ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.84K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
አታውቂም?

ጓደኛ መስታወት የኔነት ነጸብራቅ:
በሩቅም እያለ ከልብ ውስጥ የማይርቅ:
ጓደኛ ፈውስ ነው የሚስጥሬ አለም:
እንደ ብቸኝነት ከቶ የወጋኝ የለም:
እኔ አንቺን ካጣው ሞቴ ነው አታውቂም?
:
ኦ ኦ ኦ ትችላለህ አትበይኝ አልችልም ግድየለም:
አጉል ተስፋ አትስጪኝ ድጋሜ አልታመም:
ብቸኝነት ጎድቶኝ መቼም አላገግም:
አስበሽዋል...ሊያውም በድጋሜ ስጎዳ ስሰበር:
ምን የሚሉት ቁስል ወይ ላይድን ወይ ላይ ሽር:
አረ ወይኔ....ልቤ ላይ ሲወጣ እንዴትስ ሊረሳ:
ሰው የማጣት ቁስል ዘላቂ ጠባሳ::

ይድናል አትበይኝ ጊዜውን ጠብቆ:
ትዝታ እያለበት ቁስል መቼ ደርቆ:
ይታያል ብለሽ ነው ሰውን ያጣ አለም:
አንድም ባዶ ሸክም:
ሌላም
በቁሙ የሞተ መሆኑን አታውቂም???

© ሚኪ ሳ.
👍32🤮1
ኧረ 'ኔስ አላይም ደጁን!

ይመጣል ነፋሱን መስሎ
ይሄዳል ናፍቆቱን ጥሎ።
ከዝናብ ፣ ከሰንበት ጋራ፥
መጠበቅ ነው የእኔስ ስራ።
እረፍትሽ ይሉኛል ሰዎች ፥ ዓርብ ዕለት ቤቴ ስገባ፣
ቅዳሜ አለ ቀጠሮ ፥ የእኩያ ፌሽታ ስብሰባ፤
ኧረ እኔስ አላይም ደጁን ፥ አልወጣም ቤቴን ለቅቄ፣
አለኝ የምናፍቀው ፥ አለኝ ከሰው ደብቄ፤
አለኝ የምጠብቀው ፥ አለኝ ትዝታ አሙቄ።
ኧረ 'ኔስ አላይም ደጁን!

ቅዳሜ ገበያ ነበር ፥ ስሜው የወጣሁ ከቤት፣
እሁድ በተስኪያን ልንሄድ ፥ ላስገባ ጥላ ለስለት።
አብሮነት ታደልን ብለን ፥ ጎጆችን ቀና ፣ ሰመረ፥
እሁድ ምሳ ሰዓት ላይ ፥ ቤታችን ጥሪ ነበረ።
ከሸመትኩት ከገበያው፥ አልቀረኝ ቄጤማ ፣ ጡንጅት
ለምስጋና የሚሆነን ጧፍ ሻማውን አረሳሁት።

ቀረች ብሎ ወጣ ከቤት ሊጠብቀኝ ከመንገድ፣
ከሩቅ ሁኘ ነው ያየሁት ሲፈልገኝ የእኔን መውደድ።
ፈገግ አልኩኝ ጥርሴ ጠራው ከአስፓልት ማዶ፣
መጥቶ አቀፈኝ የገበያ ሸክሜን ወስዶ።
እሱን ሳገኝ ያልገዛሁት ትዝ እያለኝ፣
'እፎይ.. አንተን ሰጥቶ ገላገለኝ!'
በል ሂድ አልኩት ፥ ገዝተህ አምጣ፣
ተመልሼ ከምወጣ፤
ቡና አፍልቼ ምሳ አቅርቤ ልጠብቅህ
ብቻ እንዳትቆይ ስሞትልህ?!

ቤቱን ሰንዳ ፥ ሰንዳ...ሰንዳ፣
ሁሉ ቀርቦ ቀረብኝ ዕዳ።
አንድ ...ሰዓት
ሁለት ሰዓት ፣ሶስት ..ልቤ ፈራ፣
በዚያው ቅጽበት ስልኬ ጠራ፤
'ሄሎ?'
"ሀሎ ..ወርቃማ ጥላ የያዘ ሰው..
መንገድ ሲያቋርጥ..." ሞተ ብሎ ጨረሰው ።

ኧረ እኔስ አላይም ደጁን..
ይሄን መርጦ ወሳጁን።

ሰው ስለት ይበላል እንጂ ፤ ፈጣሪን አረሳስቶ፣
እግዜሩም ይቀማል እንዴ፥ የሰው ዋጋ ገምቶ ።

እንግዳውም በሰንበት ፥ ተሸኘ እንደታሰበው፣
ወርቅ ጥላዬን ለስለት ፥ እልል ተባለ ሳስገባው።
ጡንጅቱ ቤቴን አጠነ ፥ ወግ ነው አሉ በባህሉ ፣
ሻማናጧፍ ለፍታት በየተራ ተቃጠሉ፤
እምባ የለሽ ሐዘኔን መጠበቄን አበቀሉ።

ኧረ እኔስ አልሄድም ደጁ፣
ቢፈልግ ይውሰደኝ እንጂ
እግዜር በረጅም እጁ።

© አስካለ ልቅና
👍63
Forwarded from Ankeboot Books
👍1
ኅብረቃል ፌስቲቫል

በርካታ ግጥሞች የሚቀርቡበት፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ ጨዋታዎች፣ አዝማሪ፣ ጭውውቶች፣ መነባንቦች፣ ክፍት መድረክ፣ ኩምክና፣ መጽሐፍት፣ የጥበብ ውጤቶች እና ሌሎችም በርካታ መዝናኛዎች በኅብር የተሰናሰሉበት የመጀመሪያው የግጥም ፌስቲቫል-በግጥም ሲጥም እና በቅርንፉድ ዲጂታልስ!


#HibreQal #poetryfestival #thefirstpoetryfestival
#poetry #worldpoetryday #artinaddis #gitemsitem #krinfud #Harar_Beer #Felek #LinkUp_Addis #Poetic_Saturdays
#art #games #food #music #poetry
👍2
[ስለራሥ ጥላ እና ስለነጭ ድመት ምልኪ]
(ካልጻፍኳቸው፣ ደጋግሜ ጽፌ ቸል ካልኳቸው...)

ትዕይንት አንድ፤
ከመወራጨት ወደመዳህ
ከመዳህ ወደመንገድ ወደመራመድ
ከመቀልጠፍ እስከመንቀራፈፍ
እስከመንከርፈፍ
እግር አንድ ጉዞ አንድ መንገድ
ሙሉ ሕይወት ጀምሮ እስከማገባደድ...
_____

ባካና እግረኛ መሆኔን መች እክዳለሁ
እስከመቆም እራመዳለሁ
ምሥጋና ለራሴ
ዓለምን ለተሸከመ ሥጋና
እሱን ለተሸከመች ነፍሴ

[ለምሥጋና በቀናሁበት
ነጭ ድመት ጎኔ ቆማ
ድምጿን አጥፍታ ወይ ድምጿ ጠፍቷት
መንገዴን ትቼ ቆምኩ

ሠላም ልፈልግ የወጣሁበት ዘንድ
ሠላም አጥቼ ቀረሁ]

እርቃንን ውሸት ነው እያሉኝ
እውነቴን ኩታ አልብሼ
ስሞት ይሆነኛል ያልሁትን እንባ
ለባይተዋር መኖር አፍስሼ
ስመለስ
ጥላዬን በቀትር አጣሁት

[ድመቷ እንዳፈጠጠች ጎኔ ቆማለች
የቆመ የመሰለኝ በድኔ
ቀዝቃዛ መሬት ተደላድሏል]

የተሸከምኩት ዓለም ባዶ ነው
የተሸክምኩት እኔ ባይተዋር ነኝ
ሸክሙን አንስቼ ሳዝለው
በመቅለል ፈንታ ከበደኝ

[የሌለ ቢቀል ብዬ አለመሆንን ብመርጥ
ከመሆን የሚከብድ
እግሬን አንስቼ ብገፋ
ጥላ የሚያሳጣ
የማያደርስ መንገድ

ነጯ ድመት ቆረጠቺኝ!]

ባይተዋሬን ይዤ ብመጣ
ያንቺን ባይተዋር አልሞላ
ሸክሜን ይዤ መጥቼ
ከሸክም ውጪ አልሆንሽ
ምን ትያለሽ?
ዓለም፣ እኔ እንከብዳለን?

ይቅርብን
በእንባ እንባ ከማጠብ ውጪ
ምን እንተጋገዛለን?

______
መዝጊያ ትዕይንት፤
በወፋፍራሙ የተጻፈ
ድንጋይ ላይ የጠረበ
ያላፊ ሠው ጽሑፍ

እመኚኝ
ባዶው ከሙሉው ይከብዳል
ባይተዋር የሆነ ልቤ መሐል
ተቃርኖ ውሎ ካረፈደ
ሞት ያኔ ነው ይዞኝ የሄደ

ብርሃኔን አከሰምኩ
ጥላዬ ከመሬት ጠፋ
ብጎድል ብሞላ ሸክምሽ ነኝ
ምን ይዤ እመጣለሁኝ?

