እናትየ
ሰው መሆን ሲለካ
በርኩሰት የዳኸው ድኩም ማንነቱ
የመቃናት መንገድ
የመንጻት የመዳን የማለፍ ድርሰቱ
በፍቅር ይቃኛል
በመውደድ ይሰጣል ሰው ነኝ ለሚል ሁሉ
ዝቅ ብሎ አንሶ
በጎደፈ ሃሳብ ካላጎዳደለው የሰው ልጅ በአመሉ
የሰው ልጅ ጣእሙ
ጥፍጥናው ሲለካ ማማሩ ሲወደር
ኣንቺን ነው ሚመስል
በመዋብ ዳርቻ ማ ካንቺ ሊወደር
እናትየ አንቺ
ስመ ቅድስና የንጽህና አምሳል
መውደድሽ ደምቆ ነው ከልቤ የሚሳል
እናትየ ያልኩሽ
አተልቄው እንጂ የሴትነት ልኩን
አምላክ የቸረሽን
ሰው የመሆን መጠን የመፈጠር መልኩን
በእንስፍስፏ እናቴ
በእምቁዬዋ እንስት በስሟ ምጠራሽ
እንድትኖሪልኝ ነው
ከልቤ አዳራሽ ዉስጥ ሁሌም እንዳበራሽ
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ሰው መሆን ሲለካ
በርኩሰት የዳኸው ድኩም ማንነቱ
የመቃናት መንገድ
የመንጻት የመዳን የማለፍ ድርሰቱ
በፍቅር ይቃኛል
በመውደድ ይሰጣል ሰው ነኝ ለሚል ሁሉ
ዝቅ ብሎ አንሶ
በጎደፈ ሃሳብ ካላጎዳደለው የሰው ልጅ በአመሉ
የሰው ልጅ ጣእሙ
ጥፍጥናው ሲለካ ማማሩ ሲወደር
ኣንቺን ነው ሚመስል
በመዋብ ዳርቻ ማ ካንቺ ሊወደር
እናትየ አንቺ
ስመ ቅድስና የንጽህና አምሳል
መውደድሽ ደምቆ ነው ከልቤ የሚሳል
እናትየ ያልኩሽ
አተልቄው እንጂ የሴትነት ልኩን
አምላክ የቸረሽን
ሰው የመሆን መጠን የመፈጠር መልኩን
በእንስፍስፏ እናቴ
በእምቁዬዋ እንስት በስሟ ምጠራሽ
እንድትኖሪልኝ ነው
ከልቤ አዳራሽ ዉስጥ ሁሌም እንዳበራሽ
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ፍቺኝና ላግባሽ
ታስታውሽው ይሆን?
የተጋባን ሰሞን
ወጥቼ እስክገባ አታምኝኝ ነበር
ፍቅርሽን አልብሰኝ
በካባሽ አድምቀሽኝ
ወሰን ያጣ ነበር የፍቅራችን ድንበር
የሰሞኑን ያርቅ
የዛሬን አያድርግ
ክፉ ቀን መጣ እንጂ የሚነጣጥለን
ስናወጋ...
ስናወጋ አድረናል
ከፍቅራችን እልፍኝ ተሸፋፍነን ውለን
ታስታውሽው ይሆን
የተጋባን ሰሞን
ወጥቼ እስክገባ አታምኝኝም ነበር
አሁን ፍቅር ጎሎ
አካልሽ 'ርቆኝ
የገዘፈው ትዳር አዟል ሊሰበር
ሰርጉ ከነበረ
ሰላም የሞላልን ዳንኪራ ጭፈራው
ተረስቶሽ ከሆነ
የድስ ግርግር
ልብሽ የሚርቀኝ አካሌን የፈራው
ሁካታው ከሆነ
የሰው ግርግር
ያኔ ፍቅር አጥምቆ ለቤቴ ያስገባሽ
የጎደለው ልብሽ
ዳግም ሙሉ ይሁን
የቀረው ይቅር እንጂ ፍቺኝና ላግባሽ
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ታስታውሽው ይሆን?
የተጋባን ሰሞን
ወጥቼ እስክገባ አታምኝኝ ነበር
ፍቅርሽን አልብሰኝ
በካባሽ አድምቀሽኝ
ወሰን ያጣ ነበር የፍቅራችን ድንበር
የሰሞኑን ያርቅ
የዛሬን አያድርግ
ክፉ ቀን መጣ እንጂ የሚነጣጥለን
ስናወጋ...
ስናወጋ አድረናል
ከፍቅራችን እልፍኝ ተሸፋፍነን ውለን
ታስታውሽው ይሆን
የተጋባን ሰሞን
ወጥቼ እስክገባ አታምኝኝም ነበር
አሁን ፍቅር ጎሎ
አካልሽ 'ርቆኝ
የገዘፈው ትዳር አዟል ሊሰበር
ሰርጉ ከነበረ
ሰላም የሞላልን ዳንኪራ ጭፈራው
ተረስቶሽ ከሆነ
የድስ ግርግር
ልብሽ የሚርቀኝ አካሌን የፈራው
ሁካታው ከሆነ
የሰው ግርግር
ያኔ ፍቅር አጥምቆ ለቤቴ ያስገባሽ
የጎደለው ልብሽ
ዳግም ሙሉ ይሁን
የቀረው ይቅር እንጂ ፍቺኝና ላግባሽ
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍3
ሄዋን ነች የኔ ሴት
አለም ስትፈጠር
ሰማይም በአንድ ቃል ምድርም በአንድ ቃል
ለአምላክ ለባለ እጁ
ፍጥረትን ለመፍጠር ሁን ማለት ይበቃል
የሰውን ልጅ እንጂ
በአምሳሉ የሰራው በአፈጣጠር ክቦ
ከፍጥረታት ሁሉ
ከበላይ የሰራው በእስትንፋሱ አጅቦ
ታዲያ የኔን ሄዋን
የምኖሬን ምክንያት የአዳምነቴን ልክ
እሱ የሰጣትን
ከአለም የላቀ ወብ ጸባይና መልክ
በምድር በሰማይ
ከሷ ባነሰ አካል ሰይሜ አልንቃትም
ሰማይና ምድር ለ እንቁየ አይበቃትም
የኔ ዉዷ እንስት
የአጥንቴ ፍላጭ ሄዋኔ ብቻ እንጂ ሌላ ስም የላትም
አንዱ ሰማይ ቢላት
ከፍጥረታት ሁሉ ከበላይ ቢሰቅላት
አንዱ በምድር ስም
የሁሉም ማረፊያ መቆሚያ ነሽ ቢላት
እኔም የኔ እንስት
የስጋ እና የነፍስ የመንፈሴ ደሴት
አምላክ እንደጠራት
ክብሯ የሚገባት ሄዋን ነች የኔ ሴት
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
አለም ስትፈጠር
ሰማይም በአንድ ቃል ምድርም በአንድ ቃል
ለአምላክ ለባለ እጁ
ፍጥረትን ለመፍጠር ሁን ማለት ይበቃል
የሰውን ልጅ እንጂ
በአምሳሉ የሰራው በአፈጣጠር ክቦ
ከፍጥረታት ሁሉ
ከበላይ የሰራው በእስትንፋሱ አጅቦ
ታዲያ የኔን ሄዋን
የምኖሬን ምክንያት የአዳምነቴን ልክ
እሱ የሰጣትን
ከአለም የላቀ ወብ ጸባይና መልክ
በምድር በሰማይ
ከሷ ባነሰ አካል ሰይሜ አልንቃትም
ሰማይና ምድር ለ እንቁየ አይበቃትም
የኔ ዉዷ እንስት
የአጥንቴ ፍላጭ ሄዋኔ ብቻ እንጂ ሌላ ስም የላትም
አንዱ ሰማይ ቢላት
ከፍጥረታት ሁሉ ከበላይ ቢሰቅላት
አንዱ በምድር ስም
የሁሉም ማረፊያ መቆሚያ ነሽ ቢላት
እኔም የኔ እንስት
የስጋ እና የነፍስ የመንፈሴ ደሴት
አምላክ እንደጠራት
ክብሯ የሚገባት ሄዋን ነች የኔ ሴት
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ይድረስ ለጠበሩ✍
የተነሳውን ልብ፥ እብሪት አደፋፍሮት
አስተውሎት ይግዛው፥ ወይ መስከንሽ መክሮት
እንጂ አጉል አመል ነው፥ ሰው መሆን ያልዳኘው
ግብረ ከይሲ ኩራት፥ መጠበር ያናኘው
ስምሽን ኑሪበት ፥መልካምን ተያያት
አትኩሪ ሰው ሁኚ ፥ ደጓን አንቺብ ልያት
ይሄው እኔም ላንቺ ፥ስንኜን ሸክፌ
መልእክቴን ላኩልሽ ፥ምክር አስታቅፌ።🎷🎷🎷
ተጻፈ በ ይታያልጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
የተነሳውን ልብ፥ እብሪት አደፋፍሮት
አስተውሎት ይግዛው፥ ወይ መስከንሽ መክሮት
እንጂ አጉል አመል ነው፥ ሰው መሆን ያልዳኘው
ግብረ ከይሲ ኩራት፥ መጠበር ያናኘው
ስምሽን ኑሪበት ፥መልካምን ተያያት
አትኩሪ ሰው ሁኚ ፥ ደጓን አንቺብ ልያት
ይሄው እኔም ላንቺ ፥ስንኜን ሸክፌ
መልእክቴን ላኩልሽ ፥ምክር አስታቅፌ።🎷🎷🎷
ተጻፈ በ ይታያልጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👏4👍2
ንገሯት
አንዲት እንስት ነበረችኝ
የነበርኳት የገዛችኝ
እሷ ማለት....
