍226💯4
#ያማል!

እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶብሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ
እና እንደ ነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑችኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
ላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል
የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት
እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደ ነገርኩሽ
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረ መጣ
ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት
እ. . . .ና. . . .ቷን !
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ
ግን አንቺን ስወድሽ
ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል !!!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ሰለሞን ሳህሌ
🥰128👍4👏2
#እንባዬን_የት_ላርገው

ቀና በል ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ
በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ
ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው
ወዴት ልሸሽገው?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
6👍6🥰2😢2🔥1
#ጸሎቴ_ስለቴ

ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ለአንድ ጊዜ ብቻ፣ የለሊት ወፍን ክንፍ፤
የጨለመን ዘመን፣ ሰንጥቆ ʽሚያሳልፍ፡፡
እንደየኖህ መርከብ፣ እንደሙሴ በትር፤
ከዘመን ደንቃራ፣
ከገዢ ፉከራ፣
ከመንጋ ገጀራ፣
ፍጡራንን ሁሉ፣ ጠብቆ ʽሚያሻግር፡፡
የሆነ ምትሀት!
የሆነ ብልሀት!
. . . . . . ፈጣሪ ቢያድለኝ!
ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
እንደህጻን ትንፋሽ፣ ሳያነቃ ከእንቅልፍ፤
እንደንጋት ዝናብ፣ ህልም ሳያዛንፍ፤
በዛሬዬ ስፍር - ለነገ እንድበቃ፤
ሽንቁሬን ደፍኜ - ሰው ሆኜ እንድነቃ፤
የሆነ ምትሀት፡፡
የሆነ ብልሀት፡፡

ጸሎቴ፤
ስለቴ፣ . . .
ከታሪክ አለት ላይ፣
በጥላቻ ትርክት፣
በቂም በቀል መሮ የተፈለፈሉ፤
በየእድሩ ደጃፍ፣
በየተራራው ጫፍ፣
. . . . . . . . . . እንዳሸን የፈሉ፤
የጥፋት ርችት፣ አዳፍኔ ሀውልቶች፤
የአብሮነት ፍልፈል፣ አይጠ መጎጦች፤
እንደቅቤ ቀልጠው፣
እመቀመቅ ወርደው፣
በቆሙበት ቦታ፤
ለትውልድ የሚተርፍ፣ ጊዜን የሚረታ፤
የፍትህ፣ የፍቅር፣ የአብሮነት ቁርባን፤
ለልጅ ልጅ የሚቆይ፣ትርጉም ያለው ድርሳን፤
. . . . . . አሻራ እንዲኖረኝ፤
ፈጣሪ ቢያድለን፣
. . . . . . ፈጣሪ ቢያድለኝ!
መቼም መላ የለን፣
. . . . . መቼም መላ የለኝ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በድሉ ዋቅጅራ
2👍2🥰2