ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አንድነት በተግባር የተገለጠበት የዓምሐራ ፋኖ በደብረ ታቦር ከተማ
[የካቲት 04/2018ዓ.ም]

01 👉👉👉 13:00 ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ በደብረ ታቦር ከተማ

የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትን ለማምበርከክ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ለየካቲት 04/2018ዓ.ም የተጠና ዕቅድ ሲያዘጋጅ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክ/ጦር ገ/መሥቀል ብርጌድ አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጋራ የውጊያው ዋዜማ ከ04:00 ጀምሮ ሌሊቱን የደብረ ታቦር ከተማ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥረው ያለ ተኩሥ የአገዛዙ ወታደሮችን ሲያፈራርሥ አድሯል። ውጊያውንም ከማለዳ እሥከ ጠዋቱ 3:20 ደብረ ታቦር የከተመውን የአገዛዙ ታጣቂ በአባታቸው ውባንታዊ ሰይፍ ሲያናፍጡት አርፍደዋል። ከጠዋቱ 03:20 በኋላ የበላይ ዕዙ ግዙፍ ጉና ክፍለ ጦር እና የጠቅላይ ግዛቱ ክፍለ ጦሮች በመናበብና የውጊያ ቀጠናዎችን በመከፋፈል ጠላትን ሲያምበረክኩ ውለዋል። ከቀኑ 6:30 ገደማ ጀምሮ የ5ኛ ኮር ሰራዊት በአርበኛ ሻምበል ሙሉሰውና አርበኛ ግዛቸው አሌ የውጊያው አካል ሆኗል።

በውጊያው ተሳታፊ የሆኑ የአፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ እና ጎንደር/ጠ/ግ/ዕዝ ክፍለ ጦሮች፦
👊ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
👊ግዙፉ ጉና ክፍለ ጦር 05ቱም ብርጌዶች
👊የዕቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት
👊የጀነራል ፋንታ በላይ ክፍለጦር የተውጣጣ ሰራዊት
👊የተራራው ራሥ ጉና ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት
👊የአፄ ኢያሱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት
👊የዞዝ አምባ ንጉሱ ክፍለ ጦር የተውጣጣ ሰራዊት እና
👊የጋፋት ክ/ጦር 01 ሻለቃ
👊ታሪኳን በወርቅ የደም ቀለም የጻፈችው የነበልባሉ ፎገራ ክ/ጦር አካል የሆነችው ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ እና ከነበልባሉ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አካላት ከወረታ እሥከ ዓለም ሣጋ የሸፈኑ

የጠላት አሰላለፍ
የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ቅጥረኞች ከ13 ወረዳ የነበረው የአድማ ብተና፣ ሚሊሻ፣ ፖሊሥና ከሁሉም ወረዳ የተሰባሰበው ከሃዲ ወዶ ገብ ነው። ከቀኑ 5:30 ጀምሮ ደግሞ
በመጀመሪያው ዙር ከባሕር ዳር የመጣ 250+ መከላከያ፣ 200+ አድማ ብተና እና 60+ ወዶ ገብ ከሐዲ የጸዳሉ አጃቢዎች ከ02 ዙ-23፣ 02 ዲሽቃ፣ 120 ሞርታር ይዞ የመጣውን
በመቀጠል ከባሕር ዳር የመጣው 54 ተሽከርካሪ መከላከያ 03 መድፍ፣ 02 ታንክ፣ ከ17 ዲሽቃዎች
3ኛ ዙር ከአርኖ ጋርኖ በ10 ተሺከርካሪ የመጣውን መከላከያ
4ኛ ዙር ከአዲሥ ዘመን የመጣውን አድማ ብተና

አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጋራ በሥፋት የመጣውን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መደበኛ ውጊያ ገጥመውት ውለዋል። አገዛዙ የሰራቸው የኮንክሪት ምሽጎች ተሰባብረዋል።

ተሥፋ የቆረጠው የአቢይ አሕመድ ፋሽሥት አገዛዝ ለደብረ ታቦር ከተማ 07 ድሮኖችን መድቦ ውሏል። 14 የድሮን ጥቃቶችን በደብረ ታቦር ከተማና ታቦር ዙሪያ ቦታዎች ጥሏል። ሞርታር ክርሥትያን ታደለ ብርጌድ ላይ ብቻ 23 ጊዜ ጥሏል፤ ነገር ግን የሲቪል መኖሪያ ቤቶችንና የመንግሥት ትምሕርት ቤቶች ነው ያወደመው። ነገር ግን በዚህ የድሮን ጥቃት በጅምላ የተመቱት አገር አማን ብለው የተቀመጡ የማሕበረሰቡ አካላት ናቸው። ማሰቢያውን የተቀማው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከወጂ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማ ድረሥ 02 ዙ-23፣ ቁጥሩ ያልታወቀ ሞርታር፣ ከ17 በላይ ዲሽቃ፣ 03 መድፍ፣ 02 ታንክ እና መሰል የቡድን መሳሪያዎችን ቢይዝም ጥበበኛው የአማራ ፋኖ በክንዱ ሲያደቅቀው ውሏል።

