ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
880 subscribers
1.11K photos
93 videos
4 files
840 links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ዘመቻ አንድነት በጎንደር ግንባር
               ፱ኛ ቀን

   9ኛ ቀኑን በያዘው ዘመቻ "አንድነት " በጎንደር ግንባር ግለቱን ጠብቆ ቀጥሏል።

🔸 በደቡባዊ ጎንደር ቀጠና በስማዳ እና እስቴ ወረዳዎች ልዩ ስማቸው አጎና፣አገዛና ዝንጀሮ ገደል በተሰኙ ቦታዎች የአፋአጎ ሜ/ጀ/ውባንተ አባተ (1ኛ) ኮር መቅደላ ብርጌድ ፣እስቴ ዴንሳ ብርጌድ፣ስማዳ ሀገረ ቢዘን ብርጌድና አንዳቤት ብርጌዶች እና የኮሩ ሌሎች ሻለቆች የአገዛዙ ስራዊት ላይ በወሰዱት መብረቃዊ ድ*ም*ሰ*ሳ 02 ስንቅና ጠላት የጫነ ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን፤ ከ75 በላይ ጠላት ተ*ደ*ም*ስ*ሷ*ል በአስር የሚቆጠር ጠላትም  ቆ*ስ*ሏ*ል ቀሪውም ተማርኳል።

    ውጊያው ከሁንም ተፋፍሞ ስለቀጠለ ጠላት ላይ የደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ቁጥሩ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይጠበቃል።
በኮሩ ስር የተዋቀረው ተወርዋሪ ሀይል የድሉ ባለቤት ነው።

🔸 በሰሜን ምዕራባዊ የጎንደር ቀጠና በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጎቤ ክ/ጦር ጠራ ብርጌድ ቁጥጥር ስር ገብታለች።
በዚህ ግንባር ዛሬ አስደናቂ ፈጣን ንቅናቄ በማድረግ ጠላትን ሙ*ት ቁ*ስ*ለ*ኛና ምርኮ በማድረግ  የወረዳ ከተማዋን ቅራቅርን የተቆጣጠረው የአፋአጎ ሰራዊት በከተማዋ ተበትነው ቤት ለቤት የተደበቁ የአገዛዙ ታጣቂዎችና የፖለቲካ መሪዎች በአሰሳ እየተለቀሙ ይገኛል።በዚህ ግንባር አመርቂ ድል የተመዘገበ ሲሆን አሰሳው የቀጠለ ስለሆነ የተሟላ መረጃ በአማራ ፋኖ አንድነት Amhara fano unity in Gondar የፌስ ቡክ ገፅ የምናደርስ ይሆናል።
       
         ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

             የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
               መጋቢት 18/07/2017 ዓ.ም
                   ጎንደር/አማራ/ ኢትዮጵያ
ብርቱኳን ተመስገንን አፍኖ በማሰር ለሁለት ቀና ማለት ያለባትን ካስጠኗት በኋላ "የብርቱካን  እውነት" በሚል ፋና የተባለ የአገዛዙ አጋፋሪ ዘጋቢ ፊልም ሰርቼ ጨርሻለሁ ብሏል።

ብርቱኳን ያለፉት ሁለት ቀናት በእስር ላይ ሆና ከአምስት(5) ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ የተቀረፀች ሲሆን፡ "እናንተ ያስጠናችሁኝን አልናገርም" በማለቷ ከባድ ድብደባ ተፈፅሞብታል ተብሏል።

ዘጋቢ ፊልሙን አዘጋጀሁት ያለው የአገዛዙ አጋፋሪ ሚዲያ፡ በፌደራል ፖሊስ እያስደበደበ እነ ዳኒኤል ክብረት ፅፈው የሰጡትን ፅሁፍ እንድትሸመድድ ካደረገ በኋላ ቀረፃውን አካሂዷል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

