ግጥም ከሰሊ ነው
357 subscribers
37 photos
9 files
15 links
@ሰላሙ ግጥም #0936529834

ያላችሁን ሃሳብ፣አስተያየት እንድሁም ጥያቅያችሁን በዝህ bot
ላኩልን
@Gitimjesusbot
@Gitimjesusbot
@Gitimjesusbot
Download Telegram
“ከተሳሳታችሁ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍሩ፡፡ እንደገና ስትጀምሩ እኮ የምትጀምሩት ከዜሮ ሳይሆን ከስህተታችሁ ትምህርትና ልምድ ካገኛችሁበት ደረጃ በመነሳት ነው - ካልታወቀ ምንጭ 

ከትናንትናው ዛሬ አድጋችኋል፣ ተለውጣችኋል፣ በስላችኋል፣ ተሻሽላችኋል፣ ጥበብ አግኝታችኋል፣ በርትታችኋል፣ ነገሩ ገብቷችኋል . . . ፡፡

ብርቱ ናችሁ! በርቱ!
@gitimkesli
እግዚአብሔር - ይወድሃል!

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዩሐንስ 3፡16

✍️ ደወል እስካልደወልከው ድረስ ደወል አይደለም። መዝሙር እስካልዘመርከው ድረስ መዝሙር አይደለም።
ፍቅርም እስካልሰጠኸው ድረስ ፍቅር አይደለም።
እግዚአብሔር ከ 2,000 ዓመታት በፊት  አንድ እና ብቸኛ የሆነውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጠን፣ ይህም በምን ያህል ጥልቅ በሆነ ፍቅሩ እንደሚወደን ያሳየበት መንገድ ነው።

✍️ እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደወደደ (በኢሱስ ቦታ ስምህን ማድረግ ትችላለህ) ይወድሃል። አንድያ ልጁን ሰጠህ። በልብህ ውስጥ የሚሰማህ ሥቃይ ሁሉ፣ የሚያልፍብህ ማናቸውም ብስጭት፣ ከዓይኖችህ የሚዘንቡ ዘለላ እንባዎች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል ምክንያቱም እርሱ በጥልቀት ስለ አንተ ያስባልና።

✍️ ኢየሱስ “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።” (ዮሐንስ 10 10)። ጌታ በጣም ስለሚወድህ ስለ አንተ በመሞት የሚትረፈረፍ እና የሚበዛ ሕይወትን ሊሰጥህ መጣ። እሱ ደስተኛ እና ጥሩ ስኬት እንድታገኝ ይፈልጋል። የማይታየውን ነገር ግን በልጁ የተገለጠውን ፍቅሩን በማሰላሰሉ ወደ ታላቅ የተትረፈረፈ ሕይወት መግለጥ ጀምር ክርስቶስ ዛሬም ይወድሃልና።

join join
👇👇👇
@gitimkesli
@gitimkesli
"ከባድ ነው ስሜቱ"
መጣ ያልከው ቀርቶ ደግ ያልከው ሲከፋ
አምነህ ያስቀመጥከው  ከቦታው ሲጠፍ
ይወደኛል ባልከው  ደረትህን ነፍተህ
  በድንገት ስትደማ  ልብህን ተወግተህ
ምንም ብትሆን ብርቱ
  ከባድ ነው ስሜቱ ...
ማውጋት እየፈለክ ሲቸግርህ ሰሚ
ከቀድሞው ሳትሽር ሲያምህ በድጋሚ
ዙሪያህን ተከበህ አጂቦህ እልፍ ሰው
ልክህን  ስታጣ  ሆድህን ሲብሰው
ምንም ብትሆን ብርቱ
  ከባድ ነው ስሜቱ ...
ማልቀስ አየፈለክ እንባህ ግን ሲደርቅ
የደላው ሊመስል ጥርስህ ደግሞ ሲስቅ

እንዴት ነህ ስትባል  ታሞ ሳለ ጎንህ
ውጋቱን ደብቆ  ደህ ነኝ ሲል አፋህ
ምንም ብትሆን ብርቱ
  ከባድ ነው ስሜቱ ....
@gitimkesli ✍
@gitimkesli
💎ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

