ግጥም በግጥም
252 subscribers
1 video
4 links
ፍቅራችሁን እንጁ ሀሳቦቻችሁን አትስጧቸው!
Download Telegram
ሀሳብ

ያው በሃሳቤማ ብዙ ብዙ ሆኗል
አፍሽ ካፌ ዉሎ ጣምናሽ አይሏል
ግና
አንቺነትሽን ሳስብ ሳልም
በትዝታሽ ጭልጥ እልም
ሆኗል ኑሮ ካንቺ ወዲያ
ለአፍታ ትእይንት መታሰቢያ
ለቅፅበት ለአንድ አፍታ ለዳበሰኝ ገላ
በስምሽ ተገዘትኩ ላላይ ካንቺ ሌላ
join us👉@yiyayal05
❤3🔥1
Motivation quite 🥰🥰
ህግ 1🤔
የማይፈልጉህን😏 መፈለግ አቁም😌
👏4
Motivation 🥰🥰
ህግ 2🤔
ያንተን ውድቀት ለሚመኙት ስትል ተቀየር😏💪💪
👍5
Motivation 🥰🥰
ህግ 3 🤔
🔸የራስህን ህይወት በፍፁም ከማንም ጋር አታወዳድር ። ምክንያቱም የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ #ከሆነ_ኩራት ሲሆን ፣

🔹 ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ #ደግሞ_ቅናት ነው ሚሆነው።ሁለቱም ውጤቶች መጥፎ ናቸው።

🔸ሲለዚህ ወዳጄ ራስህን ከራስህ ጋር ብቻ ነው ማወዳደር ያለብህ።እመነኝ ያኔ ሰላምህን ታገኛለህ።

ውብ አሁን❤️
👍2🔥2
Channel name was changed to «ግጥም & Motivation👍»
Motivation 🥰🥰
ህግ 4 🤔
አደጋ ውስጥ ነኝ አትበል😏
ራስህን አደጋነኝ በል💪💪 😎
👍1🤔1
Motivation 🥰🥰
ህግ 5 🤔
እነሱ በድብቅ ከጠሉህ 😏
አንተ በግልፅ ግድ አይስጥህ😏😎
👍3
Motivation 🥰🥰
ህግ 6 🤔
ጠባብ አእምሮ 🤯 ካላቸው ሰወች ጋር ጊዜህን አታጥፋ
ወደፊት እንጂ ወደኋላ አይሉምና😏😎😎
👍3
ትኮሪያለሽ አሉ

አንድም ዉብ አይንሽን
ገርመም አድርጎ ሲያይ የሚያሰንፍ የሚጥል
ሁለትም ዉብ ጥርስሽ
ስለፈገግታሽ ሲል ሰው ሞቷል ከደጅሽ
ሶስትም ዉብ ከንፈርሽ አይን የማያስነቅል
ጥርስሽን ላያሳይ የማለ ይመስል
ይፈራል ይደፍራል ልምጣ ልሂድ ብሎ
በጥርስሽ ሰው መግደል መልካም አስመስሎ
እና
አይኔን ያየ ሁሉ አቅሙን ነው የሚያጣ
ፈገግታየን ያየ ይደርስበት አጣ
ብለሽ ጎረርሽ አሉ
አይነግርሽን እንጂ ያወራል ሰው ሁሉ
እኔ ግን
ልክ እንደሌሎቹ ዞሬስ አላማሽም
የዉበትሽን ሚስጥር አውቃለዉ ሁሉንም
አንቺም እኔም ሁሉም
አፍንጫው ሰልካካ አልያም ጎራዳ
ፀጉሩም ዞማ ደግሞም ከርዳዳ
ሁሉም በአምሳሉ ነው በ'ርሱ የተፈጠረ
ሁሉም አፈር ገቢ መሆኑ መች ቀረ
እና
አትኩሪ በውበት ሁሉም ያው አፈር ነው
ለዛላለም ህይወት
አምላክ በመጣ ቀን እኩል ነው ሚፈርደው
join us👉@yitayal05
🔥2
Motivation 🥰🥰
ህግ 7 🤔
ከማውራትህ በፊት አስተውል
ምክንያቱም አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል😎😌
🥰3
ብርሀን