የመረብ ሚዲያ ምንጮች እንደገለፁት ብርቱኳን ተፅፎ የተሰጣትን ፅሁፍ ሼምድጄ አልናገርም በማለቷ፡ ባፍና ባፍንጫዋ ደም እስኪፈሳት ድረስ ድብደባ የተፈፀመባት ሲሆን፡ ይህ የተፈፀመው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በሆነው ደመላሽ ገ/ሚካኤል ትዕዛዝ ነው ተብሉዋል።

በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኮምፒውተር የተዘጋጁ የብርቱኳንን እውነት ያስቀይራሉ የተባሉ ሰነዶች ተካተውበታል የተባለ ሲሆን፡ ብርቱኳን የማታውቃቸው ቤተሰብ ነን ብለው በዘጋቢ ፊልሙ ቃል የሰጡ ሰዎች መኖራቸውም ተጠቁሟል።

© መረብ ሚዲያ
በጎንደር ቀጠና የዋለዉ አዉደዉጊያ ማምሻዉንም የቀጠለ ሲሆን ፋኖ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።

በደቡባዊ በጎንደር ቀጠና በዋለዉ አዉደዉጊ ፋኖ አንድ ሻለቃ ሙሉ የአገዛዙን ሰራዊት እና ገብረአበሩን የሚሊሺያ እና አድማ ብተና አባላት ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ ህዝብ ግንኙነት ለአለምአቀፍ ፋኖ ሚዲያ ገልፆልናል።

በጋይንት፣እስቴ እና ስማዳ በነበረዉ አዉደዉጊያ በርካታ ሀይሉን ያጠዉ አገዛዙ ማምሻዉን ደግሞ ከእስቴ መካነየሱስ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሾለከት ከተማ በተደረገዉ ትንቅንቅ በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።

በዚህ አዉደዉጊያ አገዛዙ በርካታ የሰዉ ሀይሉን ያጣ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።

ቀኑን ሙሉ በዋለዉ አዉደዉጊያ ፋኖ በርካታ ቁጥር ያለዉ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና የቡድን መሳሪያ መማረኩን አስታዉቋል።

በርካታ የገዥው መንግስት ስርዓት አስጠባቂ ወታደር እና አንድ ኤፍ .ኤስር ተሽከርካሪ ተተኳሽ፣አንዲሁም ሁለት ተሽከርካሪ ምርኮ ተደርጓል።

በእስቴ መከናየሱስ አጎና፣ደገዛ እና ዝንጀሮ ገደል በዋለዉ አዉደዉጊያ የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማህበረሰቡ የተሸከፈ ሲሆን እስካሁን ተሸክፎ አለማለቁን የአካባቢው አርሶአደሮች መረጃዉን ለሚዲያችን አጋርተዉናል።

ማምሸዉን በእስቴ መካነየሱስ ሾለከት በተደረገዉ አዉደዉጊያ በርካታ ቁጥር ያለዉ የገዥው መንግስት ጥምር ጦር ሙትና ቁስለኛ የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በመካነየሱስ ሆስፒታል በርካታ ቁጥር ያለዉ የአገዛዙ ቁስለኛ ሰራዊት መግባቱ ተረጋግጧል።ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ስራዊት ደግሞ ወደ ደብረታቦር ሆስፒታል መላኩን የአይን ዕማኞች ለአለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ተናግረዋል።

በዚህ አዉደዉጊያ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ፣የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር፣የጉና ክፍለጦር የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ፣የሀገረ ቢዘን ብርጌድ፣የአንዳቤት ብርጌድ፣የመቅደላ ብርጌድ የተሳተፉ ሲሆን የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ አራት ምክትል አዛዥ የሆነዉ አርበኛ ገብሬ ሰባት የጠላት ሀይልን በመማረክ አስገራሚ ጀብድ በመስራት 1 ስናይፐር፣3 ክላሽ፣ሶስት አብራረዉ፣አንድ ስኬስ በመማረክ ድል መቀዳጀቱን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ሀቅያለዉ ለአለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ መረጃዉን አጋርቶናል።

አለምአቀፍ ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ የዘወትር ድምፅ!!!
እየኮበለለ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት |በጎንደር ጋይንት፣ እስቴ እና ስማዳ ከባድ ውጊያ|“በዘመቻ አንድነት”የተገኙ ድሎች
እየኮበለለ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት |በጎንደር ጋይንት፣ እስቴ እና ስማዳ ከባድ ውጊያ|“በዘመቻ አንድነት”የተገኙ ድሎች
አሳዛኝ መረጃ!

