ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ወደ ዳሞቻ ተራራ የሚደረግ ጉዞን የሚያሸልመው ውድድራችን ከ30 ደቂቃዎች በፊት ተጠናቋል! ሁላችሁም ተመስገኑልን! አሸናፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!! ተመሳሳይ ውድድሮችን እያደረግን የምንቀጥል በመሆኑ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እየተከታተላችሁን ቆዩ!

ሶስተኛ፦ ኤደን ሙሉነህ @Oritethe
192
1 #ነፍስ_ቦታ መጽሐፍ

ሁለተኛ፡- ቶፊቅ መሀመድ @Tufaw_muhe
193 ነጥብ
2 #ነፍስ_ቦታ መጽሐፍት

አንደኛ፦ ናታን ኤርምያስ @UniqueDY
242 ነጥብ
@ma_trip ተጓዦች ጋር ነጻ ጉዞ ወደ ዳሞቻ

*መግለጫ፦ ሁሉም ምልክቶች እንደ ድምጽ የተቆጠሩ ሲሆን 😍👍🏾😐 ሶስቱ ምልክቶች የተዘጋጁት እኩል ውጤት ቢገኝ እንደመለያ እንዲያገልሉ ነው። ይህንን በደንብ እና ሁኔታዎች ባለማካተታችን ይቅርታ እንጠይቃለን! በቀጣይ የሚኖሩን ውድድሮች ላይም በተሳትፎ እና በዳኝነት አብራችሁን እንደምትቀጥሉ እምነታችን ነው።
አቢሲንያ እንዳለቻችሁ ስንቄን ቅዳሜ 8 ሰዓት ብሔራዊ ቲያትር ተገኝታችሁ መርቁልኝኝኝ . . . እ!. . . እንዳትቀሩ አደራአ!

https://t.me/GitemSitem
አንተ የምትወደው ሙዚቃን በሆንኩኝ
አንተ የምትወደው ግጥምን በሆንኩኝ
እንደ እሳት ነበልባል ልብህን በላስኩኝ፤
እንዲያው ወለል ወለል
እንዲያው ከንበል ከንበል
እንዲያው ፍስስ ፍስስ
ከስጋህ ለይቼ ዛትህን ብነጥቃትስ ፤
መንፈስህ ስካር ቢሞላው
ቀልብህን ነፋስ ቢነዳው
እያገለበለበ የስሜት ገሞራው
ኩራትህ በሟሟ የትም በበተነው፤
በቻልኩበት ፣
በሆንኩበት ፣
አንጀትህን መኮልኮል
ሆድህን ማባባት
አቅልህን መንሳት
ኮከብ በፊትህ መንዛት፤
በሆነና በሆነልኝ
በውበት መስዋት
ትብትብ ብለህ በታሰረከኝ
ሰውነቴ አይደል ወይ ፊትህ ያሳነሰኝ ?!

©️መቅደስ ሞገስ

https://t.me/GitemSitem
ተወኝ
ተስፋ ፤ እንደ ጥላ አልሸሸም፣
/ልቤን...
ደግፎታል ፤ናፍቆት እየመሸም።
እንዴት ነው የናፍቆት
/ምሽት
እንዴት ነው የናፍቆት
/ንጋት
እንደ ፀሐይ ኹሉ
ኹለት ፤ መግቢያ መውጫ
ኹለት ፤ ፅንፍ አቅጣጫ
(አለው ወይ እላለኹ..)
ደግሜ ሸኝቼህ ፤ ደግሜ መጠበቅ
ከጀንበር ተላልፎ ፤ ሐፀይን መታረቅ
ጊዜ ተበድሮ ፤ በጊዜ መንፏቀቅ
በዘገየ እርምጃ ፤ በምእራብ መጥለቅ
( ሲደንቅ! )
/ ምን ማለት እደሆን ፤ አልገባህም አይደል? /
በምስራቅ ማሕፀን ፤ ንጋት እንዲወለድ
ጀንበር ነበረበት ፤ ወደ ጥልቁ መውረድ።
ተስፋ እንደዚህ ፤ አይደል የሚንከራትተው
ናፍቆት ሰውቶ ነው ፤ ፍቅርን የሚያትተው።
አንተም...
አለሁ ማለት ላ'ተው፣
እኔም ተስፋ ማድረግ ላልተው፤
አለን ናፍቆትን፤ ስንመጸውተው።
ትሔዳለህ
ትመጣለህ
'ሸኝካለኹ
ጠብቃለኹ
(እንዴት ልኹን...?)
ጎዶሎ ጨረቃ ፤ ስትሞላ እያየኹ
ተስፋ ልቆርጥ ስል፤ ምክንያት አጣለኹ።
አታውቅም ወይ፤ ቆርጦ መሄድ
አታውቅም ወይ ፤ እሩቅ መንገድ፤
ደከመኝ...
እኔን ፍለጋ ፤ ወዳ'ንተ መንጎድ።
ተወኝ
ላንገናኝ አትቅጠረኝ
በትዝታ አትጠረኝ
ማረኝ
እኔን ከብቻዬ ተወኝ
ኮከብ ሆነህ አትታየኝ
(ተወኝ !)
/ በብርሃን ካንተ ላልደርስ ፤ የመውደቅ ጸጋ አይራቀኝ።/


©️መንበረማረርያም ኃይሉ
መንቢ የሎዛ
መነሻ ሐሳብ
( ተወኝ ) ፀ.ገ .መ

https://t.me/GitemSitem
Forwarded from Mn Ale Addis
What's Addis?

Sehin Tewabe, a rising eccentiric photographer. Check out for her photography works of this outshining woman in the upcoming Mn Ale Addis e-mag!

Stay tuned!

#mnaleaddis #emagazine #BakelEdition #SehinTewabe #photography
👍1
ግጥም ሲጥም ፮

በ6ኛው የግጥም ሲጥም ምሽት የዓመቱን ቆይታ ልናጠናቅቅ ነው! እስካሁን አብራችሁን የተጓዛችሁ፣ በቅርብ የተሳፈራችሁም ሆናችሁ፣ ፌርማታ ላይ እየጠበቃችሁን ያላችሁ ሁሉ ተመስገኑልን!
ከወዲሁ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን - ዝግጅታችን ላይ እንደምትገኙም ጭምር!
በሉ ሽፍታ እንገናኝ የፊታችን ረቡዕ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 ልክ 12 ሰዓት ሲሆን ጀምሮ

Gitem Sitem 6

The 6th Episode of our Open Mic Circle of Poetry and Fun is here for the last session in this Ethiopian year. Thank you for all who have been with us along the way, those who are joining us and even those who are considering to come to one of our events.
We wish you a happy Ethiopian New Year! See you at Shifta

#gitemsitem #heransyoga #seifetemam #shifta
In our 5th episode, the photographer challenged our poets to come up with a piece using this photo.

በ5ተኛው ምሽታችን ላይ ፎቶግራፈሩ በዚህ ምስል ላይ ተንተርሰን ግጥም መጻፍ እንችል እንደሆን ምርጥ ሶስቱን ሊሸልም ቃል ገብቶ ነበር።
I was just passing through.
Or time, through me.

I froze or time did.
And just Like that,
Of all the places in the whole world, I had nowhere to be.
I had nowhere to return to.
______

እነበርኩበት ላይ
አምናን
አሁንን
ነገን
ሁሉን መምሰል መስዬ
ያለመለወጤን ሀቅ
ለመለወጥ ምሥጢር ጥዬ

አቆያየቴን
አጠባበቄን
በእርምጃ ሳሰማምር
የሚገፋኝን፤
ቀኔን ልገፋ ስዳክር

ሁሉ ጥሎኝ ከንፎ
ሁሉን ጥዬው እየከነፍኩ
አንቺን ብቻ አትርፌ
ዓለሙን ሁሉ ከሠርኩ!

[የማይደግፈኝን ደግፌ
ወደምቀርበት የምመጣው
የማልበላውን
ተሸክሜ የምወጣው

መቆሜን አልፎ እየቻለ
መንገድ አላራምድ ያለኝ
በእህል ምትክ የሚጎረስ
ሠው፤ ህይወት እየራበኝ...

ይህቺን ታህል...
እያለፍኩበት የምኖረው
አሁን ስፈልግ ነው
ሌላ አሁን ያከተመው!]

Even when I say I haven't changed a bit,
I have changed a lot.
Cos I never used to say that!

Yes I contradict my self.
And that's what kept me in one piece!

ቆሜ
መዳከሜን ላባብለው
የተራመድኩትን ባስተውለዉ

እየሄድኩ አለመድረሴን ሊያስረዳ
የተራማጁ ሲገርመኝ
ጥላዬ እርምጃዬን አስከነዳ...

[በዐይንሽ የልቤ ይደርሳልና
መሰልቸቴን እገስጻለሁ...
አለመምጣት ፊቴ ቆሞ
በመጠበቄ እረካለሁ..

ለመተው ብናስተውለው...
የሚያልፍብን
የምናልፍበት
ጊዜ ይደናበራል
መንገዱ እየነጎደ እግራችን ቆሞ ይቀራል፤

ምንገዶን...
መቆሚያ ካለ
ተስፋ አጥግቦ ያሳድራል!]

እንግዲህ...
እውነቱ እያየነው
ውሸት የሚሆንበት ቀን አለው...

ልክ አለመለወጤን እያስረዳሁ
የከበበኝ በሙሉ አዲስ እየተካ ነጎደ
የምደርስበት ዘንድ ሳልሄድ
የምደርስበት ደርሶኝ ሄደ...

ጊዜ በጎኔ አለፈ
አዲስ ትናንት አስቀረሁ
ያልኖርሁት ዕለት ትዝ ይለኛል...
አልተለወጥኩም ብል ማን ያምነኛል?

[ሁሉ ረግቶ
ሩጫው ላይ
የምረጋበት ቢያሳጣኝ
መቆሜ ነው መጽናኛዬ
ወደጥርስሽ የሚያመጣኝ...