ብርሃን ወጋገኑ ድልን ሲጎናፀፍ
ጨለማው ሲረታ መሞትም ሲታለፍ
ከተራራው ጫፍ ላይ ብርሃን ነበረ
ያልነበሩት ኖረው የኦሪት ነብያት
ደግሞም ከሃዲሱ ሐዋርያት
ብርሃንን አዩ አብም መሰከረ
የምወደው ልጄ ይሄ ነው እያለ።

እረኞች በሃይልህ አብረው ሲታደሱ
ብርሃኑ ደምቆ መምሸቱን ረሱ
ቡሄ ብርሃን በራ ደመቀ በጌታ
ለደከመች አለም የመዳን ስጦታ
እንደተበሰረ ያኔም እንዳበራህ
ከመሞት እንድንድን እርዳን በምህረትህ።
join us👉@yitayal06
👍3
አያሌ እምቢተኞች ጎልያድ ነን ብለው በእብሪት ሲነሱ
አይጠፉም ልባሞች አምላክን ተማምነው ጠጠር የሚያነሱ
join us👉👉@yitayal
👍4
ናፍቆት



ወዳጅ ባይርቅ ከጎን መለየት ባይመጣ
ናፍቆት የት ነበረ ምንስ ነበር እጣ
የወደዱት ወዳጅ ያነገሱት አጋር
በመለየት ሲርቅ በአድማስ ሲታጠር
ታድያ ናፍቆት ምነው.....
ምናለ ባልመጣ ልክ እንደወዳጄ
እንቅልፍ እየነሳ ከሚቆም ከደጄ
join us👉@yitayal05
🔥3👍2
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ቃልስ አያጥረኝም

ድንቅ ደምግባት አወይ ወዘና
ልብ የሚሰቅል ግሩም ቁንጅና
አንጀት ከሚያርስ ንግግርሽ ጋ
ዉስጥ አካል ዉጩን እየተዋጋ
ያርብርደብዳል ያንዘፈዝፋል
ሁሉን አንድ አይነት ሟች ያደርገዋል
ገና ብዙ እላለሁ ቃልስ አያጥረኝም
የዉበትሽ ነገር ወደር አያገኝም

join us👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤2🔥2
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እድል

ከምንም የሚበልጥ ከማወቅ ከማማር
የሰውን ከፍ ዝቅ ጣሪያ የሚፈጥር
እንደ እድል ማን አለ.....
አንሶ የጎበጠን በጊዜ ትኩሳት
ለሱ መች ሊሳነው በአጋጣሚ ማንሳት
ፍቅር ያድልና ረቂቅ ሚስትሩን
በእድል ያነሳዋል ዛሬ ያነሰውን

እኔም ዛሬን ባጣት ቀን ቢጎልብኝም
እድልን ያድላል አምላክ አይረሳኝም
ሰጦ አጎናፅፎኝ ከሰው ልክ አውሎ
በፍቅሯ ያክመኝ በማፍቀሯ ኩሎ።

join us👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🔥5
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንባ

የዘመን እድፍ የጊዜ ህፀፅ
ክፋት ባፀናው በሰው ሲታነፅ
ሰይፍና ሻሞላን ቆጥሮ እንደመከታ
ሰው ሰውን ይበላል በግፍ እየመታ
ሰው መሆን ያልበቃው አንሶ የጎበጠን
ያቀናትን ጎጆ ያቆማትን አለም
በእብሪት ናዱበት አንሰው አሳነሱት
አለምን ያላየ አብራኩን ነጠቁት
ከ እናቱ ማህፀን ከና ከመነሻው
ዘሩን አመከኑት ሳያይ እንደሚሻው

