ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
እዬዬ አልባ ሞቴ

ለራሴ አዝኜ ሳልጨርስ
ባዘንኩብሽ ቀን ሳልተክዝ
በሬን ሳልዘጋ ለእዬዬ
ሳልደበር ተበድዬ

አዬ. . .

በብርዳም ኮተታም ዓለም
ቁር ከውስጥሽ ሲፋለም
ጨለማ ጮሆ ሲንጫረር
ዝምታሽ ታሞ ሲጫፈር
ክፍተትሽ ከፍቶ ሲዛባ
ዛቢያሽ ከራሱ ሲቃባ
ማን ነበረ ያለበሰሽ - ያንን ጸዓዳ ጋቢ
እርምሽንም ባታወጪ - ከድንኳኑ እንድታድሪ
ብርዱን ችለሽ እንድትበሪ
ለቅሶኛውን እንድትመስዪ

አዪ. . .

የኔም ተራ ደረሰና
ስወድቅልሽ ከወና
ስንከባለል ዝምታ ጋር
እነጋንጩርን ሳናግር
እነጽልመትን ስጋግር
ከነ ጋኔንም ስበደር
ማን ነበረ ያሰከረኝ - በዚህ የሃቅ አረቄ
በወጉ እንኳ ሳላዝን - ከለቅሶ ቀድሞ ሳቄ
ድሮስ መቼ ለ'ኔ አውቄ

ብርቄ. . .

ለራሴ አዝኜ ሳልጨርስ
ባዘንኩብሽ ቀን ሳልተክዝ
በሬን ሳልዘጋ ለእዬዬ
ሳልደበር ተበድዬ
አዬ አዬ . . .
ይኸው ክፉ ቀን መጥቶ
ደጄም አደረ ተዘግቶ
ሞት ቢሞላው መንገዱን
እኔስ ሞትኩኝ የምለው
አንቺ ውስጥ ሞቼ እንደሆን

ድብን. . .

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ @poeticsaturdays @artsmailinglist
♦️ዘቢብ እና ቴምር♣️
@Tominu
♥️
1.ዘቢቤ፡
የኔ ቴምር ቃና የኔ ጽዋ ከንፈር
በፈቃድሽ አክናፍ ዘላለም መሳፈር
ከመውደድሽ ገላ ላይነሱ መስፈር
ብለኸኝ አልነበር?
እኔም
የወይኗ ፍሬ ደቃቃ
ከመሬት ማኅጸን ጠልቃ
መጣፈጥ ስላ በነቢብ
በስተርጅና ስቶን ዘቢብ
በናቴ አፍ አልኲህ 'ሀቢብ'
♥️♥️
2. ሀቢቤ
ቋሚ ነሽ ዘንባባ የሚያፈራ ለምለም
ዛፍ ነኝ አበባ ነሽ ታውቂያለሽ የኔ ዓለም?
ከአበባ እንጂ ከፍሬ ሚጀምር እንዳች'ንኳ የለም!
ብለኸኝ አልነበር?
ቴምር ብለህ ጥራኝ ቴምሬ ጠይሜ
ካፍህ ልንቀዋለል ግብር ይሁነኝ ስሜ
ምራቅህ ጣዕሜን ይጠብ
ፍሬውን ትፋው እንደ ጠብ
ጉሮሮህ ስልቅጥ ይዋጠኝ
ዘቢብ ነዋ የተሰጠኝ!
♥️♥️♥️
3.ዘቢቤ
መስቀል ካንገትህ ዋለ
አፍህ በማርያም ማለ
ሂጃብ ለበሰ ራሴ
ወላሂ ይላል ምላሴ
ያን ለታ
የሰንበት ማኅልይ ጸሎት በአፍህ እየነገሠ
ልቤ አንተን ፍለጋ ከአሚን በፊት ደረሰ
ወላሂ! ጸሎትህ ገባኝ የቀራሁትን ቃል ሳለ
በደገምከው በቀራሁት ጠይም ፍቅር ውስጡ አለ፡፡
ወደድኩህ።
♥️♥️♥️♥️
4.ዘቢቤ
ከልብህ በጨሰው እጣን
ሲያቅረቅር አፍሮ ሼጣን
ከተሳሳትን ሃቅ ካጣን
እግዜር ይፍረድ አላህ ይቅጣን!!!
♥️♥️♥️♥️♥️
5.እመነኝ ሀቢቤ፧
በዘቢባን ዓለም በቴምሮች መንገድ
የእውነት ከሆነ ድል ይነሳል መውደድ!!!
ተቀበለኝ ይላል ልቤ 'ሁቡ'ን ልኮ
ፍቅር ካሰራቸው ዘቢብና ቴምር አንድ ናቸው እኮ፡፡
Forwarded from Poetic Saturdays
https://www.facebook.com/events/534920290531894/ TODAY!!! Join us for our first online poetry session! Let's celebrate the International Day of Living Together in Peace by getting together online and reading some of our pieces! Space is limited and we've had to limit our attendees, so move quickly and be one of the first 24 people to register at the link below. To join you must register first. See you there!