ዝም ከምንለው ውጪ ምን አለን?
ምን እንተጋገዛለን?

----

[ እውነት እንግዲህ ባይተዋርነቴ ነው
እርቃኔን ተንጋልዬ
ትዝታዋን ብቻ ተጎናጽፌ ተንጋልያለሁ

በድኔን እንዲሁ ተዉት
መች መቃብር ይችለኛል
አትቅበሩኝ እነሳለሁ
ተጎትቼ ተጠግቼ ሄጄ በሯን እመታለሁ]

© ማርቆስ
በየወሩ ሽፍታ የሚካሄደው ክፍት መድረካችን መጋቢት 28 የእናንተን ስራዎች ለእናንተው ለታዳሚዎች ያቀርባል።
ዝግጅታችን ለማንኛውም ሰው ፊት መቅረብ ለሚችሉ የጥበብ ዘርፎች ክፍት ነው። ምዝገባ 12 ሰዓት ይጀመራል ዝግጅቱ ደግሞ 12:30 ይጀምራል። መግቢያ 50ብር ብቻ!

ኑ እና በነጻነት እራሳችንን እንግለጥበት!

ለመጀመሪያዎቹ 50 ታዳሚያን ነጻ አራዳ አለን።
2
Forwarded from LinkUp Addis
Gitem Sitem and Krinfud Digitals are partnering up to organize a festival titles Hibrekal Festival on Saturday 09 April 2022 at Fana Park. The event will feature poetic performances, music, live art, short plays and other performances. Entrance fee is ETB 150. Stay tuned for more info. @linkupaddis
Forwarded from Getsh 🇪🇹🇪🇹metmku🇪🇹🇪🇹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
The Mosaic Hotel is hosting a professional networking and inspirational event on Saturday 14 April 2022. The event, which will be titled Self-Reconciliation for Generation Building will be hosted by Fitsum Atnafwerk, and will feature prominent opinion leaders and social influencers. Doors will open at 4:30pm, and entrance fee is ETB 200.

@linkupaddis
Forwarded from ሊያ አበበ
"ትክክል"
~~
ትክክሉን ሁላ
ማነው ልክ ያረገው?
ልክ አይደለም ብሎስ
ማነው የደነገገው?
ሁሉም ትክክል ነው
ሁሉም እንደራሱ፣
በተረዳው መጠን
መልሱን መመለሱ፡፡
የማነው ትክክል
እነማን?የትኞች?
በወጣኸው ዳገት
ባለፍኩት መንገዶች፡፡
የየቅሉ መንገድ
ስህተት የተባለው፣
ያረከው ያረኩት
ሁሉም ትክክል ነው፡፡
በአንተነትህ መዝን
በእኔነቴ አውጣኝ፣
በዳገትህ ስፈር
በመንገዴ ለካኝ፡፡

ሊያ አበበ
1
አታውቂም?

ጓደኛ መስታወት የኔነት ነጸብራቅ:
በሩቅም እያለ ከልብ ውስጥ የማይርቅ:
ጓደኛ ፈውስ ነው የሚስጥሬ አለም:
እንደ ብቸኝነት ከቶ የወጋኝ የለም:
እኔ አንቺን ካጣው ሞቴ ነው አታውቂም?
:
ኦ ኦ ኦ ትችላለህ አትበይኝ አልችልም ግድየለም:
አጉል ተስፋ አትስጪኝ ድጋሜ አልታመም:
ብቸኝነት ጎድቶኝ መቼም አላገግም:
አስበሽዋል...ሊያውም በድጋሜ ስጎዳ ስሰበር:
ምን የሚሉት ቁስል ወይ ላይድን ወይ ላይ ሽር:
አረ ወይኔ....ልቤ ለይ ሲወጣ እንዴትስ ሊረሳ:
ሰው የማጣት ቁስል ዘላቂ ጠባሳ::

ይድናል አትበይኝ ጊዜውን ጠብቆ:
ትዝታ እያለበት ቁስል መቼ ደርቆ:
ይታያል ብለሽ ነው ሰውን ያጣ አለም:
አንድም ባዶ ሸክም:
ሌላም
በቁሙ የሞተ መሆኑን አታውቂም???

©️ከ ሚኪ ሳ.
4👍1