ቀዝቃዛው አለሜን ድቅድቁን ማንነት
በጣፋጭ ማር ጧፏ በቃሏ ሰምነት
እያበራችልኝ፥ እያደመቀችው ከሰገነት ወጣን
የአካሏ ጠረን አወደኝ እንደ እጣን
ግና...
ጸሀይ ብርሃን ፍቅሯ ሞቅታን ሲያበዛ
ተነነች፣ ተሸኘች ጠፋች እንደ ጤዛ
ሄዋኔ ነሽ ብየ አዳሜ ነህ ብላ
በአንደበቴ ምየ በልሳኗ ምላ
ፍቅር ተሸልመን መቼ ጊዜው ገፋ
መለየት ደረሰው ብን ብሎ ጠፋ
መሄድ ሸነጋግሏት አሳስቷት ሸሸችኝ
በሌላ አዲስ አዳም አዳሟን ተካችኝ
ወይኔ...
ሄደች እሷስ 'ርቃ
አልቋል ብላ በቃ
በጃኖ በካባ
ያሸበረቀውን የከበረ አለሜን
በመሄዷ ገፋ
እርቃን አቆመችው ያለምኩላት ህልሜን
ግን...
ከእኔ እንደሄደችው
ከወሰዳት ሄዳ ትመጣለች ብየ
ራሴን ሰድሬ
እንደ አንበሳ ገዳይ በጀግና መስየ
ያ ቀን ስላማረኝ
ዳግም እንድታጤዝ እጠብቃታለሁ
ንገሯት ሂዱና
ካገኘችኝ ቦታ
ልክ እንደተወችኝ ሆኘላት እንዳለሁ።
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
አንዲት እንስት ነበረችኝ
የነበርኳት የገዛችኝ
እሷ ማለት....
ቀዝቃዛው አለሜን ድቅድቁን ማንነት
በጣፋጭ ማር ጧፏ በቃሏ ሰምነት
እያበራችልኝ፥ እያደመቀችው ከሰገነት ወጣን
የአካሏ ጠረን አወደኝ እንደ እጣን
ግና...
ጸሀይ ብርሃን ፍቅሯ ሞቅታን ሲያበዛ
ተነነች፣ ተሸኘች ጠፋች እንደ ጤዛ
ሄዋኔ ነሽ ብየ አዳሜ ነህ ብላ
በአንደበቴ ምየ በልሳኗ ምላ
ፍቅር ተሸልመን መቼ ጊዜው ገፋ
መለየት ደረሰው ብን ብሎ ጠፋ
መሄድ ሸነጋግሏት አሳስቷት ሸሸችኝ
በሌላ አዲስ አዳም አዳሟን ተካችኝ
ወይኔ...
ሄደች እሷስ 'ርቃ
አልቋል ብላ በቃ
በጃኖ በካባ
ያሸበረቀውን የከበረ አለሜን
በመሄዷ ገፋ
እርቃን አቆመችው ያለምኩላት ህልሜን
ግን...
ከእኔ እንደሄደችው
ከወሰዳት ሄዳ ትመጣለች ብየ
ራሴን ሰድሬ
እንደ አንበሳ ገዳይ በጀግና መስየ
ያ ቀን ስላማረኝ
ዳግም እንድታጤዝ እጠብቃታለሁ
ንገሯት ሂዱና
ካገኘችኝ ቦታ
ልክ እንደተወችኝ ሆኘላት እንዳለሁ።
ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
🔥1
እሰይ አትይኝም?
(ቆይ ግን አታምኝኝም?)
ተራራውን ገፋሁልሽ፣ሜዳ አረኩት በትግሌ፤
ማርኮት ኖሮ ይህ አቅሜ፣ አደረክኩት ሰጋጅ ሎሌ።
አወይ እኔ ጀግናው
ሀያል ነኝ እንደ አምናው
(አሁን አምና ያልኩት!)
(ትዝ አለሽ ያረኩት?)
ውሀውን ጠልፌ፣ዳገት አስወጣሁት።
የተጠማን ቋጥኝ፣ችየው አጠጣሁት።
አጀብ ነው እጃኢብ!
ማን ሊሰራው የቱ ጠቢብ?
ላንቺ ብሎ ቀን ያበጀ፤
ጨረቃዋን ላንቺ ያስረጀ።
ማን ይገኛል በአለም መዳፍ፣ስጋና ደም የለበሰ።
የልቡን ቤት ጎጆ ብሎ፣ከልብሽ ዳር የቀለሰ።
ትላንት ለታ ስታበሪ፣ጨለማውን ስትገፊው፤
ወጋገንሽ አድማስ ደርሶ፣በውበትሽ ስታሰፊው፤
ከሰማይ ጥግ ከአንባው ላይ፣ጨረቃዋ ልትመቀኝ።
ውበትሽን ልትሳፈጥ ፣ ስትወጣ ነው የታወቀኝ።
ያኔ ብታይ ማን ይያዘኝ
አንቺነትሽም እያገዘኝ
ተነሳኋ በብርቱ አቅም
ጨረቃ ግን ይህን አታቅም
ብቻ ወሬ ተያያዝኩት፣ያው ስላንቺ በጉባኤ
እስከሰባት እስክቆጥር፣ገደምኩልሽ በሰባኤ
እቺ ደግሞ ምን አባቷ
ምትሟገት ምን እናቷ
ብርሀኔን ምትገድራት
ጨረቃናት ምትወድራት?
እያልኩኝ ብቻየን፣ከራሴው ሳወራ፤
መላ ነይ እያልኩኝ፣በልቤ ስጣራ፤
ያጠጣሁት ትልቅ ቋጥኝ፣የምለውን ሰምቶኝ ኖሮ፤
ጨረቃዋን ልገምስበት፣ከእጄ ገባ ተሰባብሮ፤
አገር ያክል በወደል፣ግዙፍ አለት ብወረውር፤
ጨረቃ ማየት ተሳናት፣ወርውሬ አደረኳት እውር፤
እሰይ አትይኝም?
ቆይ ግን አታምኝኝም?
