ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
በዲበኩሉ ጌታ 'ራስ'ነት በምድር ዘላለም ቀዳሚነት ደምቆ እና ጥሞ ተጣጥሞ ያለፈው ግጥም ሲጥም 3 በጨረፍታ ይህን ይመስል ነበር። ከመደበኛ አጣሚዎቻችን በተጨማሪ በታዳሚነትም በአቅራቢነትም በድንገቴ ተገኝተው መሰናዶውን ካጣሙሉን ውስጥ ዮሐንስ ሃብተማርያም (ጨበሬው)፣ Kal's T (The Wordsmith) እና ማሕሌት ማይረጉን እንዲሁም የተገኛችሁትን ሁሉ ምስጋና ልናቀብላችሁ እንወዳለን።
ለተሻለ ከፍታ እየተጋን ነውና አሁንም ብርቱ እገዛችሁ አይለየን!

እስቲ ደሞ ቀጣዩን 'ራስ' ገምቱ. . . ማን ሊሆን ወይም ልትሆን ትችላለች?

#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ክበባዊነት
.
.
ያ'ለሚቷን ክበብ
ያስገኘን ነጥቦች
ተቋልፈን
ተሳክረን
የሰራናት 'ዶቶች' ፤
(ክምር የህዋሶች)
..
በበቃን ተላ'ቀን
አንዳችን የሸሸን
ያፈነገጥን ለታ... ፤
ዓለም ትሞታለች
ከዛጎሏ ወጥታ፡፡
..
በጦስ ጥንቡሳሷ
እኛንም ቀላቅላ ፣
ክበብ በነጥቡ
ነጥብም በክበቡ
ይገለጣል ብላ፡፡
....
(ቀለም
ሰው
አምላክ)

©ዮሐንስ ኃብተማርያም
የብርሃን ጥላ

ነግቶ ፀሀይ ወጣች ሲመሽ ጨረቃይቱ
አንድ ዕለት ተባለ የጊዜ ግምቱ
ጨረቃና ፀሀይ እነዚ'ም ሁለቱ
በብርሃን ስም ነው የሚጠሩበቱ






ጊዜ በብርሃን እኛም በጊዜ ፊት እንደ'ማለፋችን
መተላለፍና መገናኘት አለ በእግረ - መንገዳችን

አሁን መንገድ ላይ ነን ...

እንዴት እንቃኘው ትናትን ከዛሬ ዛሬን ከነጋችን
በነዚህ መካከል ዞሮ ይዘከራል መገናኘትና መተላለፋችን

ጊዜ ግን አይገርምም ቀድሞ መፈጠሩ ከእኛነቻን
እኛስ ግን አንገርምም ጊዜን ልናዝበት መንፈራገጣችን

እላለሁ...
በብርሀሃን ጀምሬ በጌዜ አልፌ ከኛ እደርሳለሁ
ቃል እንደሁ ሎሌ ነው ይሄንን አውቃለሁ

አዎ
ቃል እናገራለሁ ቃል አበጃጃለሁ
የቃል ፅኑነቱን
በምድርና ሰማይ አረጋግጫለሁ




ቃል ከእውነት እዲወለድ
ከእመምነት ጋር እንዛመድ
እንደ ጨረቃ እንደ ጣይቱ
ምንም ቢጨልም ቢነጋ ሌቱ
ልባችን ይብራ እንደ ሁለቱ

በተስፋ ለተስፋ...







.
.
.
© መንበረ ማርየያም ሀይሉ
መንቢ የ ሎዛ
❖ንጋት እና ንቃት ❖

አይነፃፀሩም ቅድም ከ አሁን ጋራ
ቅፅበት ነበርና
ምስሉ ያልረጋ -ገፅታው ያልጠራ::
የማይጨበጥ ነው
በምኞት ተጠምዶ
ከምናብ ተዋዶ
ከህልም ተላምዶ
በአጉል አምሮት መብረር
በሃሳብ ግዞት ሰፎ
ወድቆ ክንፍን መስበር ::
ርግጥ ነው አልክድም!
መልካም ህልም ነበር ..
ጣፋጭ ዓለም ነበር ..
ልዩ ነገር ነበር ...
ሌሊቱ ባይነጋ !
አይኖቼን እያሸሁ ባልቀር ከራሴ ጋ ::
በመስኮቴ በኩል
የረፋዷ ፀሓይ ከአይኔ ቆብ ስር አርፋ ባትቀሰቅሰኝ
ሕይወት በብርሃን ጨረሯ ባትጠቅሰኝ
እውነት በሌለበት በሰመመን ነበር ስንት አዱኛ የሚያልፈኝ !

