ወሎ ሰፈር ግርጌ
ከጎተራ ራስጌ
ስሽከረከር ብውል ጠፍቶብኝ መንገዴ
በቀዝቃዛ ውሃ እንደ እሳት መንደዴ
ለሰው ልጅ ቢደንቀው አውሬ ማላመዴ
ይኸው እገኛለው
የአህያዬን በረት ለጅብ አጋርቼ
ነባቢቱን ስንቅ ዱዳውን አውርቼ
የሚሽቴን መቀነት ለውሽማ አውርሼ
ጫካ እባርካለሁ ህንጻ ላይ ቀድሼ
©️እስሩ ገብሩ
ከጎተራ ራስጌ
ስሽከረከር ብውል ጠፍቶብኝ መንገዴ
በቀዝቃዛ ውሃ እንደ እሳት መንደዴ
ለሰው ልጅ ቢደንቀው አውሬ ማላመዴ
ይኸው እገኛለው
የአህያዬን በረት ለጅብ አጋርቼ
ነባቢቱን ስንቅ ዱዳውን አውርቼ
የሚሽቴን መቀነት ለውሽማ አውርሼ
ጫካ እባርካለሁ ህንጻ ላይ ቀድሼ
©️እስሩ ገብሩ
👍1
የኅብረቃል ድምቀት የነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ!!!
ፌስቲቫሉን ስፖንሰር በማድረግ እውን እንዲሆን ያገዘን ሐረር ቢራም ውሎ ይግባ!
ፈለክ በአጋርነት አብሮን ስለነበረም ከልብ እናመሰግናለን!
Shout out to the beautiful HibreQal crowed and all who were there!!! The turn out was great, it didn't look like a first edition!
Thank you Harar Beer for sponsoring our unique festival!
Felek Notebooks, we are proud to call you a partner in pulling off this one of a kind event!
#HibreQal_Festival #World_Poetry_Day #HibreQal2022 #Poetry
#Harar #Felek #Poetic_Saturdays #LinkUp_Addis
#Krinfud #GitemSitem
ፌስቲቫሉን ስፖንሰር በማድረግ እውን እንዲሆን ያገዘን ሐረር ቢራም ውሎ ይግባ!
ፈለክ በአጋርነት አብሮን ስለነበረም ከልብ እናመሰግናለን!
Shout out to the beautiful HibreQal crowed and all who were there!!! The turn out was great, it didn't look like a first edition!
Thank you Harar Beer for sponsoring our unique festival!
Felek Notebooks, we are proud to call you a partner in pulling off this one of a kind event!
#HibreQal_Festival #World_Poetry_Day #HibreQal2022 #Poetry
#Harar #Felek #Poetic_Saturdays #LinkUp_Addis
#Krinfud #GitemSitem
👍1🔥1
የኅብረቃል ድምቀት የነበሩት መባቻዎች ደብረማርቆስ ላይ ቀጣይ ድግስ አላቸው
ለምን ከከተማ ግርግር አፍታ ወስደን ወጣ ብለን የነሱን ልዩ ቀለም ታድመን በስጦታቸውም ተደምመን አንመለስም?
ለምን ከከተማ ግርግር አፍታ ወስደን ወጣ ብለን የነሱን ልዩ ቀለም ታድመን በስጦታቸውም ተደምመን አንመለስም?