ብርቱካን ተመስገን በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ እራሷን መሳቷ ተሰማ!

ተበዳዩዋ ድብደባው የተፈፀመባት ከአገዛዙ አጋፊሪ ሚዲያዎች ተፅፎ የተሰጣትን በትክክል ሸምድዶ ለመናገር ባለመቻሏ ነው ተብሏል።

ብርቱካን ተመስገን ለእስር ከተዳረገችበት መጋቢት 16/2017 ዓ/ም ከገላን የመጡ የፖሊስ አባላት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት እየተፈራረቁ" በልማት ጎዳና ላይ ያለውን መንግስት ገፅታ ለማበላሸት ተልዕኮ ተሰጥቶሽ ነው" በሚል ባፍና ባፍንጫዋ ደም እስኪፈሳት ድረስ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውባታል ተብሏል።

ብርቱካን ተመስገን የአገዛዙ ሚዲያዎች ላስተላለፉት ዘጋቢ ፊልም ቀረፃ እየተደረገች እንዳለ ሸምድዳ እንድትናገር ተፅፎ የተሰጥትን በትክክል ማለት ባለመቻሏ ቀረፃው በተደጋጋሚ ተቋርጦ እንደነበር ምንጮች ገልፀዋል።

"ቀረፃው ሲጀመር እምባ እየተናነቃት ተፅፎ የተሰጣትን በትክክል ካሜራ ፊት ማለት አልቻለችም ነበር" ሲሉ የተናገሩት ምንጮቻችን በዚህም ድብደባ ተፈፅሞባታል ብለዋል።

ተበዳዩዋ የደረሰባትን ግፍ ሳይሆን ተፅፎ የተሰጣትን ብቻ እንድናገር በመገደዷ እምባዋን መቆጣጠር ባለመቻሏ: የካሜራ ባለሙያዎቹ በቂ የሆነ ምስል መውሰድ እንዳልቻሉ የተጠቀሰ ሲሆን፡ አብዛኻኛው የዘጋቢ ፊልሙ ማልበሻ ቀደም ብለው ተዘጋጅተው በነበሩ ሀሰተኞ ዶክመንቶች እንዲሸፈን ተወስኗል ብለዋል።

በአማራነቷ የደረሰባትን ግፍና ሰቆቃ ለምን ለሚዲያ ተናገርሽ በሚል በፌደራል ፖሊስ ታፍና በእስር ላይ የምትገኘው ብርቱኳን በተፈፀመባት ድብደባ እራሷን እንደሳተች ነው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው።

ተበዳዩዋ ብርቱኳን ከባለስልጣናት በመጣ ትዕዛዝ በቂ ህክምና እንዳላገኘች የተነገረ ሲሆን፡ ህይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ከፋኖ ጋር ውሎ| 9ኛ ቀን "ዘመቻ አንድነት " የአራቱም ማዕዘናት የፋኖ አደረጃጀቶች የግንባር ውሎ መግለጫ
ከፋኖ ጋር ውሎ| 9ኛ ቀን "ዘመቻ አንድነት " የአራቱም ማዕዘናት የፋኖ አደረጃጀቶች የግንባር ውሎ መግለጫ
ከፋኖ ጋር ውሎ| 9ኛ ቀን "ዘመቻ አንድነት " የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የግንባር ውሎ ፣ የተደረጉ አውደ ግንባሮችና የተመዘገቡ ድሎች ምን ይመስላሉ
ከፋኖ ጋር ውሎ| 9ኛ ቀን "ዘመቻ አንድነት " የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የግንባር ውሎ ፣ የተደረጉ አውደ ግንባሮችና የተመዘገቡ ድሎች ምን ይመስላሉ
ሰበር ዜና

