ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
አስተምረኝ
( ሠይፈ ወርቅ)

አስተምረኝ - ከማዕበል ጋር መደነስ
አሠልጥነኝ - በእሳት ላይ መመላለስ
ስሬን አጥብቅ - እንድታጠፍ ለነፋሳት
ልቤን ግራው - ሲቀጠቀጥ እንዲከፈት
ከዶፍ
ከጎርፍ
ከጣይ፣ ከቁር
ከበረድ ጋር
ከውሽንፍር
ከመብረቅ ጋር እንድጨፍር
ውብ ህይወትን እንድዘምር
አስተምረኝ!
ያለነፋስ - ዋሽንት በድን
ሳይገረፍ - ክራር አይድን
ሳይመታ - ሙት ከበሮ
ለሰከነ - ለነፍስ ጆሮ
በህመም ውስጥ ተቀምሮ
ውብ ዜማ አለ በተፈጥሮ
አስተምረኝ
የማየትን ጥልቀት፣ ርቀት
አሠልጥነኝ
የማድመጥን ስር መሠረት
በሸለቆ
በከፍታ፣ በቁልቀለት
ህመም ሳልሸሽ
ያለህመም ልኑርበት
#አስተምረኝ
#ምራኝ!
#ማረኝ!
( ሠይፈ ወርቅ )

#አስተምረኝ

#ሰይፉወርቁ #ሰይፈወርቅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