Forwarded from መባቻ የጥበብ ማህደር
#መባቻ_የጥበብ_ማህደር
እነሆ ወርሃዊው የጥበብ ድግሳችን የሚያዚያ ወር ዝግጅቱን መደገሱን ተያይዞታል።
በዚህ የጥበብ ምሽት ላይ በተለያዩ የጥበብ ስራዎች በመረጣችሁት ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ መሳተፍ ለምትፈልጉ
በግጥም
ወግ
የአንድ ሰው ተውኔት
ሙዚቃ እና መሠል የጥበብ ስራዎች መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ስራዎቻችሁን መጋቢት 26/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይዛችሁ መቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ 0948034115/0928567096 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
እነሆ ወርሃዊው የጥበብ ድግሳችን የሚያዚያ ወር ዝግጅቱን መደገሱን ተያይዞታል።
በዚህ የጥበብ ምሽት ላይ በተለያዩ የጥበብ ስራዎች በመረጣችሁት ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ መሳተፍ ለምትፈልጉ
በግጥም
ወግ
የአንድ ሰው ተውኔት
ሙዚቃ እና መሠል የጥበብ ስራዎች መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ስራዎቻችሁን መጋቢት 26/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይዛችሁ መቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ 0948034115/0928567096 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
Forwarded from Seife Temam
ማስ 1
ማስፈለጉን ባያይ
ከጊዜ የተጣላ የዘመን ባተሌ
ማስ ፈለኩን ባያይ
መኖር አጎድጉዶት የዛሬ ገደሌ
ማስ አልኩት ለልቤ
ለተንጎዳጎደው የትላንት ገድሌ
መቀበር ላልቀረ
ወግ ሁሉ ቀርቶብኝ
በራሴ አቆፋፈር በድኔ እንዲያርፍልኝ
ማስ ሰብን እስከውስጥ
ከላይላይ በዝቶ ነው
የምንጎደፍረው
ከላይ ልጡን ላንልጥ
ማስጠርጠሩ ላይቀር
ገና ከምጣዱ
ማስታወቁ ሳለ
ምንድነው ማስፋቱ
ጠብ የማይል እህል ?
ምንድነው ማስፋቱ
ጠብ የሚያህል እልህ?
ይኸውልህ - እኔ
ከልብ ያላደረ
እውነት መሳይ ሃሰት
ሃሰት መሳይ እውነት
እያደናበረው
ማስመሰል ምስ ሆኖት
በማሱለት ጉድ ጓድ
ያልተዛቀን ቁልል
ተራራህ ነው ብለው
ዘመን ተጋሪዬን
ይሸነግሉታል
ከፍታህ፤ ጉድጓድ ውስጥ
ከወለሉም በታች
ካሉት ከተሻለ
ምን ይሰራልሃል
ከተማሰው መውጣት
ይሉታል ያስሩታል
ሰው ከተማ ሳለ
ከተማሰው ገብቷል
... ይኸውልህ እኔ ...
ማስ መቀበሪያህን
ማንም ከሚያበጀው ምንምነትህን!
ማስተካከል ቀርቷል
እራሱ ልክነት ይሳሳት ከጀመር
ዘመናት ተቆጥረው
የርዝማኔው ስፋት
የጊዜው ክብደቱ
ስህተት ልክሆኖ
እራሱ ልክነት
ልክ የሳተበቱ
የቀናቱ ውፍረት የቀጠነበቱ
ስንት ቆጥሯል ዘመን
ማስተካከል ትተን
ማስከተል ከጀመርን
ይኸው በኔ ዘመን
ማስከተል እንደአዲስ
አሁንም ብርቅ ነው
አዲስ የእምነት በር
እንደፈለሰፈ
የፋርስ ወይ የመካ
የናዝሬት የኔፓል
የግሪክ የካም ሰው
ተከታይ ከሌለህ
ማስመስከር አትችልም
ሰው መሆንክን ለሰው
ማስፈለጉን ባያይ
ከጊዜ የተጣላ የዘመን ባተሌ
ማስ ፈለኩን ባያይ
መኖር አጎድጉዶት የዛሬ ገደሌ
ማስ አልኩት ለልቤ
... ይኸውልህ እኔ ...
ማስ መቀበሪያህን
ማንም ከሚያበጀው ምንምነትህን!
ማስፈለጉን ባያይ
ከጊዜ የተጣላ የዘመን ባተሌ
ማስ ፈለኩን ባያይ
መኖር አጎድጉዶት የዛሬ ገደሌ
ማስ አልኩት ለልቤ
ለተንጎዳጎደው የትላንት ገድሌ
መቀበር ላልቀረ
ወግ ሁሉ ቀርቶብኝ
በራሴ አቆፋፈር በድኔ እንዲያርፍልኝ
ማስ ሰብን እስከውስጥ
ከላይላይ በዝቶ ነው
የምንጎደፍረው
ከላይ ልጡን ላንልጥ
ማስጠርጠሩ ላይቀር
ገና ከምጣዱ
ማስታወቁ ሳለ
ምንድነው ማስፋቱ
ጠብ የማይል እህል ?
ምንድነው ማስፋቱ
ጠብ የሚያህል እልህ?
ይኸውልህ - እኔ
ከልብ ያላደረ
እውነት መሳይ ሃሰት
ሃሰት መሳይ እውነት
እያደናበረው
ማስመሰል ምስ ሆኖት
በማሱለት ጉድ ጓድ
ያልተዛቀን ቁልል
ተራራህ ነው ብለው
ዘመን ተጋሪዬን
ይሸነግሉታል
ከፍታህ፤ ጉድጓድ ውስጥ
ከወለሉም በታች
ካሉት ከተሻለ
ምን ይሰራልሃል
ከተማሰው መውጣት
ይሉታል ያስሩታል
ሰው ከተማ ሳለ
ከተማሰው ገብቷል
... ይኸውልህ እኔ ...
ማስ መቀበሪያህን
ማንም ከሚያበጀው ምንምነትህን!
ማስተካከል ቀርቷል
እራሱ ልክነት ይሳሳት ከጀመር
ዘመናት ተቆጥረው
የርዝማኔው ስፋት
የጊዜው ክብደቱ
ስህተት ልክሆኖ
እራሱ ልክነት
ልክ የሳተበቱ
የቀናቱ ውፍረት የቀጠነበቱ
ስንት ቆጥሯል ዘመን
ማስተካከል ትተን
ማስከተል ከጀመርን
ይኸው በኔ ዘመን
ማስከተል እንደአዲስ
አሁንም ብርቅ ነው
አዲስ የእምነት በር
እንደፈለሰፈ
የፋርስ ወይ የመካ
የናዝሬት የኔፓል
የግሪክ የካም ሰው
ተከታይ ከሌለህ
ማስመስከር አትችልም
ሰው መሆንክን ለሰው
ማስፈለጉን ባያይ
ከጊዜ የተጣላ የዘመን ባተሌ
ማስ ፈለኩን ባያይ
መኖር አጎድጉዶት የዛሬ ገደሌ
ማስ አልኩት ለልቤ
... ይኸውልህ እኔ ...
ማስ መቀበሪያህን
ማንም ከሚያበጀው ምንምነትህን!
👍3
Forwarded from Arada T-Shirts
Some of the products made for ግጥም ሲጥም
Contact us to ORDER or to take INFO. 0944213490
@A_Sentient_Being Or @Yoyo_101
Don't forget You can also order t-shirts, hoodies & mugs of your own design (pictures, text any thing)
Contact us to ORDER or to take INFO. 0944213490
@A_Sentient_Being Or @Yoyo_101
Don't forget You can also order t-shirts, hoodies & mugs of your own design (pictures, text any thing)
👍1
እንደ ብርቱ ምዕመን ፥ እንደ በቃ ወልይ
ቀኝ ብቻ ሲሆን የአህዛብ መስተሐልይ
በግራ አውለኝ ብለህ ወደ አምላክህ ፀልይ ።
ጊዜህን አትግድል ፥ ከአቅምህም አትጉደል
ስትፈልግ አቻህን ፤
አንዳንዴ
ህብረት ካላዋጣህ ሞክረው ብቻህን ።
አትችልበትም ወይ ?
እንዲሁ በሰውነት
ያለ መንግስት አዋጅ ራስን መዳኘት
ሃይማኖት ሳይኖርህ ፈጣሪህን ማግኘት
ከወተት ነጥሎ ገነትን መመኘት ?
የሸረሪት መንጋ ድሮች አሰባስቦ አንበሳን ሲያጠምደው
እስኪ አንተም ሰው ሆነህ በዜማህ አላምደው
ውደደው
ውደደው
በፖለቲካ አቋም
ድርጅት ማቋቋም
ኮሚቴና ተቋም
እንደ እህል ተዘርቶ በየ ስፍራው ሲናኝ
ልክ እንደ መናፍቅ ፥ የከተማ መናኝ
ከዓለም ተነጥለህ ፥ ከዓለም ጋ ተገናኝ ።
© Hab HD
ቀኝ ብቻ ሲሆን የአህዛብ መስተሐልይ
በግራ አውለኝ ብለህ ወደ አምላክህ ፀልይ ።
ጊዜህን አትግድል ፥ ከአቅምህም አትጉደል
ስትፈልግ አቻህን ፤
አንዳንዴ
ህብረት ካላዋጣህ ሞክረው ብቻህን ።
አትችልበትም ወይ ?
እንዲሁ በሰውነት
ያለ መንግስት አዋጅ ራስን መዳኘት
ሃይማኖት ሳይኖርህ ፈጣሪህን ማግኘት
ከወተት ነጥሎ ገነትን መመኘት ?
የሸረሪት መንጋ ድሮች አሰባስቦ አንበሳን ሲያጠምደው
እስኪ አንተም ሰው ሆነህ በዜማህ አላምደው
ውደደው
ውደደው
በፖለቲካ አቋም
ድርጅት ማቋቋም
ኮሚቴና ተቋም
እንደ እህል ተዘርቶ በየ ስፍራው ሲናኝ
ልክ እንደ መናፍቅ ፥ የከተማ መናኝ
ከዓለም ተነጥለህ ፥ ከዓለም ጋ ተገናኝ ።
© Hab HD
❤5👍3
ታላቅ የሙዚቃ ድግስ!!!
💚💛❤️
፲ ዓመት የሙዚቃ የፍቅር የጓደኝነት ጉዞ
#ሞሰብ_ባንድ የ10ኛ ዓመት ምስረታ በዓላችንን ግንቦት 8/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በ #ኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ቲያትር እናከብራለን።
በዕለቱም
⭐️መድረክ አጋፋሪ
👉#ግሩም_ዘነበ (#እያዩ_ፈንገስ)
⭐️#ሞሰብ_ባንድ
⭐️#ነጋሪት_ባንድ
👉#ተፈሪ_አሰፋ #Drum
👉#ጆርጋ_መስፍን #Saxophone
👉#ዓብይ_ወ/ማርያም #Piano
👉#እዮስያስ #BaseGuitar
👉#ቴዎድሮስ_አክሊሉ #Piano
👉#ግሩም #Saxphone
⭐️ድምጻውያን
👉#ጠረፍ_ከሳሁን ( #ኪያ )
👉#ምትኩ_በቀለ (#ቸውሲ)
👉#Surprise ድምጻዊን ጨምሮ
ስራዎቻችንን ለታዳምያን እናቀርባለን።
💚💛❤️
መግብያ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ)
ትኬቱን በዕለቱ መግቢያ በሩ ላይ ያገኙታል
Mobile: +251920326836 +251922842696
E-mail: mosebculturalband@gmail.com
Facebook: Moseb Cultural Music Group
Youtube: Moseb Cultural Music Band
💚💛❤️
፲ ዓመት የሙዚቃ የፍቅር የጓደኝነት ጉዞ
#ሞሰብ_ባንድ የ10ኛ ዓመት ምስረታ በዓላችንን ግንቦት 8/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በ #ኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ቲያትር እናከብራለን።
በዕለቱም
⭐️መድረክ አጋፋሪ
👉#ግሩም_ዘነበ (#እያዩ_ፈንገስ)
⭐️#ሞሰብ_ባንድ
⭐️#ነጋሪት_ባንድ
👉#ተፈሪ_አሰፋ #Drum
👉#ጆርጋ_መስፍን #Saxophone
👉#ዓብይ_ወ/ማርያም #Piano
👉#እዮስያስ #BaseGuitar
👉#ቴዎድሮስ_አክሊሉ #Piano
👉#ግሩም #Saxphone
⭐️ድምጻውያን
👉#ጠረፍ_ከሳሁን ( #ኪያ )
👉#ምትኩ_በቀለ (#ቸውሲ)
👉#Surprise ድምጻዊን ጨምሮ
ስራዎቻችንን ለታዳምያን እናቀርባለን።
💚💛❤️
መግብያ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ)
ትኬቱን በዕለቱ መግቢያ በሩ ላይ ያገኙታል
Mobile: +251920326836 +251922842696
E-mail: mosebculturalband@gmail.com
Facebook: Moseb Cultural Music Group
Youtube: Moseb Cultural Music Band
👍2
[ . . . እናቴ ግንባር ላይ . . . ]
▿
▿
የከተማ ልጅ ነኝ ፣ የከተማ ሰው ነኝ
መርጋት ከ'ኔ ርቆ ፣ የሚያብከነክነኝ
“ደኀና ሰንብች እማ”፣ ብያት እንደወጣሁ
“ደኀና ሰንብት”ስትል ፣ ተመልሼ መጣሁ
▿
የከተማ ልጅ ነኝ ፣ ዓይኔ የታከተ
ወንዝም ይሁን ባቡር ፣ አፉን ከከፈተ
ዘው እልበታለሁ ፣ “ቶሎ ንዳው” ብዬ
መራመድ ነው ሕይወት ፣ እግር ነው እጣዬ
“ቡና አፍዪ መጣሁ” ፣ ብያት እንደወጣሁ
አፈር ሊስማት ሲል ፣ ተመልሼ መጣሁ
▿
የከተማ ልጅ ነኝ ፣ ባሻ ወልዴ ችሎት
ቁልቁል እንደ ዝናብ ፣ ሽቅብ እንደ ጸሎት
ወዲያም ወዲህ ብዬ ፣ ለገላዬ ስጥር
ፈርሶ
ልጅ አልሆንኩላትም ፣ እናት ሆናኝ እንጂ
▿
የከተማ ሰው ነኝ ፣ ሄዳለሁ
ራሴ'ንኳ ሳይጠና ፣ ያኔ እንደወጣሁ
በቁንጮ ሸኝታኝ ፣ ዛሬ በጢም መጣሁ
▿
የሚያበራ ግንባር ፣ ሽብሽብ ቆዳ ሆኖ
ያለ ተክለጻዲቅ ፣ ታሪክ ተሸምኖ
ገለሥላሳ ጠጉሯ ፣ ሽበት ተተክቶ
ጡሌ አንገቷ ታጥፎ ፣ መራቀቋ ጠፍቶ
ይቻት
ያቺ እናት . . .
ያሳደድኳት ሕይወት ፣ በየብስ በሰማይ
ስትሞት አየኋት ፣ እናቴ ግንባር ላይ
▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
.
.
ለወ.ኃ (ሴት አያት) — ይሁን!
© HEnock Bekele
https://www.facebook.com/henock.bekele.79
▿
▿
የከተማ ልጅ ነኝ ፣ የከተማ ሰው ነኝ
መርጋት ከ'ኔ ርቆ ፣ የሚያብከነክነኝ
“ደኀና ሰንብች እማ”፣ ብያት እንደወጣሁ
“ደኀና ሰንብት”ስትል ፣ ተመልሼ መጣሁ
▿
የከተማ ልጅ ነኝ ፣ ዓይኔ የታከተ
ወንዝም ይሁን ባቡር ፣ አፉን ከከፈተ
ዘው እልበታለሁ ፣ “ቶሎ ንዳው” ብዬ
መራመድ ነው ሕይወት ፣ እግር ነው እጣዬ
“ቡና አፍዪ መጣሁ” ፣ ብያት እንደወጣሁ
አፈር ሊስማት ሲል ፣ ተመልሼ መጣሁ
▿
የከተማ ልጅ ነኝ ፣ ባሻ ወልዴ ችሎት
ቁልቁል እንደ ዝናብ ፣ ሽቅብ እንደ ጸሎት
ወዲያም ወዲህ ብዬ ፣ ለገላዬ ስጥር
ፈርሶ
ሚጠብቀኝ ፣ የመንፈሴ ቅጥር
▿
ግጥም ▹ ድሎት ▹ሥዕል
ውበት ▹ ዕውቀት ▹ገንዘብ
ፍለጋ ስማስን
ከሞቷ ጋር እኩል ፣ ከቤቷ ደረስን
ከፍቶኛል አልዋሽም
“የ
ሷ ልጅ ነህ?” ሲለኝ ፣ በመልካችን ቅጂልጅ አልሆንኩላትም ፣ እናት ሆናኝ እንጂ
▿
የከተማ ሰው ነኝ ፣ ሄዳለሁ
መጣለሁ
ሰው ይጎርፋል ወዲህ ፣ እኔ
ደበቃለሁራሴ'ንኳ ሳይጠና ፣ ያኔ እንደወጣሁ
በቁንጮ ሸኝታኝ ፣ ዛሬ በጢም መጣሁ
▿
የሚያበራ ግንባር ፣ ሽብሽብ ቆዳ ሆኖ
ያለ ተክለጻዲቅ ፣ ታሪክ ተሸምኖ
ገለሥላሳ ጠጉሯ ፣ ሽበት ተተክቶ
ጡሌ አንገቷ ታጥፎ ፣ መራቀቋ ጠፍቶ
ይቻት
ያቺ እናት . . .
ያሳደድኳት ሕይወት ፣ በየብስ በሰማይ
ስትሞት አየኋት ፣ እናቴ ግንባር ላይ
▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹▹
.
.
ለወ.ኃ (ሴት አያት) — ይሁን!
© HEnock Bekele
https://www.facebook.com/henock.bekele.79
❤8👍3