Forwarded from የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች via @like
Elias Shitahun:
(ከሚወጣው መድብል ቅምሻ
:
:
ካቲካላ የለም ፤ ከዛሬ ጀምሮ!
ለምን?
መለኪያው ተሰብሮ።
(ብለሽ
ደሞ መሸጥ ቀጠልሽ)
ጥያቄ!
መለኪያው ነው እንጂ የተሰባበረው፣
ካቲካላሽማ… በርሜሉን ሙሉ ነው።
ይሄንን ስትሰሚ
እንዳትገረሚ።
መኮመሪያ ቤትሽ ፣ መስፈሪያ የጣለ
ባገኘው ይ፟ለካል ፤ ያገኘውን ኹሉ ፣ ልኬት ነው እያለ፡፡
እረ ያንቺስ እውነት ፣ ልኩን ያሳጣሽው፣
በምን ለክተሽ ነው?
አንድ አረቄ እያሉ ፣ በርሜል የጨረሽው።
መለኪያሽን ዐየሽ ፣ ንቀሽው ተሰብሮ፤
በዋጋ ያጣላል ፤ ልክ የሌለው ኑሮ።
ለዋጋሽ መለኪያ፤
ለስካር መለኪያ፤
ለማወቅ መለኪያ፤
ለመኖር መለኪያ ፣ ጠፍቶሽ እንዳሰምጪ፤
አረቄሽን ዘግተሽ ፣ መለኪያሽን አውጪ፤
ተይ በልክ ቅጂ!
ቀጥ ብሎ እየገቡ ፣ ሲወጡ በዳዴ፣
በምን ሰጠሻቸው ፣ ሰከሩልሽ ባንዴ።
የአረቄሽ ሞገስ…
ሰው እየመሰለው ፣ ዐይኑ ደም ሲቀላ፣
ገ፟ዳም ናት ይልሻል ፤ ሰው ቤትሽ ሲሞላ።
ገድሽ መለኪያሽ ነው! የተሰበረልሽ፤
አትሰሰትም ብሎ ፣ ሰው የሚያመጣልሽ።
ሀገሬው ሀገርሽ ፣ ስስት ከመለካት ተደበላልቆበት፣
የሚለካን ኹሉ ፣ ስስታም የሚል ስም ፣ ወስዶ ለጠፈበት።
ተይ በልክ ቅጂ!
ማይለካ አረቄ ፣ እያደልሽው በገፍ፣
ሀገር ሰከረልሽ ፤ በምኑ ይደገፍ።
ተይ በልክ ቅጂ!
ጤነኛውስ ይኹን ፤ እብድ አታስብጂ፤
ተይ በልክ ቅጂ!
-------//////-------
ኤልያስ ሽታሁን
(ከሚወጣው መድብል ቅምሻ
:
:
ካቲካላ የለም ፤ ከዛሬ ጀምሮ!
ለምን?
መለኪያው ተሰብሮ።
(ብለሽ
ደሞ መሸጥ ቀጠልሽ)
ጥያቄ!
መለኪያው ነው እንጂ የተሰባበረው፣
ካቲካላሽማ… በርሜሉን ሙሉ ነው።
ይሄንን ስትሰሚ
እንዳትገረሚ።
መኮመሪያ ቤትሽ ፣ መስፈሪያ የጣለ
ባገኘው ይ፟ለካል ፤ ያገኘውን ኹሉ ፣ ልኬት ነው እያለ፡፡
እረ ያንቺስ እውነት ፣ ልኩን ያሳጣሽው፣
በምን ለክተሽ ነው?
አንድ አረቄ እያሉ ፣ በርሜል የጨረሽው።
መለኪያሽን ዐየሽ ፣ ንቀሽው ተሰብሮ፤
በዋጋ ያጣላል ፤ ልክ የሌለው ኑሮ።
ለዋጋሽ መለኪያ፤
ለስካር መለኪያ፤
ለማወቅ መለኪያ፤
ለመኖር መለኪያ ፣ ጠፍቶሽ እንዳሰምጪ፤
አረቄሽን ዘግተሽ ፣ መለኪያሽን አውጪ፤
ተይ በልክ ቅጂ!
ቀጥ ብሎ እየገቡ ፣ ሲወጡ በዳዴ፣
በምን ሰጠሻቸው ፣ ሰከሩልሽ ባንዴ።
የአረቄሽ ሞገስ…
ሰው እየመሰለው ፣ ዐይኑ ደም ሲቀላ፣
ገ፟ዳም ናት ይልሻል ፤ ሰው ቤትሽ ሲሞላ።
ገድሽ መለኪያሽ ነው! የተሰበረልሽ፤
አትሰሰትም ብሎ ፣ ሰው የሚያመጣልሽ።
ሀገሬው ሀገርሽ ፣ ስስት ከመለካት ተደበላልቆበት፣
የሚለካን ኹሉ ፣ ስስታም የሚል ስም ፣ ወስዶ ለጠፈበት።
ተይ በልክ ቅጂ!
ማይለካ አረቄ ፣ እያደልሽው በገፍ፣
ሀገር ሰከረልሽ ፤ በምኑ ይደገፍ።
ተይ በልክ ቅጂ!
ጤነኛውስ ይኹን ፤ እብድ አታስብጂ፤
ተይ በልክ ቅጂ!
-------//////-------
ኤልያስ ሽታሁን
የምስል ጥበብ ስነ-ግጥምን ስታውቃት. . . !
When photography meets poetry...!
@ribkiphoto
#ርብቃሲሳይ #ribkasisay
#ግጥምሲጥም #gitemsitem
When photography meets poetry...!
@ribkiphoto
#ርብቃሲሳይ #ribkasisay
#ግጥምሲጥም #gitemsitem
አስተምረኝ
( ሠይፈ ወርቅ)
አስተምረኝ - ከማዕበል ጋር መደነስ
አሠልጥነኝ - በእሳት ላይ መመላለስ
ስሬን አጥብቅ - እንድታጠፍ ለነፋሳት
ልቤን ግራው - ሲቀጠቀጥ እንዲከፈት
ከዶፍ
ከጎርፍ
ከጣይ፣ ከቁር
ከበረድ ጋር
ከውሽንፍር
ከመብረቅ ጋር እንድጨፍር
ውብ ህይወትን እንድዘምር
አስተምረኝ!
ያለነፋስ - ዋሽንት በድን
ሳይገረፍ - ክራር አይድን
ሳይመታ - ሙት ከበሮ
ለሰከነ - ለነፍስ ጆሮ
በህመም ውስጥ ተቀምሮ
ውብ ዜማ አለ በተፈጥሮ
አስተምረኝ
የማየትን ጥልቀት፣ ርቀት
አሠልጥነኝ
የማድመጥን ስር መሠረት
በሸለቆ
በከፍታ፣ በቁልቀለት
ህመም ሳልሸሽ
ያለህመም ልኑርበት
#አስተምረኝ።
#ምራኝ!
#ማረኝ!
( ሠይፈ ወርቅ )
#አስተምረኝ
#ሰይፉወርቁ #ሰይፈወርቅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
( ሠይፈ ወርቅ)
አስተምረኝ - ከማዕበል ጋር መደነስ
አሠልጥነኝ - በእሳት ላይ መመላለስ
ስሬን አጥብቅ - እንድታጠፍ ለነፋሳት
ልቤን ግራው - ሲቀጠቀጥ እንዲከፈት
ከዶፍ
ከጎርፍ
ከጣይ፣ ከቁር
ከበረድ ጋር
ከውሽንፍር
ከመብረቅ ጋር እንድጨፍር
ውብ ህይወትን እንድዘምር
አስተምረኝ!
ያለነፋስ - ዋሽንት በድን
ሳይገረፍ - ክራር አይድን
ሳይመታ - ሙት ከበሮ
ለሰከነ - ለነፍስ ጆሮ
በህመም ውስጥ ተቀምሮ
ውብ ዜማ አለ በተፈጥሮ
አስተምረኝ
የማየትን ጥልቀት፣ ርቀት
አሠልጥነኝ
የማድመጥን ስር መሠረት
በሸለቆ
በከፍታ፣ በቁልቀለት
ህመም ሳልሸሽ
ያለህመም ልኑርበት
#አስተምረኝ።
#ምራኝ!
#ማረኝ!
( ሠይፈ ወርቅ )
#አስተምረኝ
#ሰይፉወርቁ #ሰይፈወርቅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ታዳሚዎቹም አቅራቢዎቹም ወደነዋል፣ ጥሞናል፣ ድገሙንም ብለዋል!
የታደማችሁም ያቀረባችሁም ተመስገኑልን! መምጣት ሳትችሉ ብትቀሩም ድጋፋችሁንና ሀሳባችሁን የቸራችሁንም ክበሩ!
ቦታውን ሳታገኙት ቀርታችሁ መምጣት ያልቻላችሁ ደሞ ይቅር በሉን!
ቀጣዩ እንዳያመልጣችሁ ለታህሳስ 10 ቀጠሮ ያዙ ገጾቻችንንም ተከታተሉ
https://t.me/seifetemam
#ኤልያስ_ሽታሁን #ምግባር_ሲራጅ #አንዱ_ጌታቸው #ሌላ_ምስክር #ረቂቅ_አሰገደው
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
ህዳር 12 ከተካሄደው የመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ የተወሰዱ ምስሎች
📷 @AnimaHela
የታደማችሁም ያቀረባችሁም ተመስገኑልን! መምጣት ሳትችሉ ብትቀሩም ድጋፋችሁንና ሀሳባችሁን የቸራችሁንም ክበሩ!
ቦታውን ሳታገኙት ቀርታችሁ መምጣት ያልቻላችሁ ደሞ ይቅር በሉን!
ቀጣዩ እንዳያመልጣችሁ ለታህሳስ 10 ቀጠሮ ያዙ ገጾቻችንንም ተከታተሉ
https://t.me/seifetemam
#ኤልያስ_ሽታሁን #ምግባር_ሲራጅ #አንዱ_ጌታቸው #ሌላ_ምስክር #ረቂቅ_አሰገደው
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
ህዳር 12 ከተካሄደው የመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ የተወሰዱ ምስሎች
📷 @AnimaHela
https://www.youtube.com/watch?v=CZ_sjCXYiQ8
ይህን Amazing Addis የተሰኘ ቤት ብትከታተሉ ግጥሞችን እንዲህ ገጣሚዎቹ እራሳቸው አሳምረው ሲያነቡት ታገኛላችሁ እና እንጠቁማችሁ - ግቡ።
መታሰቢያ እታለማው በአሜዚንግ አዲስ
#መታሰቢያ_እታለማው #አሜዚንግ_አዲስ #ግጥምሲጥም
ይህን Amazing Addis የተሰኘ ቤት ብትከታተሉ ግጥሞችን እንዲህ ገጣሚዎቹ እራሳቸው አሳምረው ሲያነቡት ታገኛላችሁ እና እንጠቁማችሁ - ግቡ።
መታሰቢያ እታለማው በአሜዚንግ አዲስ
#መታሰቢያ_እታለማው #አሜዚንግ_አዲስ #ግጥምሲጥም
YouTube
ገጣሚት መታሰቢያ እታለማው " ተረት ተረት "
የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የኪነ-ጥበብ እና የባህል ባለሙያዎችን ለመደገፍ እና ለማጠናከር የሚረዳ አዲስ ከ3-5 ዓመት የሚቆይ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ለዚህም ዘለቄታዊነት ያለው እና ለእርስዎ ጠቃሚ የሆነ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የእርስዎን ጉልህ አስተያየትና እና ምልከታ እንፈልጋለን ፡፡
ስለሆነም ይህንን የዳሰሳ ጥናት በጥበብ እና ባህል ሙያ ዘርፍ ያለውን ተግዳሮትና ክፍተት ለማሻሻል ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ለማሟላት እርሶ መፍትሔ ይሆናል ብለው የሚሰጡንን ሀሳብና አመለካከት እያደነቅን ለትብብርዎ ከልብ እናመሰግናለን!
ጥናት (አማርኛ): shorturl.at/jtyK2
The Swedish government is developing a new 3-5 year-long programme to help support and strengthen art and culture practitioners in Ethiopia and we need your significant feedback and perspective to design a programme that has long-term impact and is relevant for You.
We would therefore very much appreciate if you could fill out this survey and provide your perspective on needs, gaps and possible solutions to improve your condition as an art and culture practitioner.
SURVEY (ENGLISH): shorturl.at/jmpyA
#survey #swidish #creatives #art #culture #ግጥምሲጥም
ስለሆነም ይህንን የዳሰሳ ጥናት በጥበብ እና ባህል ሙያ ዘርፍ ያለውን ተግዳሮትና ክፍተት ለማሻሻል ለዘርፉ የሚያስፈልገውን ለማሟላት እርሶ መፍትሔ ይሆናል ብለው የሚሰጡንን ሀሳብና አመለካከት እያደነቅን ለትብብርዎ ከልብ እናመሰግናለን!
ጥናት (አማርኛ): shorturl.at/jtyK2
The Swedish government is developing a new 3-5 year-long programme to help support and strengthen art and culture practitioners in Ethiopia and we need your significant feedback and perspective to design a programme that has long-term impact and is relevant for You.
We would therefore very much appreciate if you could fill out this survey and provide your perspective on needs, gaps and possible solutions to improve your condition as an art and culture practitioner.
SURVEY (ENGLISH): shorturl.at/jmpyA
#survey #swidish #creatives #art #culture #ግጥምሲጥም
Google Docs
ባህላዊ እና የፈጠራ ኢንደስትሪ በኢትዮጵያ
በ ሲዳ (የሲውዲን ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ) በተደረገልን እርዳታ በኪነጥበብና ባህል ዘርፍ ቁልፍ ከሆኑ የሲውዲን ሀገር አቀፍ ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የሲውዲን ኪነጥበብ እርዳታ ድርጅት ኮሚቴ ከ3-5 አመት የሚቆይና የኢትዮጵያን ኪነጥበብና ባህል የሚረዳ መርሃግብር እያጎለበተ ይገኛል። ይህም በዋናነት የሚተገበረው በኢትዮጵያ የጥበብ ማህበረሰብ የተለያዩ ተሳታፊዎች በማማከር ነው። የእናንተ…
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem pinned «የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የኪነ-ጥበብ እና የባህል ባለሙያዎችን ለመደገፍ እና ለማጠናከር የሚረዳ አዲስ ከ3-5 ዓመት የሚቆይ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ለዚህም ዘለቄታዊነት ያለው እና ለእርስዎ ጠቃሚ የሆነ ፕሮግራም ለማዘጋጀት የእርስዎን ጉልህ አስተያየትና እና ምልከታ እንፈልጋለን ፡፡ ስለሆነም ይህንን የዳሰሳ ጥናት በጥበብ እና ባህል ሙያ ዘርፍ ያለውን ተግዳሮትና ክፍተት ለማሻሻል…»
እወቂብኝ
ከማላቃቸው መልኮች ላይ ሳቆችሽን ዘግኛለሁ
ለራሴ
በልቤ መንገዶች ላይ በእግሬ ብዙ ተጉዣለሁ
ለነፍሴ
'ምናለውና አይኗ!'
'ትቅራ!'
ብዬም ፍቅር ስቀራ. . .
ብርሃን ተምታቶብኛል
. . .
ብራ ቀኔን ብገብር ምን ይረባታል ማለቴስ
ሰማይ ልቧ ላይ ብበራ ምኗ ነዶ ምኔ ሊጤስ...?
. . .
እኔ ተወርዋሪ ነኝ
ምኔ ጋር እንደጨላለምኩ ምኑ ታወቀኝ ገና
ዥው ብዬ እስከማልፍሽ ይጎበኘኛል ወና
አንቺ ቅጽበት የምትይዢ
ቦግ ብዬ ሳልፍብሽ በብርሃኔ የምትፈዢ
ምኞት 'ምትናዘዢ
ፍቅር የምታፍዢ
እኔ ምኑ ጋር በርቼ ምኔን ጽልመት እንደወጋኝ
ምኑም ምኑም የማይገባኝ
ተወርዋሪ
በሪ
ሰይፍ ነኝ
እወቂብኝ!
እወቂብኝ!
ሰይፈ ተማም
#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ከማላቃቸው መልኮች ላይ ሳቆችሽን ዘግኛለሁ
ለራሴ
በልቤ መንገዶች ላይ በእግሬ ብዙ ተጉዣለሁ
ለነፍሴ
'ምናለውና አይኗ!'
'ትቅራ!'
ብዬም ፍቅር ስቀራ. . .
ብርሃን ተምታቶብኛል
. . .
ብራ ቀኔን ብገብር ምን ይረባታል ማለቴስ
ሰማይ ልቧ ላይ ብበራ ምኗ ነዶ ምኔ ሊጤስ...?
. . .
እኔ ተወርዋሪ ነኝ
ምኔ ጋር እንደጨላለምኩ ምኑ ታወቀኝ ገና
ዥው ብዬ እስከማልፍሽ ይጎበኘኛል ወና
አንቺ ቅጽበት የምትይዢ
ቦግ ብዬ ሳልፍብሽ በብርሃኔ የምትፈዢ
ምኞት 'ምትናዘዢ
ፍቅር የምታፍዢ
እኔ ምኑ ጋር በርቼ ምኔን ጽልመት እንደወጋኝ
ምኑም ምኑም የማይገባኝ
ተወርዋሪ
በሪ
ሰይፍ ነኝ
እወቂብኝ!
እወቂብኝ!
ሰይፈ ተማም
#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