ግጥም በግጥም
252 subscribers
1 video
4 links
ፍቅራችሁን እንጁ ሀሳቦቻችሁን አትስጧቸው!
Download Telegram
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ምን ይሉታል

አይኔ ሞኙ ዞሮር አይታክት
ሲቃኝ ሲይስስ ድንገት ቢያያት
የአይኔን ዱካ ተከትሎ
ልቤ ሄደ እኔን ጥሎ

አይን እንዳየ ልብ ወስኖ
የእሷ ገረድ አሽከር ሆኖ
መውደቅ ማመን ደጅ መፅናቱ
በጨረፍታ መመኘቱ
ይድላት ይክፋት እንኩዋ ሳላውቅ
ዉስጤ አብዝቶ የሚጨነቅ
እንዳወቃት እንዳጠና
መናፈቁ ያን ቁንጅና
ይህን ተግባር ምን ይሉታል
ማንስ ብለው ይጠሩታል
ያላዩትን አለም ያክቃኙትን መንደር
በሃሳብ እያሰሱ ሲዳክሩ ማደር

አምላክ ፈጥሮ ለአዳም ብርታት
አብራክ ክፍሉን ሄዋን አላት
የእኔም ሄዋን ግራ ጎኔ
ፍቅር ልትሆን በዘመኔ
ቀን መጣልኝ ብየ ማስብ
ተስፋን ከእሷ ፍቅር የምክብ
ምን ይባላል ምን ቃል አለው
ልክ አጣሁኝ እሚወክለው

Join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👏5👍2
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንደ ፈጣሪየ

ክርስቶስ አደለ አምሳያ ፍጡሩርን
ሞቶ ያስተማረው እጅጉን ማፍቀሩን
እኔም እንደጌታ ልክ እንደፈጠረኝ
ንፁህ ፍቅሩን ሲሰጥ ፋቅር እንዳስተማረኝ

ከልቤ መውደዴን ካንጀቴ ማፍቀሬን
ማሳያ እጅ መንሻ ይሄው እኔነቴን
እሰዋልሻለሁ፣ አቀርብልሻለሁ፣ ንፁህ ስሱን ልቤን።

ልክ እንደፈጣሪ በፍቅርሽ ስቅላት
ላንቺ ተሸንፎ ዉስጥ አካሌ ሲሞት
ለፍቅርሽ ቀላልጦ የፈሰሰው ልቤን
ካካሌ ተቆርሶ፣ ወዳንቺ የመጣው የዘነጋኝ ቀልቤን
ከስጋ ወደሙ ከአምላክ ፍቅር ቆጥረሽ
በካህኑ ፍቅር በመውደድ ላቁርብሽ

ቁርባኑ ይጠበቅ ትንከባከቢው ዘንድ
ልብሽ ከልቤ ዉስጥ በጥብቁ ይገመድ
ዉሀም እንዳትነኪ አርካሽ አፍራሹን
ቁርባኑን ዘንግተሽ እንዳትይዥ ሌላውን።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👏6
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰው ልሁን??
ሰው ልምሰል??

አይ! ሰው ልምሰል መሰለኝ
ደልቃቃ የደላው ኑሮ እንዲኖረኝ

የጊዜ ትኩሳት የዘመን ረመጥ
ዝቅ ዝቅ አድርጎት ሰው ሁሉ ሲጎብጥ
በእርሱ እየተሳለቅኩ ሰው መሆኔን ጥዬ
ሰው ልምሰል መሰለኝ ራሴን አታልዬ

እምደውም ሰው ልሁን!!!
በአምሳል ከፈጠረኝ ከአምላክ ከጌታዬ
በአካል ከመሰልኩት ግብሬንም አክዬ
ሰው ልርዳ ሰው ልውደድ
የስጋውን ትቸው በነፍሴ ልዛመድ
መመዘን መለየት መምረጡን ዘንግቼ
ሰው ብሆን ይሻላል ሰው መምሰሉን ትቼ።

join us 👉👉 @yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍6👏1
#መገላገል
እሰየው አረፍኩት 😉😉
😁3
😁3
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የባከነ ገላ

