ግጥም በግጥም
252 subscribers
1 video
4 links
ፍቅራችሁን እንጁ ሀሳቦቻችሁን አትስጧቸው!
Download Telegram
ፍሬ

ስለ'ኔ አስብ ካልሽኝ ከጠየቅሽኝ ቃሉን
ፍቅርሽ ነው ደራሹ ከአንደበቴ ልሳን
ፍሬ ቃል ቢነግስ ውበት ልቤን ቢያጥረው
አይከፍት ለማንም ውስጥሽ ካልፈቀደው
ጥሪ በዝምታ አልልታ በአርምሞ
ተደበላልቆብኝ ቀልቤ ባንቺ ታሞ
በሁዳዴ ቋንጣ ሳግበሰብስ ኖሬ
ፋሲካን ላከፍል እበላለሁ ጥሬ
ግራ አጋባኝ ፍሬ ዘሩ
ለምሞት መሆኑ ከመሬት ማደሩ
ሳይሞት ላያፈራ ላያምርበት ዳግም
ዘር ከመሬት አንጂ በጎተራ አይከርምም
አንቺም ...
እንዳበብሽ ያፈራሽ እንቁ ፍሬህይወት
ተዘሪ በአካሌ እኔን ያርገኝ መሬት

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👏2
አርቲ ቡርቲ ድሪቶ
ወርዶ ለብሶ ቦትቶ
መብላት ሳይችል ራት ምሳ
ለፀብ ተንኮል የሚነሳ
ማነው ስሙ ምንስ ይባል
አይነሳ ከአዘቅቱ አዛው ይጣል።


✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍5
ልደት

አምላክ ምድር መጣ፥ወረደ ከአርያም
አጠረ ጠበበ፥ለበሰ ስጋ ደም
ከማርያም በእናቱ፥ጌታ ሰው መሰለ
ከግርግም ተወልዶ፥ከበረት ስር ዋለ
ንጉስ ሆኖ ሃያል፥ንፁህ ሆኖ ቅዱስ
በእንስሣት ትንፋሽ፥በከብቶስ ቢታረስ
ቀን ቢለዋወጥ ፥ ዘመናት ቢያልፉም
የአምላክ መወለድ፥ይወራል በአለም
ይጠራል በይፋ፥ይለፈፋል በደብር
ሰርክ ይነሳል ቃሉ፥ይዘከራል እግዜር
ግና...
የጌታን ሰው መሆን፥ከበረት ማደሩን
ስናስብ ስንዘክር፥ዋዜማ በአሉን
ከየትኛው ሆቴል፥ከማንኛው እልፍኝ
አቅደን አስበን፥ስንዘሙት ልንገኝ
ስንት አለን ትህትናን፥በማሰብ አሳበን
ዉለን የምናድር፥ከሃጥያቱ ድንኳን።

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍2🔥1
ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በጉጉት የሚጠበቁትን የገናና የጥምቀት በዓላት እንደ አደይ ፈክተው፣ ደምቀውና አሸብርቀው ያከብሩ ዘንድ  
   ልዩ ልዩ የኅትመት ውጤቶችን ይዞልዎት ቀርቧል።

ቀድመው ለሚያዙን ልዩ ቅናሽ ከማድረጋችን ሌላ በውጭና በክፍለ ሀገራት ለምትገኙ ደንበኞቻችን በፖስታ መላክ የምንችል መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ይደውሉ! ይዘዙን!
   👇👇👇👇
@bitaaa99
+251942501754
🚚 fast delivery
❤2
ዛሬ ልደቴ ነው

ዛሬ ልደቴ ነው

ጨለማ በሚሏት
ፅልመት በለበሰች በዚች አሰልቺ አለም
ዛሬ ነበር አሉ
ወድ ምድር የመጣሁ ለቅሶን በማስቀደም
ግን...
አንኳንም ተወለድክ
አጋር መከታችህን የመኖራችን ዋስ
ነፍ አመት ኑርልን
አንድሜህን ያርዝመው ሺ ዘመን እስኪደርስ
ያለኝ ወዳጅ የለ
ቄስና መፅሃፉ ዝምታን አንግበው
ቀኝም ዝም ግራም ዝም
እኔ አሰብኩት አንጂ ማንም ትዝ አላለው
.....