ከዛ ቀን ጀምሮ፣እንቺ ስትሄጂ፤
ጨረቃም አትሞላ፣ትጎላለች እንጂ።
(ለምን ማለት ጥሩ)
ነገር ነው ከስሩ
ውሃም ነው ከጥሩ
ጨረቃ አንዴ ሙሉ፣ጎደሎም ምትሆነው።
በሌላ እንዳይመስልሽ፤
ወሬም አያታልሽ
ጨረቆች በዝተዋል
እኔ የሰበርኳት፣ስትወጣ እኮ ነው።
አየሽ እኔ ጀግናው፤
የፍቅር ጎዳናው፤
አልፎ ያገደመ የሚማማልብኝ፤
እንኳን ሰዉ ቀርቶ ምች የማይደርስብኝ፤
ተራራ የገፋሁ፣ጨረቃን የሸረፍኩ፤
ውሃን ወደዳገት፣አንደፍድፌው ያረፍኩ፤
እውነትን እየኖርኩ ፣ሃቅን የማወራ፤
የቤታችን መሪ ፣ያንቺው አባ ወራ፤
እኔው ነኝ!
ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
(ቆይ ግን አታምኝኝም?)
ተራራውን ገፋሁልሽ፣ሜዳ አረኩት በትግሌ፤
ማርኮት ኖሮ ይህ አቅሜ፣ አደረክኩት ሰጋጅ ሎሌ።
አወይ እኔ ጀግናው
ሀያል ነኝ እንደ አምናው
(አሁን አምና ያልኩት!)
(ትዝ አለሽ ያረኩት?)
ውሀውን ጠልፌ፣ዳገት አስወጣሁት።
የተጠማን ቋጥኝ፣ችየው አጠጣሁት።
አጀብ ነው እጃኢብ!
ማን ሊሰራው የቱ ጠቢብ?
ላንቺ ብሎ ቀን ያበጀ፤
ጨረቃዋን ላንቺ ያስረጀ።
ማን ይገኛል በአለም መዳፍ፣ስጋና ደም የለበሰ።
የልቡን ቤት ጎጆ ብሎ፣ከልብሽ ዳር የቀለሰ።
ትላንት ለታ ስታበሪ፣ጨለማውን ስትገፊው፤
ወጋገንሽ አድማስ ደርሶ፣በውበትሽ ስታሰፊው፤
ከሰማይ ጥግ ከአንባው ላይ፣ጨረቃዋ ልትመቀኝ።
ውበትሽን ልትሳፈጥ ፣ ስትወጣ ነው የታወቀኝ።
ያኔ ብታይ ማን ይያዘኝ
አንቺነትሽም እያገዘኝ
ተነሳኋ በብርቱ አቅም
ጨረቃ ግን ይህን አታቅም
ብቻ ወሬ ተያያዝኩት፣ያው ስላንቺ በጉባኤ
እስከሰባት እስክቆጥር፣ገደምኩልሽ በሰባኤ
እቺ ደግሞ ምን አባቷ
ምትሟገት ምን እናቷ
ብርሀኔን ምትገድራት
ጨረቃናት ምትወድራት?
እያልኩኝ ብቻየን፣ከራሴው ሳወራ፤
መላ ነይ እያልኩኝ፣በልቤ ስጣራ፤
ያጠጣሁት ትልቅ ቋጥኝ፣የምለውን ሰምቶኝ ኖሮ፤
ጨረቃዋን ልገምስበት፣ከእጄ ገባ ተሰባብሮ፤
አገር ያክል በወደል፣ግዙፍ አለት ብወረውር፤
ጨረቃ ማየት ተሳናት፣ወርውሬ አደረኳት እውር፤
እሰይ አትይኝም?
ቆይ ግን አታምኝኝም?
ከዛ ቀን ጀምሮ፣እንቺ ስትሄጂ፤
ጨረቃም አትሞላ፣ትጎላለች እንጂ።
(ለምን ማለት ጥሩ)
ነገር ነው ከስሩ
ውሃም ነው ከጥሩ
ጨረቃ አንዴ ሙሉ፣ጎደሎም ምትሆነው።
በሌላ እንዳይመስልሽ፤
ወሬም አያታልሽ
ጨረቆች በዝተዋል
እኔ የሰበርኳት፣ስትወጣ እኮ ነው።
አየሽ እኔ ጀግናው፤
የፍቅር ጎዳናው፤
አልፎ ያገደመ የሚማማልብኝ፤
እንኳን ሰዉ ቀርቶ ምች የማይደርስብኝ፤
ተራራ የገፋሁ፣ጨረቃን የሸረፍኩ፤
ውሃን ወደዳገት፣አንደፍድፌው ያረፍኩ፤
እውነትን እየኖርኩ ፣ሃቅን የማወራ፤
የቤታችን መሪ ፣ያንቺው አባ ወራ፤
እኔው ነኝ!
ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤1
አመሰግናለሁ🙏🙏
አይንሽን አይኔን ያየውን ጥርስሽን የሳቅሽበትን
ከናፍር እና ፀጉርሽን እግርሽን የሄድሽበትን
አካልሽን እየዘረዘርኩ እንደልምድ አላወድስም
ብስለትሽ ይበልጥብኛል ተመስገን አልኩኝ ባንቺ ስም
አንደበትሽን በምን ሰራው በምን ቃሉስ አዋቀረው
ለመኮብለል መደንፋቴን መልካም ቃልሽ ሰባበረው
አውሎ ነፋስ ላያጠፋሽ ፋኖስ ሆነሽ መሰጠቴ
የፀሎቴ ፍፃሜ ነው የምድር ላይ በረከቴ
አመሰግናለሁ🙏🙏
በይታያል ጌቴ @gtmwustie
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
አይንሽን አይኔን ያየውን ጥርስሽን የሳቅሽበትን
ከናፍር እና ፀጉርሽን እግርሽን የሄድሽበትን
አካልሽን እየዘረዘርኩ እንደልምድ አላወድስም
ብስለትሽ ይበልጥብኛል ተመስገን አልኩኝ ባንቺ ስም
አንደበትሽን በምን ሰራው በምን ቃሉስ አዋቀረው
ለመኮብለል መደንፋቴን መልካም ቃልሽ ሰባበረው
አውሎ ነፋስ ላያጠፋሽ ፋኖስ ሆነሽ መሰጠቴ
የፀሎቴ ፍፃሜ ነው የምድር ላይ በረከቴ
አመሰግናለሁ🙏🙏
በይታያል ጌቴ @gtmwustie
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍4❤1
ይሄን አዳም አልነበርኩም (በ ይቴ)
በፍቅር ተቃኝተን
ስለስሜት አብደን ባደረግነው ነገር
ከየት አመጣሽው
ሴትነቴን ጣልኩት የሚል መደናገር
ይቺን ሴት ግን አልነበርኩም
ክት ነበር አካላቴ ማንም ደርሶ የማይገልጠው
ጨዋ ነበር ውብ ቀሚሴ በእማ ጥለት የተጌጠው
ላንተ ሲሆን ባንተ ምክንያት ተሰበረ የልቤ ቃል
ሽፍንፍኑን ገላለጥኩት ካንተ ምኔ ይደበቃል
ይችን ሴት ግን አልነበርኩም
ትይኛለሽ በመፀፀት ውስጥሽ እንጃ ምን እንዳለ
ከኔ ጋራ ባሳለፍሽው ምንን አጣሽ ምን ጎደለ
አየሽ
ማንነቱን ቃል እምነቱን
ሰው በምድር ባይለውጥም
እንዳመጣው እንዲመልስ
ለሰው አመል አይሰጥም
የቀሚስሽን ወግና ህግ
ፍቅር ገልጦ ቢሽረውም
ልብሽ ለምን ይከፋዋል
ላያስችለው አልሰጠውም
ባደባባይ ስታገድሚ
እልፉ በአይኑ ቢዘልፍሽም
በገላችን ተክሰሻል
መፅናኛውን አላጣሽም
አለነበርኩም ብሎ ማለት
ከመሆንሽ አያርቅም
ያንቺው ብቻ አልነበረም
የኔም ገላ ሌላ አያውቅም
ከምንሽ ተነሳሁ በምንሽ አበቃሁ
ህልም መስሎኝ ነበር ባንኜም አልነቃሁ
እንዳንቺ ለማለት
ያሄን አዳም አልነበርኩም
የሚል ሃረግ ስገነባ
አይኔ እንዳየው ይናፍቃል
ተናነቀው ጥቁር እንባ
ያሄን አዳም አልነበርኩም!
