ግጥም በግጥም
252 subscribers
1 video
4 links
ፍቅራችሁን እንጁ ሀሳቦቻችሁን አትስጧቸው!
Download Telegram
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ጉድ ሳይሰማ

በመጨረሻው ቀን በስንብቱ እለት
አልገታ ብሎኝ ከሃሳብ ስጓተት
ለካ....
ጉድ ሳይሰማ መስከረም ላይጠባ
ጉዴ መታችብኝ ታሽጋ በአበባ
ካንተ ዉጪ ሌላ ሁሉም ይቅር ሁሉ
ሁሉም ቀን ላንተ ነው አይቀር ለቱ ሁሉ
ስትለኝ ከራርማ ስትኩል ስትደልለኝ
ለካስ ዉሸት ኖሯል አውቃ ነው ሳትወደኝ
join us👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥4
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አዲስ ግን ምንድን ነው????

ካቻምና ያስከፋን ያሳዘነን ጊዜ
አንገት ያስደፋን የጎዳን ትካዜ
ከሰው ያሳነሰን ከትቢያ ቀላቅሎ
አቁሞ ያስቀረን ሃውልት አስመስሎ

ያ ቀን ዛሬም አለ ዘንድሮም አራቀን
ማን ያውቃል....
ከርሞም እንደማይኖር የዛረው ሰቀቀን

እና.... አንዱ የከረመ አንዱ አዲስ መባሉ
ዘመን መቁጠር ብቻ የቱ ላይ ነው ውሉ
ዛሬ ካለፈው ቀን ምንም ካለወጠ
የአምናው ረጋጭ ዛሬም ከረገጠ
አዲስ ምን ማለት ነው??
የዘመን መለወጥ ትርጉሙ የት ላይ ነው
ቀንና ሳምንትን
ወራት አመታትን
ቁጥር ከመጥራት ዉጭ እየደረደሩ
ስራ ሳይሰራ ዘመንን ቢያከብሩ
ምንም አዲስ የለም ያው አምና ዘንድሮም
አዲስ ተባለ እንጂ ምንም አዲስ የለም።
join us👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥6
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አንድ አመት ጨምረኝ

ልክ እንደ አምናው ዛሬም
ከአመት እስከ አመት ህይወቴን ሳልተልም
ፍሬ ሳላፈራ በክብረህ ሳላብብ
ትኩስ አልሆን በራድ ከሁሉም ሳልሳብ
ከመካከል ቆሜ አለሁ እንዳልሁኝ ለብ

አዉቃለሁ አምላኬ
አምና በዚ ሰአት
አዲስ አመት ሲቀርብ ጳጉሜን ስሸኛኛት
ምድር ፈክታ ለምታ አሸብርቃ ሳያት
መዋብ እያማረኝ ነፍሴን አጀብ መሙላት
የዘንድሮን ማረኝ ብየህ ነበር አማና
ልክ እንደዘንድሮው መስከረም ሲያቀና

በርግጥ ብዙ ጊዜ....
ከቃልህ ላልወጣ ቃልኪዳን ገብቼ
ዳግም ላላጠፋ በክፋት ላይ ዝቼ
ከቃልህ ወጥቼ ከጥፋት ዉያለሁ
በስምህ ስገዘት ስዋሽ ከርሜአለሁ

ግን አምላክ....
የዘንድሮም ማረኝ አንድ አመት ጨምረኝ
ለክብርህ ለፍቅርህ ተገዝቸ እነድገኝ

ያው ላንተ.....
አመት ቅፅበት በጣም ትንሽ አፍታ
አንድ አመት ጨምረኝ እባክህን ጌታ

አመቱን በሙሉ ልክ እንዳለቀው ቀን
ከቤትህ ባልገኝ ባላከብር ቃሌን
እባክህ አምላኬ.....
አንድ አመት ጨምረኝ ዉስጤ አይተራመስ
ከርሞም ይህች ቀን ደርሳ ...... አንድ አመት ጨምረኝ እስከምልህ ድረስ።
join us @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤6🔥1😱1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ልክ እንደ ዳዊቴ

ከየንታ ፊት ስቆም ገልጬ ዳዊቴን
ስቀፅል ስቀበል ዉዳሴ መዝሙሩን
ከገለጥኩት ዳዊት ከቅዱስ መዝሙሩ
ከፆመ ድጓው ከዜማ ከቁጥሩ
አንዱንም ሳልጨብጥ እንዲያው ላመል ብቻ
አንቺን ነው የምማር ለነፍሴ መባቻ

