ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ሰው በሞላው ሃገር
ሰው ባረፈ ቁጥር ትንሽ እሞታለሁ
አገር 'ሚያሰድብ ያገር ሰው እያየሁ
በከሰሩ ቁጥር ትንሽ እረክሳለሁ
በሰከሩ ቁጥር ትንሽ አከስራለሁ
በረከሱ ቁጥር ትንሽ እሰክራለሁ
በከሰሱ ቁጥር ዶሴ አቀብላለሁ
ሰው በሞላው ሃገር
የሰው ያለህ እላለው

ሲመርቁኝ አሜን አልል
ሲነጅሱኝ የምነቅል
ስንቀለቀል የማልነድድ
ሳልለኮስ የምከስል

ሰው በሞላው ሃገር ያውም የረገፈ
አፈር ነካው ዘሬን ጸድቆም ተገዘፈ
ሃሳቤም ተምቧችሮ እልፍ ረፈረፈ
ሆዴም ልብ የባሰው
ልቤም ሆድ የባሰው
ሆኖት እያረፈ

ሰይፈ ተማም

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ሥራችንን በአዲስ መልክ ጀምረናል ሳይሆን አዲሱ ሥራችንን ጀምረናል።

አእምሮ: የበላውን የማይረሳ፣ ባላመጠ መጠን የማይደክም፣ ባመነዠከ ቁጥር የሚሰላ የሚጠነክር ነው፡፡ ሆድማ ላሽ ነው፤ ቅድም የበላውን ምጥን ረስቶ እንቶፈንቶ ሲያቀርቡለት ስልቅጥ ነው፡፡

ለዚህ ውለታ አይረሴ አእምሮ መጽሐፍትን ለራሳችሁ እንዲሁም እንደ ሀብል፣ እንደ ቀለበት አሸብርቆ ለወዳጅ እና ለዘመድ ለመስጠት ስትፈልጉ፣ እኛ አለን።

Book Bouquet/ የመጽሐፍት ጥምር
ለየትኛውም ዝግጅት መጻሕፍትን በስጦታ መስጠት ለምትሹ የመጻሕፍት ጥምር አዘጋጅተን፥ ሊደርስ የምትፈልጉበት ቦታ ላይ ለማድረስ ተዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ ነው፡፡

ለእንዲህ አይነት ሰው ምን መጽሐፍ ልስጥ ብትሉም፣ ግዴለም እኛ የሚገባቸውን እና የሚመጥናቸውን ዝርዝር አውጥተን እና ከእናንተ ጋር ተማክረን ለመስጠት ዝግጁ ነን፡፡

**ደራሲያን ወዳጆች ደግሞ ልዩ በደራሲያን የተፈረሙ፣ የተመረጡ መጽሐፍትን አዘጋጅተናል።

-ከአዲስ አበባ፣ በተጨማሪ
--ባህር ዳር እና አማራ ክልል አገልግሎት እንሰጣለን።
--ባህር ማዶም።

እዘዙን እንታዘዛለን

ታዘን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን!

በኢንቦክስ ጻፉልን።

በ0993514883 ደውሉልን።

_ _
የምስል ጥበብ ስነ-ግጥምን ስታውቃት. . . !
When photography meets poetry...!