ቡታንታየን ከሄዋን ፊት
ስለስሜት አላላላም
ጨዋ ቀሚስ አራክሼ
በክብር ደም አላቀላም
እንጃ ብቻ ባንቺ ሲሆን
ያልነበርኩት ሆኜ አረፍኩት
የፈቀደው ውብ ገላሽን
ልዳብሰው እጄን ላኩት
የሳመኝን ከንፈርሽን
ደጋግሜ እኔም ሳምኩት
ግን
ያሄን አዳም አልነበርኩም
እንዳልካድሽን የማልክደው
ያረሳሽው የማረሳው
በፍቅራችን ድርሳን መጻ'ፍ
በፊደሌ የማወሳው
ያልነበርነው አዲስ እውነት
በገላችን የፈጸምነው
ይሄን አዳም እኔ ባልሆን
ይቺን ሴትም ባትሆኚ
የእድሜአችን ስጦታ ነው
ይሄን አዳም አልነበርኩም።
✍✍✍ ይታያል ጌቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
በፍቅር ተቃኝተን
ስለስሜት አብደን ባደረግነው ነገር
ከየት አመጣሽው
ሴትነቴን ጣልኩት የሚል መደናገር
ይቺን ሴት ግን አልነበርኩም
ክት ነበር አካላቴ ማንም ደርሶ የማይገልጠው
ጨዋ ነበር ውብ ቀሚሴ በእማ ጥለት የተጌጠው
ላንተ ሲሆን ባንተ ምክንያት ተሰበረ የልቤ ቃል
ሽፍንፍኑን ገላለጥኩት ካንተ ምኔ ይደበቃል
ይችን ሴት ግን አልነበርኩም
ትይኛለሽ በመፀፀት ውስጥሽ እንጃ ምን እንዳለ
ከኔ ጋራ ባሳለፍሽው ምንን አጣሽ ምን ጎደለ
አየሽ
ማንነቱን ቃል እምነቱን
ሰው በምድር ባይለውጥም
እንዳመጣው እንዲመልስ
ለሰው አመል አይሰጥም
የቀሚስሽን ወግና ህግ
ፍቅር ገልጦ ቢሽረውም
ልብሽ ለምን ይከፋዋል
ላያስችለው አልሰጠውም
ባደባባይ ስታገድሚ
እልፉ በአይኑ ቢዘልፍሽም
በገላችን ተክሰሻል
መፅናኛውን አላጣሽም
አለነበርኩም ብሎ ማለት
ከመሆንሽ አያርቅም
ያንቺው ብቻ አልነበረም
የኔም ገላ ሌላ አያውቅም
ከምንሽ ተነሳሁ በምንሽ አበቃሁ
ህልም መስሎኝ ነበር ባንኜም አልነቃሁ
እንዳንቺ ለማለት
ያሄን አዳም አልነበርኩም
የሚል ሃረግ ስገነባ
አይኔ እንዳየው ይናፍቃል
ተናነቀው ጥቁር እንባ
ያሄን አዳም አልነበርኩም!
ቡታንታየን ከሄዋን ፊት
ስለስሜት አላላላም
ጨዋ ቀሚስ አራክሼ
በክብር ደም አላቀላም
እንጃ ብቻ ባንቺ ሲሆን
ያልነበርኩት ሆኜ አረፍኩት
የፈቀደው ውብ ገላሽን
ልዳብሰው እጄን ላኩት
የሳመኝን ከንፈርሽን
ደጋግሜ እኔም ሳምኩት
ግን
ያሄን አዳም አልነበርኩም
እንዳልካድሽን የማልክደው
ያረሳሽው የማረሳው
በፍቅራችን ድርሳን መጻ'ፍ
በፊደሌ የማወሳው
ያልነበርነው አዲስ እውነት
በገላችን የፈጸምነው
ይሄን አዳም እኔ ባልሆን
ይቺን ሴትም ባትሆኚ
የእድሜአችን ስጦታ ነው
ይሄን አዳም አልነበርኩም።
✍✍✍ ይታያል ጌቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
🥰2
CBE
ሀገር ሰላም ብየ በተኛሁበት ሌት ህልሜን እያለምኩኝ
በደረቀው ሌሊት ስልኬ ድንገት ጮሆ ከእልቅልፌ ባነንኩኝ
ደግሞ ምናባቱ ሰው አይተኛ እንዴ የሚደውልብኝ
የሚበጠብጠኝ እረ ምን ጣለብኝ
ግራ እየተጋባሁ
ሄሎ
አቤት ጓደኛየ ምነው ምን ሆነህ ነው ምነው በዚ ሰአት
ምን ቢገኝልኝ ነው በድቅድቅ ጨለማ በደረቀው ሌሊት
ወደኔ የደወልክ ብየ ስጠይቀው
ሁሉም ሀብታም ሆነ ገንዘብ ታፈሰልህ ይሄንን እወቀው
የትም ሳትለፋ ወዴትም ሳትደክም ባለህበት ቦታ
መበልፀግ መጣልህ አሁኑኑ ሞክር ነቃ በል በል በርታ
ሲለኝ ስለሰማሁ እኔም ከመ ቅፅበት ስኩን አቋርጬ
ወደ ስልኬ ማውጫ በፍጥነት አፍጥጬ
ኮኮብ ስምንት ስምንት ዘጠኝ መሰላል
ስደውል ስሞክር ልቤ ይጠረጥራል
ይሰራል አይሰራም? ብየ ስደናበር
አንዴ እስኪገባልኝ አላመንኩም ነበር
ከዛ
ስሞክር ሲገባ ስደግም ሲደመር ገንዘብ ሲጠራቀም
የተሰማኝ ደስታ ከዚ በፊት ጭራሽ ተሰምቶኝ አያውቅም
እየተጯጯህን የኔ እንደዚ ሆነ የኔም ይሄው ጨመረልኝ
በዚ ገንዘብማ ነገ የማደርገው ብዙ ነገር አለኝ
እየተባባልን እየተመካከርን ድንገት ተቋረጠ
ወይኔ ብዙ ሳይሆን
በሚል ሌላ ጩኸት ዶርሙ ተቀወጠ
ከዛ
ትንሽ እምደቆየን ነገ እንዳይወስዱት የሚል ስጋት ስለመጣ
በደረቀው ሌሊት ከግቢያችን ወጣን ብሩን ልናወጣ
ጨለማን አልፈራን ብርዱም አልበገረን ሰንጥቀነው ወጣን
በኪስ ሙሉ ገንዘብ እየተሳሳቅን አፋፍሰነው መጣን
ልክ ዶርም ስንደርስ
ተበተነ ብሩ ወለሉ በሙሉ ገንዘብ አጠገበው
ብርቅ ሆኖብናል እጠግብ አይመስለው እጅጉን የራበው
ስንጫወትበት ጮቤ ስንረግጥ መንጋት አይቀር ነጋ
በጠዋት ገባነው ብሩን መጨረሻ መዝናኛን ፍለጋ
ተገዛዛ እቃው ተጠጣ በበቃም ደግሞ ለዚ ገንዘብ
ዝም ብለህ ብላ እስከ ጥግ ተዝናና የምን ማገናዘብ
እየተባባልን ብሩ ሲገፋፋ ለማለቅ ሲቃጣው
ያንን ሁሉ ገንዘብ መልሱ ተባለ አሁን መጣ ጣጣው
አቤት መኮሳተር አቤት መኮስመን ያንን ስንሰማ
በጠራራው ፀሀይ የሚያሞቀን ቀትር ሆነብን ጨለማ
ስልኬ ይጠራና ባነሳሁት ቁጥር ገንዘብ አትመልስም
የሚል ነው ምሰማው ፍዳ ነው በእግዜር ስም
ይሄው ግራ ሲሆን በበላሁበት ብር የመኖር መንገዴ
ሁሉን እርዱኝ አልኩኝ ወይ እዳ ወይ ጉዴ
የተገዛው እቃ በርካሽ ተሸጠ አወየው ኪሳራ