ደሞ እንደተማረ ከየንታ ፊት ዉሎ
ልቤ.....
ሄዶ ይመለሳል ናፍቆትሽን አዝሎ
ጋራ ተራራውን
ሸንትረር ገደሉን
ብወጣ ብወርድም
ቆንጅየ እንዳንቺ ግን ምኑም አያደክምም።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👏4❤2
በመስከረም ወር ለተወለደችዋ ፍቅሬ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


እንኳንም ተወለድሽ🎂🎂🎂🎂


እሰይ መጀን ወሎ
አቦ ጀባ ወሎ
ፀደይ ፍካት ለብሶ አብቦ ሲያቀና
ፈጠረሽ ፈጣሪ አልብሶ ቁንጅና
አጀብ ነው
ድንቅ ነው
የአካልሽ ደም ግባት የዉስጥሽ ልእልና
ዉስጤን ዉሃ አረገው ልክ እንደቦርከና
እሰይ ... የአጥንቴ ፍላጭ እሰይ ግራጎኔ
ሲያማትር ያመመው ታከመብሽ አይኔ

ለዳንሁት ከህመሜ ላዳነኝ ልደትሽ
ቃሌን እሰጣለሁ ለገዛኝ መውደድሽ

ዙሪያ እንደከበበሽ ልክ እንደተራራው እንደ ሰንሰለቱ
ላይነቅል ካለበት ለቤ ተገዝቶ ቆሟል ከመሬቱ
ልክ እንደታደለኝ ልክ እንደልደትሽ የፀደይ ምርቃት
አካልሽ ከአካሌ ልብሽ ከልቤ ጋር ቢሆን ምን አለበት
እምነቴ ታምኖልሽ መውደዴም ተወዶ ከዉስጥሽ ቢከርም
እጣንና ከርቤ
ወርቅጥላ ይዤ ከመቅደሱ አልቀርም

የልቤ ሰማዩ ደመና ያዘለው የከፋው ዉሎየ
በፀደይዋ ፀሃይ በአደይ ፈገግታ ብርሃኔ ታየ

እንዲህ ነው መወለድ እንዲህ ነው ሲቀና
እንዲህ ነው ሲሰምር አምላክን ልመና
እንኳንም ተወለድሽ እንኳንም አመጣሽ
በይ ነይ ግራ ጎኔ ከጎኔ ተቀመጭ ከጎኔ እንደወጣሽ
join us👉yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍9❤1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ልበ ብርሃን

ዳግም ላላይ የአለም ደጇን
ላልገረም አድንቄ ዉበቷን
አላፊ አግዳሚውን ተራማጅ ቋሚውን
ለይቼ ላላየው አጭር ረጅሙን
ላልተች ላላደንቀው ሚያስጠላ ሚያምረውን
የአይኔ መቅረዝ ቢገፈፍ
የስዕል ሸራው ቢቀጠፍ
ፀሀይ ለኔ ማገልገሏን
በጨለማ ድል መንሳቷን
መርገጥ ላልችል በአይኔ ዱካ
ጉዞን በዘንግ የምለካ
ልበ ብርሃን ብርሃን አልባ
አይኔን ጋርዶት ግርዶሽ ካባ
ከአይኔ ፀዳል መግባት ባይችል
እፅናናለሁ እንባን ሳብል።

join us 👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍2🔥1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ገዳምና ዉጪ

ከመናንያን ቅጥር ከአፀድ ከደብሩ
ከንፁሃን አምባ ከድባብ ከአድባሩ
እግር የረገጠ ቀን አካል ከመሬቱ
ቀና ንፁህ መሆን ይመጣል ስሜቱ።

ፊቱ ፀዳል ለብሶ ፈገግታው ሚያበራ
ሃጥያትን አጭዶ ፅድቅን የሚዘራ
ካህን መነኩሴውን ጿሚ ፀላይውን
ማየት ስትጀምር......
አለም ምን አባቷ ገንዘብ ምን አባቱ
መልበስ መዘነጡም የማይጠቅም ከንቱ
ስንል እንቆይና
ልክ ከገዳሙ ከቅጥሩ ስንወጣ
ያው ሃጥያት ዝሙት ነው መሞት ነው የእኛ እጣ
ለጠላነው ገንዘብ ከገዳም ተቀምጠን
ለሱ እንገዛለን ህግጋቱን ትተን።

join us👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍3
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከእለታት በአንድ ቀን

ከአድማስ ባሻገር የነበረች ፀሃይ
ብርሃን ለግሳ ወጋገኗ ሲታይ
በቃ ነጋ ብየ ተዘገጃጅቸ
ገና በማለዳው ከቤቴ ወጥቸ
ከሰዉ ግርግር ከአላፊ አግዳሚው ስር
እንደተቀላቀልኩ በሃሳብ ስዳክር
ለካ.....
የያዝኩትን ትሪት ያለኝን ሁሉ ሃብት
ለሌባ ለግሸው ከቦታው አጣሁት
አበድኩኝ
አዘንኩኝ
ጨነቀኝ
ብቻ ብዙ ብዙ ምን ያልሆንኩት አለኝ
ከዛ.....
ያው በወጣው እግሬ ሥዞር ሳስስ ዉዬ
ማታ በቴ ገባሁ ቀኑ መሸ ብዬ
ለካ ነጋ ያልኩት ለኔ የመሸ ቀን
አሸክሞኝ ሄዶ ሃዘን ከሰቀቀን
ከእለታት አንድ ቀን ያልኩት ያለፈው ቀን።

join us👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍4
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

መውደድሽን ልስማው

እንደ አምላክ ቃሉ እንደተሰማው ድምፅ
በምስማቴ ገብተሽ ፍቅርሽ ዉስጤ ቢያምፅ
ፍጡር እንደ ፍጡር መመልከቱን ትቼ
አንቺን ማምለክ ጀመርኩ እጆቼን ዘርግቼ።

ማመን መማረኬን መውደቄን ከደጅሽ
እጄን አንስቻለሁ አምናለሁ ጀግና ነሽ

ድምፅሽን ስሰማ......
መላ ሰውነቴ ያብባል ይፈካል
አይንሽን እንዳየሁ......
ከአይንስ ሰሌዳ ከብሌንሽ መሀል
ፀጋ በረከቱ ፍቅር ይታየኛል

ልክ እንደወደድኩሽ እኔም እንዳወራሁ
መውደድሽን በቃላት ማናለ በሰማሁ
በስርቅርቅ ድምፅሽ
ልብን በሚገዛ ማራኪ አንደበትሽ
መውደድሽን ንገሪኝ ማፍቀርሽን ልወቀው
በመንገድ የለፋው መውደዴን ልካሰው።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🥰3❤1👍1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ነበር

ገና ድሮ ድሮ በልጅነታችን
ሳይጎላ ሳይገዝፍ አካል ሃሳባችን
እወድሽ ነበር
እሳሳልሽ ነበር
አይንሽን ለማየት እጓጓልሽ ነበር
ነበር ብቻ አደለም ያው አሁንም አለ
ያንቺው ግን ሰውነት ስስትሽ የታለ??
join us👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍7
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ምን ይሉታል

አይኔ ሞኙ ዞሮር አይታክት
ሲቃኝ ሲይስስ ድንገት ቢያያት
የአይኔን ዱካ ተከትሎ
ልቤ ሄደ እኔን ጥሎ

አይን እንዳየ ልብ ወስኖ
የእሷ ገረድ አሽከር ሆኖ
መውደቅ ማመን ደጅ መፅናቱ
በጨረፍታ መመኘቱ
ይድላት ይክፋት እንኩዋ ሳላውቅ
ዉስጤ አብዝቶ የሚጨነቅ
እንዳወቃት እንዳጠና
መናፈቁ ያን ቁንጅና
ይህን ተግባር ምን ይሉታል
ማንስ ብለው ይጠሩታል
ያላዩትን አለም ያክቃኙትን መንደር
በሃሳብ እያሰሱ ሲዳክሩ ማደር

አምላክ ፈጥሮ ለአዳም ብርታት
አብራክ ክፍሉን ሄዋን አላት
የእኔም ሄዋን ግራ ጎኔ
ፍቅር ልትሆን በዘመኔ
ቀን መጣልኝ ብየ ማስብ
ተስፋን ከእሷ ፍቅር የምክብ
ምን ይባላል ምን ቃል አለው
ልክ አጣሁኝ እሚወክለው

Join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👏5👍2
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንደ ፈጣሪየ

ክርስቶስ አደለ አምሳያ ፍጡሩርን
ሞቶ ያስተማረው እጅጉን ማፍቀሩን
እኔም እንደጌታ ልክ እንደፈጠረኝ
ንፁህ ፍቅሩን ሲሰጥ ፋቅር እንዳስተማረኝ