ከ11:30 በኋላ የፀዳሉ ደሴን ወደ ዓለም በር መምጣት መረጃው የደረሳቸው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በፍጥነት ወደ ቦታው አምርተው ከበባ ፈጽመዋል። ፀዳሉ ደሴን መከላከያው ወደ ባሕርዳር እንዲያመልጥ ሲያደርጉ ራሳቸው ዋጋ ከፍለዋል። ምሽት 01:00 ፀዳሉ ደሴ ከመማረክ ያመለጠበት መዳኛ ሠዓቱ ሆኖ ተመዝግቧል።

ሙሉ ቀናትን በተደረገው አውደ ውጊያ ከሁሉም ሰራዊት የተማረከውን ቅጥረኛ፣ መሣሪያ፣ ተተኳሽና ቁሥ በነገው ዕለት በቪዲዮ እና በማሥረጃ የምናቀርብ ይሆናል።

02.👉👉👉ደራ ሐሙሲት
ከአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በትናንትናው ዕለት 01 ዲሽቃ፣ ከ115+ ክላሽና አንድ ኦባማ ሙሉ የክላሽና የዲሽቃ ተተኳሽ መማረካቸው ይታወሳል። በተመሣሣይ ከትናንት የተረፈውን 01 ክላሽ በጠዋቱ ሐሙሲት ከተማ ላይ ማርከውታል።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
2🙏1
ጀምበር የጠለቀችበትና ጣዕረ ሞት ላይ ያለው ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን እርምጃ እየወሰደ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ ንብረትም እያወደመ ነው።

ሽንፈቱን በተግባር የተረዳው ተረኛ ስብስብ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ነውና የቻልኩትንና ያገኘሁትን የአማራ እና አማራ አጥፍቸ ነው በማለት ሲጠፋ አመታቶች አስቆጥሯል።ዛሬ ግብዓተ መሬቱ ሲቃረብ ደግሞ በክፋትላይ ክፋት በጭካኔ ላይ አረመኔዊነቱን በንፁሀን ላይ እያሳየን ይገኛል።በዛሬው እለት ደቡብ ወሎ ወረኢሉ ወረዳ ላይ የሶስት አርሶ አደሮች ቤት ከነሙሉ ንብረቱ ቤንዚን አርከፍክፎ ያቃጠለ ሲሆን ቤት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው አርሶደሮች ፦

1. አቶ አያሌው አህመድ ሁለት ቆርቆሮ ቤት
2. አቶ አሊ ይማም ሶስት ቆርቆሮ ቤት
3. አቶ ከበደ ማህሙድ ሁለት ቆርቆሮ ቤት

የሶስቱም አርሶደሮች ከነሙሉ ንብረቱ በሀገር አፍራሹ የብልፅግና ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሰየመ የአብይና ሽመልስ አማራን የማጥፋት፣የማቆርቆዝና የማዳከም ልዩ ተልኮ የተሰጠው ተላላኪ ቡድን አማራ መቸም የማይረሳውና ይቅር የማይለው ነውር እየፈፀመ ይገኛል።

በመጨረሻም ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጋር ሆናችሁ ወገናችሁ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀማችሁና ቤት ንብረት እያወደማች ያላችሁ ሃይሎች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡና ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦር
የካቲት 4/2018 ዓ.ም
3💔1
ኑ ጠላትን በጋራ ታግለን የአማራን ህዝብ ሕልውና እናረጋግጥ!
የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ የምህረት አዋጅ
ሀ) መግቢያ:
አረመኔው የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጀመረውን ጦርነት ለማሳካት ይችል ዘንድ በርካታ አረመኔያዊ ተግባራትን ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል።
የአማራን ህዝብ ያለ ልዩነት ለመፍጀት አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ እየተጠቀመ ያለው አገዛዝ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጂኦ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በማገልገል በፈጠረው የማውደም አቅም ተማምኖ በከፈተው ጦርነት ራሱ እየተለበለበበት ይገኛል።

የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል ነባሩን የብአዴን መዋቅር በመጠቀም ባሰባሰበው የምሊሻ እና የአድማ ብተና ኃይል ከፋኖ ጋር እንዲዋጋ እና ህዝባችን በሁለት ጎራ ተሰልፎ እንዲጠፋፋ የሞከረበት መንገድ አንደኛው ነው።
በአንድ ህዝብ መካከል እና በኢትዮጵያዊያን መካከል እንዲሁም ቀጠናዊ ጦርነቶችን በማስነሳት ለአፍሪካ ቀንድ የቀውስ ዘበኛ የሆነውን አገዛዝ በወንድማማችነት እና በጥበብ በማስወገድ የጋራ መንግስት መመስረት እንደሚገባን በተደጋጋሚ ጥሪወች ስናስተላልፍ የቆዬን መሆኑ ይታወቃል።
በተለይም ከሰሞኑ ደግሞ ጠላት በአንድ በኩል የህዝብ መገናኛ መስመሮችን በመዝጋት ንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ እያደረገ በሌላ በኩል ደግሞ ብሔራዊ አጀንዳ ያለው እና ለሀገር ብሔራዊ ተልዕኮ የተሰለፈ በመምሰል የሚያደርገውን የማደናገሪያ ስልት በንቃት በመከታተል የፋኖ ሰራዊት በወሰዳቸው እርምጃወች ወራሪው የብልፅግና ኃይል ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ገብቷል።
የድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መወለድ ያስገኘው የአንድነት መንፈስ ለተገኙ ወታደራዊ ድሎች ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። የድላችን ምስጢር ያለው አንድነታችን ላይ መሆኑም በተግባር ተረጋግጧል። ድርጅታዊ አንድነታችንን በጠበቀ መልኩ ከኢትዮጵያዊያን እና ከቀጠናው ኃይሎች ጋር የሚደረግ ትብብር አገዛዙን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ወሳኝ ሂደት መሆኑ ግልፅ ነው። ህዝባዊ ዓላማችንን የተጋራን ጋር በመርህ የምናደርገው ትብብር እና አንድነት የአረመኔውን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር ትልቅ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው።
ይህንን ተከትሎ ባቀረብነው ወገናዊ ጥሪ በርካታ የአገዛዙ አገልጋይ የነበረ ምሊሻ፣ አድማ ብተና እና የመከላከያ ኃይል የወገንን ኃይል እየተቀላቀለ ይገኛል።
ስለሆነም ዛሬም አገዛዙን በማገልገል ላይ ለምትገኙ የምሊሻ፣ የአድማ ብተና፣ የመደበኛ ፖሊስ፣ መከላከያ እና በሌሎች የአገዛዙ ታጣቂ አደረጃጀቶች ውስጥ ላላችሁ ተመሳሳይ ጥሪወችን እናስተላልፋለን።
ይህንን ጥሪ ያስተላለፈው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስራ አመራር በጉዳዩ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ጥሪዉን በመቀበል ወገናቸውን ለመካስ ለሚፈልጉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የካድሬ መዋቅር የምህረት አዋጅ አውጇል።
ለ) የምህረት አዋጁ የተላለፈላቸው የአገዛዙ መዋቅር አካላት:-
፩) በየደረጃው የሚገኙ የብልፅግና አመራር አባላት
፪) ምሊሻ፣ ሰላም አስከባሪ እና በሌላም ስያሜ ብልፅግና ያደራጃቸው ታጣቂወች
፫) የክልል አድማ ብተና እና መደበኛ ፖሊስ አባላት
፬) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም በየቀጠናው የተሰማሩ እግረኞች እና የአገዛዙ መኮንኖች
ሐ) የምህረት አዋጁን ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት
ሶስት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ጊዜ በቀረው የጦርነት ሂደት በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የብልፅግና መዋቅር በአማራ ህዝብ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ድቀት ላይ ስልጣኑን ከማራዘም ያለፈ ለአማራ ህዝብ የሚጠቅም አንድም አጀንዳ የሌለው በመሆኑ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በተለያዬ ጎራ የተሰለፍን የአማራ ልጆችም እንደ የአንድ እናት ልጆች በመቀናጀት የህዝባችንን ህልዉና ማስጠበቅ ከእኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው። በመሆኑም:-
፩) ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ መብት እና ነፃነት እንጅ ለአብይ አህመድ ወንበር መፅናት የሚወድቅ የአማራ ወጣት መኖር ስለሌለበት፤
፪) ህዝባችንን በጅምላ ለሚጨፈጭፍ አገዛዝ በማገልገል የዘቀጠ ታሪክ ውስጥ ራስን ከማግኘት ይልቅ ለነፃነቱ የሚዋደቅን ኃይል በመቀላቀል ደማቅ ታሪክ መፃፍ ታሪክ የጣለብን ግዴታ በመሆኑ፤
፫) ህዝብን ታግሎ ያሸነፈ አገዛዝ እንደሌለው ሁሉ አብይ አህመድም የአማራን ህዝብ ማሸነፍ ስለማይችል እና በተሸናፊነት ለሚያጠናቅቀው ብልፅግና በመላላክ እና በራስ ወገን ላይ በመተኮስ የታሪክ፣ የህሊና እና የፍትህ ተጠያቂነትን ከማስተናገድ ለመዳን ሲባል፤
፬) አገዛዙን በጋራ ታግለን በማሸነፍ ለህዝባችን ሰላም ማምጣት የትውልዱ ግዴታ በመሆኑ፤
፭) እንዲሁም የምንታገለው ለአማራ ህዝብ ህልውናና መዳን እንደመሆኑ መጠን የፋኖ ትግልም የአማራ ህዝብ ትግል ስለሆነ በሁሉም ጎራ ላሉ አማራዊ ወንድሞች ጥሪ ማድረግ እና ማታገል የድርጅታችን ተልዕኮ በመሆኑ፤
