ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ስህተቴ

ያለፈውን ትቼ ከአሁን ጋር ለመኖር
ከራሴ ስማከር
'አሁን' ጣዕም አለው ልብን የሚያሰክር
'አሁን' እውነታ ነው አለምን የሚያስር
ብዬ ፎከርኩና ትናንትናን ትቼ
ወደ ዛሬ መጣሁ ካለፈው ወጥቼ
የሰበሰብኩትን ሳልይዘው በእጆቼ
ግን በግዜ ቀመር ከቀደመው ሁሉ
ዕልፍ እና ዐዕላፍ ጥቅሞች ነበሩ
… … … ስህተት የሚባሉ

@seifetemam #seifetemam
👍1
ገራገር ገል

የተሰበረ ገል
ለጋ ገር ገራገር
ያልቦረቀ ግልገል
ካ'ለም ጋር ሲታገል
'ራሱን ያገኘው
በመከራ ነበር
መከራም ያጠናው
አልነቃም ሲነከር

ሰይፈ 2008
@seifetemam #seifetemam
መምጣትሽን ሳስስብ

ህይወቴ መምጣትሽ እኔኑ አምጥቶኝ
መምጣትሽን ሳስብ እኔው ነኝ የመጣሁ
ደረጃ ወልውዬ ኩሽናውን ኮሻኝ
እዚህ እሚያመጣኝ ፈልጌ እንዳላጣሁ
መምጣትሽን ሳስብ መምጣትሽ ተሰማኝ
አገር እንደሰጡት
አደብ እንደነሱት
ከሰማያት መርጠው አንዱን እንደቸሩት
ለዛውም በጥምቀት
እንዳሽሞነሞኑት
́ሚያደርገኝ ፍቅርሽ ሲመጣ ተሰማኝ
አቴጂበት ነገር ውጅንብር ጎዳና
ካይኖችሽ ታየቶኛል ያለሽበት ቀና
መጣሁ ስትይቀርቶ ሳትመጪም ነይና
መምጣቴን ላምጣልሽ ቀና በዪቀና
ስትመጪም ነይና ከከንፈርሽ ላውጋ
ስትመጪም ነይና አይንሽን አይኔጋ
ጣ́ምሽን ጣ́ሜ ጋ
ጎህ እስከሚናጋ
መምጣትሽን ሳስብ እንደዚህ ነው ሆዴ
መምጣትሽ አይደል ወይ መምጣትሽን መውደዴ


@seifetemam #seifetemam
መሄድሽን ሳስብ

ከህይወቴ መሄድሽ እኔን ግን አመጣኝ
ከፍቅር መዝገብ ላይ ሰው ሁሉ እንዳላጣኝ
መሄድሽ አልከፋም ፍቅር ላይ ካሰጣኝ
ማነው ያለው ሆዴ?
ከህይወቴ ስቴጂ ይጠፋል ወይ ገዴ?
ያላንቺ ተሳትፎ አይደምቅም መውደዴ?
ማነው ያለው ከቶ ኧረ ማነው እንዴ?
መምጣትሽን ሳስብ የፀዳው ደረጃ
ላንቺ ክብር ነፅቷል በያ በሱ ሂጃ
ሰው አለምድም አልል የነገን እኔእንጃ
መምጣትሽ ያመጣኝ መሄድሽ ያልገታኝ
የመውደድ ታላቁ የፍቅር ኩረጃ
ሆኜልሽ አለሁኝ
መሄድሽን ሳስብ መታነበር ያልኩኝ
ስትሄጂ ቀርቶ ሳቴጂም ነይና
መውደዴን ላስኪደው ቀና አርጊኝ ቀና
በሰማይ በምድሩ እንዳንቺ ባይኖርም
በሳር በቅጠሉ ስምሽን ባትምም
መሄድ አስደስቶት እግርሽም ቢያዘግም
መምጣትሽ ባነቃው ይህ ቀጥቃጣ ቀልቤ
መሄድሽ ሊያሰኬደኝ እጅግ ተቃርቤ
ስንብት በእጄ ፍቅርን ግን በልቤ
…..
መሄድሽን ሳስብ እንደህ ነው አንቺ ሴት
መሄድሽ አይደል ወይ ያረጋገጠለት
የኔም ልብ እንደሰው ፍቅር እንዳለበት


@seifetemam #seifetemam
መመለስሽን ሳስብ
(በ ሰይፈ ተማም)

'አሁን ይብቃን' ብለሽ ተነስተሽ ስትሄጂ
ልቤን መች ዘጋሽው በሬን ነበር እንጂ
አንቺ የሌለሽበት ይህ የሰብ ስብስብ
ምንም እንኳ ባይስብ
አብዝቼ እኖር ጀመር መመለስሽን ሳስብ
የቤቴ ደጃፉን ደረጃ ባፀዳ
አቆሽሾ ሂያጅ ነው አይዘልቅም እንግዳ
ኩሽናው ቢኮሸን
ኦልፍኙ ቢፈለኝ
ተመኝታው ላይ ነው እንቅልፌን የማገኝ
መመለስሽን ሳስብ መምጣቴ እየታየኝ
አይጠረቃም ሃሳብ ጭንቅላት ቦርጭ የለው
መጣች ሄደች ብዬ ያልሆነ ምራየው
መመለስሽን ሳስብ እንደው ቀድሞነገር
አለመሄድሽ ነው
ለልቤ ሚታየው

እግርሽስ ባዳ ነው ይመጣል ይሄዳል
ፍቅርሽን ወደድኩት መች ከልብ ይወጣል
. . . . . . . .
መመለስሽን ሳስብ እንዲህ ያረገኛል
መመለስሽን ሳስብ ባሳብ ይበልጠኛል
ያላጣሁት ልቤ እንዳዲስ ይገኛል


@seifetemam #seifetemam
እንኳን አደረሰኝ

ከሰማዩ ጓሮ መላክ የቀደሳት የውሃ ጠብታ
ከምድሩ ወለል የሰው ጥሬ እቃ የአፈሩ ሽታ
መሬቴን ሳጸዳ ሳሳጥብ ከርሜ ሳሳሽ በበረዶ
ክብሬን ሳንደባልል ባልነቃው ሃሳቤ ተሻግሮ ከማዶ
የመራስ ወራቴን አሳልፌው ኖሮ ቀን ጨረስኩ እያለ
በጉማጅ ወር አዝሎ ከነባዶ ቤቴ ልቤን ቀንላይ ጣለ

. . . እንኳን አደረሰኝ!

እንኳን አደረሰኝ እያወዛወዘ ደሞ እያገጫጨኝ
አመት አለሁ ብሎ አመት እያሸሸኝ

ውስኪ በብርሌ ብርንዶ በካቻፕ አደይ በግራፊክስ
ቤት ሆኜ ቤት ጠፋኝ ቤት መምቻዬን ሳስስ
ቤት ሆኜ ቤት አሻኝ ደግሞ ቤት መቀለስ
ልጆቹን በትኜ ከመስኩም ከወንዙ ከጫካው ከጨፌ
በረጠበ ሙዳይ ትንሽዬ ተስፋ ከቀን ላይ ጨልፌ
እጠባበቃለሁ 'አበባ አየሁ' የሚል ለማበብ ነጥፌ

አመት አለሁ ብሎ አመት እያሸሸኝ
እያወዛወዘ ደሞ እያገጫጨኝ
እን ኳን ደረሰብኝ እንኳን አደረሰኝ

@seifetemam #seifetemam
👍1
የአዲስ ቀን አብሳሪ ለብሩህ ተስፋ ዘማሪ የእንቁጣጣሽ ለዛ እና ጣእም ያለው የስንኝ ቋጠሮ በ @Seifdman ስማችሁን አክላችሁ ላኩልኝ ግጥም ሲጥም ላይ በብዙ ሰው የተወደደው የ15 ብር የሞባይል ካርድ ይሸለማል። ብዙ ሰው የ👎 ምልክት የሰጠው ደሞ የ5 ብር ካርድ ያገኛል ። እስቲ በአሉን አድምቁት ። እንኳን አደረሳችሁ!
እሺ..... እስካሁን ምንም ባለመቀበሌ ሽልማቱን ለማሳደግ ተገድጃለሁ ለ'👍' 25 ብር ለ'👎'ግን እዛው 5 ። በሏ....!
እንቁጣጣሼ የኔ በአል
እጓጓልሻለው እንደ እንቁላል

ቅድስት በ.
እባካችሁ ድምጽ በመስጠት የ👍 አና የ👎 አሸናፊዎችን እንለይ
መልካም የበአል ቀን ለሁላችሁ ። ውድድራችን 10 ሰአት ላይ ያበቃል ።
አበባዮሽ ስል ለምለም በል ደሃ
ብንሸለም መብራት ብንሸለም ውሃ

ፍሰሐ ተ.
4 👍 4 👎 ቅድስት እና ፍሰሐ እየመሩ ነው
ዘመነ... በድጋሚ

ከአመራሩ ተባልተን
ከየጎረቤቱ ተዋርፈን

ሳሙና መምጠጥን
ለምዶ ገላችን
በመጋገሪያ ዕጦት
ተደፍቶ ሊጣችን

የዘር ሀረጋችን
ሰፍሮ ከመታውቂያችን
በበላይነት ስሜት
ታመን በዘር ምጥ በሽታ
.
.
.
እንኖር ይሆን ፤ እንኖር ይሆን
በዘመነ ማርቆስ
ዘመነ...በድጋሚ


በረከትአብ ፍ.
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በዚህ አመት ደግሞ ሌላ ውድድር አዘጋጅቼላችኋለሁ በማንኛውም ርዕስ ላይ የተጻፈ የራሳችሁ ግጥም ። format: ርዕስ ፣ ግጥም ፣ የጸሃፊ ስም መልካም ዕድል!!! የሽልማቱን አይነት እና መጠን ከነገ ወድያ አሳውቃለሁ ። ልብ በሉ ተሸላሚ የሚሆነው በብዙ ሰው የተወደደው ብቻ ሳይሆን የ 👎 ምልክት የተሰጠውም ጭምር ነው ። ለመላክ @seifetemam የሚለውን በመጠቀም በቀጥታ አድርሱኝ ። በድጋሚ መልካም በዓል!!!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ጥንብ አንሳ

በዘመነ ጥንባት ሰው ከሰው ተሻትቶ በረከሰበቱ
ብዙኃን አሉና ሰውነታቸው ውስጥ ሞተው የሸተቱ
ወይ ልብህን አንፃ ሙታኑን ቀስቅሳ
ወይ ሆድህን ሙላ ሁንና ጥንብአንሳ

@seifetemam #seifetemam
👍1
እሺ እንዴትናችሁልኝ? አዲሱ አመት አያያዙ የተመቻችሁ ይመስላል ። የግጥም ውድድራችን ተጀምሯል እስከ እሁድ አስር ሰዓት ይቆያል ። ግጥማችሁን በ @Seifdman አድርሱኝ ። ከመሳተፍ ማንበብን የምትመርጡ ከሆነ ለ 👍 እንዲሁም ለ 👎 በመምረጥ አሸናፊ ግጥሞችን እንለይ ። በድምጽ የተቀዱም ካሉ እቀበላለሁ ። መልካም ውድድር ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በዚህ አመት ደግሞ ሌላ ውድድር አዘጋጅቼላችኋለሁ በማንኛውም ርዕስ ላይ የተጻፈ የራሳችሁ ግጥም ። format: ርዕስ ፣ ግጥም ፣ የጸሃፊ ስም መልካም ዕድል!!! ልብ በሉ ተሸላሚ የሚሆነው በብዙ ሰው የተወደደው ብቻ ሳይሆን የ 👎 ምልክት የተሰጠውም ጭምር ነው ። ለመላክ @seifetemam የሚለውን በመጠቀም በቀጥታ አድርሱኝ ። በድጋሚ መልካም በዓል!!!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