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የአርበኞች ክፍለ ጦር በዛሬዉ እለት ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በተደረገዉ አዉደዉጊያ ከፍተኛ ድል መጎናፀፉን አስታወቀ።

በማእከላዊ አርማጭሆ ወረዳ በደዊ ከተማ ላይ መሽጎ በሚገኝ ጠላት ላይ በተወሰደ እርምጃ ጠላትን በመደምሰስ ከተማዋን በፋኖ ቁጥጥር ስር ማዋሉን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የአርበኞች ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ ባንዲራዉ ግርማይ ለአለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ አስታዉቋል።

ዛሬ አመሻሹን በተደረገዉ አዉደዉጊያ ከፍለጦሩ ጠንከር ያለ ዘመቻ በማድረግ በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ እና ሰባዊ ኪሳራ ማድረሱን ጭምር ኃላፊዉ አያይዞ ገልፆልናል ።

በቀጠናዉ በርካታ ጀብዶች የተፈፀሙ ሲሆን መረጃዉን ነገ በመረጃ ቴሌቪዥን በዝርዝር የምናደርሳቹህ ይሆናል።

አለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ የዘወትር ድምፅ!!
ቀሽም ደራሲዎች አበላሽተውት ነውጂ...!

ቀሽም ደራሲዎች አበላሽተውት ነውጂ ብርቱካንን በድንግልና አገባች ብሎ ከተረከ በኋላ፣ እሷ ቀጥላ በአንደበቷ "አርግዤ ነው የተጋባነው" አያስብሏትም ነበር። 🤔

ቀሽም ደራሲዎች አበላሽተውት ነውጂ "ኢቢኤስ በጽንፈኛው ለድራማው ተመረጠ" ካሉ በኋላ መልሰው ደግሞ "ከጽንፈኞች" መካከል ድምጻቸው ነው ተብለው ያወሩት እነ መዓዛ "ኢቢኤስ እና መንግስት አብረው ነው የሚሰሩት" የሚለውን ንግግር መቁረጥ ነበረባቸው። 🤔

ቀሽም ደራሲዎች አበላሽተውት ነውጂ "ገንዘብ ተከፍሏት ነው" የሚል መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ፣ "ጽንፈኞቹ" እነ ተስፋዬ ብርቱካን ለትራንስፖርት ይሆናል በሚል አምስት ሺ ብቻ እንደተሰጣት የሚናገሩበትን መቁረጥ ነበረባቸው። 🤔

ቀሽም ደራሲዎች አበላሽተውት ነውጂ .... እያልን ብዙ መቀጠል ይቻላል። 🤔

በነገራችን ላይ በሚዲያ አሰራር መሰረት የብርቱካን ጉዳይ የተሳሳተ ነገር አለው ከተባለስ በራሱ በኢቢኤስ አልነበረም ወይ መቅረብ የነበረበት? እኔ የሚገባኝ ኢቢኤስ የሰራሁት ፕሮግራም ችግር የሌለበት ነው በሚል አቋሙ ስለጸና ይሆን?

ለማነኛውም የብርቱካን ታሪክ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ታሪክ መሆኑን ሚሊዮኖች ያውቃሉ! ያለፉት ዓመታት ብዙ ታሪኮችን ትተን ባለፈው ሳምንት አሊደሮ ላይ የታገቱትን አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ወገኖቻችን በዚህ ሰዓት ምን እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው!
ጥንቃቄ ይደረግ
የድሮን አሰሳ አቸፈር፣ሻውራ አካባቢ
ጥንቃቄ ይደረግ