Topic: The virtual Poets
Time: May 16, 2020 03:00 PM EAT

Join Zoom Meeting
https://us04web.zoom.us/j/71147805916?pwd=aklBWU56WjZSVzBzY09EZm0zRzdxQT09
Forwarded from RasJany Muzik
የራስ ዐይን
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ አካባቢያችንን እንጠብቅ።
Ras Eyes
Please Keep The Environment Clean!
#rasyohannes #rasjany #hitsanlijproject #raseyes
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
Great news for all artists aged between 18 and 35 working in any medium! The application procedure for the 6th edition of the Future Generation Art Prize is open 🖼

The main prize winner receives US$ 100,000 and up to five artists will be awarded special prizes $20,000.

➡️ Apply now by clicking: https://futuregenerationartprize.org/
Forwarded from Poetic Saturdays
https://www.facebook.com/events/760779921124044/

ሠላም ሠላም ጤና ይስጥልን ፣ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን (ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ) የመጀመሪያውን የመስመር ላይ (ኦንላይን) ግጥማዊ ቅዳሜ እናስተናግዳለን! ይህ ምናባዊ የግጥም መድረክ ለሁሉም ሰው ክፍት ነው።
"ዙም" ላይ ይቀላቀሉ ወይም በፌስቡክ ቀጥታ ይመልከቱን! ለማንበብ ፍላጎት ካለዎት አስቀድመው በውስጥ መስመር መልዕክት በመላክ ያሳውቁን፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ያለ ቋንቋ፣እድሜ እና ርዕስ ገደብ አምስት ደቂቃ ይኖርዎታል። እዚያው እንገናኝ!

https://us02web.zoom.us/j/71147805916

Hey everyone, this Saturday, June 6th at 2:30pm, we will host our first ever online Poetic Saturdays! Virtual Poetry is open to everyone. Call in and join by Zoom or watch live on Facebook! If you're interested in reading, let us know beforehand or, if you join in on Zoom, send us a private message. As always, you'll have five minutes and we encourage all languages, all ages, and all topics. See you there!
ገጣሚ ሲሞሸር

ፍቅርን ፍቅር ይዞት. . .
የሰማያት ምንጣፍ ከንጻትም ላቀ
ሁሉ ብሩህ ሆነ ጌትየው ታወቀ
ለሰው ተገለጸ ቃል ሰውን ታጠቀ

ስጋም ወግ ደረሰው በአምላክ ተጠለቀ
ሰውን አጠለቀ
ሰውን አመጠቀ

ፍቅርን ፍቅር ይዞት እዩት ሲነፋረቅ
ግረፉኝ ስቀሉኝ እያለ ሲማቅቅ
ከቅዱስ ማደሪያው ሳይለይ ለአፍታ
ማጥንቱ ሲያደምቀው ሲገለጥ በማታ
እንደ ብርሃን ፈለግ መታየት ሲጀምር
እንዳዘቀዘቀች እንደ ማታ ጀምበር
ከድርደራው መሃል እንዳልተነካ አውታር
ከማለዳው በፊት እንደሰሙት አዛን
ኅያሉ ተገልጾ ለታናሾች ታየ
ተሰማ በጆሮ ውብ ዜማው ተለየ
በሙዚቃ - ሰረገላ - አረገ - መጠቀ
ከመንፈሱ መዳፍ ውበት ተጨመቀ
ከውበት ጭማቂም ጥበብ ተጠመቀ
ውሃው ወይን ሆነ አየሩ ታወደ
መውደድም እራሱ መውደድን ወደደ

ከድርደራው መሃል እንዳልተነካ አውታር
እንዳዘቀዘቀች እንደ ማታ ጀምበር
ከአይን ሲገባ
መታየት ሲጀምር
ግጥም ተጫጫሰ ገጣሚ ሲሞሸር


ሰይፈ ተማም 2012
Forwarded from Zellan Creative and Cultural Centre
Forwarded from LinkUp Addis
Join the conversation this evening!
Power of Art: Performance and Collaborative Expressions
Event Format: Online (Zoom)
Event Date: 11 June 2020 at 6:00pm
Hosted by Goethe-Institut Addis Abeba
Event Link: https://bit.ly/2Ap8RaM
Part of Tibeb Online

Make sure to download and enjoy the June 2020 edition of LinkUp Addis digital magazine: https://bit.ly/2Mg68CO #linkupaddis #eventsinAddis #EthiopianCulture
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem pinned «አበቦቹ ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች የብራ አለም ሰዎች የንጹህ አገር ዜጎች ለሃሴት አፎቱ ለፍቅርም ቤቱ ውበት ምልክቱ . . . ትናንሽ አበቦች. . . እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ ውስጠትን ሰርሳሪ በውበት አሳሪ. . . እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ (ለልጆቻችን. . .)…»
Forwarded from ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem (S e i f e - T e m a m)
አበቦቹ

ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች
የብራ አለም ሰዎች
የንጹህ አገር ዜጎች
ለሃሴት አፎቱ
ለፍቅርም ቤቱ
ውበት ምልክቱ
. . . ትናንሽ አበቦች. . .
እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ
እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ
ውስጠትን ሰርሳሪ
በውበት አሳሪ. . .

እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ
እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ
ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ

(ለልጆቻችን. . .)
#seifetemam
@seifetemam
Forwarded from Getz_mag
We are happy to announce that you can now find all our previous articles and magazine issues on our website www.getzmag.com
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
የዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ " ሰበዝ " የተሰኘው ዐዲሱ መጽሐፍ በሳምንት ውስጥ ስድሳ ሺህ ቅጂ ታትሞ ነው ለንባብ ገበያ የቀረበው ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::

ለቴሌግራም - @jafbok
ለዌብሳይታችን - www.jaferbooks.com


መገኛችን :- ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
ጌትዬ በማርያም - 1

"ጌትዬ በማርያም!" አለችኝ
የደረቀ ስንጥቅ እጇን - ወዳይኔ ጫፍ ሰንዝራ
የተዝረከረከ ያ ቆንጅዬ ልጇን በእጆቿ ጠፍራ
''ጌትዬ'' አለችኝ አንዱን ምስኪን ባርያ

መንገድ የጠፋበት መሄጃውን 'ማያቅ
ሰው አገኘሁ ብላ የሚያበራ ድቅድቅ
መች አወቀች እሷ የስልኬን ውስጥ ድብቅ
እየተከተለች ትለምነኛለች ይቺ የኔው ቢጤ
መንገድ ያከነፈኝ ሁል ጊዜ መጤ
መንፈግ ያስኮፈሰኝ - ጌታ የጠማው ለት የሆንኩኝ ኮምጣጤ
እኔ ደባብቄው አፍኜው እያለሁ ሁሉንም በውስጤ

በእናትየው ስም ለምና - በልጅየው ስም ጠራችኝ
''ጌትዬ በማርያም በማርያም'' አለችኝ
ማርያምና ልጇ ማናለ ቢራሩ
ለሷ እንድደርስላት ለኔ ቢለመኑ ?