ይህንን የምህረት አዋጅ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስራ አመራር ውሳኔ መሰረት ለህዝብ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
መ) የምህረት አዋጁ አተገባበር
፩) የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካላይ በተራ ቁጥር "ለ" ስር የተዘረዘሩት የምሊሻ፣ አድማ ብተና፣ መከላከያ እና ሌሎች የታጠቁ የብልፅግና ኃይሎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮች በየአካባቢያቸው ላለው የድርጅታችን መዋቅር እና ለዚህ ጉዳይ በተቋቋመው ግዜያዊ ግብረ ኃይል በአካል ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ።
፪) ምህረት ጠይቀው ወገናቸውን ለመካስ የሚመጡ ግለሰቦች የአካል ደህንነት ዋስትና ይሰጣቸዋል። በተዘጋጀላቸው ማረፊያ የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋል።
፫) ለትግል አገልግሎት ከሚዉል የጦር መሳሪያን ጨምሮ ማንኛውም የምህረት ጠያቂወች ንብረት በባለቤቶች እጅ ይቆያል።
፬) ምህረት የተደረገላቸው ግለሰቦች ድርጅቱ ባዘጋጀው ፎርም መሠረት ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሊሰሩ ካልተቻለም ከጠላት ወገን ላይሰለፉ ቃለ-መሃላ ይፈፅማሉ።
፭) አቅሙ እና ፍላጎቱ ያላቸው የምህረት ተጠቃሚወች የወገንን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ተቀላቅለው ለህልዉና ተጋድሎው የበኩላቸውን ድርሻ ይወጡ ዘንድ በሌላ ማናቸውም ለህዝብ ጠቃሚ በሚሆኑ ተልዕኮወች ላይ ይሰማሩ ዘንድ ድርጅቱ ሁኔታወችን ያመቻቻል።
፮) ይህ የምህረት አዋጅ ከዛሬ የካቲት 04 ቀ 2018 ዓ.ም ላሉት ተከታታይ 15(አስራ አምስት ቀናት) ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል።
ሠ) የምህረት አዋጁን በማስፈፀም የሰራዊታችን እና የድርጅታችን አመራር ግዴታ
፩) የምህረት አዋጁን አፈፃፀም ለመከታተል በማዕከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመመሪያዉን አተገባበር ይከታተላል፤ መረጃወችን ይሰጣል፤ መፍትሔ ያስቀምጣል።
፪) የድርጅቱ መዋቅር አመራር እና ሰራዊቱ ለምህረት ጠያቂወቹ የአካል ዋስትና መስጠትን ጨምሮ በእንክብካቤ በማስተናገድ በፍፁም ጨዋነት አዋጁን ይተገብራል።
፫)በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ወዲያውኑ ለግብረኃይይሉ ያሳውቃል፣ የተሰጠዉን የመፍትሔ አቅጣጫ ይተገብራል።
፬ በግል ቂም ቁርሾ ወይም በሌላ ግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎቶች ምክንያት ከዚህ አዋጅ በተቃረነ መንገድ በማንኛውም ምህረት ጠያቂ ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ ወይም ንብረት መቀማት ፍፁም የተከለከለ ተግባር ነው።
🙏1
፭) የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌወችን እና መርሆወችን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የጦር ህግጋትን የተከተለ አሰራር ይተገበራል።
፮) ይህንን አዋጅ ጥሶ የተገኘ ማንኛውም የድርጅቱ አመራር እና አባል ወይም ሌላ አካል ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል።
ረ) የሕዝቡ፣ የሀገር ሽማግሌወች እና የኃይማኖት አባቶች ሚና
በየቀጠናው ያለው ህዝብ፣ የሀገር ሽማግሌወች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ሌሎች ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች በጠላት የፀጥታ እና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ያሉ ግለሰቦች በዚህ አዋጅ መሰረት አፈሙዛቸውን ወደ ዋናው ጠላት እንዲያዞሩ ካልሆነም ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲኖሩ እና የአማራው ኃይል ፍፁም ህብረት እንዲኖር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ይጠበቃል።
በመጨረሻም የአማራ ልጆች በጋራ ተባብረን ህዝባችንን ሊያጠፋ የተነሳውን ጠላት እናስወግድ ዘንድ አንድነት እና ህብረት ያስፈልገናል እና ወደ አማራ የምንተኩሰው ጥይት እንዳይኖር እና አንድ ጠላት ላይ ብቻ አነጣጥረን እናሸንፍ ዘንድ ኑ እንላለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
👍2🙏1
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 49ኛ ክፍለ ጦር የሆኑ አምስት አባላት ከኦህዴድ ብልፅግና ጋር ሆነን ወገናችንን አንወጋም በማለት ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: ክፍለ ጦሩም አቀባበል አድርጎላቸዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 5/2018 ዓ.ም
3🙏1
የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች በብልፅግናው አገዛዝ ባደባባይ እየተዘረፉ መሆኑን ነዋሪዎች በማስረጃ እያጋለጡ ቀጥለዋል::