🔑ስለተቸኮለ አይደረስም ...
      ስለተዘገየም አይቀርም ........
የቀርፋፋዋን ኤሊ ምግብ ፈጣንዋ ጭልፊት አትወስድባትም።ሁሉም በጊዜው  በፈጣሪ ሀይል ውብ  ይሆናል።
@gitimkesli
ከሚሸጠው ጋር እንጀራን የሚቆርስ፤ከሚክደው ጋር ገበታ የሚቀመጥ፤ የሚያዋርደውን እግር የሚያጥብ፤ ጌታ ዛሬ ካንተ ጋር የፍቅር ገበታን ይዘርጋ፤ ፍቅርን ጠቅልሎ ያጉርስህ፤ በጠራው የመስቀል ደሙ ይጠብህ፤ ከአይንህም ላይ አዚሙ እንደቅርፊት ይውደቅልህ፤ ወጥተህ ወደቤትህ ስትገባ በረከት እንጂ ቫይረስ አብሮህ መግባት አይሁንለት፤ ሰው ለመጣል የምትፀየፍ የወደቀን ለማንሳት የፈጠንክ ያድርግህ፤ በተዘጋው ልብህ ላይ የመለኮት ብርሃን ይፈንጥቅበት፤ የቆሰሉ እጆቹን ያሾልክበት፤ ህይወትህ መጠገን ይሁንላት፤ ምንም ነገር ጥያቄ አይሁንብህ፤ ሰላምህ ሞቶ አይቀበርብህ፤ ደስታህ የቀን ሳይሆን እንደዘመን ይርዘምልህ፤ በጠላትህ ፊት በደስታ ዘይት ተቀባ፤ እንጀራህ ከሞሰብ አይጉደል፤ በቁጥ'ቁጥ ሳይሆን በመትረፍረፍ መኖር ይሁንልህ፤ ነፍስህን ለአንተ አይስጥህ በእጁ ላይ ያኑርልህ፤ የሚያታግልህን ከፊትህ ይገንደስልህ በብቸኝነትህ እግዚአብሔር ያጫውትህ መላዕክቶች ይክበቡህ። የተወደደ ጊዜ እንድሆንልህ ተመኘሁ

@gitimkesli
@gitimkesli
"ህይወት ደስ የሚል የታሪክ መፅሃፍ ነው። እስከፍፃሜው ማንበብ ይጠበቅብሃል።  አሳዛኝን ምዕራፍ ብቻ አንብበህ  እንዳታቆም። ከዚያ በኋላ ያለው ምዕራፍ ደስ የሚል ሊሆን ይችላል። ፍፃሜው ደግሞ ይበልጥ ውብ ሊሆንም ይችላል።"
@gitimkesli
@gitimkesli
👩‍👦👩‍👧ውዷ እናቴ👩‍👦‍👦👩‍👧‍👧

ሲከፋኝ ሚከፋሽ ስስቅ የምትስቂ

ስሳሳት ምትመክሪኝ አንቺ የኔ አዋቂ

የአምላክ ስጦታ ለአንዷ ህይወቴ

ምን ይውጠኝ ነበር ያላንቺ እናቴ
:
:
ጓደኛ ወዳጄ ከኔ ማትርቂ

ጉዳዬን ማዋይሽ ሚስጥሬን ጠባቂ

በማንም በምንም መተኪያ የሌለሽ

በደስታ ኑሪልኝ ሳለሽ በህይወትሽ

ሁሌም ወድሻለው እኔ ያንቺ ልጅሽ::


@gitimkesli
@gitimkesli
ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቦአልና።  ሌሊቱ ሊያልፍ፣ ቀኑም ሊጀምር ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን፣ የብርሃንን ጦር ዕቃ እንልበስ።  በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።  ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ  በሐሳባችሁ አትመቻቹለት።
ሮሜ 13:11-14
(መዝሙረ ዳዊት 34)
----------
12፤ ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?

13፤ አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።

14፤ ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።
ህማም

የክርስቶስ ልጆች ልብ በሉልኝማ
ስቃይ ሲሰረስር ህመሙ ሲሰማ
እስቲ ከኛ መሀል ማነው ያስተዋለው
መከራው ሲበዛ በሚዛን የለካው
እንኳን ሚዛን ቀርቶ ስፍር ቢደረደር
የኢየሱስን ህማም አይለካውም ነበር
ታዲያ ለዚህ ጌታ ውለታው ምንድነው
በዘፈን ዳንኪራ አዳራሽ መርገጥ ነው
አይደለም ወገኔ እባክህ ተመለስ
የአዶናይን ህማም አይቻልህም መቅመስ
ፅድቁ እንኳን ቀርቶብህ በቅጡ ተኮነን
ማስመሰሉን ትተህ ለህሊናህ ታመን

@gitimkesli
@gitimkesli
ክርስቶስ ተነሳ

ድውይ በፈወሰ ሙታንን ባነሳ
ይሰቀል ተባለ ውለታው ተረሳ።
ክርስቶስ ይሰቀል በርባንን ልቀቀው
ብሎ ተናገረ ሀጢያት የናፈቀው።
የይሁዳ ክህደት ዓይኑን ያፈጠጠ
ለሰላሳ ብር ሲል አምላኩን የሸጠ።
ቸሩ መድሐኒዓለም ብዙ ተገረፈ
መከራው ቢጠናም በትዕግስት አለፈ።
እየተጋገዙ ጨርሶ እስኪቀር አጥንቱ
የአዳም ዘርን ሁሉ ከሲኦል ለማውጣት
ፈጣሪ በፍጡር ተቀበለ ቅጣት።
ተሰቀለ ብላ ስታዝን እናቱ
ገድለነዋል ብለው አህዛብ ሲዘብቱ
አዳኙን ቢገድሉት ያለ አንዳች አበሳ
ሞትን ድል አድርጎ ክርስቶስ ተነሳ።

@gitimkesli
@gitimkesli
.....የከርሞ ሠው ያድርገን......
‎፡
‎ውበት አጣና ነው... ሆድ ሲራብ ይረግፋል
‎ ዝናም እንደ ጅረት....ደራሽ ሁኖ ያልፋል፡
‎ እድሜ ክዱ ልብስ ነው...ኖርኩ ሳይባል ያልቃል፡
‎ ተስፋም ያዝኩት ሲባል...ከሰማይ ይርቃል
‎ከሠው ጋር ለመኖር....ሠው መሆን ይበቃል።!!"
‎፡
‎
‎የከርሞ ሠው ይበለን
ቻናላችንን ይቀላቀሉ   
join 👇👇👇👇👇
   ..   
@gitimkesli
         
@gitimkesli
         
"ምናለ ብታስተምረኝ"

በክብር በሞገስ በመወደስ ፈንታ
መቀመጥ እንድችል ከመዋረድ ተርታ
ስድብን እየሰማሁ ያለ አንዳች ሁካታ
ለመቆም እንድችል ልቤ ሳይረታ
ምናል ብታስተምረኝ ብታስችለኝ ጌታ!?

ለእኔም አስተምረኝ ባላጠፉት ጥፋት
በጸጋ መቀበል የአይሁድን ትፋት
እንዴት እንደሚቻል ሳያጉረመርሙ
ንገረኝ ጌታዬ ይረዳኝ ትርጉሙ!
የመናቅን ጥበብ የውርደትን ዘዴ
እባክህ አስረዳኝ አስተምረኝ አንዴ
ብዔል ዜቡል ተብለህ ያልተበሳጨኸው
የኃጢአተኞች ወዳጅ መባል ያልጠላኸው
ጋኔን ይዞታልን የሰማህ በጸጋ
ለእኔም አስተምረኝ በቂም አልወጋ!
አልወጋ እባክህ በመራርነት ጦር
በቁጣ ጥላቻ ነፍሴ አትሰበር
እንዴት ነበር ያኔ የይሁዳን እግር

ዝቅ ብለህ ያጠብኸው ስታውቅ ሁሉን ነገር?
ለእኔም አስተምረኝ ብዙ ሳልናገር!
በችንካር ተጣብቀህ ከመስቀሉ ጋራ
የደምህ ነጠብጣብ ገና ሳያባራ
አያውቁትምና የሚያደርጉትን
ይቅርታን የለመንህ ላጠጡህ ሐሞትን
ምናል ብታስተምረኝ እንዲህ ዓይነት ሕይወትን?
አሁን ምን ቸገረህ ብትሰጠኝ ለአንድ አፍታ
የትሕትናን ቀሚስ የትዕግሥትን ኩታ
እያየህም አይደል ነፍሴ እንዲህ ተራቁታ?

የመሰደብን ዘውድ የመናቅን ካባ
ምናለ ብትኖር ይ’ች ልቤ ደርባ!?
ትዕቢት ለተሞላው ለአትንኩኝ ባይ ልቤ
ለክብሩ ለሚኖር ለኮርማው ሃሳቤ
ምናለ ብትቀባው የትሕትናን ሽቶ
እንደዚህ ከሚኖር ሸትቶ ተበላሽቶ!?
ኸረ እኔ አልቻልኩም አቅቶኛል በጣም
ስድብን መቀበል ሐሜትን ማጣጣም

ስተርከው እንጂ ስኖረው አቃተኝ
ይህን መራር ኑሮ አንተው ይዘህ ጋተኝ!
እንኳን እንደ አንተ ዝም ልል ሲረግጡኝ
ቁጣዬ ነደደ ስለገላመጡኝ
ያንን ሁሉ ታሪክ ያን ሁሉ ጥቅስ ረሳሁ
በቂምና በቀል በጥላቻ ከሳሁ
እንደ አራስ ነብር ለክብሬ ተነሣሁ!

#ሼር
ቻናላችንን ይቀላቀሉ 

     join 👇👇👇👇👇
     @gitimkesli
      @gitimkesli
1 ጠሞ 1/ 15 ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤
♥️ #የተፀፀተ_ሰው_ፀሎት
ከሰጠኸኝ የአካል ክፍል የእኔ የምለው የቱን ነው ? ካንተ ውጭስ አላጣውም ብዬ የምፎክርበት ንብረቴ እኮ የቱ ነው ? በየዕለቱ ካንተ በቀር የእኔ የምለውን ነገር እየፈራሁ እኖራለሁ ። ጥዋት ተናግረውለት እስከ ማታ የማያመሽ ፣ አለኝ ሲሉት የጉም ስፍር የሚሆን ይህ ዓለም ምንድነው ? ትላንት የነበርኸኝ ፣ ዛሬም ያለኸኝ ፣ ነገም የምትኖረኝ አንተ ነህ ። ሕፃን ልጅ የሰጡትን አምጣ ሲሉት እንደሚያለቅስ እኔም አንተ ከሰጠኸኝ ላይ አሥራት በኩራት ለመስጠት አለቅሳለሁ ። እባክህን ይህን መንፈሳዊ ሕፃንነቴን አሳድገው ። ነገሥታትን ስለምፈራ በግድ ግብር እከፍላለሁ ። ቅጣትም ፈርቼ በጊዜው እሰጣለሁ ። የፍቅር መንግሥት የምትሆን ያንተን መንግሥት ግን ችላ ብያለሁ ። ወንጌል ሲበደል ፣ አገልጋዮች ተስፋ ቆርጠው ወደ ሥጋዊ ኑሮ ሲመለሱ እያየሁ ገና እሰስታለሁ ። ላለመስጠት ብዙ የደለቡ ምክንያቶችን አዘጋጅቻለሁ ። የማይመለከተኝን እናገራለሁ ። እባክህን የሰጪ ጌታ ልጅ ፣ ስስታም አይደለምና መስጠትን አለማምደኝ ። የማይሰጥ ደስታ የለውምና እባክህን ይህን ብፅዕና ጨምርልኝ ። ብሰጥም ያንተን ላንተ ነው ።ስለሰጠሁም ራሴን ከማድነቅ ጠብቀኝ ። ገበሬ ዘሩን አይበላምና ዘር የተባለውን አሥራት በኩራት ከመብላት አድነኝ ። ሕይወቱን በመስቀል ላይ ሰጠኝ እያልሁና እየሰበክሁ ገና በገንዘብ ካልታመንሁ በእውነት ከንቱ ነኝና ይህን ግብዝነት አርቅልኝ ።

☦️በሰጠኸኝ እውቀት ፣ በሰጠኸኝ ጉልበት የማገለግልበት ዘመን አድርግልኝ ። በሚያልፍ ዕድሜ የማያልፈውን ለመሥራት አብቃኝ ። መስጠት ዕድል ነው ። መስጠት ያልቻለ ተቀባይ ይሆናልና እባክህን መስጠትን አለማምደኝ ። ስለ ድሆች ፣ በየመንገዱ ስለወደቁ ያንተ ሕንፃዎች እንዳዝንና እንድተጋ እርዳኝ ። እኔ ጥዋት ለከሰዓት እየራበኝ ምንም የሌላቸውን ድሆች እንዳስብ አግዘኝ ። አሁንም ብሰጥ እንኳ ደግነቴ ሳይሆን ግዴታዬ መሆኑን አስተምረኝ ። ሁሉ ያንተ ነውና ያንተን ላንተ እንድሰጥ በሁለንተናዬ አንተን እንዳከብር እርዳኝ ። ስላደረግህልኝ ነገር ሁሉ ምስጋና ላንተ ይሁን ። ለዘላለሙ አሜን ።🙏♥️


ቻናላችንን ይቀላቀሉ   

   
     join 👇👇👇👇👇
   @gitimkesli
@gitimkesli
" ዛሬ ልደቴ ነው " 🕺
...... ተፈቅዶልኝ  አዲስ የመኖር ጉዞን ልጓዝ ነው .... በእኔ ሳቅ ውስጥ የሚስቁ ፣በእኔ ስኬት ከእኔው ጋር እኩል የሚቦርቁ ፣ ሀዘኔ የሚያሳዝናቸው  ፣መድከሜ የሚያዝላቸው  የእኔ የምላቸው ጥቂት ሠዎች በዙሪያዬ አሉኝና     መኖሬን ከነ ጋሬጣው  ከነ አረሙ እወደዋለሁኝ  ። አሻግሬ የማማትረው ፡በጉጉት የምጠብቀው  ፡ተስፋ የሰነቅኩበት ሁኖ ላየው የምቋምጥለት የራሴ የሆነ የሂዎት ግብ ስላለኝ አዎን መኖሬን ከነምናምኑ እወደዋለሁኝ 🤷‍♂እናንተም ጋር ለመተዋወቅ መብቃቴ  በመኖሬም አይደል 🤔 ዃላስ "አያችሁ መኖር ደግ ነው" እንኳንም ኖርኩ
#እንኳንም_ተወለድኩ 📸🎂🍫
ሁሉንም ታልፋለህ!

በሰዎች መካከል ልዩነት የሚፈጥረው አንዱ ለማድረግ የሚከብደውን ወይ የሚፈራውን ነገር ሌላኛው እየደበረውም ቢሆን ጨክኖ ማድረጉ ነው። ህይወት ቀላል እንዲሆን አትመኝ፤ ከባድ ቢሆን እንኳን አንተ ከሱ በላይ ከባድ ሆነህ ማሸነፍን አስብ!

መጀመሪያ ተመኝ እንድታገኝ! ከዛ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ያኔ በህይወት ሚዛን አንተ የማታልፈው ፈተና የለም፤ ወዳጄ ብርሀን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ጨለማውን ታግሶ ማሳለፍ አለበት!

በጋራ ወጀፊት🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♀🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂እንጓዝ
 
    ሀሳብ አሰተያየት እንዲሁም ምክር 👇🏻👇🏻
           @gitimkesli
           @@gitimkesli
🔥🔥የክብሪትእንጨት🔥🔥

እሱ ለቁምነገር ተጠቅሞት ባያቅም

ተሰጥቶት ነበረ   ትልቅ እምቅ አቅም

የሆነው ሆነና

አንድ የክብሪት እንጨት  ቢይዝም ጭንቅላት

ካኖረው ቤቱ ጋ   ሁሌ በመጣላት

ሄዶ እየተጋጨው   ነገር በመቆስቆስ

ቀልጣፋ ነው ሁሌም   እሳት ለመለኮስ::

      

@gitimkesli
@gitimkesli
@gitimkesli
"ልፈወስ ተብሎ ህመም ከተሻረ
ይጠጣ የለም ወይ ኮሶ እየመረረ
አንዳንድ ቀን ዘራፍ ልበል እንጂ እንደወንድ
ወተት ብቻ እኮ ነው መገፋት የሚወድ"

━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ   
◦◦✧join 👇

@gitimkesli