ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
እንግዲህ በየወሩ የዘመናችንን የግጥም ጀግኖች እንዲህ አንዳቸውን ከፊት እያዘመትን ስራዎቻቸው የሚገባቸውን ቦታ እንዲያገኙ እንጮሃለን!


የመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት 'ራስ' ይህ ድንቅ ገጣሚ ነው!

ምግባር ሲራጅን እስካሁን ለማታውቁ ጥሩ አጋጣሚ መጥቶላችኋል።



#ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤሊያስ ሽታሁን በግጥም ሲጥም!
በመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ የተገኛችሁ ሁሉ ተመስገኑልን!

ዝግጅቱን እንዴት አገኛችሁት? አጣሚዎቻችንስ እንዴት ነበሩ?

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #መግባርሲራጅ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥዑም ግጥም ቅመሱማ!

ዮሐንስ ላቀው በግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ

#ዮሐንስ_ላቀው #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ምግባርሲራጅ
Elias Shitahun:
(ከሚወጣው መድብል ቅምሻ
:
:
ካቲካላ የለም ፤ ከዛሬ ጀምሮ!
ለምን?
መለኪያው ተሰብሮ።
(ብለሽ
ደሞ መሸጥ ቀጠልሽ)
ጥያቄ!
መለኪያው ነው እንጂ የተሰባበረው፣
ካቲካላሽማ… በርሜሉን ሙሉ ነው።
ይሄንን ስትሰሚ
እንዳትገረሚ።
መኮመሪያ ቤትሽ ፣ መስፈሪያ የጣለ
ባገኘው ይ፟ለካል ፤ ያገኘውን ኹሉ ፣ ልኬት ነው እያለ፡፡
እረ ያንቺስ እውነት ፣ ልኩን ያሳጣሽው፣
በምን ለክተሽ ነው?
አንድ አረቄ እያሉ ፣ በርሜል የጨረሽው።
መለኪያሽን ዐየሽ ፣ ንቀሽው ተሰብሮ፤
በዋጋ ያጣላል ፤ ልክ የሌለው ኑሮ።
ለዋጋሽ መለኪያ፤
ለስካር መለኪያ፤
ለማወቅ መለኪያ፤
ለመኖር መለኪያ ፣ ጠፍቶሽ እንዳሰምጪ፤
አረቄሽን ዘግተሽ ፣ መለኪያሽን አውጪ፤
ተይ በልክ ቅጂ!
ቀጥ ብሎ እየገቡ ፣ ሲወጡ በዳዴ፣
በምን ሰጠሻቸው ፣ ሰከሩልሽ ባንዴ።
የአረቄሽ ሞገስ…
ሰው እየመሰለው ፣ ዐይኑ ደም ሲቀላ፣
ገ፟ዳም ናት ይልሻል ፤ ሰው ቤትሽ ሲሞላ።
ገድሽ መለኪያሽ ነው! የተሰበረልሽ፤
አትሰሰትም ብሎ ፣ ሰው የሚያመጣልሽ።
ሀገሬው ሀገርሽ ፣ ስስት ከመለካት ተደበላልቆበት፣
የሚለካን ኹሉ ፣ ስስታም የሚል ስም ፣ ወስዶ ለጠፈበት።
ተይ በልክ ቅጂ!
ማይለካ አረቄ ፣ እያደልሽው በገፍ፣
ሀገር ሰከረልሽ ፤ በምኑ ይደገፍ።
ተይ በልክ ቅጂ!
ጤነኛውስ ይኹን ፤ እብድ አታስብጂ፤
ተይ በልክ ቅጂ!

-------//////-------
ኤልያስ ሽታሁን
የምስል ጥበብ ስነ-ግጥምን ስታውቃት. . . !
When photography meets poetry...!

@ribkiphoto

#ርብቃሲሳይ #ribkasisay
#ግጥምሲጥም #gitemsitem
አስተምረኝ
( ሠይፈ ወርቅ)

አስተምረኝ - ከማዕበል ጋር መደነስ
አሠልጥነኝ - በእሳት ላይ መመላለስ
ስሬን አጥብቅ - እንድታጠፍ ለነፋሳት
ልቤን ግራው - ሲቀጠቀጥ እንዲከፈት
ከዶፍ
ከጎርፍ
ከጣይ፣ ከቁር
ከበረድ ጋር
ከውሽንፍር
ከመብረቅ ጋር እንድጨፍር
ውብ ህይወትን እንድዘምር
አስተምረኝ!
ያለነፋስ - ዋሽንት በድን
ሳይገረፍ - ክራር አይድን
ሳይመታ - ሙት ከበሮ
ለሰከነ - ለነፍስ ጆሮ
በህመም ውስጥ ተቀምሮ
ውብ ዜማ አለ በተፈጥሮ
አስተምረኝ
የማየትን ጥልቀት፣ ርቀት
አሠልጥነኝ
የማድመጥን ስር መሠረት
በሸለቆ
በከፍታ፣ በቁልቀለት
ህመም ሳልሸሽ
ያለህመም ልኑርበት
#አስተምረኝ
#ምራኝ!
#ማረኝ!
( ሠይፈ ወርቅ )

#አስተምረኝ

#ሰይፉወርቁ #ሰይፈወርቅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ታዳሚዎቹም አቅራቢዎቹም ወደነዋል፣ ጥሞናል፣ ድገሙንም ብለዋል!
የታደማችሁም ያቀረባችሁም ተመስገኑልን! መምጣት ሳትችሉ ብትቀሩም ድጋፋችሁንና ሀሳባችሁን የቸራችሁንም ክበሩ!
ቦታውን ሳታገኙት ቀርታችሁ መምጣት ያልቻላችሁ ደሞ ይቅር በሉን!

ቀጣዩ እንዳያመልጣችሁ ለታህሳስ 10 ቀጠሮ ያዙ ገጾቻችንንም ተከታተሉ

https://t.me/seifetemam

#ኤልያስ_ሽታሁን #ምግባር_ሲራጅ #አንዱ_ጌታቸው #ሌላ_ምስክር #ረቂቅ_አሰገደው

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም

ህዳር 12 ከተካሄደው የመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ የተወሰዱ ምስሎች

📷 @AnimaHela