ያንን ሳስብ ውየ ህይወቴ ሲናጋ እንዴት ስራ ልስራ
ቁጥር ባየሁ ቁጥር እዳ ትዝ እያለኝ
ባንክ የሚል ስሠማ እያብሰለሰለኝ
እንዴት ኑሮ ይሁን በተክለፈለፉ
ሆኖ በአፍ ይጠፉ
እርሜን ይሁን አልኩኝ ከእንግዲህ በሌሊት ስልኬን አላነሳም
ሆኦኦኦ ደሞ ምን በወጣኝ የሆንኩትን ነገር ዘላለም አረሳም
አመት ከምተክዝ ለአንድ ቀን ሳቄ
ይሻላል ሁሉንም ያኔ አለማወቄ
ሆሆሆሆ
ደሞኮ ባልነቃ ህልሜ ባይቋረጥ ምናል በጨረስኩት
የህልሜን አጫዋች ያንን የውብ ከንፈር ምናለ በሳምኩት
ጨለምለም ባለው ብርሀን ያጠረው ግንቡን ተጠልለን
እየተለፋፋን እየተሟዘዝን ይሉኝታንም ጥለን
ጠጋ ጠጋ ስላት እሷም ስትጠጋኝ ልክ ልስማት ስል
ማቋረጤ ቆጨኝ እንዴት ካይኔ ይጥፋ የውበቷ ምስል
ስልኬ ከሚጠራ ሳልስማት ሳልነካት ያኔ ከምነቃ
ምናለ ባይደውል ብሩስ ቢቀርብኝ አሁን ቆጨኝ በቃ።
✍✍✍ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ሀገር ሰላም ብየ በተኛሁበት ሌት ህልሜን እያለምኩኝ
በደረቀው ሌሊት ስልኬ ድንገት ጮሆ ከእልቅልፌ ባነንኩኝ
ደግሞ ምናባቱ ሰው አይተኛ እንዴ የሚደውልብኝ
የሚበጠብጠኝ እረ ምን ጣለብኝ
ግራ እየተጋባሁ
ሄሎ
አቤት ጓደኛየ ምነው ምን ሆነህ ነው ምነው በዚ ሰአት
ምን ቢገኝልኝ ነው በድቅድቅ ጨለማ በደረቀው ሌሊት
ወደኔ የደወልክ ብየ ስጠይቀው
ሁሉም ሀብታም ሆነ ገንዘብ ታፈሰልህ ይሄንን እወቀው
የትም ሳትለፋ ወዴትም ሳትደክም ባለህበት ቦታ
መበልፀግ መጣልህ አሁኑኑ ሞክር ነቃ በል በል በርታ
ሲለኝ ስለሰማሁ እኔም ከመ ቅፅበት ስኩን አቋርጬ
ወደ ስልኬ ማውጫ በፍጥነት አፍጥጬ
ኮኮብ ስምንት ስምንት ዘጠኝ መሰላል
ስደውል ስሞክር ልቤ ይጠረጥራል
ይሰራል አይሰራም? ብየ ስደናበር
አንዴ እስኪገባልኝ አላመንኩም ነበር
ከዛ
ስሞክር ሲገባ ስደግም ሲደመር ገንዘብ ሲጠራቀም
የተሰማኝ ደስታ ከዚ በፊት ጭራሽ ተሰምቶኝ አያውቅም
እየተጯጯህን የኔ እንደዚ ሆነ የኔም ይሄው ጨመረልኝ
በዚ ገንዘብማ ነገ የማደርገው ብዙ ነገር አለኝ
እየተባባልን እየተመካከርን ድንገት ተቋረጠ
ወይኔ ብዙ ሳይሆን
በሚል ሌላ ጩኸት ዶርሙ ተቀወጠ
ከዛ
ትንሽ እምደቆየን ነገ እንዳይወስዱት የሚል ስጋት ስለመጣ
በደረቀው ሌሊት ከግቢያችን ወጣን ብሩን ልናወጣ
ጨለማን አልፈራን ብርዱም አልበገረን ሰንጥቀነው ወጣን
በኪስ ሙሉ ገንዘብ እየተሳሳቅን አፋፍሰነው መጣን
ልክ ዶርም ስንደርስ
ተበተነ ብሩ ወለሉ በሙሉ ገንዘብ አጠገበው
ብርቅ ሆኖብናል እጠግብ አይመስለው እጅጉን የራበው
ስንጫወትበት ጮቤ ስንረግጥ መንጋት አይቀር ነጋ
በጠዋት ገባነው ብሩን መጨረሻ መዝናኛን ፍለጋ
ተገዛዛ እቃው ተጠጣ በበቃም ደግሞ ለዚ ገንዘብ
ዝም ብለህ ብላ እስከ ጥግ ተዝናና የምን ማገናዘብ
እየተባባልን ብሩ ሲገፋፋ ለማለቅ ሲቃጣው
ያንን ሁሉ ገንዘብ መልሱ ተባለ አሁን መጣ ጣጣው
አቤት መኮሳተር አቤት መኮስመን ያንን ስንሰማ
በጠራራው ፀሀይ የሚያሞቀን ቀትር ሆነብን ጨለማ
ስልኬ ይጠራና ባነሳሁት ቁጥር ገንዘብ አትመልስም
የሚል ነው ምሰማው ፍዳ ነው በእግዜር ስም
ይሄው ግራ ሲሆን በበላሁበት ብር የመኖር መንገዴ
ሁሉን እርዱኝ አልኩኝ ወይ እዳ ወይ ጉዴ
የተገዛው እቃ በርካሽ ተሸጠ አወየው ኪሳራ
ያንን ሳስብ ውየ ህይወቴ ሲናጋ እንዴት ስራ ልስራ
ቁጥር ባየሁ ቁጥር እዳ ትዝ እያለኝ
ባንክ የሚል ስሠማ እያብሰለሰለኝ
እንዴት ኑሮ ይሁን በተክለፈለፉ
ሆኖ በአፍ ይጠፉ
እርሜን ይሁን አልኩኝ ከእንግዲህ በሌሊት ስልኬን አላነሳም
ሆኦኦኦ ደሞ ምን በወጣኝ የሆንኩትን ነገር ዘላለም አረሳም
አመት ከምተክዝ ለአንድ ቀን ሳቄ
ይሻላል ሁሉንም ያኔ አለማወቄ
ሆሆሆሆ
ደሞኮ ባልነቃ ህልሜ ባይቋረጥ ምናል በጨረስኩት
የህልሜን አጫዋች ያንን የውብ ከንፈር ምናለ በሳምኩት
ጨለምለም ባለው ብርሀን ያጠረው ግንቡን ተጠልለን
እየተለፋፋን እየተሟዘዝን ይሉኝታንም ጥለን
ጠጋ ጠጋ ስላት እሷም ስትጠጋኝ ልክ ልስማት ስል
ማቋረጤ ቆጨኝ እንዴት ካይኔ ይጥፋ የውበቷ ምስል
ስልኬ ከሚጠራ ሳልስማት ሳልነካት ያኔ ከምነቃ
ምናለ ባይደውል ብሩስ ቢቀርብኝ አሁን ቆጨኝ በቃ።
✍✍✍ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍9
አልቀጥርም ጠበቃ
ተጎዳሁኝ ብየ አልከስም በሸንጎ
ላንቺ ክፉ ሚመኝ
የሚያስፈርድብሽ ልቤ እንዴት አድርጎ
እንዳንቺ አይነት እንኮይ
ፈልጌ ላላገኝ ምትሆን ለእኔነቴ
ከስሼሽ ላልካስ
ዳኛ በመፈለግ አይዝልም ጉልበቴ
አይታገሉትም
ጦር አይመዘዝም አይገታው ጠብመንጃ
ምን ሹም ሊፈርድበት
ምን ችሎት ሊፈታው የማፍቀርን ፍርጃ
✍️✍️✍️ይቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ተጎዳሁኝ ብየ አልከስም በሸንጎ
ላንቺ ክፉ ሚመኝ
የሚያስፈርድብሽ ልቤ እንዴት አድርጎ
እንዳንቺ አይነት እንኮይ
ፈልጌ ላላገኝ ምትሆን ለእኔነቴ
ከስሼሽ ላልካስ
ዳኛ በመፈለግ አይዝልም ጉልበቴ
አይታገሉትም
ጦር አይመዘዝም አይገታው ጠብመንጃ
ምን ሹም ሊፈርድበት
ምን ችሎት ሊፈታው የማፍቀርን ፍርጃ
✍️✍️✍️ይቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍4👏2🥰1
አንዲት ሴት ነበረች
ቤትና ትዳሩን
ህይወቱን የረሳ
ዘወትር በስካር
ዱላ የሚያነሳ
ቀን የጣለው ባሏን
ተቋቁማ የኖረች
ወዟ የነጠፈ
አንዲት ሴት ነበረች።
የእናትነቷን
ቤቷን ላለመፍታት
መበደሏን ችላ
መኖር ያታከታት
ግፍ ስለበዛባት
ጉንተላ ግርፋት
የደም እንባን
ማፍሰስ ሁሌም ያለጥፋት
የአብራኳን ክፋዮች
እንቁ ልጆች ጥላ
አንድ ጨቅላ ህጻን
በጀርባዋ አዝላ
ልብስ ሳትል ለአካል
ጫማ ሳትል ለእግሯ
ሀገር ጥላ ጠፋች
እናት ገራገሯ
ገደሉን ወረደች
ተራራውን ወጣች
እንባ እያወረደች
ክብሯንም ስላጣች
የአንገቷ ማስገቢያ
አንድ ወዳጅ ስታጣ
ከጎዳና አደረች
ለስቃይ ተጋልጣ
እድለ ቢስ እናት
በድካም ስሜቷ
ረሀብ ደቁሷት
ባልቀመሰ አንጀቷ
ልጇን ለመመገብ
ፍፁም ስላልቻለች
የእሷን ጥም ረስታ
ስለ ልጇ አዝናለች
እንባ ጉንጯን ሞልቷል
ጎስቋላ አይኗ ቀልቷል
ምንም እንደማትችል
የአቅሟን ማለቅ አምና
እጇን ዘረጋችው
ቆመች ለልመና
ይቺ ምስኪን እናት
ደስታ የማይቀናት
✍️✍️✍️ይቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ቤትና ትዳሩን
ህይወቱን የረሳ
ዘወትር በስካር
ዱላ የሚያነሳ
ቀን የጣለው ባሏን
ተቋቁማ የኖረች
ወዟ የነጠፈ
አንዲት ሴት ነበረች።
የእናትነቷን
ቤቷን ላለመፍታት
መበደሏን ችላ
መኖር ያታከታት
ግፍ ስለበዛባት
ጉንተላ ግርፋት
የደም እንባን
ማፍሰስ ሁሌም ያለጥፋት
የአብራኳን ክፋዮች
እንቁ ልጆች ጥላ
አንድ ጨቅላ ህጻን
በጀርባዋ አዝላ
ልብስ ሳትል ለአካል
ጫማ ሳትል ለእግሯ
ሀገር ጥላ ጠፋች
እናት ገራገሯ
ገደሉን ወረደች
ተራራውን ወጣች
እንባ እያወረደች
ክብሯንም ስላጣች
የአንገቷ ማስገቢያ
አንድ ወዳጅ ስታጣ
ከጎዳና አደረች
ለስቃይ ተጋልጣ
እድለ ቢስ እናት
በድካም ስሜቷ
ረሀብ ደቁሷት
ባልቀመሰ አንጀቷ
ልጇን ለመመገብ
ፍፁም ስላልቻለች
የእሷን ጥም ረስታ
ስለ ልጇ አዝናለች
እንባ ጉንጯን ሞልቷል
ጎስቋላ አይኗ ቀልቷል
ምንም እንደማትችል
የአቅሟን ማለቅ አምና
እጇን ዘረጋችው
ቆመች ለልመና
ይቺ ምስኪን እናት
ደስታ የማይቀናት
✍️✍️✍️ይቴ(@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍9😢8❤5
የእኔን ማኅሌት በዚ ባገኛት😜😜😜
[ማኅሌት ]
ንዑድ ክቡር ብዬ፣
እንደ ወንጌል ተቀብዬ፣
ሰግጄለት ያንቺን ምስል፣
(ያፀድቀኝ ይመስል... )
የስምሽን ማእተም አስሬ፣
እንደ አምላክ አክብሬ፣
ስሠግድልሽ ባለኝ አቅም፣
(እግርሽ መምታት ምን ባያውቅም...)
ምስጋና መስዋእቴ ላንቺ ስም አያልቅም።
[ሳልሞት…]
እንድትደርሺ በነፍሴ፣
(ሳልፈርድበት በራሴ... )
ወደሰማይ አንጋጥጬ፣
ውብ ቃላትን መራርጬ፣
አምጣት አምጣት እለዋለሁ፣
ወደ ሰማይ እጮሀለሁ፣
እንደያሬድ ዜማ ባልፈጥር፣
ከፀጋውም ባልቆነጥር፣
(በናፈቅሽኝ ቁጥር....)
(በተክሌ ዝማሜ.... )
ማኅሌቱን ቆሜ፣
ኪዳኑን አድርሼ፣
ቅዳሴ ቀድሼ፣
የማነጋበት ህልም፣
በቁም ቅዠት ሳልም፣
ማኅሌት ብቻ ነው የሚደጋገመው፣
ጅል አፌ 'ሚጥመው፣
እሱ ነው ማእተሜ
(የመናፈቅ ስሜ… )
ጠርቼ ማልጠግበው፣
ሁሌም እለት እለት
የሚወጋኝ ስለት
የማነበንበው፤
ፅድቅን የመሰለ
(ስምሽ ከውስጤ አለ… )
ሰር በሰረከ
ጠዋቱም በነጋ፣
እያደር ታካቅ ነው
ለኔ ያንቺ ዋጋ።
ከመግዘፍ ይገዝፋል
ከልቀት ይልቃል፣
ከመርዘም ይረዝማል
ከጥልቀት ይጠልቃል፣
ከስፋት ይሰፋል
ከርቀት ይርቃል።
የተሰጠሽ ፀጋ
እግዜር የተመነው፣
መጠን አይገልፀውም
ከልኬት በላይ ነው።
ዜማ ነሽ አራራይ
ግእዝና ዕዝል፣
ልቤ አንቺነትሽን ነው
በጀርባው የሚያዝል፣
እያንጎራጎረ
የእሹሩር ዜማ፣
በጣም በለሆሳስ
ላንቺም ሳይሰማ፣
ማ ማን ይስማኝ እያለ
ለሚጮኸው ጩኸት፣
ኅ ኅሊናው ሸፍቶ
ባይታመንለት፣
ሌ ሌት ሲያዜምሽ
ያድራል፣
ት ትምጣልኝ እያለ
ጮሆ ይዘምራል።
ርክራክ አርዝሞ
ዜማን እየቃኘ፣
ቃላት አፈራርቆ
ውስጥሽን ተመኘ።
ተራራ ወጥቼ
የምለፈልፈው፣
(በልቤ ምፅፈው)
ታላቁ መልክሽ ነው
ውስጤ የገዘፈው።
ልቤም ፈሪነቱን
ባንቺ ይደብቃል፣
የግጥሙ ቤት መድፊያ
በማኅሌት ያልቃል።
የመኖር ሰዋስው
የመናፈቅ ስሌት
የዜማዬ ቅኝት
ድንቅ ነሽ ማኅሌት።
✍ ይቴ (@gtmwustie)
አርብ 12/12/2016
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
[ማኅሌት ]
ንዑድ ክቡር ብዬ፣
እንደ ወንጌል ተቀብዬ፣
ሰግጄለት ያንቺን ምስል፣
(ያፀድቀኝ ይመስል... )
የስምሽን ማእተም አስሬ፣
እንደ አምላክ አክብሬ፣
ስሠግድልሽ ባለኝ አቅም፣
(እግርሽ መምታት ምን ባያውቅም...)
