ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
አቋራጭ

የኔን መጥፎ 'ሚሻ መሆኑን እያየሁ
እንዴት እንደራሴ ጠላቴን ልውደደው
… ይልቅስ…
ከቃሉ እንዳልወጣ እንዳይቀየመኝ
እራሴን ጠልቼ ጠላቴን ባልወደው
አቋራጭ መሰለኝ

ሰይፈ ተማም 2004
#seifetemam #አቋራጭ
ምርጫ
====
ቤት ሥራ ፤ ተፈንከት
ምርጫው የራስህ ነው ድንጋይ ሲወረወር
አናትህን ስትባል ግንባር እየሰጠህ ሕይወትህን ማማረር?
ወይ እየጠራረብህ በልክ እየሰተርህ ግንብህን ማበጀት አጥርህን መደርደር

#የጌታነህ_ልጅ
ነሐሴ 2009
ባንቺ መንቃት

ፈዝዘሃል አትበሉኝ ነቅቻለሁ በጣም
ከዓይኔ 'ሚገባ የሚታይ ሰው ባጣም
ስለሷ አስባለሁ እጅጉን ታትሬ
መኖሯን ለከርሞ ማደሯን ለዛሬ

#seifetemam
ሃሞተ ቢስ ጀግና

ዛሬ አዲስ አባ ውስጥ
ብዙ ሰው መሮታል
አፉ ሬት ሆኖታል
የሚጠጣው ድራፍት
መሪር እንደጅኑ
እንደጠላው ሁሉ
የሚበላውም ጫት
መሪር እንደኑሮ
የሚጣፍጥ መርሮ
ይህን ጀግና ትውልድ
እንደው በለበጣ
ሃሞተ ቢስ አሉት
ሃሞት እየበላ
ሃሞት እየጠጣ

#seifetemam
Forwarded from ቶኔቶር
ውዴ ፦
እንደኔ ያለ አፍቃሪ
እንደኔ ያለ ፈሪ
ቃላት ካፉ ጠፍቶ
ሚናገረው አጥቶ
ለፍቅር እጁን ሰጥቶ
ጉልበት ተቀምቶ
ስርሽ ተጎልቶ
ዐይን ዐይንሽን ሲያይ
ቀናት በጊዜ ቦይ ዘመን ሆነው አለፉ
ጨረቃና ፀሐይ በቀን ተቃቀፉ።
አጠገቤ እያለሽ ከዘመናት ርቀሽ
ጠፈር ሆነሽ ሰማይ
ምስልሽን ስጠብቅ አንጋጥጬ ወደላይ
ቀኑን አጨልመው ጉዳቸው እንዳይታይ
ከንፈር ይጋራሉ ጨረቃና ፀሐይ።

@TONETOR
@TONETOR
@TONETOR
ፍቅርና ደሞዝ

ስራ ተቀጥሬ ከዋክብት ቆጠራ
እጅግ አደከመኝ እንዴት ብዬ ልስራ
ቆጥሬ ቆጥሬ እየተምታታብኝ
አልሰራህም ብለው ደሞዝ ከለከሉኝ
ስራዬ ፍቅር ነው ከዋክብት ውበቷ
ደሞዜም እሷው ነች በጄየገባች ለታ
(ለ...)
ሰይፈ ተማም 1996
ድምጽ፣ ሽታ፣ ጣዕም

ምስኪኑ ሰአሊ በወጠረው ሸራ
የሳላት ጉራንጉር የሳላት መንደሯ
ድምጽ የላትም ጭራሽ
ምኗም አይሰማም
ድምጽ ቀለም ሆኖ ከሸራው ላይ የለም
እነማማ እንትና ሰውን ሲቦጭቁ
እነ ጋሽ እከሌ አዳልጧቸው ሲወድቁ
ወይዘሮ እከሊት ጠበል ሲጠድቁ
የተሰማው ሁሉ የለም ከቀለሙ
የተጠጣው አቦል ከየት አለ ጣ'ሙ
ከየት አለ ሽታው የቡናው የጣኑ
ድምጽ ሽታ ጣዕም
በቀለም አይወጡም
በብሩሽ አይሰፍሩም

ወይስ
አይን የለም እነዚን ለማስፈር ከሸራ
አይን የለም እኒህን ለማየት ከሸራ
ምስኪኑ ሰዓሊ የሳላት መንደሯ
ስንቱን እንዳወጣች ስንቱን ነገር ቀብራ

ወይም
ድምጽ ሽታ ጣዕም ከዚህ ሰፈር የሉም
አይሰሙ አይሸቱ ጨርሶም አይጥሙም
እንደድሮ አይደሉም
ወይም...

ወይም ይጮሃሉ
ወይም የገማሉ
ወይም ይመርራሉ

ድምጽ ሽታ ጣዕም ኑሮነን እያሉ
ባለመሳል መስመር ሁሌ እየተሳሉ

#seifetemam #ድምጽሽታጣዕም
ለአከራዬ ልጅ

መብራት የጠፋ ለት ሻማ ስታበሪ
ጥላሽን አየሁት ልብስ ስትቀይሪ
ልብስ የምታጥቢም ለት ጨምረሽ ከሳፋ
(መብራትስ ሁሌ ይሂድ ውሃ ግን አትጥፋ)
ጦረኞቹን አየሁ ሲሉ ቀና ደፋ
ቀና ደፋ እያልኩኝ ስሰራ የምታይ
እንዳያልፍብኝ ነው የናትሽ ቤት ኪራይ
ቤት ኪራይ ፍለጋ ጊቢያችሁ ስመጣ
አንቺን ብዬ ከፈልኩ ቤቱስ አያዋጣ
አያዋጣም ከቶ 'ማይከለል መስኮት የማይዘጋ በር
እናትሽ ሲወጡ ካልመጣሽ በስተቀር


#seifetemam #አሁን
@seifetemam @seifetemam
አቻ

ቃላት ሳታረቁ
ነገር ሳታደቁ
ያላቻ ጋብቻ
ይቅር ብሎ ብቻ
አቻ ደሃ አጥተን
ይኸው ቆመን ቀረን

ሰይፈ ተማም
2007
#seifetemam
Forwarded from ቶኔቶር
Seife Temam:
አቻ

ቃላት ሳታረቁ
ነገር ሳታደቁ
ያላቻ ጋብቻ
ይቅር ብሎ ብቻ
አቻ ደሃ አጥተን
ይኸው ቆመን ቀረን

ሰይፈ ተማም
2007
#seifetemam


@TONETOR
@TONETOR
@TONETOR
አበቦቹ

ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች
የብራ አለም ሰዎች
የንጹህ አገር ዜጎች
ለሃሴት አፎቱ
ለፍቅርም ቤቱ
ውበት ምልክቱ
. . . ትናንሽ አበቦች. . .
እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ
እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ
ውስጠትን ሰርሳሪ
በውበት አሳሪ. . .

እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ
እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ
ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ

(ለልጆቻችን. . .)
#seifetemam
@seifetemam
የኔ ክረምት

የከረረን ጽልመት
በምናቤ ሳክም
በከረረ ክረምት
በነጠላ ሳዘግም
ጽልመቱም አልነጋ ክረምቱም አልባተ
ልቤን ከገላዬ መለየት አቃተ

@seifetemam
#seifetemam
👍1
አንዷ መንገድ

አንዲት መስመርብቻ
በዓይኔ ፊት አለች
ደሞም ከሷ ውጪ
ችክችክ እና ድልዝ
ለንባብ አይመች
ይቺ ደማቅ መስመር
ይቺ ደማቅ መንገድ
እራሷን ዘርግታ
ወደራሷ ምትወስድ
እራሷን አንድዳ
ነድዳ ‘ምትማገድ
ይኧው ከሷ ውጪ
ቅዠት ነው ድንብርብር
ሰልፍ የሳተ ጉንዳን
የማይቀድስ ደብር
ጭስ የሌለው እጣን
የሚያሳስቅ ቀብር
የሚታለም እውን
የሚላፋ ነብር

እውነትን ፈለኳት
እንኋት ደማምቃ
አየኋት ሳልለፋ
በመስመሯ መጥቃ
በጉልህ ተጽፋ

ማተርኩ ወደ ፍቅር
ትታያለች ዘልጋ
ክረምቱንም በጋ
ሌሊቱን ቀን አርጋ
መስመሯን አፍቅራ
ፍቅር መስመር ፈጥራ

ባ’ለም ካለው ሁሉ
በጎውን ተመኘው
በአንድነት አንድ ሁኖ
አንዲት መስመር ላይ ነው
ከዛች መስመር ውጭ
ሁሉ ችክችክ ሁሉ ድልዝ
ለንባብ አይመች
እውን አልባ ውጥንቅጥ
የ’ልም አለም አደንዛዥ
ያለ መስሎ ሚያጥጥ
ሰው በቁም ‘ሚያስቃዥ
ያባይ ስጋ ቅጥቅጥ
የበረሃ ሚራዥ
2008
@seifetemam #seifetemam
Forwarded from 🤴ⒾⓁⒶ via @like
...ብዕር ለ ግጥም

እጆች ሁሉ ይፅፋሉ
ዓይኖች ሁሉ ያነባሉ
ጆሮዎች ሁሉ ይሰማሉ
Join ያርጉ
https://t.me/joinchat/C_70PQ0-ZY4kCH214gXV2Q
Seife Temam:
እንዋዋል

ስንቱን ውሎ
ስንቱን አዳር
ስንቱን ፍቅር
ስንቱን አሳር
ስንቱን ገድለን
ስንቱን አስረን
ስንቱን ቀብረን
ስንቱን አምነን
በአንዲት ቅጠል እንጠለል
ከማን አብረን እንገንጠል
ከማን እንሂድ ከማን እንዋል
ማን ይፈርም እንዋዋል?

@seifetemam #seifetemam
አወይ አንቺ አወይ እኔ

አንቺ ማለት’ኮ የሌሊት ጨረቃ
ሰስቼ የማይሽ እንደ ድንቡሽ ጮርቃ

… አንቺ ማለትማ የቀትር ፀሃይ
ደፍሬ ‘ማላይሽ ያላንቺም አላይ

..እያልኩኝ ሳወድስ እኔ ማለት ለካ
ምድጃ ሟቂ ነኝ
የነደደ ክሰል ባመድ በተተካ

@seifetemam #seifetemam
ኋላ የቀረን ኋለኞች

“ፊተኞች ኋለኞች … ‘’
ልክነው አምነናል
ከፊት የነበርነው
ከኋላ ቀርተናል
ግና ይህ ሰልፍችን
ምነው ግፉ በዛ
መጨረሻ ስንቆም
ፊት አንሆንም ‘ሳ

@seifetemam #seifetemam
2008