ሰውነትሽ ጥሩ ነበር ምንም ከሰው የማይከፋ
ዉበትሽም ድንቅ ነበር ከህሊና የማይጠፋ
ዉብ ምግባርሽ ሰናይ ፀባይ እንዳደለሽ
ድሎት ሳይሆን አጉል መሆን ሆኗል እጣሽ
ለአምላክ የዘመረ የጮኸው አንደበትሽ ግራ ቢዘም
አካልሽ ከመቅደሱ ይዉል ዘንዳ አልታደለም
ፅድቅን ጥሎ ሃጥያት ማንሳት እያደፉ
ማመን ሳይሆን አማኝ መምሰል በግርድፉ
ሰውን ሞላው ሰው ጎደለ ኖሮ ሳይኖር
ክፋት ሞላው መጨካከን ሰፋ በአገር
አንድ አድርገው አምላክ በጅህ ባካኝ ገላን
መግደል ማጥፋት እጅን በእጅ እንዲበቃን።

join us 👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍6
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ትዝታ

ትዝ አለኝ ያለፍነው
ያኔ ሆነን የነበርነው
ትላንትና ያደረግነው
ትዉስ አለኝ ያነበርነው

ትዝታ አዛዡ ትዝታ አለቃው
ፈረስ አርጎኝ ሲጨብጠኝ እንደጋማው
ሰጋር መሆን ቢለምድብኝ
በትዝታሽ ተጋለብኩኝ

join us👉👉 yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ገብርኤል

ሰው ከእርግማኑ ከዉርሱ ሃጥያት እንዲያገግም
መዳን ትሆንም ዘንድ በፀሎት ፀነሱ ሃናና እያቄም
ስለት ነበርና ከአምላካቸው ኪዳን የተሳሰሩበት
ለመቅደስ ሸለሟት ማርያም ብለው የስሟን ጥለት

ከመቅደስ ያለችው ትልቅ ብላቴና
ድንኳነ መድህን ሆና ተመርጣለችና
ብስራታዊ መልአክ ገብርኤል ከበላይ
መጦ አበሰራት እንደምትፀንስ አምላክን ከሰማይ
ከልሎ በአክናፉ አልብሶ ብርሃን
ብስራቱን ነገራት እመ አምላክ መሆኗን

ገብርኤል ሊቀ መላእክት ሃዲስ
ከክፉ አውጪ ደራሽ ቅዱስ
ምልጃህ ይርዳን ሰላም አብስር
ፍቅር አድለን እንድንከብር

ስለ ክብርህ ተሰብስበን ስንጠራህ
አስታርቀን አማንደን ከአምላካችን ከአምላህ
እሳት የወረውሰው ሃጥያት ያጠላውን አለም አስረስተህ
ከመንግስቱ አስገባን በምልጃህ አንፀን ከእንፋሎቱ አውጥተህ
እንደ አናንያ እንደ አዛርያ ደግሞ እንደ ሚሳኤል
አድነን ከአጥፊዎች ፈውሰን ገብርኤል

እንደህፃኑ ፅኑ ቅዱስ
እንደ አማኙ እንደቂርቆስ
ደግሞም እንደ እናቱ ልክ እንደ እየሉጣ
ከሞት አድን ህዝቡን ከንፍረቱ አውጣ

መሃላችን ተገኝ በጠራንህ ቁትር
ፅናት ይኑርበት ያገናኝን ፍቅር

ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል
ብለን አንታክትም ስምህ ይጣፍጣል
አንተን አምኖ ወጦ የወደቀ የታል
አንድ አርገን መልሰን ፍቅር ዋልታው ይቁም
ያገናኘን ካስማ ዝክርህም ያገግም
በአለም በደጇ ሰላም ልናሰፍን
ተነስተናልና ገብርኤል ሆይ እርዳን።

join us👉👉@yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


ይቅር በል ፈጣሪ

መጀመሪያዉኑ እኔ አስቤያት መች አውቅና
የት አይቻት ፀሀዬን ጋርዷት ደመና
ንፁህ እንደሸማው ልክ እንደጋቢዬ
ከቤትህ የማልቀር ዳዊት አንጠልጥዬ
ጨዋ ልጅ ነበርኩኝ አሁን ክብሬን ብጥል
ወድጄ እኮ አይደለም አምላኬ ይቅር በል

ገና በማለዳው ቸር አውለኝ ልልህ
ስለምን ቆይቼ ቁጭብዬ ከደጅህ
ከዛ ወደ ቤቴ መጣሁ
ተመስገን እያልኩህ ተመልሼ ወጣሑ
ከዛ
አንዷ አምሳለ ፀሃይ
ጨረቃንም መሳይ
ብትስመኝ ተስቷት
ድንገት ከሁዋላየ ሌላ ሰው መስያት
ደጅህን ረሳሁ እሷን ነው ምሳለም
በነጋ በጠባ መሳሜን ስተልም
ይቅር በል ፈጣሪ
ተስሜ ነው እንጂ ወድጄ እኮ አይደለም።

join us👉👉 @yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥5😁1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንዳታጭኝ

የተገዛልሽን የወደቀልሽን እኔነቴን ትተሽ
ፍቅርሽ ያቀናውን የሞላውን ቤቴን ወና ባዶ አደርገሽ
ገለል ገሸሽ ካይኔ መራቁን መምረጥሽ
በምን ይካስ ይሆን በምንስ መልሸሽ

የዋህ ልቤ አማኝ ገሩን
ምን ባታምኝው መታመኑን
አትጠርጥሪው አምነሽ ታመኝ
እደተውሽኝ እኔም ትቸሽ እንዳታጭኝ።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍1🔥1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እናት

በአንቺ አይደል ወይ ሰው መሆኔ
ለአንቺ አይደል ወይ ማውረድ ቅኔ
እንዲደላኝ እንዳይከፋኝ ስትይ ዝቅ ያልሽ
እጅሽ ሻክሮ አይንሽ ዳምኖ እያነባሽ
ደስታን ለኔ ያለበስሽኝ
አንቺ እናቴ እንዴት ቻልሽኝ

እየጠቆርሽ ያቀላሽው
እየራበሽ ያጠገብሽው
አካል ክብሬ በእጅሽ እቅፍ
የዘመመው ባንቺ ድግፍ
ሀዘን መድከም ባንቺ ግፍፍ
ፍቅርሽ ዘክሮኝ ዉለታሽን
ከመውደድሽ እንደዘገንኩ ስስትሽን
ከፋይ ያርገኝ መላሽ
ለረሃብሽ አጉራሽ
ለበረደሽ አልባሽ
እንዳኖርሽኝ በእኔም ተራ
ደግ ልሁን ልብሽ ይኩራ።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤4👍1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ህይወት

ህይወት ማለት
ከቪላ ከፎቁ ከማንጎው ጥላ ስር
ጥዋት ቁርስን በልቶ ተካፍሎ በፍቅር
በሸታታው መንገድ በቆርቆሮ ፈረስ
ከሃይቁ ተነስቶ ከፏፏቴው መድረስ
ሢጨፍሩ ውሎ ሲዘፍኑ ሲያወኩ
ዐብዝተው ጠጥተው ሣይታወቅ ልኩ
ይመሻል የነጋው መልሶ ሊነጋ
ስካር አድሏቸው ለውሏቸው ዋጋ
አንዲህ ነው ይላሉ እነንተና መንደር
ህይወት በአመስጥሮ በአምድምታ ሲዘከር

ወደኛ ሰፈር ግን ደሞም ወደኛ ቤት
ህይወት ማለት
ያገኙ መስሎ ማጣት
ከጉልበት ሸብረክ ከወገብ ጎብደድ
ከአንገትም ደፋ እንባ አይንን ግርድ
ሰብሰብ ወደመሬት ዘቅዘቅ ወደአፈሩ
የሞት ደጅ አዳራሽ አስኪከፈት በሩ
አንደዚህ ነው አውዱ የመንጋት መምሸቱ
ሲባል ሰማን አንጂ የህይወት መጣፈጥ የለም ምልክቱ።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥3
ጉልበት

ሰው ልቡ አንጂ ሃይልና አቅሙ
ሰው ከመንፈሱ አንጂ ብርታት ድካሙ
ከጉልበት መች ሆነ በአካል ቁመናው
ያለ ልብ ምን ሊሆን ጉልበት ከንቱ መናው
ማሸነፍ ማለፉ አንከን አንቅፋቱን
በጉልበት አይደለም ላወቀ ነው ልቡን።