@ribkiphoto

#ርብቃሲሳይ #ribkasisay
#ግጥምሲጥም #gitemsitem
°ሠው ሙሉ ትዝታ° ያይቆብ ነኝ -አታላዩ

እሱን ተደግፋ እሷን እንዳቀፈ
በወርቃማ ፍሬም በፎቶ ሰማይ ላይ ምስላቸው አረፈ
..
.
.
ይሔም ቀን አለፈ።
ከብዙ አመት ሗላ ጊዜ እሷን ነጥቆት
ትራስ እያቀፈ
ከግድግዳው ደረት ከሰቀለው ፎቶ
አይኑን አሳረፈ።
[መሽቶ ነበር]
ካፊያ ነበር ቀኑ
በታላቅ ፍርሃት
ጧቷን ይዞ ነበር ወደ ቤት ሲያቀኑ
የተውሶ ጃኬት አምሮ ለመታየት!
አዲስ ሚኒ እስከርቷ
ሳታየው በጣቱ ታጉን ያነሳላት ያነሳላት!
እሱ በተውሶ እሷ አዲስ ገዝታ
ፍቅራቸው ሲጀመር
ሲፃፍ በትዝታ።
ቀጠሮ ለማክበር የተለበሰው ጨርቅ
እርቃን ሊተያዩ ለደስታቸው ሳይወልቅ
(በመጀመሪያው ቀን።)
አንድ ሰው ጠራቸው ቆሞ ፎቶ ቤት ጎን
"አምሮብሃል " አለው
ፎቶ ይነሱ ዘንድ ተጭኖ አስገደደው
በደንገት ያየችው ኢሔ እንግዳ ሰው
-ቀናችው ያምር ዘንድ ጃኬቱን ያዋ-ሰው
እንደሆነ ነግሮአት
ካለፈ በሗላ የሳቀችለት ሳቅ
አሁን የሆነ ያህል በልቡ ሲደልቅ
አቤት አጋጣሚ አቤት ሬ
ከልብሶቹ መሃል ሲመረጥ ለዛሬ
እድለኛ ሲሆን
እሱን ተደግፋ እሷን እንዳቀፈ
በፎቶ ሰማይ ላይ በተውሶ ልብሱ ምስላቸው አረፈ
እሱን ተደግፋ እሱ እሷን አቅፎ
ከቀኖቹ መሃል ሳይሞት ይታየዋል ይሔ ቀኑ ተርፎ።( ገዝፎ)
እለቷን አሰበ
በዕዝነ ህሊናው የሃሊት ተሳበ
ተስፋ የገመደው
ያ ታላቁ ፍቅር በቀናት ሲከዳ
ትዝታ ትርፍ ሆኖ ፎቶ ይሆናል እዳ።
እንደ ጊዜ አምሮ እንደ እለት ያለፈ
ይሔ ውበታም ቀን
ከአራቱ ግድግዳ በአንደኛው ያረፈ
ፎቶ የለንም ወይ ተሰቅሎ የሚያን ዛሬን ያኮረፈ።
ደሞ ስንተውን
በሂወት መድረክ ላይ ድራማ ስንሰራ
ታዛቢ ካልሆነ ፎቶና ካሜራ
ሰው ድፍረት የለውም
ትናንቱን ዘጋቢ ዛሬ ስለሌላው ነገን የሚያብራራ
(ወይም)
ከትናት ቀኖች ውስጥ በስሜት በእውነት
ሊታረም የሚሻ ገጠመኙን ጥሎ
ዛሬ ታሟል ይላል በትናንቱ ቆስሎ።
በትዝታ ገመድ ለመሳብ ሲሞክር
ዐይን ጨፈን አርገው ሊያዩት የሚቸግር
ስንት ቀን ተሸኘ ከፎቶ ላይ ሳይቀር
በአይምሮ ነየሚኖር
ትዝታን መታመን አጉል ትምክህት ነው
ስንት ትውስታ አለ..? በስሜት ተረድተን
በምስል ያጣንው
እዛጋር ነበርን..
እዚጋ ነበር..ን
ለምን ወዲያ ሔድን
ለምንስ ወዲ መጣን.?
ምክንያቱ ምን ነበር ያወለካከፈን?
.
በቦታ በጊዜ ብልጭ የሚል ምስል
አቅ በፎቶ ላይ ሳይቀር
ከድሜ ጀንበር ደጃፍ ከምኔው ደረስን..?
ዓለም ነን እያለን ከዓለም እያነስን።
ሁሉም ጋር ለመኖር ቀን እንደባከንን
ያልኖርን ናፈቀን የኖርን አስተከዝን...
ሠው ሙሉ ትዝታ-ተነሳ በርጅና
ሊፅፍ ወደሃላ -ሊያለቅስ እንደገና

#ያይቆብ_ነኝ_አታላዩ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
Forwarded from Events Ethiopia (Events Ethiopia Bot 🤖)
Art Exhibition: "የጉንጉን ድሮች" / Threads of Fabric
📅 December 27, 2020
📍 Guramayne Art Center
🙏 Events

By Meron Hailu
Open till Dec-27
.
@eventsethiopia
Forwarded from ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem (S e i f e - T e m a m)
ስራቸውን በመድረክ ለማቀረብ ዕድል አግኝተው የማያውቁ ብቁ ገጣሚያንን ፍለጋ የዋጣ ጥሪ።

ግጥም ሲጥም በወርሃዊ የግጥም ዝግጅቱ ላይ በየወሩ ለሁለት ገጣሚያን ይህን ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ መሳተፍ የምትፈልጉ ገጣሚያን ስራችሁን በድምጽ ቀድታችሁ በ @seifdman ወይንም በ @Tominu ብትልኩልን ስራችሁ ልምድ ባላቸው ገጣሚዎች ተመዛዝኖ ይበልጥ ይጥማሉ ያልናቸውን እናሳውቃለን።

#ግጥምሲጥም
Forwarded from ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem (S e i f e - T e m a m)
A call for poets !

We are looking for amateur poets who deserve a stage.
Gitem Sitem is organizing a monthly poetry event. Each month, we give the opportunity for two upcoming poets if their sample work got selected by our experienced group of poets.

Please send us an audio through @seifdman or @Tominu and be part of our event.

