ግጥም
4.29K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
በመንጋ በመንጋ ሆናችሁ ስትሄዱ
አደራ በሞቴ እኔን አትውሰዱ።
የጅምላ ፍረጃ ወንዝ ላያሻግር
ህልሜን ልኑርበት እያልኩ ሀገር ሀገር።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👍1🤔1
ቤተሰብ ዛሬ የፍቅር ግጥም ይለቀቅ?
👍64
#አልተኛም_ከእንግዲህ

በህልም ዓለም መጥተሽ
በሁኔ ከማጣሽ
አትምጪ ልንገርሽ
ድሮም ስቃዬ ነሽ
ስተኛ አይሻለለሁ
ስነቃ አጣሻለሁ
አንቺ የጠዋት ጤዛ
መጥተሽ መሄድ በዛ
በህልሜ እየመጣሽ መንገዴን ከምስት
አልተኛም ከእንግዲህ አንቺን ላለማየት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👍2👎1
ሰላም 🕊
🕊7
#ሸማኔ_የለንም

ጥበበኛ ጠፍቶ በጥበበኛ ሀገር
አስማምቶ አሻጋሪ በእውነተኛ ፍቅር
ፈታይ ሳይቸግረን ድርና ማግ ሞልቶ
ሸማኔ የለንም ሀገር ሰሪ አስማምቶ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6👍2
አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ
ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ
ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም
ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም
ቅዝምዝሙ ይለፍ ገንበስ ልበልና
ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🔥8👍2
ቀልድ ያስፈልጋል?
👍9
ማዘር👵ምጣድ ልትገዛ ሄዳ 2500 ብር ሲሏት
.
.
ምንድነው አንዱን ጋግሬ ሌላውን Copy ነው እንዴ ማደርገው?🤔
አይ ማዘሯ 💋❤️
🤣13👍3
ዛሬ አንዷን አናድጃት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው

እስኪ ቂጤን አቀብለኝ የምትል ሚስት ይስጥህ አላለችኝም እግዞ
😁11🙈5
የዝምታ ቅኔን መፍታት ሲሳናቸው
ዝም ያለ ፈሪ ነው ማለት ቀለላቸው
ከብዙ ዋይታ ከልፍ አላፍ ጋጋታ
ብቻውን ያስፈራል ቅኔ ነው ዝምታ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
4👍2🔥1
#የቀበጦች_ቀበጥ

አንድ ላም አለችኝ ከሰማይ መስክ ላይ
ማንም የማያልባት ወተቷንም አላይ
ባዶ ተስፋ ብቻ ወተትን የማትሰጥ
አለችኝ አንድ ላም የቀበጦች ቀበጥ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
😁91👍1
አጥብቄ እይዛለሁ ቀሚስሽን ጠፍሬ
እናቴ ባንቺ ነው የቆምኩኝ ጠንክሬ
አንቺን ሲነኩብኝ አምርሬ እቆጣለሁ
በእንባ በለቅሶዬ አትንኳት እላለሁ
ብርታት የማገኘው በጠረንሽ ናርዶስ
በክፉ የሚያይሽ ሁለት ዓይኑ ይፍሰስ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👏1
👋ቤተሰብ👋
#የከበረ_የለም

ሁሉም እዩኝ እዩኝ ልውጣ ከአደባባይ
የሚለው ሰው በዝቶ ከነነውሬ ልታይ
ለዝና ለክብር ፈጥኖ ሲሽቀዳደም
ውርደቱን ይዘግናል የከበረ የለም
እውቀትን ፍለጋ በጥበብ ካልወጣ
በአቋራጭ ጎደና ከዝናው ቢወጣ
መልሶ ይወርዳል ቁልቁል ተንደርድሮ
ሁሉም አንቱ በሉኝ አዛዥ ነው ዘንድሮ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍73🔥2
#ሞኝ_ነው_ይሁዳ

በሰላሳ ዲናር ወዳጁን የከዳ
የራሱን ሞት ገዛ በተሰጠው ዋጋ
ህይወቱ ላያድን ለስጋው ላይረዳ
ሞቱን በሞት ገዛ ሞኝ ነው ይሁዳ
ተጸጽቶ ሲድን ጴጥሮስ ዶሮን ሰምቶ
ይሁዳ ግን ሸጠው ዋጋውን አስልቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
5👍1
ምን አንሰማው አለን እኛማ ዘንድሮ
ወይ ገደቡን አያውቅ ሞልቶ አይሞላ ጆሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
4
#በተራበ_ተራ

የአንተን ቤት አፍርሶ የራሱን ቢሰራ
እርሱም ይደርሰዋል በሌላኛው ተራ
አንዱ የሰራውን አንዱ እያፈረሰ
የዘመናት እድሜ አልቆ ገሰገሰ።
እግዜሩ ታረቀን " ና " ውረድ " ና " ፍረድ
ልማዳችን ሆኗል እየሰሩ መናድ።
እንዴት ሰው ይኖራል ሰርቶ እያፈረሰ
ከቤታችን ቀድሞ ልብ ካልታደሰ።
አንዱ ያበጀውን ደክሞ ትላንትና
በተራበ ተራ ይቀጥላል ገና።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍53
React በማረግ አብሮነታችሁን አሳዩኝ
🥰9💯1
#አምላክ_ጥበበኛ

የሚታደል ቢሆን እድሜ በስም ጥሪ
ሁሉም ድሃ ሞቶ ሀብታም ነበር ነዋሪ
ስልጣኑ ቢገባ በቀበሌው መሪ
ልክ እንደ ዳቧችን ቢሆን በስም ጥሪ
የድሃ እድሜ ሁሉ ለሀብታም ተሽጦ
ከምድሩ በጠፋ እስካሁን ተመርጦ
አምላክ ጥበበኛ ሰውን ጥንት ሲሰራው
እንኳን የእድሜን ገደብ በእራሱ አደረገው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👍3👏1
ከልቡ ሳይመክር ሰው እየመከረ
ለእራሱ ሳይገባው እያደናገረ
ስንቱ ነው በምላስ ተስፋን የሰበረ
የመከረ መስሎት ብሶትን የሚያብስ
በሰው ጉዳይ ገብቶ ስቆ የሚያስለቅስ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍53
በበጎች ሀገር ላይ የቀበሮ እረኛ
ከአህዮች ጉባኤ ቆሞ የጅብ ዳኛ
ለፍርድ የማይመች ለሰሚውም ግራ
ጭብጥ በሌለው ዘመን እውነት አይወራ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏2