ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 49ኛ ክፍለ ጦር የሆኑ አምስት አባላት ከኦህዴድ ብልፅግና ጋር ሆነን ወገናችንን አንወጋም በማለት ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: ክፍለ ጦሩም አቀባበል አድርጎላቸዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 5/2018 ዓ.ም
3🙏1
የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች በብልፅግናው አገዛዝ ባደባባይ እየተዘረፉ መሆኑን ነዋሪዎች በማስረጃ እያጋለጡ ቀጥለዋል::

ጀምበር የጠለቀችበትና ተስፋ የቆረጠው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የህዝብ ሃብት መዝረፉን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የሰሜን ወሎ ዞን ወልድያና ቆቦ ከተማ ካድሬዎችም የከተሞቹን የህዝብ ሃብት ባደባባይ እየዘረፉ መሆኑን ነዋሪዎች በማስረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፈው ጊዜ ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽን ሸጠው የተከፋፈሉ ሆድ አደርና አገር አፍራሽ የዞንና የወረዳ ካድሬዎች እንዲሁም የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አመራሮች በማስረጃ የተጋለጡ መሆኑ ይታወሳል:: ጉዳዩም በፍርድ ቤት ተይዞ የህዝብ ሃብት የሆነው ቆቦ ሁለገብ አዳራሽ ተመላሽ እንዲሆን ተወስኖ እንደነበር ከፍርድ ቤት ያገኘነው ማስረጃ ይናገራል::

ስለሆነም አሁንም ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሎ ከዚህ በታች በማስረጃ የተዘረዘሩት የወልድያ ከተማ እና የቆቦ ከተማ መሬቶች ለጦርነት አላማ ሊውሉ ጥርና የካቲት/2018 ዓ.ም በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ለሽያጭ መቅረባቸውን የከተሞቹ ህዝብ ባደረሰን ማስረጃ አረጋግጠናል::

ወልድያ ከተማ በክልሉ ከፍተኛ የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች የሚዘረፉበት ከተማ ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ድሃ የቀበሌ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የአገዛዙ ሹማምንቶች እንደተከፋፈሉትና ዛሬም ተጠናክረው እንደቀጠሉበት ከህዝብ የደረሰን ማስረጃ ያሳያል::

ቆቦ ሁለገብ አዳራሽ ባለፈው ጊዜ ሰማኒያ ሚሊየን ብር እና ከዛ በላይ ተሽጦ ገንዘብ ሲካፈሉ ተጣልተው በፍርድ ቤት ትዛዝ ገንዘቡ ለገዥ ተመላሽ ከሆነ በኋላ እንደገና ለጨረታ የቀረበ ሲሆን እነዚህና ሌሎች ለጊዜው በስም ያልተጠቀሱ የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ላለው የብልፅግና አገዛዝ ለጦርነቱ አላማ ለማዋል እየተዘረፉ በህገወጥ ጨረታ ለገበያ መቅረባቸውን ነዋሪዎች በማስረጃ አስደግፈው አድርሰውናል::

በመጨረሻም ለመላው ህዝባችን ምኒልክ ዕዝ ከሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ያፀደቀውን መመሪያውን መሰረት በማድረግ የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ ለህዝብ መሆኑና መመለሱ አይቀርምና ተስፋ የቆረጠው አገዛዝ ካድሬዎች የጦር መሪዎች ስግብግብ ነጋዴዎችና ህገወጥ ደላላዎች ተቀናጅተው ከሚሰሩት የመሬት ወረራና ዘረፋ ባለመሳተፍ ሃብታችሁን እንድትጠብቁ ብሎም ከህልውና ትግሉ ጎንም እንድትቆሙ ስንል ዛሬም እንደ ትላንቱ መልክታችንን እናስተላልፋለን!

*ማስታወሻ፦ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም የወሎ ቤተ-አማራ አካባቢዎች በአገዛዙ እየተዘረፉ ያሉ የህዝብ ሃብቶችን የሚከታተልና ማስረጃ የሚይዝ ህቡዕ (ስውር) አደረጃጀት እንዳለው ለህዝብ ማሳወቃችን የሚታወስ ነው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 5/2018 ዓ.ም
2🔥2
ፋሽስቱን አገዛዝ ብልፅግና ወግነው ህዝባቸው ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ የነበሩ የሚሊሻ አባላት ነባራዊ ሁኔታውን በመረዳት በውጊያና በፈቃዳቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ ቀጥለዋል!

በዚህም ዘጠኝ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የሚሊሻ አባላቶቹ መካነ ሰላም ዙሪያ በነበረ አውደ ውጊያ በቀላል መስዋዕትነት እጃቸውን ለክፍለ ጦሩ በመስጠት ህይወታቸውንም ማትረፍ ችለዋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ወግዲ ወረዳ ዙሪያ ከንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት መቋቋም አቅቶት ከመቶ በላይ ንፁሃኖችን መጨፍጨፉ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በዚሁ በወግዲ ወረዳ ዙሪያ በዘሞድ ከተማ ከ150 ኩንታል በላይ የማህበረሰቡን እህል ዘርፎ በመውሰድ ፀረ-ህዝብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
👍2🙏1
የአደረጃጀት ዜና!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክ/ጦር አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የአመራር መተካካትና አጠቃላይ ግምገማ አድርገዋል።

በተጨማሪም በባለፈው በነበረው አጠቃላይ የ102ኛ ኮር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የድርጅት አመራር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ዞብል አምባ ክፍለጦር ይባል የነበረውን ስያሜ 12ኛ ክፍለጦር በማለት እንዲጠራ የተወሰነ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ- ሂስ(ግምገማ) በማድረግ በቀን 5/06/2018 ዓ.ም አዳድስ የስራ ሀላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል።

1.ወታደራዊ አዛዥ...........አርበኛ ሀብተማሪያም መንበሩ
2.ም/ወታደራዊ አዛዥ........አርበኛ ነጋ ከበደ
3.ዘመቻ መሪ ..................አርበኛ ጌታሁን ደመቀ
4.ም/ዘመቻ.መሪ..............አርበኛ አማረ ሞገስ
5.የፖለቲካ መምሪያ...........አርበኛ መ/ር በላይ አረፍ
6.ወታደራዊ አሰተዳር.........አርበኛ ሞላ ዝናቤ
7.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ አሸናፊ በላይ
8.ኦርድናንስ መምሪያ...........አርበኛ ሻምበል ሞላ
9.ም/ኦርድናንስ.................አርበኛ አድሱ ሞላ
10. ጤና መምሪያ.............አርበኛ ወርቁ ተበጀ
11.ስልጠና መምሪያ..........አርበኛ አለሙ መልኩ
12.ሎጂስቲክ መምሪያ........አርበኛ ኑርየ ይማም
13.ም/ሎጂስቲክ...............አርበኛ አማረ ይርዳው
14.ፋይናንስ ሀላፊ..............አርበኛ ሙሉጌታ ዘውዱ
15.የህዝብ ግንኙነት...........አርበኛ ዳዊት ጌትነት
16.ሀብት አፈላላጊ..............አርበኛ ነጋ ፈንታው
17.የህግ መምሪያ..............አርበኛ አበበ በላይ
18.ሴቶች ጉዳይ..................አርበኚት ቤቲ ተሾመ
19.የክ/ጦር ዳኛ................አርበኚት አበባ ሲሳይ
20.ንብረት ክፍል.........አርበኛ ጥላሁን አየነ (አባ ጫንቃ)

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
5👍1
አንድነታችን ሸዋ፣ ወሎ እና ጎጃም ላይ የተከፈተብንን ጥቃት በመመከት ጎንደር ላይ ባገኘነው የድል ማህተም ታትሟል።

የካቲት 07 ቀን 2018 ዓ.ም

የጎንደሩን ድል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
ሀ) መግቢያ
``````

የጨፍጫፊው ብልፅግና አገዛዝ የሰሞኑ አዲስ ቀጠናዊ ጦርነት ድግስ ምስጢር አማራን የማጥፋት ፕሮጀክት ነው። በሁለት ቀን ትጥቅ አስፈትቸ አማራውን በባርነት እገዛለሁ ርስቶቹንም መደራደሪያ አደርጋለሁ በሚል እብሪት በህዝባችን ላይ ጦርነት ያወጀው አገዛዝ ቅስሙ የተሰበረው ገና ጦርነቱን በለኮሰው የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ነበር።

የመጀመሪያውን ኮሎኔል ባህርዳር ከተማ ላይ የማረክነው ጠላት በጎጃም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በወሎ እና በወለጋ ቀጠናወች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያወችን፣ ሚሊዮን ተተኳሾችን፣ ታንክና ዙ-23 ን ጨምሮ ከባድ መሳሪያወችን ማርከነዋል።
በርካታ አሃዶችን በተለይም በክፍለ ጦር እና በሬጅመንት ደረጃ ያሉትን ከእነ አመራሮቹ በተደጋጋሚ ደምስሰናል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምርኮኞወችን ወደ ቤተሰባቸው ልከናል ከፊሉንም ለቀይ መስቀል አስረክበናል። የክልሉን ዋና ከተማ ጨምሮ በሁሉም ከተሞች ጠላት ላይ ከባድ ምቶችን አሳርፈናል። በዚህ የትውልዱ አስደናቂ ተጋድሎ ነባሩን የብአዴን መዋቅር በማፈራረስ አገዛዙን አየር ላይ የተንሳፈፈ ፊኛ ማድረጋችንን መሬት ያለው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም በገሃድ የመሰከረው ሐቅ ነው።
በዚህም ምክንያት አገዛዙ በውጊያ እንደማያሸንፈን ሲያውቅ ሌሎች የጥፋት እና የማደናገሪያ ስልቶችን ሲጠቀም ቆይቷል። ከእነዚህ የጥፋት ፕሮጀክቶቹ መካከልም:-
1) ንፁሃን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት

የአማራን ህዝብ ማንበርከክ የአገዛዙ የጦርነት ተልዕኮ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በህዝቡ ላክ በድሮን፣ በጀትና በሌሎችም ከባድ መሳሪያዎች ድብደባ በማድረግ የኃይል የበላይነትን ማሳዬት እና የወገን ኃይል ላይ የስነ ልቦና ጫና መፍጠርን እንደ ስልት ለመጠቀም ሞክሯል። በዚህም የንፁሃን መኖሪያ መንደሮችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ቤተ-እምነቶችንና ጤና ተቋማትን ጨምሮ ኃላፊነት በማይሰማው መልኩ ጭፍጨፋዎችን ፈጽሟል፡፡ 
በዚም ምክንያት በርካታ ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዉያንን ጨምሮ ሲቪሊያንን በገፍ ጨፍጭፏል። ይሁን እንጅ የአገዛዙ ጭካኔ ህዝባዊ መሰረታችንን ከማጠንከር እና አረመኔነቱን ከማረጋገጥ ያለፈ ፋይዳ አላመጣለትም።

2) ብሔራዊ አጀንዳወችን እንደ ማደናገሪያ ስልት
````````````````````````````````````````````````

በራሱ ህዝብ ላይ ጨካኝ አረመኔ ተግባራትን የሚፈፅም አገዛዝ ለሀገር ክብር እና ብሔራዊ አጀንዳወች ትኩረት ሊሰጥ አይችልም። በተለይም ግጭት ጠማቂው የብልጽግና አገዛዝ የሀገርን ሉዓላዊነት አሳልፎ ለመስጠት የማያመነታ ስለመሆኑ ባለፉት ሰባት ዓመታት ሀገር ውስጥ አንዱን በአንዱ ላይ በማስነሳት ግጭትን በመለኮስ በፍቅር የሚኖሩትን ማህበረሰቦች ሳይቀር ለራሱ ፕሮጀክት በሚመቸው መልኩ ስውር ጦር በማስገባት ሲወጋና ሲያስወጋ ቆይቷል፡፡
ከዚህም ባሻገር ለዘመናት በመከባበርና በፍቅር የኖሩ አጎራባች ሀገራት ድረስ በመዝለቅ እርስ በእርስ እንዲከፋፈሉ አለማቀፍ የሉአላዊነት ህግን በመጣስ ታጣቂዎችን በማሰልጠንና በማሰመራት ለጎረቤቶቻችን ጠንቅ እየተከለ ይገኛል፡፡

አብይ አህመድ የቀጠናው የሰላም ፀርና አተራማሽ ስለመሆኑ በየጊዜው ያደረጋቸው መርህ አልባ ስምምነቶች፣ የአደባባይ መግለጫዎች እና መሃላዎች በቂ አመላካች ናቸው። ከምንም በላይ የቱርክ፣ የዩናይትድ አረብ ኤምሬት፣ የቻይና፣ የአዘርባጃን ድሮኖች እና ሌሎች ዘመናዊ የጦር መሳሪያወችን በአማራ ህዝብ ላይ በመሞከር የሀገሪቱን ህዝብ የአዳዲስ የጦር መሳሪያ መሞከሪያ ያደረገው አገዛዝ የኢትዮጵያን ክብር እና ሉዓላዊነት ተራ ሸቀጥ እንዳደረገው ሌላኛው ማሳያ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንድ ጊዜ በባህር በር ጉዳይ፣ ሌላ ጊዜ በሉዓላዊነት እና የወደብ ጉዳይን አጀንዳ በማድረግ የህልውና ተጋድሎ ውስጥ የገባን ህዝብ ለማዘናጋትና በሌላ ትኩረት ተጠምዶ ዋናውን አጀንዳውን ቸል እንዲለው እና የትግላችንን ማህበራዊ መሰረት ለመናድ ጥረት አድርጓል።
በእርሻ ማሳው፣ በንግድ ቦታው፣ በአምልኮ ቦታወች እና በመኖሪያ ቤቱም ጭምር እያለ የሚጨፈጭፈውን ህዝብ በዚህ መልኩ ለማታለል ያደረገው ሙከራም አገዛዙ በፖለቲካ መቀንጨር መጠቃቱን ያረጋገጠ እና የከሸፈ ጉዳይ ነው።

3) የስሁት ትርክቶች ግንባታ ሙከራ

የፋኖ ኃይል ከአብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ጦርነት በጀመረበት ወቅት አገዛዙ ከሌሎች ኃይሎች ጋር አፍላ ፍቅር ላይ ነበር። በተለይም ከአገዛዙ ሰራዊት የመጀመሪያዎቹን በርከት ያሉ የቡድን መሳሪያወች በመማረክ ኃይላችንን ባጠናከርንበት ወቅት አገዛዙ ከትግራይ ኃይልም ጋር ሆነ ከሌሎች የቀጠናው ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ አልገባም ነበር። ፋኖ በራሱ አቅም ወራሪውን ሰራዊት በመመከት ወደ መልሶ ማጥቃት ይሸጋገራል ብሎ ማሰብ የተሳነው የብልፅግና ቡድን ተከታታይ ባዳ እና ባንዳ የሚሉ መሰረተ ቢስ ፍረጃወችንም ሊያለማምድ ሞክሯል። 

የማጥቃት ዘመቻወችን በራሱ የእብሪት እቅድ ጀምሮ በሂደት መቋቋም ያልቻለውን ኃይል በስም ማጥፋት እና በሀሰት ትርክት ዘመቻ ለማዳከም ሞክሯል። አንድ አይሆንም በትነነዋል የተባለው ፋኖ በረቀቀ የአመራር ጥበብ እንደ አለት የጠነከረ ድርጅት ሲፈጥር "በሌሎች ኃይሎች ትዕዛዝ" ነው፤ "የጠላት ድጋፍ" ነው፤"አንደኛው ወደዚህ ሌላኛው ግን ወደዚያ" ነው በሚል መቀባጠር ጀመረ። ይህም አልበቃ ብሎት ሎጅስቲክ፣ ፕሮፖጋንዳ፣ እና ፖለቲካ የሚሰፍርልን ሐይል እንዳለ አድርጎ ያለማቋረጥ በመለፈፍ ላይ ይገኛል።

ከገባበት የእብሪት ጦርነት መውጫ ያጣው አገዛዝ ለአማራ ህዝብ አጀንዳዎች በመታመን፣ በብሔራዊ ጀግንነትም ሆነ በራስ በቅነት በመታገል የፋኖን ሰራዊት እና አመራር የሚቀድም እንደሌለ ጠንቅቆ ያውቃል።
4)የጦርነቱን ገፅታ ቀጠናዊ የማድረግ ግብግብ
`````````````````````````````````````````````````

ኢትዮዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ የምትታወቅባቸውን የውጭ ግንኙነት መርሆወችን በመጣስ በሶማሊያ፣ በሱዳን እና ኤርትራን ጨምሮ የዲፕሎማሲ ሀ ሁን በጣሰ መንገድ የትንኮሳ ተግባራትን ፈፅሟል። ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ እና ዚምባቡዌን ጨምሮ ለአፍሪካ አገሮች ነፃነት የቀዳሚነት ሚና የተጫወተችው ኢትዮጵያን ገፅታ እና ታሪክ በማይመጥን ሁኔታ በሌሎች ሀገራት ላይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶችን ጭምር አድርጓል። በዚህም ከአማራ ህዝብ ጋር የገባበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ቀጠናዊ እና ዓለማቀፋዊ መልክ እንዲኖረው ሞክሯል።

የአማራን ህዝብ የተጋድሎ ትርክት በቀጠናዊ ጦርነት ውስጥ እንዲዋጥ በማድረግ በስኬት ላይ ያለውን የህልውና የተጋድሎ በአርቴፊሻል ብሔራዊ ጀብደኝነት ለማደብዘዝ ጥረት አድርጓል። ይህም እንደሌሎች ማደናገሪያዎች ከጅምሩ የከሸፈ ነው።
ለ) የድርጅታችን ውልደት

አገዛዙ ቢሊዮን በጀት መድቦ ብዙ የደከመበት ጉዳይ የፋኖ ኃይል አንድ ወጥ ድርጅት እንዳይኖረው ድርጅት ከተፈጠረም እንዳይፀና ማድረግ ነበር። ገና የአንድነቱ ውይይት መስመር መያዝ ሲጀምር የቆዩ የጠላት ተላላኪዎች ሮጠው ጠላት ጉያ በመሸሸግ የአሉባልታ ናዳ የሚያወርዱት የድርጅቱ መፈጠር የተልዕኳቸውን ክሽፈት ስለሚያንፀባርቅባቸው ነበር። ፋኖ መስለው በመተወን ከመወለድ ያላስቀሩትን ተቋም በሐሜት ሊያፈርሱ መሞከራቸው ከንቱ ድካም ሆኖባቸው ህዝብም ታሪክም እየሳቀባቸው ይገኛል።
የውስጥ ሰርጎ ገቡን ሴራም የውጭ ጠላትን ሁሉን አቀፍ የብረት አጥር ሰባብሮ አንድ ተቋም መውለድ የትውልዱ ታሪካዊ ግዴታ ነበር እና በድል ተወጥተነዋል።

ሐ) ከድርጅት ምስረታው ማግስት የተዘጋጀ የጥፋት ድግስ
````````````````````````````````````````````````````

የድርጅቱ መወለድ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የከተተው አገዛዝ አለኝ የሚለውን የጦር መሳሪያና የማጥቃት ስልት ተጠቅሞ ዘመቻዎችን በማድረግ በዋናነትም ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጥቃት በማድረስ የድርጅት ምስረታ ሂደቱን ማደብዘዝ እና የፕሮፖጋንዳ እና የስነ ልቦና የበላይነት ለመያዝ ተፍጨርጭሯል።

በተለይም በሸዋ፣ በወሎ እና በጎጃም ቀጠናዎች ኔትወርኮችን በማጥፋት የተጀመረው ዘመቻ በሁሉም ቀጠና ባለው ሰራዊት የተጠናከረ መከላከል ተደርጎበታል። አልፎ አልፎም በመልሶ ማጥቃት ድሎችን መጎናፀፍ ተችሏል። በተለይ በሸዋ የተሰማራው የአገዛዙ ኤሊት ኃይል ያሰበውን ሳያሳካ በሚገባ ተመክቷል። በእነዚህ አካባቢዎች በተፈፀመ ቀጥተኛ የንፁሃን ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ከመረሸናቸውም ባሻገር መንደሮች በከባድ መሳሪያ ወድመዋል፤ የቤት እንስሳት ተጨፍጭፈዋል። ይህም የአገዛዙን አረማኔያዊ ባህሪ በግልፅ ያሳዬ ሆኗል።

መ) የአገዛዙ የበቀል እርምጃ በደብረ ታቦር እና
አካባቢው:-

ይህ የሽብር እና የቀውስ አገዛዝ ብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮችን በሸፈነው የጎንደሩ ተጋድሎ የደረሰበትን ከባድ ውርደት በጦር ሜዳ ውሎ ማካካስ ስላልቻለ ሆን ተብሎ በታቀደ ሁኔታ ከውጊያው ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ንፁሐን በመጨፍጨፍ በሽብር መንገድ ወታደራዊ ሽንፈቱን ለመቀልበስ ሰፊ ጥረት አድርጓል። በተለይም የደብረ-ታቦር ከተማ እና አካባቢው ህዝብ እና የህዝብ ተቋማት ላይ የአለማቀፍ ሕግን በመጣስ ተከታታይ የድሮን ድብደባዎችን አድርጓል።
በዚህም ደብረ-ታቦር ከተማ ላይ ብቻ ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአስራ ስድስት ጊዜ በላይ ስትራቴጅክ ድሮኖችን ያለምህረት በመጠቀም የአረመኔነት ባህሪውን አሳይቷል።