ከዛማ
መልካም ልደት የሚል አስታዋሽ ሲጠፋ
ልደቴን አወጅኩት ለፈፍኩኝ በይፋ
ልደቴ ነው ዛሬ እንኳን ደስ አላችኁ
እንኳንም ተወለድክ በሉኝ አባካችኁ
እያልኩኝ ስተርክ ምኞትን ሳከማች
የልደቴን እለት ሳልውላት አረጀች

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
🎉3❤2
ከሎሚ ከኮብል

ዉዴ ዛሬ አምሮብሻል በጣም
ዉበትሽን ካየች ጨረቃም አትወጣም
(ትሸማቀቃለች)
ቁንጅና መልክሽን ያየው ሳር ቅጠሉ
ከሊቅ እስከደቂቅ ደንቆታል ሰው ሁሉ
ታቦተ ህጉን ላከብረው ላነግስ
ከቤቴ ብወጣም ብሄድ ደጁ ድረስ
አልልታየ ላንቺ ሽብሻቦው ለክብርሽ
ዝማሬው ተረስቶ
መወድስ አዘልኩኝ ተቀኝ አለኝ መልክሽ

ተሰናዳ ሎሚ ተዘጋጅ ለመብረር
ይዘህልኝ ክነፍ ልቤን ልቧ አሳድር
ብየ እልከዋለሁ ከድንቁ ደረትሽ
ጨብጭው ሎሚየን አስገቢኝ ከልብሽ
(አይሆንም ካልሽ ግን)
የመጣው ይምጣ አንጂ ሰማይም ቢታረስ
ተቀበይ መውደዴን ልትገቢ ቤቴ ድረስ
(አለበለዚያ ግን)
የሚያምረው ደረትሽን የልቤ ኢላማ
ለሌላ ሰው ሆኖ ዉስጤ ከሚቀማ
ሎሚየን በኮብል በክፋት ተክቸው
በላኩት ፍቅር ልክ ጥፋትን አውጄው
መጥፋትን ከማነግስ በአካልችን ዙፋን
አንቺም ለሌላ አትሆኝ እኔም ለሌላ አልሆን

ወይ ጥፊ በፍቅሬ ወይ ሙቺ በበትሬ
ከሎሚ ከኮብል ምረጭልግ ዛሬ

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍2😁2
ጥምቀት

ሀጥያት ያቆሸሸኝ ያጠለሸኝ አኔን
ጨለማን ስከተል ያጣሁኝ ብርሀኔን
ብኩን ሰው ነበርኩኝ ወንበር የሚያጓጓኝ
በጥምቀትህ ኪዳን ከሞት አወጣኸኝ

እልልበል ከንፈሬ ምስጋና አውርድ አፌ
ሸብረክ በል ጉልበቴ አሸብሽብ መዳፌ
ከሰው ፊት ቆሜአለሁ ከሞት ሞት ተርፌ

አንዲት ጥምቀት ፍፁም ምህረት
መዳን ሞልቷል ከአማኙ ቤት
አጠብከን በጥምቀት አነፃኸን ከእድፍ
የነፍሳችንን ስም ከፅድቁ እንድናፅፍ

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤4
(( በቃ እወድሻለሁ))
  ————————

ለምን አትበይኝ ምክኒያት የለኝም፣
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም፣
ብቻ እወድሻለሁ መዉደዴም ጥልቅ ነዉ፣
ፍቅርሽ ለእኔነቴ የልቤ ዙፋን ነዉ፣
ህያዉ የምሆነዉ አንቺን በማፍቀር ነዉ፣
ቂልነት አይደለም ሁሌ አንቺን ማለቴ፣
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርሽ መክሳቴ፣
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ፣
በቃ አንቺን መዉደድ ነዉ ደስታ መደሰቴ፣
ዉለታን ፈልጌ ዉደጂኝ አላልኩም፣
ፍቅር ሰጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም፣
እንዴት ለምን ካልሺኝ እኔም አላወኩም፣
በቃ እወድሻለሁ ማለቴን አልተዉኩም፣
አዎ እወድሻለሁ፣
አዎ አፈቅርሻለሁ፣
ፍቅርቅር አድርጌሽ በፌሽታ እኖራለሁ፣
ዉድድ አድርጌሽ አንቺን እፎይታ አገኛለሁ፣
ዉዴን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ፣
በፍቅርሽ ዉቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ፣
አንቺ ካለሽልኝ ህያዉ እሆናለሁ፡፡
  
ይድረስ ❤️ልቤን ለሰረቅሺዉ ሌባ...

By
@Bini_smart
@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm

🌹✽‌»‌✨🌹💕✿💕🌹✨»‌✽?
👍4❤3
አለሁ

አንገት መድፋትህ አሞኛል
ቅስምህ ተሰብሮም ከፍቶኝል
ምን ልሁንልህ ወንድሜ?
በምን ላፅናናህ አለሜ?
እግዜር ምርጫው ብዙ አሰራሩ የአይነት
እያዝጎረጎረ የሰውን ሰውነት
ነጠለን በግብሩ ለያየን ከአንድነት
በትንሳኤ በኪዳኑ
ሊያጣምረን በቃሉ 'ለት
ማነስ በንጽጽር ዝቅታም ከአንፃሩ
የአለም ድንበሯ ባይታወቅ ዳሩ
ሰው በራሱ ሚዛን እየከፋፈለ
ተናነስን ቢልም በስሙ እየማለ
መምሰሉ ይበልጣል አኩል መሆን ልቆ
ከምድር እስከ ሰማይ በመክበር ደማምቆ
አለሁ እስካለኸኝ እስከ መሞቴ እለት
የመኖሬን እለት በዕውቀት ቃኝቻት።

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👏3❤2
አዋሪኝ

ጋራ ተራራውን እንደ መውረድ መውጣት
ስድኸው ብውልም የፍቅርሽን ዳገት
ከሰው አልቀማሽም ለኔም አትሆኚ
አየሁ በፍቅር ሀይቅ ከሌላ ስትዋኚ
ግን እኔ
ላገኝ አይደል
የሰጠሁሽ ንፁህ ልቤን
ላተርፍ አይደል
ያስገዛሁት መሪ ቀልቤን
ብቻ ድምፅሽ
ይህ ጆሮየን ሲዳብሰው
ሰማይ ያህላል
ልቤ ደስታው ልቆ ከሰው
እንደ አብርሃም
አምላክ ደጁን አንዳየለት
አንቺን ሳስብ
ብርሃን ነው ድቅድቁ ሌት

እሱ ይበቃኛል
ከበቴ ባትገቢ መምጣትሽ ቢቀርም
ልቤ ፍቅርሽ ያለው
በድምፅሽ መምታቱን ለቅፅበት አይተውም
እኔ ላንቺ ባልሆን
አንቺም ለኔ ባትሆኝ ቢቀድመኝ ቀዳሚ
ባይሆን አንኳ አዋሪኝ
ገደለደችው ተብለሽ ኋላ እንዳትታሚ።

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤4👍3
አድዋ


ስንክሳር ናት ሀግሬ፥የጀግኖቿ ገድል ቀለም
የሞታቸው ልኬት፥የነፍሳቸው ሰላም
እልፍ እጆችሽ ፥ ፍቅርሽን የጨበጡ
አንቺን ይዘው፥ ከመገዛት አመለጡ
የሃገርን ፍቅር፥የመውደዱን ዳሩ
በሞት አውጀውት፥ በድልሽ ከበሩ
ነገድ አምሳል ቁጥር፥ከመቁጠር የላቀ
አእላፋት ስጋቸው፥ ለፍቅርሽ ወደቀ
ምድር ከብራና፥ ዉቅያኖስ ከቀለም
ቢሰሩም ለድልሽ፥አያልቅም ገድልሽ
አንድ ግን አንድ ቃል፥አለም ያስደነቀ
አድዋ ይባላል፥ሆኖ የታወቀ
ምኒሊክ ሲደግም፥ጠይም እንስፍስፉ
እጅጉን በረታ፥ ጠላት ማሰፍሰፉ
አራስ ነብር ጣይቱ፥አይዞህ እያለችው
ንጉሱን ንግስቷ፥ ወደ ጦር መራችው
ድል በራ በአፍሪቃ፥ሽንፈት ገዛ ጠላት
ጥቁር ብርሃን በራ፥ፀሃይ ወጣች በሌት።

✍¥ïŧä¥äļ(
@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤5
እውነት ስለሆነ


ከቀራንዮ አደባባይ ከጎለጎታ ከምድሩ
ንፁህ ቅዱሱን ሊሰቅሉ አይሁዳውያን ሲያሴሩ
እልፍን ያዘለ ጀርባውን
የአለም መቆሚያ መዳፉን
ሰውን መስለው ሰው ያልሆኑ የአምላክ ክብር ያልገባቸው
ፍቅርን ጥሰው አንግሰውት እብሪት ሰፍኖ በውስጣቸው
አዛኝ እሱ ጅራፍ ቅስሙን የሰበረው
የእሾህ አክሊል ብርሃን ፊቱን ደም ሸፈነው
አየን ቆሞ በሃጥእ ሰው ቅዱስ ሲዳኝ
ከንቱ ፍጡር ፈጣሪውን መግደል ሲመኝ

አልባሱን ያጣው ክርስቶስ
ስለሰው ያነሰው ንጉስ
ሀመ ወሞተ በመስቀል
መከራን አየ ለሰው ሲል


ግማደ መስቀሉ ተጭኖት ሃያሉ ጌታ ደከመ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ አዳኙ ሰው ስለሆነ ታመመ
የአዳም እዳን በማሰብ ፍቅሩ ዳር ድንበር ስላጣ
ሞትን በሞቱ ሊሽረው ስለአምሳሉ ሰው ተቀጣ

ጅራፍ በዝቶበት አካሉ ቁንዳላው በደም ተዋጠ
ደምግባት ዉበት ፀዳሉ ለግፍ መከራ ተሰጠ
አክሊል ደፋ ለስቃይ ፊቱን ደም ብቻ ሸፈነው
እልፍ አእላፍ ስቃይን አዘዙ ለጌታ በመጮህ አብረው

የትኛው ይበልጥ ይሰማው የትኛው ግፍስ ይልቃል?
ግርፋት ግፊያው ጉንተላው ወይስ አክሊሉ አሞታል?
የቀኙ ይሆን የግራ የትኛው ችንካር ብሶታል?
ለውሃ ጥሙ ሃሞት ነው ወይስ ሳቃቸው መሮታል?
ብሎ ለጠየቀ ከአለም መልስ ይገኛል?

ቢገኝም ባይገኝ አንድ እውነት ግን አለ
የነበረው ቀደም የሚኖርም ያለ

ስለ ክርስቶስ ስም ሰው ሁሉ ካመነ
እውነት ስለሆነ
ፍቅር ስለሆነ
ግፍን ሊቀበል ነው ጌታ ሰው የሆነ።

ተፃፈ በYitayal G(@gtmwustie)

መልካም በአል ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ክርስቶስ ተንስአ እምሙታን በአቢይ ሃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም።


ሞትን በመስቀል ያገኘ ስለሰው የተንገላታ
ሞትን በሞቱ የሻረ መቃብር ያደረው ጌታ
ተነስቷል ልኡሉ ከሙታን መካከል ማን ይፈልገዋል
ከመቃብር የለም እየሱስ ተነስቷል

ከፍጥረት በላይ ነውና ከራሱም ከሞት የላቀ
ከሞት ተነስቶ ክርስቶስ አለም በብርሀን ደመቀ
አለም አታውቀው ስልጣኑን መለካት አትችል በአቅሟ
ያረግዳል ፍጥረቷ ሙሉ እንጂ በአምላክ ሲጠራ ስሟ

ሄዋን ስትስት ትእዛዟን አዳምም ሲክድ በደሉን
አሳሳች እሱ ዲያብሎስ በቃህ ተባለ መግዛቱን
ታሰረ አበቃ መፈንጨት ሰንሰለት ያዘው አካሉን

ቃል አለውና የሰጠው ሞቶ በደልን እንዲሽር
አዳም ነፍሱ ተማረች አዛኝ በሆነው እግዚአብሄር
አስገባው ከዘላለም ቤት ከመንግስቱ አምባ ከእርስቱ
ሀጥያጥ መስራቱ ቢያስቀጣም ክብርን አደለው ፀፀቱ

ሰላም ሰፈነ በምድር ወጀብ ግዞቱም አለፈ
ሰው ሁሉ በስራው ሊዳኝ ከውርስ ሃጥያት አረፈ
የመከራው ዘመን ተሻረ ምህረት ለአለም ተሰጠ
መራራው ጊዜ ተሽሮ ለሰው ልጅ ሰላም ተሰጠ

ደስታና ተድላም ሆነ አለም በሞቱ ተምራ
ከሞት ተነስቶ ክርስቶስ ከፀሃይ ልቆ ሲበራ



ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ፉንጋዋን

ከግንባሯ መለጥ
ከወደ አይኗ ፈጠጥ
ከአፍንጫዋ ደምጠጥ
ከከንፈሯ ሞጠጥ
ለደረቷ ምጥጥ
ወደ ሆዷ ሾጠጥ
ከጀርባዋ ጎበጥ
ያለች ስጠኝ እንጂ አይን የማይበዛባት
ከቆንጆ ጋር ሆኘ አደከመኝ ቅናት
ያያት ወንድ ሁሉ የኔ ናት እያለ
አላፊ አግዳሚው ቀልቡን እየጣለ
ከሚያንገበግበኝ ቅናት ነበልባሉ
ፉንጋዋን ጠበሰ ይሻላል መባሉ።

ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤2👍2👏2😁1
እውነት ስልሽ


አንቺን ይንሳኝ እውነት ስልሽ
ባንቺ ምየ ሀሰት የማውቅ እንዳይመስልሽ
ግዞት ዝቅታው ላንቺ ነው ለፍቅርሽ ነው ያነስኩልሽ
ብዙ ቀሚስን ቢያማትር አይኔ ብዙ ቢንቀዋለል
አንቺን ካየ ወዲያ በአላፊ አግዳሚው መች ሊታለል
ቅኔ አካሉን ከሁለት ከፍሎ አንዱን በአንዱ እየመራ
ወርቁን መርጧል ዉበት አይቶ ሰሙን ላንቺ እያበራ
ወርቁ ፍቅርሽ ብኩን ልቤን ስላረጋው
በምን ይሰጥ ሽልማቱ ይቆጠርስ በምን ዋጋው
አንቺ ብቻ ንግስት ዙፋን ክብር የተቀባሽ
ብዙ ገብተው ሲመለሰው ለዘላለም ቤቴ የገባሽ
አንቺ ብቻ ሄዋን ሁለመናሽ ልዩ
በውበትሽ ስፋት ይቀናል ሰማዩ
ደሞም
ፊትሽ ያለ አመሉ ኮስተር ሲል ገና
እንደሰማይ ኩርፊያ ጠቋራ ደመና
ያስፈራራል እጅግ ፍቅርሽ ዳብሶ ለወረሰው
ፀሀይ ሳቅሽ ደመናውን እስካልጣሰው
አታኩርፊ ፈገግ በይ ባክሽ ሳቂ
ኩርፊያ ጎዳኝ ማየት ናፍቆኝ ስትደምቂ
ያየሁ ትላንት እንጂ ባከተመው ዘመን
አግረኛ ነህ እያልሽ ስለምን ይመመን
እሙ
እውነት አንቺን ይንሳኝ አማላጇን ስልሽ
ሌላ እንስት አላይም አውሮኝ አካልሽ
ፈራሽ እንጂ
እያየ የማያይ ሰምቶ የማይሰማ
ጭምት ሆንኩ ወዳጅሽ ጨዋ 'ማይታማ
ፍቅርሽ ዘመን ያስገበረኝ በመዳፍሽ ያስቀመጠኝ
ዝሙትን ከኔ ወስዶ መታመን የሰጠኝ

ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)


@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
አድነኝ
ከአሳ ነባሪው ጉሮሮ ከሞት እቅፍ እንድወጣ
አምላክ ፍርጃህ ማዳንህስ መች በመጣ
ህልም አለ እንጂ ከስቃይ ፅንፍ የሚነጥቀኝ
ስኖርማ ድሎት ደስታ መች አወቀኝ
እየኝ እንጂ በምህረትህ ዳብሰኝ እንጂ በመዳፍህ
ትረፍ የሚል ድምፅ ልስማ ቃል ይበቃል ልዳን በአፍህ
ሽንቁር መሀል እምደገባሁ ከወናው ስር እምዳልከርም
ብርሀን ስጠኝ ነፍስ ልዝራ ልትረፍ ዛሬን ሞት ባይቀርም

ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ያምራል ግን ያስፈራል


ከናፍሮችሽ ሲላቀቁ ፈልቀቅ ሲሉ ለፈገግታ
እንጃ ልቤ ተርበትብቷል ካለወሰን ነው የመታ
ጥርስሽ ከሳቅ  ሲገጣጠም
ውብ ፈገግታሽ አቤት ሲጥም

እንደ ካህን
መቅደስ መሃል እንደቀዳሽ
ስጋ ወደም
መዳን እጣን ለሰው አልባሽ
እንደሆንኩኝ
ልቤ ሲያስብ ሳቅሽ ባርኮት
ቤተልሄም መግባት ሲመኝ
ፍቅር ቁርባን ለመፈተት
እንቅፋቱን
መች አለፈው እየፈራ ፈገግታሽን
ፀዳል ለባሽ
እንቁ ምስል ዉበትሽን
ፈገግታሽ
አምላክ ነው ያሰግዳል እልፉን
ተሳስቶም ላየ
ይቀጣል በምርኮ ይመዛል ወንጭፉን
ፈገታሽ አለቃው ልቤን ያደከመ
ታውይቶም አይታወቅ ሌትም አልታለም
አይጣል ነው በጣም በጣም ያምራል
                        ግን ደሞ ያስፈራል

ተፃፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍8
እዮሪካ

ከአይኔ ርቆ ተሸሽጎኝ ያጣሁትን
ቀን በሃሳብ ሌትም ሳይቀር ያለምኩትን
ናፍቆት ቀርጾ የሰራውን ገላ አካልሽን
በአይኔ አየሁት ዉብ አይንሽን
እዮሪካ
እዮሪካ
እዮሪካ. . .
ማየት ብቻ መች ሊያረካ
አገኘሁሽ በሃሳቤ በአይኔ በኩል
ዉበትሽን ከልቤ አጸድ ስክብ ስኩል
እፎይ
እፎይ
አገኘሁሽ እሰይ


የኔ እዮሪካ

ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
❤3👍2
እናትየ

ሰው መሆን ሲለካ
በርኩሰት የዳኸው ድኩም ማንነቱ
የመቃናት መንገድ
የመንጻት የመዳን የማለፍ ድርሰቱ
በፍቅር ይቃኛል
በመውደድ ይሰጣል ሰው ነኝ ለሚል ሁሉ
ዝቅ ብሎ አንሶ
በጎደፈ ሃሳብ ካላጎዳደለው የሰው ልጅ በአመሉ
የሰው ልጅ ጣእሙ
ጥፍጥናው ሲለካ ማማሩ ሲወደር
ኣንቺን ነው ሚመስል
በመዋብ ዳርቻ ማ ካንቺ ሊወደር
እናትየ አንቺ
ስመ ቅድስና የንጽህና አምሳል
መውደድሽ ደምቆ ነው ከልቤ የሚሳል
እናትየ ያልኩሽ
አተልቄው እንጂ የሴትነት ልኩን
አምላክ የቸረሽን
ሰው የመሆን መጠን የመፈጠር መልኩን
በእንስፍስፏ እናቴ
በእምቁዬዋ እንስት በስሟ ምጠራሽ
እንድትኖሪልኝ ነው
ከልቤ አዳራሽ ዉስጥ ሁሌም እንዳበራሽ


ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
ፍቺኝና ላግባሽ

ታስታውሽው ይሆን?
የተጋባን ሰሞን
ወጥቼ እስክገባ አታምኝኝ ነበር
ፍቅርሽን አልብሰኝ
በካባሽ አድምቀሽኝ
ወሰን ያጣ ነበር የፍቅራችን ድንበር
የሰሞኑን ያርቅ
የዛሬን አያድርግ
ክፉ ቀን መጣ እንጂ የሚነጣጥለን
ስናወጋ...
ስናወጋ አድረናል
ከፍቅራችን እልፍኝ ተሸፋፍነን ውለን
ታስታውሽው ይሆን
የተጋባን ሰሞን
ወጥቼ እስክገባ አታምኝኝም ነበር
አሁን ፍቅር ጎሎ
አካልሽ 'ርቆኝ
የገዘፈው ትዳር አዟል ሊሰበር

ሰርጉ ከነበረ
ሰላም የሞላልን ዳንኪራ ጭፈራው
ተረስቶሽ ከሆነ
የድስ ግርግር
ልብሽ የሚርቀኝ አካሌን የፈራው
ሁካታው ከሆነ
የሰው ግርግር
ያኔ ፍቅር አጥምቆ ለቤቴ ያስገባሽ
የጎደለው ልብሽ
ዳግም ሙሉ ይሁን
የቀረው ይቅር እንጂ ፍቺኝና ላግባሽ

ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)

@gitimtm
@gitimtm
@gitimtm
👍3