'ማርያም ትስጥልኝ' ልበላት ወይስ ልጇን ልጥራ
አላህ ይስጥሽ ልበል ወይስ ኪሴን ላጥራ
ጌታ ተብላለች ልቤ እንዴት አትፈራ
ይች የምርያም ወዳጅ እኔን ጌታ ብላ

ጌትዬዋ ሆንኩኝ ባስረገዛት ወንዱ
የበላይዋ ሆንኩኝ ጠቦባት መንገዱ
እኔስ ጨልሞብኝ ጠፍቶብኛል ገዱ
አለብኝ ቀጠሮ በ'ለት ሃያ አንዱ

የምድሩን ህግ የናቀ የሳምዩን ላያከብር
እንደ ክቡር ዳኛው ልንገራት እንደምን
መጥሪያ ተቀብዬ እንደምሄድ ችሎት
እንዳለብኝ እስር

መንገዴን ሰርዤ ከኮንትራት ታክሲ
በሚኒባስ ልግባ እንድሰጣት ሳንቲ
ወይስ ሚኒባሱ ይቅርና ከቶ
በባሱ ታጭቄ ልስጣት አንድ መቶ
በእግር ብጓዘው አልደርስም ከችሎት
ወይ ጌትዬ መባል ጌታው የረሳን ለት!
Black church services, murderers, Arabs serving burgers
As cats with gold permanents, move they bags as herbalists
The dirt isn’t just fertile, it’s people working and earning this
The curb getters go where the cash flow and the current is
It’s so hot that niggas burn to live
The furnace is, where the money moving, the determined live
We talk shit, play lotto, and buy German beers
It’s so black packed with action that’s affirmative
The corners

Common
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem pinned «አበቦቹ ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች የብራ አለም ሰዎች የንጹህ አገር ዜጎች ለሃሴት አፎቱ ለፍቅርም ቤቱ ውበት ምልክቱ . . . ትናንሽ አበቦች. . . እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ ውስጠትን ሰርሳሪ በውበት አሳሪ. . . እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ (ለልጆቻችን. . .)…»
"Let's take a trip but not of the physical Sense of direction on a kid who's artistical
Through a gallery of thoughts, of course it's dope
Pay it tough like the name on my rope
Watch it be weary instead of steppin' wit the boys
A musical massacre of inadequate noise
By the new authority 'cause of majority
Of peers who hear will award superiority
To those who know you knew now it's inevitable
I laid the track and it's simple unforgettable..."

The D.O.C. - "Portrait of a Masterpiece" (Verse 1)
". . . ፎጋሪና ፎካሪስ መሃልስ አንድ ፊደል ነው
ልዩነት የሚያመመጣው ሁለቱም ግን ለወግ ነው
ትልቅነት የጎደለው ውሃ ውስጥ መስመጥ ባይቻልም
ያንሳፍፋልም እንጂ አገር አያቋርጥም
እውነት አልዋጥ ያለው ትውልድስ ምን ላይ ያተኩራል. . .

. . . የዛሬ ሰው ሲጠማውስ ቁምነገሩም በልኩ
ፊትለፊት 'ሚናገር 'ሚያወጣውስ ከልቡ
ልብ መርጫለሁ እኔም ይቅርብኝም ስኬት
ከመቶ አጨብጫቢም አንድ ወዳጅን በልክ. . . "

ፓምፋሎን