በዚህ ጥቃት የፋርጣ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ፣ የገብርየ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ፣ የዞን ጤና መምሪያ፣ የዞን ሲቪል ሰርቪስ እና ፋይናንስ ቢሮ፣ የቴዎድሮስ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ማህበራዊ ተቋማትን እና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ተቋማት አውድሟል። በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ እና በየቤታቸው የነበሩ የከተማ ነዋሪወችንም በድሮን ጨፍጭፏል።

ይህ አሳፋሪ ተግባር በሰራዊታችን ላይ ያደረሰው ተጨባጭ ጉዳት ካለመኖሩም በተጨማሪ የውጊያውን ውጤት በመለወጥ ደረጃም ሆነ ሰራዊታችን ደብረ ታቦርን ጨምሮ በሁሉም አካባቢወች የተደረገለትን ህዝባዊ እና ደማቅ አቀባበል ማደብዘዝ እንኳን አልቻለም። የድሮን ቦንቦች ጥቃት ያልበገረው የድርጅቱ ሰራዊት የከተማው እምብርት ድረስ በመግባት የሚፈልጋቸውን ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በሚገባ በማከናወን አይበገሬነቱን እና ጀግንነቱን አሳይቷል።

ሠ) በጎንደሩ የወንድማማቾች ድል የተገመደው አፋብን
`````````````````````````````````````````````````````

በሸዋ፣ በጎጃም እና በወሎ ኔትወርክ በማጥፋት የጀመረው የአገዛዙ ጥቃት ሸዋ ላይ በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ እና በአሳምነው እዝ ሰራዊት በቅንጅት፤ በደቡብ እና ምዕራብ ወሎም በምኒልክ እዝ ብርቱ ተጋድሎ ተመክቷል።

ጎንደር ላይ መሀል አርማጭሆን እና ሁለቱን በለሳወች ባካለለው ማእከላዊ የጎንደር ክፍል፤ ከስማዳ እስከ ደብረ ታቦር፤ ከደራ ሀሙሲት እስከ እብናት፤ ከጋይንት እስከ አለምበር ድረስ በሸፈነው ደቡባዊ የጎንደር ክፍል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የበላይ ዘለቀ እዝ እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በጋራ በፈፀሙት ልዩ ተጋድሎ ከደቡብ እና ማእከላዊ ጎንደር በርካታ ወረዳወች የአገዛዙን ሰራዊት በመጠራረግ የድርጅታችን አንድነት በድል እንዲታጀብ አድርገውታል። ከ2540 በላይ የጠላት ኃይል ምርኮኛ ሲሆን በርካቶችም እጅ ለመስጠት በመዘግየታቸው ምክንያት ተደምስሰዋል፡፡

በዚያው ልክም የአፋብን ሰራዊት ከነፍስወከፍ እስከ ድሽቃ ድረስ ለማስታጠቅ ተችሏል፡፡ የሎጅስቲክ እጥረቱንም እንደተለመደው ከጠላት በመረከብ ተንበሽብሷሻል፡፡

በዚህ የጠላት አቅም እና አቋም ልፍስፍስነት ገሃድ በወጣበት ወታደራዊ ኦፕሬሽን የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ ቋንቋ ሲደበላለቅ ታይቷል። የአገዛዙ ባሪያ የሆነው ካድሬ በሚያሰማራቸው አክቲቪስቶቹ በኩል እርስ በእርሱ መካሰስ አልበቃ ብሎት ለህዝብ የሚያስብ በመምሰል ፋኖ ከተማ ላይ ውጊያ ማድረግ እንደሌለበት ለመምከርም ሞክሯል። የእምነት ተቋማትን ምሽግ አድርጎ የሚዋጋን ጨፍጫፊ ሰራዊት የፕሮፖጋንዳ ድጋፍ የሚሰጥ ስብስብ እንደ ጨዋ ለመጫወት መሞከሩ በመጨረሻዋ ሰዓት ላይ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችን ግልጽ አድርጎ አሳይቶናል።

ህሊናቸውን እና ህዝባቸውን በሆዳቸው ይሸጡ የነባሩ ብአዴናዊ በሽታ ተጠቂዎችን ማደናገሪያ በመረማመድ የልዩነቱን ሸለቆ የደፈነው ባለማተብ ትውልድ መራር መስዋዕትነት በከፈለበት የጎንደሩ ተጋድሎ መላው የአማራ ህዝብ እና የድርጅታችን አመራር ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶታል። በተመሳሳይ ጊዜ ምዕራቡን የጎንደር ክፍል ሊያካልል በጃዊ እና መተከል የዘለቀውን የጠላት ኃይል ላይ ከባድ ምት በማሳረፍ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያችን የማረከው የቴወድሮስ ዕዝ ለጎንደሩ ድል ሌላ ድምቀት ጨምሮለታል።

የድላችን የምስጢር ቁልፍ አንድነታችን ላይ መሆኑ በተግባር በተተረጎመበት የጎንደሩ ተጋድሎ ለማረክነው የጠላት ሰራዊት ርህራሔን፣ ሰብአዊነትን እና ወገናዊነትን በማሳዬት እጅ ሊሰጥ ያልፈቀደውን ደግሞ እስከ መጨረሻው በመዋጋት የአማራን ህዝብ የሞራል ልዕልና ያሳዬንበትም ሁኔታ ነበር። የጠላትን ስስ ብልት በተደጋጋሚ በመምታት ትግሉን በፅኑ አለት ላይ ያቆሙት የጎንደር ቀጠና የሰራዊቱ አባላት በራስ በቅነት አመራር እና ስምሪት በመስጠት ኩራት የሆኑትን ወታደራዊ አመራሮች ለበለጠ ድል የሚያነሳሳ ሞራል ጭምር ኖኗል።

በመጨረሻም ሰራዊታችን በየደረሰበት ሁሉ ተባባሪ በመሆን እና ፍቅር በመስጠት ከጎናችን ለቆመው የጎንደር ህዝብ ልዩ ምስጋና እያቀረብን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ነፃ በወጡ አካባቢዎች የህዝብ አስተዳደር መዋቅሮችን በመዘርጋት፣ ጠላትን ደግሞ በፅናት በመፋለም ለአማራ ህዝብ ነፃነት ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የወትሮ ዝግጁነትን ባነገበ አመራር እና ሰራዊት የታነፀ መሆኑን እናረጋግጣለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
🙏1
ቀን 07/06/2018 ዓ.ም

ከአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ 3ኛ ኮር አስተባባሪ ግብረሀይል የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ህዝብ የገጠመውን ስርዓትና መዋቅራዊ መር ለህልውናው ስጋት በሚሆን ደረጃ በተፈፀሙ ግፍና በደል ምክንያት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቀልበስ እና ዘላቂ የአማራን ህዝብ መብትና ጥቅም ለማስቀጠል ሁለንተናዊ የትጥቅ ትግል ከጀማመረ ሶስት አመታትን ሊያስቆጥር ውስን ወራት ቀርተውታል። የህልውና ትግሉ ከየት ወደ የት በሚለው መነሻና ማዳረሻ ፤ በትግሉ ሂደትም ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሄዎቻቸው ፤ በፖለቲካዊና ወታደራዊ ጥንካሬዎቻችንና ድክመቶቻችን ፤ ዲፕሎማሲያዊ ስራወቻችንና ውጤቶቻቸው እና መሰል ጉዳዮችን እንደ ተቋም በላይ ዕዝ አመታዊ ግምገማና ውይይት አድርጎ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
እንደተቋም አቅጣጫዎችን ሰጥቶ በእየ ኮሩ የተቋም አመራሩን በሙሉ በግብረሀይል ደረጃ አዋቅሮ የአመራር ስምሪት ተሰጥቶ ወደ ስራ ገብቶ ቆይቷል። በዚህም መሰረት ወደ 3ኛ ኮር በአርበኛ አስቻለው በለጠ አስተባባሪነት ፣ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው ፣ አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ ፣ አርበኛ እያቸው ብርሀኑ እና አርበኛ አስፋው ሰርፀ በተሰጣቸው ተቋማዊ ተልዕኮዎች ይዞ በቀጠናው ሲሰራ ቆይቷል።
ግብረሃይሉ ከሰራቸው ስራዎች መካከልም በቀጠናው የነበሩ ችግሮችን መለየትና የመፍትሔ ሀሳብ ማስቀመጥና ችግሮችን መፍታት ፤ ፖለቲካዊና ወታደራዊ የድርጅት አቋሞቻችንን ፤ ወቅታዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችን ፤ የለውጥ መሪነት እና ውሳኔ አሰጣጥ እና በመሰል ጉዳዮች ግንዛቤና ስልጠና እንዲሁም አጠቃላይ በቀጠና የኮር ስራ አስፈፃሚ አፈፃፀም ከክፍለ ጦር አመራሮች ጋር መወያየት እንዲሁም ከነበሩት ቀጠናዊ ችግሮችና ከተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች እና አፈፃፀምን መሰረት እንዲሁም ለትግሉ ካላቸው ቀናነት ፣ ቁርጠኝነትና ፣ ታማኝነትና በህዝብና በሰራዊቱ ካላቸው ቅቡልነት እና መሰል ጉዳዮችን ታሳቢነት በማድረግ የኮር ስራ አስፈፃሚ መልሶ የማደራጀት ስራ በሚከተለው መንገድ ተሰርቷል።
1. አዛዥ .......ጋሻው መብራቱ(ሸሪፎ)
1.1. ወ/ቃል አቀባይ.....ሳሚ
1.2. ፅ/ቤት .......አብረሀም
1.3. ህግና ስነምግባር ክፍል......ለምለሙ
1.4. ወታደራዊ መረጃና ደህንነት....... አዳነ
2. ምክትል አዛዥ........መ/አለቃ ባምላኩ
2.1. ዘመቻና ....... ሃ/አለቃ አስራት ጌታቸው
2.2. ሀይል ስምሪት ......
2.3. መገናኛ ....... ስመኘው
2.4. ስልጠና ...... ሃ/አለቃ አለሙ ሙሌ/ደሳለኝ ራስ ደጀን
2.5.  ቃኝና መሀንዲስ .......ማርየ በለጠ
3. የፖለቲካ ኃላፊነት........ ፃዲቅ ዋለልኝ
3.1.  ም/ፖለቲካ ኃላፊነት ..... ማርሸት
3.2.  አደረጃጀት .......ማምነው
3.3.  ህዝብ ግንኙነት ......ዘመነ ተሾመ
3.4.   ህዝብ አስተዳደር ጌታቸው ጌጡ
3.5.   ቀጠናዊ ትስስር .... ወልዴ
3.6. ትምህርትና ስልጠና.... እሸቱ/ቄስ ገ/ስላሴ ነሲቦ
3.7.   ማህበራዊ ጉዳይ..... ጤናው አየነው
3.8.   ወጣቶችና ሴቶች ......አታላ አለሙ
4.      ወ/አስተዳደር ኃላፊ ........ይርጋ ክቡሬ
4.1.   ም/ወ/አስተዳደር ........ማሩ አዴ
4.2.    የሰው ሀይል........ በውቀት አላቸው/ክቡሬ አገሩ
4.3.    ፋይናንስና ግዥ ......ማርሸት ንጋት/መልካሙ ሙሉ
4.4.    ሀብትና ንብረት አፈላላጊ ....
5.      ሎጂስቲክ ኃላፊ ........በሬ አወቀ
5.1.    ም/ሎጀስቲክ ........ብርሀን ወርቄ
5.2.    ኦርዲናንስ ........ ሀብታሙ ምሕረቴን/አድባሩ
5.3.    ህክምና ክፍል ሀላፊ ....... ቢልልኝ
6. ኦዲት ክፍል ሰብሳቢ .......ጣመ ዋለልኝ
ለህልውና ትግሉ ደጋፊ ማህበረሰብ ፤ ለትግሉ ባለቤት የአማራ ህዝብም ሆነ በቀጠናው ላለ ሰራዊታችንና ህዝባችንም ማሳሰብ ምንፈልገው ቀሪ ስራዎችንም ከአዲሱ የኮር ስራ አስፈፃሚ ጋር በጋራ እንደሚፈፀሙ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናልና ለዚሁ ሁሉም የቀጠናው ማህበረሰብ እና ሰራዊት ቀና ትብብር እንድታደርጉ አደራ ማለት እንፈልጋለን። በተለይም የህልውና ትግሉን ወደ ጎን በማድረግ ከተቋማዊ መርህና አሰራር ባፈነገጠ መንገድ የግልና የቡድንን ጥቅምና ስልጣንን መሰረት በማድረግ የህልውና ትግሉን ወደ ኋላ ሚያጓትትና የህዝባችንና የሰራዊታችን አደራ በማይወጣ እንዲሁም የህዝባችንን እንግልት እና ብዝበዛ የማንታገስ እና በቁርጠኛነት እርምጃ ስለምንወስድ እሄን በመገንዘብ ህዝባችን እና ሰራዊታችን ከጎናችን እንዲሆን ማሳሰብ እንፈልጋለን።

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የበላይ ዘለቀ ዕዝ ግብረሀይል
አጅሬ ፣ ጎንደር ፣ አማራ ፣ ኢትዮጵያ
የካቲት 07/2018 ዓ.ም
🙏1