መድረሻዬን ሊመትር መሰለኝ
ጥላዬ ቀድሞኝ ሮጧል
ስንዝር ብጨምር አልቀድመው

ወዴት እራመዳለሁ?
ወደአመጣኝ ዘፍጥረቴ
ወደእቅፍሽ እመለሳለሁ!

በአንቺ ተስፋ ለመለምኩ እንጂ
ለምለም እንጀራ ቢጠቀለል
ለዳረጎት ቢጣል ከአፍ ላይ

ነፍሴ ተርባ አታውቅም
ቀምሳ ከማረፍ ከመንካት
አንቺን ከመጉረስ በላይ..]

እያለፍኩ
እንደአሁን
እጠብቅሻለሁ

I was just passing through.
Or time, through me.

I froze or time did.
And just Like that,
Of all the places in the whole world, I had nowhere to be.
I had nowhere to return to, but you!

_

Inspired by: The Photograph brought forward for #Gitem_sitem6 challange...

©️ MarkO's

Gitem Sitem 6
የዓመቱ የግጥማዊ መቋጫ ደረሰች! እንግዲህ ተከሰቱና ክስተት የሆኑ ገጣሚያንን ግጥሞች እንዲሁም ሌሎች የጥበብ ስራዎችን ታደሙ!
Forwarded from Poetic Saturdays
የ2013 የመጨረሻ ግጥማዊ ቅዳሜ!
22 ከቅዱስ ገብርዔል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው GUAC-ON ሬስቶራንት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ቅዳሜን አስውበን እንጠብቃችኋለን!

Come join Poetic Saturdays at GUAC-ON in Hayahulet this coming Saturday, September 4th 2021!

https://www.facebook.com/guaconaddis
- As usual, we will start registration at 2: 00 pm.
- Only perform YOUR ORIGINAL work. The audience is there to listen to your truth!
- Each performer gets 5 minutes total. You can perform as many times but respect the time limit.
- All languages welcome.
All performance art forms welcome!
- We are excited our audiences and honored our performing family is growing. So come by and witness the amazing talents brewing in our city.
- Tell a friend!
6ተኛውን ዝግጅት በቀትጥታ ከሽፍታ በድምጽ ተከታተሉንማ
Forwarded from Poetic Saturdays
የ2013 የመጨረሻ ግጥማዊ ቅዳሜ!
22 ከቅዱስ ገብርዔል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው GUAC-ON ሬስቶራንት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ቅዳሜን አስውበን እንጠብቃችኋለን!

Come join Poetic Saturdays at GUAC-ON in Hayahulet this coming Saturday, September 4th 2021!

https://www.facebook.com/guaconaddis
- As usual, we will start registration at 2: 00 pm.
- Only perform YOUR ORIGINAL work. The audience is there to listen to your truth!
- Each performer gets 5 minutes total. You can perform as many times but respect the time limit.
- All languages welcome.
All performance art forms welcome!
- We are excited our audiences and honored our performing family is growing. So come by and witness the amazing talents brewing in our city.
- Tell a friend!
Forwarded from Deleted Account
አሳብ

ስለ ማሰብ ላለማሰብ
ማሰብ ባያስፈልግ
ምንኛ ደግ ነበር አሳብ ተሰንጥቆ
አሳብ እስቲጠግግ

'ካሳብ አሳብ በልጦ
'ላሳብ አሳብ ቆርጦ
አሳብ 'ካሳብ መርጦ
የሚታሰብ አሳብ..?

...ሰበብ!
ላለማሰብ:

ሰበብ... ላለመንቃት
ሳይጀምሩ ማሰብ..
ሰበብ ማበጃጀት
እፍፍፍ...
እውነት: ይሁን ቅዠት!
ቅዠት 'ያሳብ ጉዞ
አሳብ ተያይዞ
ካሳብ ላይ ተመዝዞ
አሳብ ተጎዝጉዞ
በሰበብ ሀዲድ ላይ
እየተጓተቱ
አሳቦች በረቱ

'ላሳብ የሚታሰብ
የአሳብ ዥጉድጉዶሽ
አሳብ ያዝ ለቀቅ
የነገር አባርሮሽ
አሳብ 'ካሳብ ሲሸሽ
ሲፋተግ ሲተሻሽ

ወዴት ልሽሽ?

ይኼም ሌላ አሳብ...
እዚህ ሸብ
እዚያ ሸብ
አሳብ ማሰባሰብ
አሳብ 'ባሳብ መክበብ
አሳብ 'ባሳብ ማጥበብ
ማሳመር መቀንበብ
...ጥበብ!
ጉራማይሌ ንባብ
ባለ ቀለም ምናብ
ድምፅ አልባ ንትርክ
የሽቅድድም ታሪክ
በምናብ ብራና
ቀድሞ የሚተረክ

እንደ ሰማይ ስንጥቅ
ብሩህ ብርቅርቅታ
አድማስ የሚያዳርስ የቀለም ጠብታ
ብትንትን እያለ
አሳብ 'ካሳብ ላቀ
አሳብ 'ላሳብ ፍሞ
አሳብ ተቃጠለ

ባላስብ ምናለ?
ይኼም ሌላ አሳብ...

(የጌታነህ ልጅ)
#poeticsaturdaya #gitemsitem
👍1