ከልቤ መውደዴን ካንጀቴ ማፍቀሬን
ማሳያ እጅ መንሻ ይሄው እኔነቴን
እሰዋልሻለሁ፣ አቀርብልሻለሁ፣ ንፁህ ስሱን ልቤን።

ልክ እንደፈጣሪ በፍቅርሽ ስቅላት
ላንቺ ተሸንፎ ዉስጥ አካሌ ሲሞት
ለፍቅርሽ ቀላልጦ የፈሰሰው ልቤን
ካካሌ ተቆርሶ፣ ወዳንቺ የመጣው የዘነጋኝ ቀልቤን
ከስጋ ወደሙ ከአምላክ ፍቅር ቆጥረሽ
በካህኑ ፍቅር በመውደድ ላቁርብሽ

ቁርባኑ ይጠበቅ ትንከባከቢው ዘንድ
ልብሽ ከልቤ ዉስጥ በጥብቁ ይገመድ
ዉሀም እንዳትነኪ አርካሽ አፍራሹን
ቁርባኑን ዘንግተሽ እንዳትይዥ ሌላውን።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👏6
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰው ልሁን??
ሰው ልምሰል??

አይ! ሰው ልምሰል መሰለኝ
ደልቃቃ የደላው ኑሮ እንዲኖረኝ

የጊዜ ትኩሳት የዘመን ረመጥ
ዝቅ ዝቅ አድርጎት ሰው ሁሉ ሲጎብጥ
በእርሱ እየተሳለቅኩ ሰው መሆኔን ጥዬ
ሰው ልምሰል መሰለኝ ራሴን አታልዬ

እምደውም ሰው ልሁን!!!
በአምሳል ከፈጠረኝ ከአምላክ ከጌታዬ
በአካል ከመሰልኩት ግብሬንም አክዬ
ሰው ልርዳ ሰው ልውደድ
የስጋውን ትቸው በነፍሴ ልዛመድ
መመዘን መለየት መምረጡን ዘንግቼ
ሰው ብሆን ይሻላል ሰው መምሰሉን ትቼ።

join us 👉👉 @yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍6👏1
#መገላገል
እሰየው አረፍኩት 😉😉
😁3
😁3
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የባከነ ገላ

ሰውነትሽ ጥሩ ነበር ምንም ከሰው የማይከፋ
ዉበትሽም ድንቅ ነበር ከህሊና የማይጠፋ
ዉብ ምግባርሽ ሰናይ ፀባይ እንዳደለሽ
ድሎት ሳይሆን አጉል መሆን ሆኗል እጣሽ
ለአምላክ የዘመረ የጮኸው አንደበትሽ ግራ ቢዘም
አካልሽ ከመቅደሱ ይዉል ዘንዳ አልታደለም
ፅድቅን ጥሎ ሃጥያት ማንሳት እያደፉ
ማመን ሳይሆን አማኝ መምሰል በግርድፉ
ሰውን ሞላው ሰው ጎደለ ኖሮ ሳይኖር
ክፋት ሞላው መጨካከን ሰፋ በአገር
አንድ አድርገው አምላክ በጅህ ባካኝ ገላን
መግደል ማጥፋት እጅን በእጅ እንዲበቃን።

join us 👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍6
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ትዝታ

ትዝ አለኝ ያለፍነው
ያኔ ሆነን የነበርነው
ትላንትና ያደረግነው
ትዉስ አለኝ ያነበርነው

ትዝታ አዛዡ ትዝታ አለቃው
ፈረስ አርጎኝ ሲጨብጠኝ እንደጋማው
ሰጋር መሆን ቢለምድብኝ
በትዝታሽ ተጋለብኩኝ

join us👉👉 yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ገብርኤል

ሰው ከእርግማኑ ከዉርሱ ሃጥያት እንዲያገግም
መዳን ትሆንም ዘንድ በፀሎት ፀነሱ ሃናና እያቄም
ስለት ነበርና ከአምላካቸው ኪዳን የተሳሰሩበት
ለመቅደስ ሸለሟት ማርያም ብለው የስሟን ጥለት

ከመቅደስ ያለችው ትልቅ ብላቴና
ድንኳነ መድህን ሆና ተመርጣለችና
ብስራታዊ መልአክ ገብርኤል ከበላይ
መጦ አበሰራት እንደምትፀንስ አምላክን ከሰማይ
ከልሎ በአክናፉ አልብሶ ብርሃን
ብስራቱን ነገራት እመ አምላክ መሆኗን