Join us👉👉 @yitayal05
👏6👍1
ሰሎሞን

ሀያል ፣ ጠቢብ ፣ ንጉስ ሰሎሞን ሀያሉ
አያሌ አቁባቶች ከእልፍኙ አያሉ
የሳባዋን ንግስት ውበት ደምግባቷን
ቢያቅተው መቋቋም አካል ሰውነቷን
ቢገረም አጀብ ቢል ስለአፈጣጠሯ
በጥበቡ ነድፎ ላካት ወደ ምድሯ።


Join us 👉👉@yitayal05
👍6
አትመጪም

አንችን ላናገኝሽ እድል ፊቷ ሲዞር
ለምኑ እንዳከም ላናመጥሽ በጦር
እድላት አንጂ ችሮት ስጦታ
ምን ቢታገሉት ጠዋትም ማታ
አትመጪም ከአንባው ላይ አትወጪም ከደብሩ
በክፋቱ ሳንቃ ተሰንቅቷል በሩ
አትገቢም ቤታችን ጓዳው አይዳሰስ
ያው ድቅድቅ ጨለማ እስካልመጣሽ ድረስ
መምጫሽ መንገድ አይደል በፈረስ በአየሩ
ሰላም ነው ጎዳናሽ መዋደድ ነው ግብሩ
ከሚያዋድደን እልፍ ከበዛው 'ርቀን
ስንጥር ከምታክል መለያየት ገብተን
አልበቃን አለና እልፍኝ አዳራሹ
ሞት ማለቅን መምረጥ ሰላም እየሸሹ
ልማድ ሆነ ቅቡል የዘወትር ምግባር
ዝም አትበል ፍረድ አስታርቀን አግዚአብሔር።

Join us 👉👉 @yitayal05
❤3👍1
ወይ ነይ

ዜማ ቅኝቱን መጮህ ማዜም ባልችል
ማኅሌትሽን ቆሜ የመሸው ይነጋል
ከበሮ ልቤ ነው ሲመረገድ ያድራል
ፀናፅል ትንፋሼ ከፍ ዝቅ ፍጥንጥን
ለከበሮው ልቤ ለድምድምታው ልሳን
ያነሱሻል አብረው ያነግሱሻል ሁሌም
እንደ አምላክ ስለውሽ በናፍቆትሽ ቀለም
ወይ ነይልኝ በአክል ወይ ቅሪ ከሀሳቤ
አየዋዠቀብኝ አረጋ አለኝ ቀልቤ።

Join us 👉👉 @yitayal05
👍4
ፀሀይ አልልሽም

ፀሃዬ ብርሃኔ ፀዳሌ ነሽ ለ'ኔ
አለም ጨለማ ናት ከለለሽ ከጎኔ
ጨረቃና ኮከብ ፍጥረተ ብርሃናት
አይደምቁም አይበሩም አንች በሌለሽበት
ብየ ውሸት ትርክት ልብሽን አልሞላም
አንቺ ሄዋን አንጂ ፀሃይ አይደለሽም
የመኖሬ ዋስ ነሽ የኑሮየ ድምቀት
ከማለት በስተቀር ዉዴ ነሽ ከማለት
ብርሀኔ ነሽ ብየ ዉሸትን አላውቅበት
ግን ደሞ...
በፀሀይ ባልጠራሽ በኮከብ ጨረቃ
አንቺ ሳትኖሪ ነው ህይወቴ 'ሚያበቃ
አለም ባትጨልምም ምን ፅልመት ባይወርሳት
በቀላሉ አልችልም ባጣሽ አንቺን መርሳት።

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤3
ዛሬ

አ ረ ጀ ን
አ ፈ ጀ ን
ወጣት ሆነን ጃጀን
አንቺም አኔም አኛም
የተለየን የለ እንዲህ ሁላችንም
በለቅሶ በጩኸት አንደተወለድን
ዛሬም በሞታችን አንዳለቀስን አለን
አጎበጠን ድካም ደቆሰን ጥላቻ
ፍረደን ፈጣሪ አንድ አድርገን አቻ።

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤3👏3🔥1
ምኑን ቤት ላስመታው

ከአውላላ ሜዳ ላይ ዳርቻ በሌለው
ተፈጥሮው ቢገዛኝ ድንቅ ዉበቱን ሳየው
ብእር ወብራና አንዳኖረው ጠቢብ
ወረቀት አወጣሁ ግጥሜን ልከትብ
አንድ ስንኝ ፅፌ ልከልት ብደግም
ምኑን ቤት ላስመታው ምንም ጣራ የለም
ከአውላላ ሜዳ ላይ ሰው ባላረፈበት
ግጥም ልፃፍ ብሎ ከቃላት መሟገት
ትርፉ ስርዝ ድልዝ አይገኝ ቁም ነገር
ካለመቻል ጋራ ከመታገል በቀር።


✍¥ïŧä¥äļ(@gtmwustie)


@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍6
አምላኬ
ጌታ ሆይ
አምሳልህ አይደለሁ ወይ የሶስትነትህ ምስል ፍሬ
ምነው አታይ መበደሌን ቤቴ አትገባ እስከዛሬ
በአንድ አጅ አጨብጫቢ የከፋውን ሞኝ ሆኜ
ዝቅ ብየ ብታይ ዛሬ ቃልህ በመሞት ተዳኘ
ከሞት ያዳነኝ ቃልህን በፅልመቱ ሞት መዳኘት
አምላክ ክብርህን አለማወቅ አንሶ ማነስ ነው መሞኘት
ታዲያ....
ክብህን ባውቅም ጠንቅቄ ፆም ስግደቱን ምን ባላጎል
መች ጎበኘህ መበደሌን ደጀ ሰላም ቆሜ ስውል
ፈጣሪ
ጌታየ
ልኡል ሆይ
የነዳያን አልባሻቸው የድኩማን ድጋፍ ምርኩዝ
ለኔም እርዳ ፍረድልኝ ድህነትና ምህረት አዝዝ
ወይኩን ፈቃድከ አምላከ ኩሉ አለም
ፍቀድልኝ ብርሀን ልልበስ ፍርድህ ቀርቶ አንዳልጨልም
ሰው መሆኔን የአዳም ልጁ እንዳሰብከው በመስቀልህ
ወይ አድነኝ ከጥላቻው ወይ አስገባኝ ከመንግስትህ።



✍¥ïŧä¥äļ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
🙏2
የሳምንት ፍቅር

ትዝ ይለኛል ሁሉም ነበረ ቅዳሜ
መልክሽን ያየሁት ጎዳናው ዳር ቆሜ
ዘንከትከት ሸሞንሞን ስትይ ሞነን ቀዳ
ከአንጀቴ ገብተሻል ልብ ውስጤም ተረዳ

ጀምሬ የተውኩት ያየሁሽ ቀን ውሎ
ሌሊቱም የነጋ አይኔ ጣራ ተክሎ
ጎህ እንደቀደደ በጀንበሯ ፍጥነት
ካይሁሽ ቦታ ላይ ተገኘሁ በሰንበት
ቅዳሴውን አልቆም ተአምሯን አልሰማ
ሰርቃኝ ሄደች እያልኩ አንቺን ነው የማማ
በሃሜት የመሸው በህልም አለም ነጋ
ዛሬም ልዘልቀው ነው ከፍቅርሽ ስዋጋ
ማየት አሞኝ አስሮኝ ተዘለቀ ሰኞ
እንደሆንኩ አንዳለሁ አለፈ ማክሰኞ
ከጎዳናው ቆሜ ተደገመ ረቡ'
ድንገት ያየሽ አይኔ ባሰበት መራቡ
በፍቅርሽ የነጋው ያልቀመስኩት ሃሙስ
ቢያመጣሽ እያልኩኝ ይሄ የቀን ቅዱስ
ስጠብቅሽ ዉዬ ሳስብሽ ሌላ ቀን
አርብንም ጀመርኩት በፍቅርሽ ሰቀቀን
መቋቋም ቢያቅተኝ ለፍቅርሽ ባጣ ልክ
ስለፍቅር ብሎ የሞተውን አምላክ
ብረሳሽ ለመንኩት ውስጤ አንዳይታወክ
ስሰግድ ስፀልይ ከቤቱ ገብቼ
አንቺን የተራቡሽ እንዲያዩሽ አይኖቼ
መሸ ነጋ ቀኑ
ሳምንቱን ደፈነ የልቤ ማዘኑ
አንቺም ሄደሽ ቀረሽ ዳግምም አልመጣሽ
ጉዞ ልጀምር ነው አንቺን አንድረሳሽ።

✍¥ïŧä¥äļ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍2