በአሁኑ የግጥም ሲጥም 'ራስ' ዲበኩሉ ጌታ ነው። 'የምድር ዘላለም' የተሰኘች ግሩም የግጥም ስብስብ መጽሐፍ አለችው!
ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።
https://t.me/GitemSitem
በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም
የ'ራሱ'ንም የራሳቸውንም ግጥም ሊያቀርቡ እንዲሁም ዝግጅቱን ሊያጥሙ የተዘጋጁት ደግሞ እኚሁላችሁ !
መቅደስ ሞገስ፣ ምትኩ ምድሩ፣ ሊያ አበበ፣ ልዩ ናቃቸው፣ ኪሩቤል ዘርፉ (ድሬ)፣ አናንያ ተሾመ፣ ቲና በላይ፣ ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል፣ ቃልኪዳን (Everted), ሻሎም ደሳለኝ፣ አስታወሰኝ ረጋሳ (አስቱ) እና ሌሎችም
ትጉንጬ ካፌ እና ሬስቶራንት /Tigunche cafe and Resturant
ካዛንቺስ ኢሲኤ መንገድ ከእፎይ ፒዛ ጀርባ
Kazanchis ECA road behind Efoy Pizza
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers

Forwarded from LinkUp Addis
Green Ethiopia will host an exhibition featuring eco-friendly businesses, entrepreneurs, creators and artists at Fendika Cultural Center on 16 January 2021. Doors will open at 10:00am. For more information contact +251 92914 3012. @linkupaddis
Download and enjoy the January 2021 edition of LinkUp Addis digital magazine: https://bit.ly/3hyyMxI @linkupaddis
Download and enjoy the January 2021 edition of LinkUp Addis digital magazine: https://bit.ly/3hyyMxI @linkupaddis
ዘላለም ናፋቂው
(በሻሎም ደሳለኝ)
በ2012 ዓ፡ም ከወጡ የግጥም መድብሎች ውስጥ "የምድር ዘላለም" የተሰኘው የዲበኩሉ ጌታ መጽሀፍ አንዱ ነው። መፅሀፉ 106 ያህል ግጥሞችን በ202 የገፅ ብዛት ላይ አስፍሮ ይዟል።
በመድብሉ ውስጥ ከቁጥር እንደተኳረፉ የጥንት ዘመን ሰዎች እድሜያቸውን ያላሰሉ ግጥሞች እንዱሉ ሁሉ የልደት ቀናቸው የታወቀ፣ የተቆጠረ፣ የተሰፈረ ድርሰቶችም አሉ። ተቆጠሩም አልተቆጠሩ ፣ ተሰፈሩም አልተሰፈሩ እድሜያቸው የትየለሌ ዘመናቸውም እስከ ዘለዓለም እንዲሆን ተብለው በደራሲው የተሸመኑ ናቸው። በጎጥ ያልታጠሩ ፤ በደም ያልሰከሩ።
"ማነህ መዝሙር ያለህ" የተሰኘው ግጥም ይሄን ሃሳቤን ያስረዳልኝ ይመስለኛል። ይሄ ግጥም ከ2005-2008 ዓ፡ም ድረስ ሲገመድ ሲበጠስ ፣ ሲቀጠል ሲበጠስ ቆይቶ እንካችሁ የተባለ ነው።
ዘመን - ድንበር የማይጋርደው ምስል
በቃሎችህ የምትስል
***
በዩኒቨርስ ሰማይ
እኩል የወጣህ ፀሐይ
ካለህ…አውጣው - ቅኔህ ይታይ…
ለአንድ ሉል
የሰው ዘር ውል . . .
የብርቱ ገጣሚ አገሩ የት ነው? ድንበሩስ? ምናቡ አይደለምን? ነው እንጂ! ገጣሚው መላዕክ ነው። ለመድብሉ ጥሩ ስም አውጥቶለታል ። አልያም ስምን መላዕክ ብቻ አያወጣም ፤ ገጣሚ ጭምር እንጂ። "የምድር ዘላለም"!
"እሱ" በተሰኘው ሌላ ግጥሙ ላይ እንዲህ ይለናል…
ህግ፣ ሐሳቡን ከዘላለም አቆራኝቶት
እየተራመደው ዘመኑን መች ደርሶት።
በስንኞቹ ልሳን ገጸ ሰቡ የሚተርክልን ሐሳብ ከዘላለም አቆራኝቶት "የቆመበቱ ወይም የመሻቱ ዘመን ላይ መች ደርሶበት" እያለን ይመስላል። ነገር ግን እሱ ሰም ነው ፤ ወርቁ "ወሰኔ ይህ ዘመን አይደለም ድርሰቴ ዘላለማዊነት ነው" የሚል ነው...

የፊታችን ቅዳሜ በግጥም ሲጥም 3 ላይ የአሁኑን 'ራስ' አጅበው ጥዑም ግጥም ከሚያቀርቡላችሁ ውስጥ ሁለቱ ፦ ምትኩ ምድሩ እና ቲና በላይ እንኋቸው!
ዛሬ ብሔራዊ ትያትር 11፡30 ጀምሮ ብትገኙ ደግሞ ምትኩ ምድሩን ለበጎ ዓላማ ግጥም እንካችሁ ሲል ታገኙታላችሁ።
https://t.me/GitemSitem
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #ምትኩ_ምድሩ #ቲና_በላይ #poeticsaturdays #Dibekulu_Geta #Mitiku_Midru #Tina_Belay #artinaddis #poetry #poetrylovers

አበባ ናት
ለጋ ቀንበጥ
በአረንጓዴ ዘንግነቷ
ከሩቅ የምትታይ
ውሃን ነሷት የምራቃቸውን ጠብታ እንኳ ነፈጓት !
ጠደቀች
አፈር ነሷት የምትደላደለበት
ጠደቀች
በውበቷ አሰማመረቻቸው
በፍቅሯ አቅበጠበጠቻቸው
እስትንፋሷን እፍፍ ብላ ህይወት ዘራች
የመጣችው በምክንያት ነው
ልታኖር
ያላኖሯትን
ልታደላድል
የጎረበጧትን
ፍቅር ሆነችላቸው
ህይወት ሆነችላቸው
ውበት ሆነችላችው
ሲሆንላት ፈክታ ፍንድቅድቅ ብላ
ደሞ እየጠወለገች እየሞተችም
ጠደቀች
እየረገፈች ጠደቀች
ሞቷም ውበት ነው::
ትገርመኛለች !!!
እውነቷን ያሠረችበት ዘመኗ ግን ብዙም አይደል
አጃኢብ እላለሁ ሁሌም ሳስባት !
©መቅደስ ሞገስ
#Mekdes_Moges #መቅደስ_ሞገስ #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers

ጭጭ ኡኡኡታ
ዝም ጭጭ
ምጭጭ
ፀጥ እርምም
እምምም
የተቆለፈበት በውሸት ተገፍቶ
የተገራረደ ድምጽነቱ ጠፍቶ
የተቸመቸመ ከንግግር እኩል
ታናናሽ ህመሞች በዝምታ 'ሚኩል
ስንትናስንት ቡራ ብዙ ሺ ከረዩ
ላንቃዬ ያልነካቸው ልሳኔን ያላዩ
እልፍ ኡኡታዎች መዓት ወዮ ወይኔ
ቃሌን እየፈሩ 'ሚደፍሩ የኔን ወኔ
አሸን 'ኤጭ ወደዛ!' ነፍ 'አልበዛም እንዴ?!'
አይሆንምን ከአፌ መቁረጥን ከሆዴ
ሰርክ እያዳፈኑ
ለእያሪኮ ይመስል የሚያጠራቅሙ
ከለሆሳሴ ላይ ጮኸው የሚሰሙ
ዝም ያሉ ጩኸቶች ድምጾቼን ለቀሙ
... ዝም እሪሪሪ !!! ... ዝም ኡኡ!
©ሰይፈ ተማም - ግጥም
©ሙኒት ተስፋዬ - ምስል
ዝም ጭጭ
ምጭጭ
ፀጥ እርምም
እምምም
የተቆለፈበት በውሸት ተገፍቶ
የተገራረደ ድምጽነቱ ጠፍቶ
የተቸመቸመ ከንግግር እኩል
ታናናሽ ህመሞች በዝምታ 'ሚኩል
ስንትናስንት ቡራ ብዙ ሺ ከረዩ
ላንቃዬ ያልነካቸው ልሳኔን ያላዩ
እልፍ ኡኡታዎች መዓት ወዮ ወይኔ
ቃሌን እየፈሩ 'ሚደፍሩ የኔን ወኔ
አሸን 'ኤጭ ወደዛ!' ነፍ 'አልበዛም እንዴ?!'
አይሆንምን ከአፌ መቁረጥን ከሆዴ
ሰርክ እያዳፈኑ
ለእያሪኮ ይመስል የሚያጠራቅሙ
ከለሆሳሴ ላይ ጮኸው የሚሰሙ
ዝም ያሉ ጩኸቶች ድምጾቼን ለቀሙ
... ዝም እሪሪሪ !!! ... ዝም ኡኡ!
©ሰይፈ ተማም - ግጥም
©ሙኒት ተስፋዬ - ምስል
👍1
The Human In Us
They think they have figured it out, Humans. They believe they have Deconstructed and traced back the universe and God himself to the origins.
Yet, look at them Enslaving others for a path of freedom. Creating chaos in the name of peace. Taking more lives in hopes they can reduce death...
All they do is Destroy themselves.
They gather in their circle of pity and mock another Circle of pity [So as I keep doing now..] They've made God Vulnerable, so lonely and insecure... smiling for the Heathen souls they killed and Getting angry at them for being happy.
They think they have figured it all out.
Yet all that's out there is contradiction.
In a world of change, I envy how some are willing to die for somethings that exist in just their minds.
But then I would die for You!
[Did I just contradicted my self?]
In the manner of contradiction God is more human than humans themselves!
https://t.me/thegreyspot
©ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል
©Markos
©Fasika Kebede

ተማፅኖ
አንተ የማላውቅህ ኃያሉ ዳኝነት - ገናናው ዝግ ሠሚ
በማትለይበት ሁሉን ዐካል የሆነክ፤
ብርሃን ጨለማን ዳር ድንበር አስማሚ፤
አንት የተምኔት ዐለም - ንጉስ ምናቤ ሆይ . . .
[ከበፊት ያልታዬ - ያልነበረን ዘር ግንድ]
እባክህን ችረኝ!
[አዎን———-]
አንዲት ቅንጣት ነገር
ትንሽ ሚጢጥ ሥልጣን
ሰውን፣ ከእግዜር ሰይጣን - ከራሱም ለማስጣል።
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
አንተ የማላውቅህ ኃያሉ ዳኝነት - ገናናው ዝግ ሠሚ
በማትለይበት ሁሉን ዐካል የሆነክ፤
ብርሃን ጨለማን ዳር ድንበር አስማሚ፤
አንት የተምኔት ዐለም - ንጉስ ምናቤ ሆይ . . .
[ከበፊት ያልታዬ - ያልነበረን ዘር ግንድ]
እባክህን ችረኝ!
[አዎን———-]
አንዲት ቅንጣት ነገር
ትንሽ ሚጢጥ ሥልጣን
ሰውን፣ ከእግዜር ሰይጣን - ከራሱም ለማስጣል።
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
We are so honored to have amazing poets like Kalkidan with us along side our headline poet Dibekulu Geta !!!
''I didn't grow up to be a poet because I loved the art. I am not a writer because I love spilling words. My writing experience never came from a loving place. It came from a place of need. A need to escape, to be alone, to feel out loud, to let go or to just talk to myself without labeling the process. I needed to talk to myself and listen to myself in return. I believe writing a single poem takes a lot of courage. It starts from revisiting your past and ends with acceptance, but a lot goes in between. There is a lot of feeling in there, from love to resent'' - Kalkidan
"poetic disruption through bold and uncensored self-expression''
-Everted
Check out her amazing poetry collection here at Everted https://t.me/Everted
#Kalkidan #Everted #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers

አዬ ሰው ጎስቋላ
አዎን...!
አውርተነው ነበር
ይህንን ሰውነት
ይህን የሞት እብለት!
ላይዙት ላይጥሉት
መሐላ እንዳለበት፤
ያው ሆነለት ያልነው
ገላ ላይ ሲያደርጉት
እንዶድም እድፍ ነው።
©ዲበኩሉ ጌታ
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
አዎን...!
አውርተነው ነበር
ይህንን ሰውነት
ይህን የሞት እብለት!
ላይዙት ላይጥሉት
መሐላ እንዳለበት፤
ያው ሆነለት ያልነው
ገላ ላይ ሲያደርጉት
እንዶድም እድፍ ነው።
©ዲበኩሉ ጌታ
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
Forwarded from #𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
ከፊል መልክሽ ዐይን ሸሽቶ
ግራጫ ላሁጫ ጠጉርሽ
ከሻሽ መሐል ሾልኮ ወጥቶ
እዛ ጥግ...
አንቺ
በግማሽ እየገባሺኝ
መረዳቴን በግማሽ መርሳት ልትረቺ
እያየሁሽ..
አስታወስሁኝ ዕለት
ከእቅፍሽ አንገቴ
ፀጉርሽ መሐል ፊቴ..
ነፍሴ ላይ ጠረንሽ
አንቺ - ዙሪያዬ
እኔ - ውስጥሽ....
መውደቅ ስንረታ ወድቀን
አሳላፊያችን ሲያልፈን
አስታወስሁ
ትዝ አለኝ
የረሳሁት ያልረሳኝ
ሳውቅሽ የማውቃት ሽበት
እንግዳ ነገር ትመስል
ከሌላው ዕለት ጎልታ ታይታኝ..
መቼ ማርጀት ጀመርሽ?
..
(ጠሩኝ
አልሽኝ..
ወዳሉበት
የምትወጃቸው
...ተ ከ ተ ል ሻ ቸ ው!
መንገድ ያህል ነገር
ያለስንብት
በእስትንፍስ ፍጥነት
ቶሎ
ጥድፍ
ክንፍ
አንዴ ተንፍሶ
መኖር ጨርሶ
...ቀድሞ ለመድረስ....
ጠሩኝ አልሽ
ጥድፍ
(አቤት እንደማለት...)
እፍፍፍፍፍ
ሸኘሁሽ ሄደሽ ከጨረስሽ...
መቼ ነበር ማርጀት የጀመርሽ?)
ከፊል አንቺ ጎኔ
ጠጉርሽ መሐል የኖረችን
አንዲት ሽበት እየቆጠርሁ
ጎንሽ እኔ..
ምን ያህል ዘመን እጅሽን ያዝሁ
ስንት ዕለታት ተቃቅፈናል?
ዘለዓለም ይሁን ሰከንድ
ከፍቅራችን በልጦ
ጊዜ እኛን ይመዝነናል?
ዛሬኣችን ላይ አድፍጦ ዕድሜን የተደገፈ
ጠጉርሽን እያየሁ በከፊልሽ ስደመም
መቃናችንን እየታከከ
ዘጠኝ ሞት መጣ ዘጠኝ ሞት አለፈ...
ትዝ አለኝ
እንግዳ ያላየሁት
እያየሁ የዘነጋሁት
ክንዴ መሐል ሆነሽ
ከኖርነው የበለጠ አዲስ
ረዥም ዕድሜ ወረሰሽ
መቼ አረጀሽ?
(...እዚያች
ከፊልሽ ያረፈችባት
እቅፌ መሐል የወደቅሽባት።
ወርደ ጠባብ መደብ ላይ ጥላ እየጣሉ
"አቤት" እና ስምሽ ተቀምጠዋል...
ያን 'ለት ዘጠኙ አለፈ
አሥርኛው ገባ...
ቤት ለእንግዳ!
በሚያልፍበት ቅጽበት
እንኳን ያልተረዱት
የሚያውቁት ይሆናል ባዳ
ደነቀኝ
እየፈካሽ ማርጀትሽ
መኖር ምልክትሽ
መዋቲ የመሆንሽ...
"አቤት!"
በእስትንፋስ ዕድሜ
ስትጀምሪ ማብቃትሽ
ያውም መንገድ ያህል ነገር
እስካሁን የነበርሽው መሄድሽን ነበር?
መቼ ጀመርሽ ማርጀቱን?
እፎይ!)
-----አስታወስሁ ያልሁሽ ትዝ ያለኝ
እንዲህ እየሆንሁ ነው!----
ከፊልሽ ካረፈበት መደብ
አንዱን ዕድሜ ብንተራሰው
እንግዳ ያላስተዋልሁት
እያየሁ የዘነጋሁት
ጠጉሬን ሽበት ወረሰው..
(ለግርምቴ ደግሞ ቀለሙ ያንቺን የሚመስል!)
ዕድሜዬን መቼ ኖርሁት
መምጫ ስጠብቅ እንጂ የሸበትሁት
አረጀሁ!
ቀትር - ጀንበር በፈካችበት
ጥላሽ ቤቴን ሞልቶታል
ከአንቺ ጋር የወሰደኝ
ዳግም ደጃፌን ይመታል...
(ምን ቀረው?)
ከፊልሽን መርታት ያቃተው ብርሃን ቤቴ ዘለቀ
(በሬን ማን ገፋው? ግባ! ቤት ለእንግዳ)
ግማሽ ጥላሽ ሞላኝ ከፊሌ ላይ ወደቀ!
አስታወስሁ ዕለት መዘንጋት ረሳሁ
(ከመ ጽጌ ረዳ መዓዛኪ ጥዑም
ዘያበርሆ ለጽልመት ገጽኪ ግሩም...
ዜማ ሆነሽ ፊቴ ሰፈፍሽ)
ተፈለቀቀ ከንፈርሽ
አሸበሸበ ከፊልሽ..
ስታዜሚ
ስትዜሚ
መዝሙርሽ ላይ ስሜን ሰማሁ
ከመኝታዬ ተራገፍሁ ከፊሌን ይዤ ተነሳሁ...
(እፎይ! በእስትንፋስ ዕድሜ
ልከ'ተልሽ!
ያውም
መንገድ ያህል ነገር
መጠበቄ መድረሴን ነበር!)
ተከተልሁሽ!
"አቤት ዓለሜ? ጠራሺኝ መሰል"
#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#𝖒𝖆𝖗𝖐 𝖔'𝖘
Forwarded from Jafer Books 📚
የገጣሚን በቃሉ ሙሉ " እኔና ክርስቶስ " የተሰኘው የግጥም መድብል ለንባብ በቃ ::
ግጥማዊ ቅዳሜን የሚያውቁ ሁሉ ማርቆስንና ጥዑም ግጥሞቹን ያውቃሉ። የተማረው ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ቢሆንም የሳይንስም የኪነ ጥበብም ሰው መሆንን ከታደሉ ጥቂት ጸኃፍት አንዱ ነው - ባለ ብዙ ተሰጥዖም ነው። 'እናንንብብ፣ እንወያይ፣ ነጻ እንውጣ' በሚል በንባብ ዙሪያ የማሕበራዊ ሚድያውንና መተግበሪያን በመጠቀም ለጸኃፊዎችን አንባቢዎችም ዘመኑን የዋጀ ስራ ለመከወን የተነሳው የ'ንበብ' ባልደረባ ነው።
ግጥሞቹን በዚህ እዩበት 👉🏾 https://t.me/thegreyspot
#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#ማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
ግጥሞቹን በዚህ እዩበት 👉🏾 https://t.me/thegreyspot
#𝖊𝖓𝖙𝖗𝖔𝖕𝖞
#ማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል #ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
Forwarded from LinkUp Addis
Gitem Sitem will host its third edition on Saturday 16 January 2021 from 4:00pm to 6:00pm. The event will feature Dibekulu Geta. The event, which will include poetic performances, music, food and drinks, will take place at Tigunchie Cafe and Restaurant (Kazanchis, Behind Efoi Pizza). @linkupaddis
ገጽ ቲዩብ በሚዲያ አጋርነት እገዛቸውን ስለለገሱን እናመሰግናለን! በንሸጣችን ከዋናው መሰናዶ ኋላ የተነሸጡ ገጣሚያን ስንኝ የሚማዘዙበት፣ ዜማና እንጉርጉሮዎች የሚፈሱበት የእሳት ዳር ጨዋታችን ላይ ታዳሚው ሁሉ አቅራቢ ይሆናል!
https://youtu.be/0MP7K_cPc24
https://youtu.be/0MP7K_cPc24
our surprise act for the third episode at Gitem Sitem
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers
#ዲበኩሉ_ጌታ #የምድር_ዘላለም #ግጥምሲጥም3 #ግጥማዊቅዳሜ #artinaddis #poetry #poetrylovers