ገብርኤል ሊቀ መላእክት ሃዲስ
ከክፉ አውጪ ደራሽ ቅዱስ
ምልጃህ ይርዳን ሰላም አብስር
ፍቅር አድለን እንድንከብር

ስለ ክብርህ ተሰብስበን ስንጠራህ
አስታርቀን አማንደን ከአምላካችን ከአምላህ
እሳት የወረውሰው ሃጥያት ያጠላውን አለም አስረስተህ
ከመንግስቱ አስገባን በምልጃህ አንፀን ከእንፋሎቱ አውጥተህ
እንደ አናንያ እንደ አዛርያ ደግሞ እንደ ሚሳኤል
አድነን ከአጥፊዎች ፈውሰን ገብርኤል

እንደህፃኑ ፅኑ ቅዱስ
እንደ አማኙ እንደቂርቆስ
ደግሞም እንደ እናቱ ልክ እንደ እየሉጣ
ከሞት አድን ህዝቡን ከንፍረቱ አውጣ

መሃላችን ተገኝ በጠራንህ ቁትር
ፅናት ይኑርበት ያገናኝን ፍቅር

ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል
ብለን አንታክትም ስምህ ይጣፍጣል
አንተን አምኖ ወጦ የወደቀ የታል
አንድ አርገን መልሰን ፍቅር ዋልታው ይቁም
ያገናኘን ካስማ ዝክርህም ያገግም
በአለም በደጇ ሰላም ልናሰፍን
ተነስተናልና ገብርኤል ሆይ እርዳን።

join us👉👉@yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


ይቅር በል ፈጣሪ

መጀመሪያዉኑ እኔ አስቤያት መች አውቅና
የት አይቻት ፀሀዬን ጋርዷት ደመና
ንፁህ እንደሸማው ልክ እንደጋቢዬ
ከቤትህ የማልቀር ዳዊት አንጠልጥዬ
ጨዋ ልጅ ነበርኩኝ አሁን ክብሬን ብጥል
ወድጄ እኮ አይደለም አምላኬ ይቅር በል

ገና በማለዳው ቸር አውለኝ ልልህ
ስለምን ቆይቼ ቁጭብዬ ከደጅህ
ከዛ ወደ ቤቴ መጣሁ
ተመስገን እያልኩህ ተመልሼ ወጣሑ
ከዛ
አንዷ አምሳለ ፀሃይ
ጨረቃንም መሳይ
ብትስመኝ ተስቷት
ድንገት ከሁዋላየ ሌላ ሰው መስያት
ደጅህን ረሳሁ እሷን ነው ምሳለም
በነጋ በጠባ መሳሜን ስተልም
ይቅር በል ፈጣሪ
ተስሜ ነው እንጂ ወድጄ እኮ አይደለም።

join us👉👉 @yitayal05


፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥5😁1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንዳታጭኝ

የተገዛልሽን የወደቀልሽን እኔነቴን ትተሽ
ፍቅርሽ ያቀናውን የሞላውን ቤቴን ወና ባዶ አደርገሽ
ገለል ገሸሽ ካይኔ መራቁን መምረጥሽ
በምን ይካስ ይሆን በምንስ መልሸሽ

የዋህ ልቤ አማኝ ገሩን
ምን ባታምኝው መታመኑን
አትጠርጥሪው አምነሽ ታመኝ
እደተውሽኝ እኔም ትቸሽ እንዳታጭኝ።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍1🔥1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እናት

በአንቺ አይደል ወይ ሰው መሆኔ
ለአንቺ አይደል ወይ ማውረድ ቅኔ
እንዲደላኝ እንዳይከፋኝ ስትይ ዝቅ ያልሽ
እጅሽ ሻክሮ አይንሽ ዳምኖ እያነባሽ
ደስታን ለኔ ያለበስሽኝ
አንቺ እናቴ እንዴት ቻልሽኝ

እየጠቆርሽ ያቀላሽው
እየራበሽ ያጠገብሽው
አካል ክብሬ በእጅሽ እቅፍ
የዘመመው ባንቺ ድግፍ
ሀዘን መድከም ባንቺ ግፍፍ
ፍቅርሽ ዘክሮኝ ዉለታሽን
ከመውደድሽ እንደዘገንኩ ስስትሽን
ከፋይ ያርገኝ መላሽ
ለረሃብሽ አጉራሽ
ለበረደሽ አልባሽ
እንዳኖርሽኝ በእኔም ተራ
ደግ ልሁን ልብሽ ይኩራ።

join us 👉👉 @yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤4👍1