እናት ይሄን ስታይ
ደመና እንዳዘለ እንደከፋው ሰማይ
የሰቀቀን እንባ ይፈሳል ከአይኗ ላይ
የት አለህ ና ዉረድ
ዘገየህ ና ፍረድ
የእንባ ደብዳቤ የፍረድ ልመና
በደም የታተመ በመሞት የፀና
በሞተው ልጇ ስም በተሰዋው ባሏ
ዛሬም ትጣራለች አልደከመም ቃሏ።

join us👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍5
Channel name was changed to «ግጥም»
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


አምላክ....
ልመና ፀሎትክን መማፀን ትጋክን
ለአፍታም ሳያዘገይ ከመለሰ መልሱን
ክብርህን ሊያድስ ነው ሊያፀና እምነትህን

ደሞ ከዘገየ ብዙ ካስጠበቀህ
በመጠበቅህ ዉስጥ ይለካል ትእግስትህ

ለብዙ ጥያቄህ ካላሳየህ ምንም
አልሆን አልችል ብሎ አቅቶት አይደለም
ጠልቶህ ወይ ረስቶህ አይደለም ቅያሜም

ለጠየከው ነገር ምላሹን ያልሰጠህ
ስለሚጨነቅ ነው.......
ከፈለከው በላይ ስለሚያስፈልግህ።
join us👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
❤1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ስንኩል ልብ


አንዴ ብድግ..... ብድግ.....
በመውደድ መነሳት
አንዴ ደሞ ቅጭጭ ደሞ ድብን እርፍ
በፅልመት መረሳት
ከዛ እንደበደለ እንዳጠፋ ታውቆ
በፀፀት መታደስ
ደሞ....
በፀፀቱ ቅፅበት ያፀናውን አውቆ
በእብሪት መደርመስ

አንዴ ከፍ..... አንዴ ዝቅ.......
ወላዋይ ልብ ይዞ ስንኩል ስብእና
ሰው መሆን አረጋም ይዋዥቃል ገና።
join us👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👍4❤1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


የደም ዝውውሬ ከፍ ዝቅ ማለቱ
ላንቺ አይደልወይ እቱ
ማጎንበስ ማነሴ ዝቅ ያልኩኝ መምሰሌ
ለጎሰቆለ ሰው መሆኔ ምሳሌ
ስላንቺ አይደለም ወይ
ከሰው ሁሉ በታች ከግርጌ ምታየው

እውነት አይደለም ወይ ከደጅሽ መዋሌ
ተዘንግቶሽ ነው ወይ በስምሽ መማሌ
እንዳላወቀ ሰው ምንም እንዳላየ
ፊትሽን እየነሳሽ ምትርቂኝ አንችየ

ቀን ያነሳው ቅል ድንግይ ቢሰብር
መጣሁ ከቤትሽ ከቅትርሽ ላድር
ያን ኩሩነቴን ክብሬንም ትቼ
አቅሜን አሳንሼ ባንቺ ተረትቼ
ደጅ መፅናት ብውል ከቤትሽ ባልጠፋ
ፈሪ ሆኘ አይደለም ስላለኝ ነው ተስፋ
join us👉👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👏4👍1
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ጉድ

እፁብ ድንቅ ተአምር
አጀብ ታላቅ ሚስጥር
እንዲህ ነው መታደል ሲሰራ ተጠቦ
ከጨለማዋ ፈርጥ ከ ጨረቃ አስውቦ
ደግሞም....
በብርሀኗ መንገድ
በፀዳሏ መውደድ
ከምትሸልመው ፀሀይ ስወድራት
እሷ ትበልጣለች ጉድ ነው! አቻም የላት
በሳቅ በጨዋታው ፈገግታዋን ያየ
በፍቃዱ መርጦ ከቀልቡ ተለየ
ስትስቅ ስትፈነድቅ ማማሯስ አይደንቅም
እኔን የገረመኝ ታምራለች አኩርፋም።
join us👉@yitayal05

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
🥰4👍1🔥1