©መቅደስ ሞገስ
The absoluteness of one's state
Expresses itself through contradiction..

የሚነካሽ አንድ ቃል አጣሁ
ብዙ ሐረግ አወጣሁ..
ሁሉም ነጠፈ
ሳይነካሽ አለፈ!

ብዙ የምልሽ ነበረኝ
ዝም አልሁ!
ተገለጠልሽ?


©ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል
Forwarded from Addis Powerhouse
Dear Feminist Fighters,

Let us make something romantic this February 14th - the safety and protection of female bodies.

Feminist Front is planning to publish a V-Day monologue based on your experiences with love, sexuality, and abuse. V-Day is an event aimed at ending violence against women and girls everywhere – and Feminist Front wants to co-create a monologue out of all the personal experiences you send to us. The stories you send can be anonymous – but will undoubtably show the beautiful, gruesome, scary, and sad experiences we have as Ethiopian women and help us love and heal collectively.

There are three guiding questions under the shared link and you are only expected to answer one. Your stories will go through an editorial process that will not affect the content in any way. As our V-Day monologue will be published on February 14, make sure to submit your story before February 11. Be part of this highly confidential valentine’s day project.


The Writer in you can save other women!


V-Day Monologue
Somedays
I’m done with poetry
Some days
Poetry is done with me
Some days it calls my name
And
My name stays quiet as if it doesn’t belong to me

©Everted
እጭ

እናቴን ለ9 ወር ያስታቀፍካት ዘር
ገረመኝ
እኔን ሆኖ ሲገኝ
ዘመን ጥላ እየጣለ
የእድሜ ተዳፋቱ እንደት ይነጉዳል
ቀን እንደት ያረግዳል?
ያው ለተራ እንቁላል ጣይነት ደደርኩ
ማስካካት ጀመርኩ
(ዘሩ በዙር ይቀጥላል )
ትላንቴ እኔን አህሎ ስትጨፈልቀው
የማህፀኔ በር የደም እንባ ተናነቀው
ጭን'ቅ እያስቀመጠኝ
ሲቃ እያስማጠኝ
እያስቧጠጠኝ
አመለጠኝ
....
በትግላችን መሀል
የያዝኩት እንቁ'ላል ደርሶ ተሰበረ
እንጭጭ እኔነቴ
እጭ ህይወት ነበረ

©ባንችአየሁ አሰፋ
#ባንችአየሁ_አሰፋ
👍1
Forwarded from Poetic Saturdays
ሠላም ሠላም ግጥማዊ ቅዳሜያውያን ወርሃዊውን የጥበብ ድግሳችንን ይዘን ብቅ ብለናል!
ከረጅም ጊዜ መነፋፈቅ በኋላ ቅዳሜ ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በፈንድቃ የባህል ማዕከል በአካል ተገናኝተን ናፍቆታችንን እንወጣ ዘንድ ደግሰናል፡፡

በአካል መገኘት አይችሉም? እንግዲያውስ በዙም ይቀላቀሉና!

ሊንኩም ይኸው! https://us02web.zoom.us/j/71147805916

እንደተለመደው ከ8 ሰዓት ጀምሮ ምዝገባችንን እንጀምራለን፡፡
አዳዲስ እና የራስዎን ፈጠራ ብቻ እንዲያቀርቡ ይመከራል
ለእያንዳንዱ አቅራቢ 5 ደቂቃ ብቻ ቢፈቀድም የፈለገውን ያህል ማቅረብ ይችላል።
ምንም አይነት የቋንቋ እና የይዘት ገደብ የለውም
ምንም አይነት የጥበብ ስራ ይበረታታል

ይምጡና የጥበብ ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ!