ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ግጥም ሲጥም በመጫን ላይ ነች . . . 20 %
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2013

Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም loading . . . 20%
December 19, 2020
Poetic Saturdays finalizing installation . . . 90% completed

#ጥዑምግጥም #ግጥምሲጥም #ሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #gitemsitem #poeticsaturdays #poetry #artinaddis #poetryinaddis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
What lights us is within!

Thank you for the beautiful fire taken from the very first edition of Gitem Sitem's event @Do1iy
Forwarded from ማረፊያ ጥበብ

***
የሕይወት ሙቅ ትንፋሽ
የ'ለት ተ'ለት ሐሴት፣
ኹሌም ከመኖር ነው
መቼም አይፈልቅ ከሞት።

መኖር የኹሉም ሥር
ኅላዌ የጣ'ም ጫፍ፣
መሰንበት አልፋ ጌጥ
ውሎ አዳር - የኢንፊኒቲ አጽናፍ፤
ደኅንነት እሩቅ ስም
የውበት ዳርቻው - ዖሜጋዊ ምዕራፍ፤
ከመሞት ፈጽሞ -
ከመኖር መዝገብ ነው - የሰው ክብር ሚጻፍ።

"ተዋርደህ ከምትኖር - ሙተህ ክበር" ማለት፣
"ስለ'ኔ ተሰቀል - ስላንተ ልተርት!"
የሚል ነው ትርጉሙ - የብልጥ ዐይን ስብከት።

*

"ለእምነት ለአስተዳደር"
"ለወንዝ ለደንበር"
"ለጣዖት ለወገን...፣"
ቁመት ክብር ተብሎ፣
የተመረተው ሞት
ሰው በሰው ተታ'ሎ፣
[ከሥር ከመሰረት
ከፍጥረት ጀምሮ፣
ላይጠረቃ ርዕዮት
እስካ'ሁን ዘንድሮ፣...]
ሲገለጥ በታሪክ
ሲደመጥ በእሮሮ፣...
እኩል ሰው ነው ሚነድ
ልዩ ላልሆነ አዳም
አንዳንዱ በእብሪት - ለ'ራሱ ስም ፈጥሮ።

ቤዛ ልትሆን አንተ
ለጌቶች ቅብጥ ሕይወት፣
'ሳት ለብሰህ በ'ሳት ላይ
ስትላክ ወደ ሞት፣
"ለምን!?" በል ትሑት ሰው
ጠይቅ ለአንድ ጊዜ "እንዴት?!"
ሰው እስካላመፀ - አይቆምም የሰው ሞት።

ዲበኩሉ ጌታ ከምድርዘላለም
ግጥም ሲጥም አሁንም በመጫን ላይ ነች . . . 65 % ተጠናቋል
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2013
Gitem Sitem - ግጥም ሲጥም loading . . . 65% Completed
December 19, 2020

የአሁኑ 'ራስ' ማን ይመስላችኋል? (የምታውቁ🤫) እነማንንስ እናመጣለን? አብረን እንከታተል!

ያለፈውን ያጣማችሁልን የዕለቱ 'ራስ' የነበረው Migbar Siraj እንዲሁም
Seifu Worku Andu Getachew ኤልያስ ሽታኹን Rosie Shita Lella Misikir ቃለአብ አባይነህ Rekik Asegidew Yohannes Lakew Adomia Fekede ወይኔ ጉዴ ያልተጠቀሰ ባልኖረ ... ያቀረባችሁ፣ ያጣማችሁ ሁላችሁም እጅግ ተመስገኑልን!! የደገፋችሁን፣ የታደማችሁልን፣ ሃሳብ ያቀበላችሁም ምስጋና ይድረሳችሁ!!

https://t.me/seifetemam

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም2 #artinaddis #poetry #poetrycommunity #poetrylovers #poetsinaddis
👍1
እንሆ የህዳር ወር የግጥም መጽሔ

በቀጣይ መጽሔታችን አሁንም የእናንተኑ ስራ እንጠብቃለን።

shorturl.at/duyO9 ገብታችሁ እዩልን፣ አውርዳችሁም የራሳችሁ ልታደርጉት ትችላላችሁ - ለሌሎችም አጋሩልን። አይታችሁ ስታበቁ አስተያየት አቀብሉን።

ግጥማቸውንና ምስሎቻቸውን እያቀበሉ ወሩን ላደመቁልን ሁሉ ምስጋና ይድረስ!!!
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #የግጥምመጽሔት #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
#gietmsitem #poeticsaturdays #artinaddis #poetrybooklet

Cover Photo Credit: Hermela
በሁለት ቋንቋ ላይ የምትሰለጥን ሰናኝ - እቴናትን እወቁልንማ!

We present to you the poet of two languages, Etenat

#እቴናት_አወል #Etenat_Awol #ግጥምሲጥም #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #አንዱ_ጌታቸው #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis #poetrybooklet
Forwarded from Poetry ሲጥም
ፌስቡክ ላይ ያለው የሲጥም ግሩፕ አንድ ትልቁን ተሻግሯል! እዛም ሰፈር ያላችሁ ጎራ በሉ - ተቀላቀሉ!
ይህን ባለ ብዙ ተሰጥዖ (ሰንካኝ) ተዋወቁልን!

ቴዲ ዝግጅታችንን በራሱ ቀለም ሊያጥም ቃላቱን ከሽኖ አቀራረቡን አስውቦ ተቋደሱ ሊላችሁ ነው!

#ቴዎድሮስ_ወንድምአገኝ #የኔ_አለም #ግጥምሲጥም #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #አንዱ_ጌታቸው #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #Tewodros_Wondimagegn #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
መንቢ ከጥዑም አቀራረቧ ጋር ዝማሬዋን ከንባብ ንባብዋን ከዝማሬ የማትነጥል ሰናኝ ነች! በተለያዩ መድረኮች ላይ የምታውቋት በእኛም ላይ አግኟት እስካሁን ካላወቃችኋት ግን እንኋትላችሁ!


#መንበረማርያም_ኃይሉ #ግጥምሲጥም #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #አንዱ_ጌታቸው #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #Menberemariam_Hailu #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
...👓
.
የሚያምር ነገር _ለምን ይሞታል ?
የቀረኝ ስባሪ ልብ ነው
ያጣሁሽ ዓይኔ ተሸፍኖ ሲገለጥ
ባለ ቅፅበት - ባለ ቅጥፈት ነው ።
.............
የቡና ፍቅሬን
የጠላ ፍቅርሽ ያህል ብንዋደድ _ብዬ አሰብኩ
ስንለያይ _ እንደ ውሻ አፍንጫ ቀዘቀዝኩ ።
...
ህመሜ እስከማትወጂ ድረስ የወደድሽ ነገር
ትግሌ ነበር ውስጥ እንደልከትሽ ነበር ።
..
አውቃለሁ ግማሽ ሞት ነው _ መርጦ ማሞገስ
አውቃለሁ ግማሽ ሞት ነዉ _በጋራ መውቀስ
ታውቂያለሽ በጣም ረዥሙ መንገድ _ ወደ ኃላ መመለስ ።.
.
.(ወየው .....
ምኞታችን ከግብ _ ግባችን ከስራ አልገጠመ
በርግጥ መውደቅ _ ሁለተኛ ስማችን ሆኖ ቀጠለ ።
.
#1ዱ (2012)


#አንዱ_ጌታቸው #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤ #ግጥምሲጥም #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
Meet this Drum addict, Fitz who loves playing drum since childhood. Though he was a reserved and shy kid, he used to express his thoughts through arts, he loves to sketch, sculpt, and drum. He studied architecture, which he considers as one stream of art.

#ፍጹም_አበራ #ግጥምሲጥም #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #አንዱ_ጌታቸው #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #Fitsum_Abera #Djembe #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
የገጣሚ ነፍስ

የገጣሚ ነፍስ፣
ከእውር መንፈስ ነው ጥሏ፣
ከጽጌሬዳ ውበት ይልቅ - ስለ እሾኋ ሲዘምር።
የገጣሚ ነፍስ፣
ከቆሰለ ቀን ነው ጥሏ፣
የሠይፍን መሳል - ለአፎቱ ሲነግር።
ከመፀው ነፋስ ነው ጥሏ፣
በፀሐይ ብርሃን -
የጧፏን ጸዳል ሲሰርቃት፤
የገጣሚ ነፍስ ከአምላክ ነው ጥሏ፣
‘እውነት እኔ ነኝ።’ ሲላት።

የገጣሚ ነፍስ ከተረበበ ቅጠል ነው ጥሏ፣
‘’ዛፉ ላይ እናምጽ” ብላ፤
ከቆራጭ ስትመክር።
ከቸር መጽዋች ነው ጥሏ፣
ከማግኘት ጽዋ አጎንጭቷት ስጸክር።
. . . . . . .
የገጣሚ ነፍስ ከሁሉ ነው ጥሏ !
ከሁሉ !
. . . . . . . ከ. . . ሁ. . . ሉ. . . !

አንዱ ጌታቸው
ከባዶ ሰው በባዶ

#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
በጦቢያ፣ ሰም እና ወርቅ፣ ግጥማዊ ቅዳሜ እና ሌሎች በርካታ መድረኮች ላይ የምታውቁት ሰይፍሻ የበርካታ ጥዑም ግጥሞች ባለጸጋ ነው።

በብዙዎች እንደሚባለው መጽሐፍ ማሳተም እንደመውለድ ከሆነ ይህ ሰው የ 'ባዶ ሰው በባዶ ቤት' አዋላጅ ሳይሆን አይቀርም። መጽሐፏም ከአርትዖት እስከ መግቢያዋ ከዓይን ያውጣሽ እስከተባለላት ምርቃቷም የ'ርሱ ነች!

#ሰይፈ_ወርቅ #Seifu_Worku #አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis
ለሚኖሮት ማንኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያያት ወደ setaweetmovement@outlook.com መልክት በመላክ የሴታዊትን ቡድን ማግኘት ይችላሉ ፡፡
የዚህ ወር 'ራስ' Andu Getachew ባዶ ሰው በባዶ ቤት የተሰኘች ግሩም የሥነ-ግጥም ስብስብ አለችው። ግድ የላችሁም አንብቧት በዩቱብና ቴሌግራም በምስልና ድምጽ የተቀናበሩ ግጥሞቹንም እንድትቃኟቸው ተጋብዛችኋል!

https://t.me/AndugetachewDnd

https://www.youtube.com/channel/UCJI2mmHpHddlQJabYGekFEw

ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።

https://t.me/seifetemam

በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም

የ'ራሱ'ንም የራሳቸውንም ግጥም ሊያቀርቡ እንዲሁም ዝግጅቱን ጠዓም ሊዘሩበት የተዘጋጁት አጣሚያን ደግሞ እኚሁላችሁ !
ሰይፉ ወርቁ፣ ዲበኩሉ ጌታ፣ እቴናት አወል፣ ቴዎድሮስ ወንድማገኝ፣ መንበረማርያም ኃይሉ፣ ፍጹም አበራ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ ሰይፈ ተማም፣ ሳምራዊት ውለታው እና ሌሎችም

ትጉንጬ ካፌ እና ሬስቶራንት /Tigunche cafe and Resturant
ካዛንቺስ ኢሲኤ መንገድ ከእፎይ ፒዛ ጀርባ
Kazanchis ECA road behind Efoy Pizza

http://shorturl.at/blAUY

#አንዱ_ጌታቸው #1ዱ #ባዶ_ሰው_በባዶ_ቤት #ጥዑምግጥም2 #ግጥማዊቅዳሜ #gietmsitem #poeticsaturdays #Andu_Getachew #DND #artinaddis #poetry #poetrylovers