ምስጋና መስዋእቴ ላንቺ ስም አያልቅም።
[ሳልሞት…]
እንድትደርሺ በነፍሴ፣
(ሳልፈርድበት በራሴ... )
ወደሰማይ አንጋጥጬ፣
ውብ ቃላትን መራርጬ፣
አምጣት አምጣት እለዋለሁ፣
ወደ ሰማይ እጮሀለሁ፣
እንደያሬድ ዜማ ባልፈጥር፣
ከፀጋውም ባልቆነጥር፣
(በናፈቅሽኝ ቁጥር....)
(በተክሌ ዝማሜ.... )
ማኅሌቱን ቆሜ፣
ኪዳኑን አድርሼ፣
ቅዳሴ ቀድሼ፣
የማነጋበት ህልም፣
በቁም ቅዠት ሳልም፣
ማኅሌት ብቻ ነው የሚደጋገመው፣
ጅል አፌ 'ሚጥመው፣
እሱ ነው ማእተሜ
(የመናፈቅ ስሜ… )
ጠርቼ ማልጠግበው፣
ሁሌም እለት እለት
የሚወጋኝ ስለት
የማነበንበው፤
ፅድቅን የመሰለ
(ስምሽ ከውስጤ አለ… )
ሰር በሰረከ
ጠዋቱም በነጋ፣
እያደር ታካቅ ነው
ለኔ ያንቺ ዋጋ።
ከመግዘፍ ይገዝፋል
ከልቀት ይልቃል፣
ከመርዘም ይረዝማል
ከጥልቀት ይጠልቃል፣
ከስፋት ይሰፋል
ከርቀት ይርቃል።
የተሰጠሽ ፀጋ
እግዜር የተመነው፣
መጠን አይገልፀውም
ከልኬት በላይ ነው።
ዜማ ነሽ አራራይ
ግእዝና ዕዝል፣
ልቤ አንቺነትሽን ነው
በጀርባው የሚያዝል፣
እያንጎራጎረ
የእሹሩር ዜማ፣
በጣም በለሆሳስ
ላንቺም ሳይሰማ፣
ማ ማን ይስማኝ እያለ
ለሚጮኸው ጩኸት፣
ኅ ኅሊናው ሸፍቶ
ባይታመንለት፣
ሌ ሌት ሲያዜምሽ
ያድራል፣
ት ትምጣልኝ እያለ
ጮሆ ይዘምራል።
ርክራክ አርዝሞ
ዜማን እየቃኘ፣
ቃላት አፈራርቆ
ውስጥሽን ተመኘ።
ተራራ ወጥቼ
የምለፈልፈው፣
(በልቤ ምፅፈው)
ታላቁ መልክሽ ነው
ውስጤ የገዘፈው።
ልቤም ፈሪነቱን
ባንቺ ይደብቃል፣
የግጥሙ ቤት መድፊያ
በማኅሌት ያልቃል።
የመኖር ሰዋስው
የመናፈቅ ስሌት
የዜማዬ ቅኝት
ድንቅ ነሽ ማኅሌት።
✍ ይቴ (@gtmwustie)
አርብ 12/12/2016
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍4❤3❤🔥1👏1
[እንኳን አደረሳችሁ]
ነይልኝ!
ይጠየቅ ታቦር
ይመስክር ተራራው፣
እግዜር በመለኮት
እንዴት እንዳበራው፣
ይመስክር ኤልያስ
ይናገር ለአለሙ፣
ማመን ያነሳቸው
ያልሰሙ እንዲሰሙ።
ሆያ ሆዬ ይባል
ይዘመር መዝሙሩ፣
ከበሮው ይመታ
ይሟሟቅ አድባሩ፣
እውነት እንዳዘለ
የአምላክ መገለጡ፣
ለእርሱ ምስጋና
አፎች ቃል አወጡ።
ከተራራው መሀል
ብርሀኑ በርቷል፣
የመለኮት ምስጢር
ለአለም ተዘርቷል።
ያንን የሰማ 'ለት
አለማዊ ልቤ፣
አንቺን ያስብለኛል
ይርቀኛል ቀልቤ፣
ሆያ ሆዬ ብየ
መምጣት እመኛለሁ፣
ልብሽ እንደ ሙልሙል
ቢሰጠኝ እላለሁ፣
ስትናፍቂኝ ነው
እኔ ምን አውቃለሁ።
ከልማዱ ቢርቅ
ምን ለጆሮ ባይጥም፣
ያንቺው ሆያ ሆዬ
ይሄው የኔ ግጥም።
ሆያ ሆዬ ሆ
ሆያ ሆዬ ሆ
አይንሽን ማየት ሆ
ናፍቆ ያደረ ፣ ሆ
ባታውቂለትም ሆ
ልቤ ነበረ ፣ ሆ
ባህር እንዳጣ ሆ
ባይተዋር አሳ፣ ሆ
አንቺን በማሰስ ሆ
ወድቆ ሚነሳ፣ ሆ
የፍቅርሽ ናፋቂ፣
እኔው ነኝ እወቂ።
የምመኘው ፍቅር፣
ይምጣልን ተይ አይቅር።
የወፍ አፋ የወፍ አፋ፣
ልቤ ባንቺ ጥሎኝ ጠፋ፣
የወፍ ደግ የወፍ ደግ፣
ነይ ፍቅራችን ይደግ።
ላቀረብኩ ቅኔ
ለፍቅርሽ መወድስ፣
ሰላሜን አግኝቼ
ራሴን እንዳድስ፣
በሙልሙሉ ፋንታ
ልብሽ ይታደለኝ።
አንቺም አይተሽዋል
በገጠምኩት ግጥም
መፅደቅ እንደለለኝ።
ለአምላክ ጀምሬ
ላንቺ ስጨርሰው
እግዜሩስ ምን ይለኝ?
ይቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ነይልኝ!
ይጠየቅ ታቦር
ይመስክር ተራራው፣
እግዜር በመለኮት
እንዴት እንዳበራው፣
ይመስክር ኤልያስ
ይናገር ለአለሙ፣
ማመን ያነሳቸው
ያልሰሙ እንዲሰሙ።
ሆያ ሆዬ ይባል
ይዘመር መዝሙሩ፣
ከበሮው ይመታ
ይሟሟቅ አድባሩ፣
እውነት እንዳዘለ
የአምላክ መገለጡ፣
ለእርሱ ምስጋና
አፎች ቃል አወጡ።
ከተራራው መሀል
ብርሀኑ በርቷል፣
የመለኮት ምስጢር
ለአለም ተዘርቷል።
ያንን የሰማ 'ለት
አለማዊ ልቤ፣
አንቺን ያስብለኛል
ይርቀኛል ቀልቤ፣
ሆያ ሆዬ ብየ
መምጣት እመኛለሁ፣
ልብሽ እንደ ሙልሙል
ቢሰጠኝ እላለሁ፣
ስትናፍቂኝ ነው
እኔ ምን አውቃለሁ።
ከልማዱ ቢርቅ
ምን ለጆሮ ባይጥም፣
ያንቺው ሆያ ሆዬ
ይሄው የኔ ግጥም።
ሆያ ሆዬ ሆ
ሆያ ሆዬ ሆ
አይንሽን ማየት ሆ
ናፍቆ ያደረ ፣ ሆ
ባታውቂለትም ሆ
ልቤ ነበረ ፣ ሆ
ባህር እንዳጣ ሆ
ባይተዋር አሳ፣ ሆ
አንቺን በማሰስ ሆ
ወድቆ ሚነሳ፣ ሆ
የፍቅርሽ ናፋቂ፣
እኔው ነኝ እወቂ።
የምመኘው ፍቅር፣
ይምጣልን ተይ አይቅር።
የወፍ አፋ የወፍ አፋ፣
ልቤ ባንቺ ጥሎኝ ጠፋ፣
የወፍ ደግ የወፍ ደግ፣
ነይ ፍቅራችን ይደግ።
ላቀረብኩ ቅኔ
ለፍቅርሽ መወድስ፣
ሰላሜን አግኝቼ
ራሴን እንዳድስ፣
በሙልሙሉ ፋንታ
ልብሽ ይታደለኝ።
አንቺም አይተሽዋል
በገጠምኩት ግጥም
መፅደቅ እንደለለኝ።
ለአምላክ ጀምሬ
ላንቺ ስጨርሰው
እግዜሩስ ምን ይለኝ?
ይቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍11❤7
በእናትህ እቀፈኝ
ለልጅህ እጅ ዘርጋልኝ ማደፌን አይተህ ላታልፈኝ፣
ጌታ ሆይ አምላኬ ባክህ በእናትህ አግዜር እቀፈኝ።
በእናትህ እቀፈኝ ...
ከክንድህ አፈንግጫለሁ በተግባር ከቤትህ 'ርቄ፣
በሀጥያት ተጎሳቁዬ ቆሽሼ በአለም ወድቄ፣
አትሁን ያልከኝን ስሆን አትስራ ላልከኝ ስተጋ፣
ጎንህን እንደ ለንጊኖስ አድፌ አንተን ስወጋ፣
መቅደስህ ውብ ሰውነቴን በእርኩሰት እቆሽሻለሁ፣
በእናትህ እቀፈኝ ጌታ ካቀፍከኝ እመለሳለሁ።
ለበደልኩህ በደል ላደረስኩብህ ግፍ፣
በምህረት ካልመጣሁ ከላይ መቅሰፍት አርግፍ፣
አንደበቴን ዝጋው ቅስሜንም ሰባብረው፣
ሃሳቤን አጨልም እውቀቴን ቅበረው።
መዝለሌን ግታልኝ ለሀጥያት ምርኮ፣
አቅሜን አንበርክከው ለክርብርህ አምልኮ፣
የአለም ጉልበቴን በሽንፈቴ ተካ፣
አለምን ልናቃት በስምህ ልመካ፣
ሰው አርገኝ ጌታዬ ልጅህን አትርፈኝ፣
አምላኬ በድንግል በእናትህ እቀፈኝ፣
ማወቄ አልጠቀመኝም ማደጌ እያደር ጎዳኝ፣
መናገር ከንቱ ልፋት ነው ለነፍሴ አንድም አልረዳኝ፣
ባውቀውም ምን እንደማደርግ በሀጥያት እንደተመራሁ፣
መመለስ ባለመቻሌ ለነፍሴ አሁንስ ፈራሁ፣
ፍርሀቴን ተቀበልና ለቤትህ ለንስሀ አብቃኝ፣
በእናትህ ጌታዬ እቀፈኝ ከእቅፍህ መራቈ በቃኝ።
በእናትህ እቀፈኝ ...
✍ ይቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ለልጅህ እጅ ዘርጋልኝ ማደፌን አይተህ ላታልፈኝ፣
ጌታ ሆይ አምላኬ ባክህ በእናትህ አግዜር እቀፈኝ።
በእናትህ እቀፈኝ ...
ከክንድህ አፈንግጫለሁ በተግባር ከቤትህ 'ርቄ፣
በሀጥያት ተጎሳቁዬ ቆሽሼ በአለም ወድቄ፣
አትሁን ያልከኝን ስሆን አትስራ ላልከኝ ስተጋ፣
ጎንህን እንደ ለንጊኖስ አድፌ አንተን ስወጋ፣
መቅደስህ ውብ ሰውነቴን በእርኩሰት እቆሽሻለሁ፣
በእናትህ እቀፈኝ ጌታ ካቀፍከኝ እመለሳለሁ።
ለበደልኩህ በደል ላደረስኩብህ ግፍ፣
በምህረት ካልመጣሁ ከላይ መቅሰፍት አርግፍ፣
አንደበቴን ዝጋው ቅስሜንም ሰባብረው፣
ሃሳቤን አጨልም እውቀቴን ቅበረው።
መዝለሌን ግታልኝ ለሀጥያት ምርኮ፣
አቅሜን አንበርክከው ለክርብርህ አምልኮ፣
የአለም ጉልበቴን በሽንፈቴ ተካ፣
አለምን ልናቃት በስምህ ልመካ፣
ሰው አርገኝ ጌታዬ ልጅህን አትርፈኝ፣
አምላኬ በድንግል በእናትህ እቀፈኝ፣
ማወቄ አልጠቀመኝም ማደጌ እያደር ጎዳኝ፣
መናገር ከንቱ ልፋት ነው ለነፍሴ አንድም አልረዳኝ፣
ባውቀውም ምን እንደማደርግ በሀጥያት እንደተመራሁ፣
መመለስ ባለመቻሌ ለነፍሴ አሁንስ ፈራሁ፣
ፍርሀቴን ተቀበልና ለቤትህ ለንስሀ አብቃኝ፣
በእናትህ ጌታዬ እቀፈኝ ከእቅፍህ መራቈ በቃኝ።
በእናትህ እቀፈኝ ...
✍ ይቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤9👍4
ንገሯት
ፍቅሯን መግለፅ ስታውቅበት
ማታ ሲመሽ ተከስታ፣
ብርዱ ቁሩ አይበግራት
ለጨለማው ሳትረታ፣
ግንባር ጉንጬን መደባበስ
መሳምና ማሽሞንሞኑ፣
መላ አካሌን ለማዳረስ
ሳይሰለቻን መብከንለኑ፣
ድንበር አጥሬን ከለላዬን
በምትሀት ተሸጋግራ፣
ፊቴን ሙሉ ማህተሟን
አሳርፋው አሳምራ፣
የሷነቴን ስመሰክር
ቀኑ መሽቶ ቀን ይነጋል፣
ከልብስ አልፋ ባገኘችው
መላ አካሌም ይዘረጋል።
አይመዘን ፍቅሯ ከባድ
ስማ ስማ አትሰለችም፣
መግቢያ መንገድ ይገኝ እንጂ
ቀጥራ ምትቀር አይደለችም።
የሞት ዘመድ እንቅልፍ እንኳን
ሳያግደው የሚሰማ፣
መላ አዳሬን ለማሳመር
እያዜመች ጥዑም ዜማ፣
እንቅልፌን አርቃው
ነቃ ብዬ እንዳድር ለኔ ሁሌ አሳቢ፣
ፍቅሯ ሊገለኝ ነው
ንገሯት ለቢንቢ😃😃
✍ ይቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ፍቅሯን መግለፅ ስታውቅበት
ማታ ሲመሽ ተከስታ፣
ብርዱ ቁሩ አይበግራት
ለጨለማው ሳትረታ፣
ግንባር ጉንጬን መደባበስ
መሳምና ማሽሞንሞኑ፣
መላ አካሌን ለማዳረስ
ሳይሰለቻን መብከንለኑ፣
ድንበር አጥሬን ከለላዬን
በምትሀት ተሸጋግራ፣
ፊቴን ሙሉ ማህተሟን
አሳርፋው አሳምራ፣
የሷነቴን ስመሰክር
ቀኑ መሽቶ ቀን ይነጋል፣
ከልብስ አልፋ ባገኘችው
መላ አካሌም ይዘረጋል።
አይመዘን ፍቅሯ ከባድ
ስማ ስማ አትሰለችም፣
መግቢያ መንገድ ይገኝ እንጂ
ቀጥራ ምትቀር አይደለችም።
የሞት ዘመድ እንቅልፍ እንኳን
ሳያግደው የሚሰማ፣
መላ አዳሬን ለማሳመር
እያዜመች ጥዑም ዜማ፣
እንቅልፌን አርቃው
ነቃ ብዬ እንዳድር ለኔ ሁሌ አሳቢ፣
ፍቅሯ ሊገለኝ ነው
ንገሯት ለቢንቢ😃😃
✍ ይቴ (@gtmwustie)
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍7❤4🔥4😁2🥰1