#gitemsitem
Hurting Beat

the blood is coming out as if the valves loosing control the pain is beyond her body just like a sinner as if she do something wrong the ache keeps throbbing and make her hate being a girl at all the pain wont stop until the menopause, and will start again with different version , with different beat and applause .
✍🏾 Hayu

#Hayu #gitemsitem #poeticsaturdays
Forwarded from Poetic Saturdays
https://fb.me/e/ZNe979Zn

ሠላም ሠላም ጤና ይስጥልን ፣ ቅዳሜ ኅዳር 26 ቀን 2013 (ከቀኑ 10:00 ጀምሮ) የመስመር ላይ (ኦንላይን) ግጥማዊ ቅዳሜ እናስተናግዳለን! ይህ ምናባዊ የጥበብ መድረክ ለሁሉም ሰው ክፍት ነው።
"ዙም" ላይ ይቀላቀሉ ወይም በፌስቡክ ቀጥታ ይመልከቱን! ለማንበብ ፍላጎት ካለዎት አስቀድመው በውስጥ መስመር መልዕክት በመላክ ያሳውቁን፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ያለ ቋንቋ፣እድሜ እና ርዕስ ገደብ አምስት ደቂቃ ይኖርዎታል። እዚያው እንገናኝ!
https://us02web.zoom.us/j/71147805916
Passcode is 1234 (if asked)
Hey everyone, this Saturday, December 5th at 4pm, we will host online Poetic Saturdays! Virtual Poetry is open to everyone. Call in and join by Zoom or watch live on Facebook! If you're interested in reading, let us know beforehand or, if you join in on Zoom, send us a private message. As always, you'll have five minutes and we encourage all languages, all ages, and all topics. See you there!
https://us02web.zoom.us/j/71147805916
Passcode is 1234 (if asked)
የመንገደኛ ትርፍ
,
,
የቀዘፍኩት ታንኳ ያጎበጠኝ ቀንበር
ያቆሰለኝ እሾህ የመንገድ ላይ ጠጠር
የዘመናት ጅራፍ
ደሞ የታራክ ሰይፍ
አንጋጥጬ እያየሁ አሻግሬ ከሩቅ
ልቃ'ና በመንፈስ ወደ-ልዕልና
ወደ ሂዎት በራፍ
ትርጉምን በመሻት ከመኖር ብሰንፍም
በመንገድ ዛልኩ እንጂ
ስጋዬን አልፌ ካለም አልመነንኩም!

እቴናት አወል
@solemn_ly

#እቴናት_እወል #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅድሜ
So delighted that Fendika Cultural Center has been awarded the Prince Claus Laureate for 2020!!!! Congratulation & elelelelelelelele!!!!

Source: @artsmailinglist
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem pinned «https://fb.me/e/ZNe979Zn ሠላም ሠላም ጤና ይስጥልን ፣ ቅዳሜ ኅዳር 26 ቀን 2013 (ከቀኑ 10:00 ጀምሮ) የመስመር ላይ (ኦንላይን) ግጥማዊ ቅዳሜ እናስተናግዳለን! ይህ ምናባዊ የጥበብ መድረክ ለሁሉም ሰው ክፍት ነው። "ዙም" ላይ ይቀላቀሉ ወይም በፌስቡክ ቀጥታ ይመልከቱን! ለማንበብ ፍላጎት ካለዎት አስቀድመው በውስጥ መስመር መልዕክት በመላክ ያሳውቁን፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ያለ ቋንቋ፣እድሜ…»
ሠላም ሠላም ጤና ይስጥልን ፣ ቅዳሜ ኅዳር 26 ቀን 2013 (ከቀኑ 10:00 ጀምሮ) የመስመር ላይ (ኦንላይን) ግጥማዊ ቅዳሜ እናስተናግዳለን! ይህ ምናባዊ የጥበብ መድረክ ለሁሉም ሰው ክፍት ነው።
"ዙም" ላይ ይቀላቀሉ ወይም በፌስቡክ ቀጥታ ይመልከቱን! ለማንበብ ፍላጎት ካለዎት አስቀድመው በውስጥ መስመር መልዕክት በመላክ ያሳውቁን፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ያለ ቋንቋ፣እድሜ እና ርዕስ ገደብ አምስት ደቂቃ ይኖርዎታል። እዚያው እንገናኝ!

https://us02web.zoom.us/j/71147805916
Passcode is 1234 (if asked)

Hey everyone, this Saturday, December 5th at 4pm, we will host online Poetic Saturdays! Virtual Poetry is open to everyone. Call in and join by Zoom or watch live on Facebook! If you're interested in reading, let us know beforehand or, if you join in on Zoom, send us a private message. As always, you'll have five minutes and we encourage all languages, all ages, and all topics. See you there!

https://us02web.zoom.us/j/71147805916
Passcode is 1234 (if asked)

https://fb.me/e/ZNe979Zn

https://t.me/PoeticSaturdays