ጀምበር የጠለቀችበትና ተስፋ የቆረጠው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የህዝብ ሃብት መዝረፉን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የሰሜን ወሎ ዞን ወልድያና ቆቦ ከተማ ካድሬዎችም የከተሞቹን የህዝብ ሃብት ባደባባይ እየዘረፉ መሆኑን ነዋሪዎች በማስረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፈው ጊዜ ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽን ሸጠው የተከፋፈሉ ሆድ አደርና አገር አፍራሽ የዞንና የወረዳ ካድሬዎች እንዲሁም የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አመራሮች በማስረጃ የተጋለጡ መሆኑ ይታወሳል:: ጉዳዩም በፍርድ ቤት ተይዞ የህዝብ ሃብት የሆነው ቆቦ ሁለገብ አዳራሽ ተመላሽ እንዲሆን ተወስኖ እንደነበር ከፍርድ ቤት ያገኘነው ማስረጃ ይናገራል::

ስለሆነም አሁንም ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሎ ከዚህ በታች በማስረጃ የተዘረዘሩት የወልድያ ከተማ እና የቆቦ ከተማ መሬቶች ለጦርነት አላማ ሊውሉ ጥርና የካቲት/2018 ዓ.ም በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ለሽያጭ መቅረባቸውን የከተሞቹ ህዝብ ባደረሰን ማስረጃ አረጋግጠናል::

ወልድያ ከተማ በክልሉ ከፍተኛ የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች የሚዘረፉበት ከተማ ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ድሃ የቀበሌ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የአገዛዙ ሹማምንቶች እንደተከፋፈሉትና ዛሬም ተጠናክረው እንደቀጠሉበት ከህዝብ የደረሰን ማስረጃ ያሳያል::

ቆቦ ሁለገብ አዳራሽ ባለፈው ጊዜ ሰማኒያ ሚሊየን ብር እና ከዛ በላይ ተሽጦ ገንዘብ ሲካፈሉ ተጣልተው በፍርድ ቤት ትዛዝ ገንዘቡ ለገዥ ተመላሽ ከሆነ በኋላ እንደገና ለጨረታ የቀረበ ሲሆን እነዚህና ሌሎች ለጊዜው በስም ያልተጠቀሱ የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ላለው የብልፅግና አገዛዝ ለጦርነቱ አላማ ለማዋል እየተዘረፉ በህገወጥ ጨረታ ለገበያ መቅረባቸውን ነዋሪዎች በማስረጃ አስደግፈው አድርሰውናል::

በመጨረሻም ለመላው ህዝባችን ምኒልክ ዕዝ ከሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ያፀደቀውን መመሪያውን መሰረት በማድረግ የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ ለህዝብ መሆኑና መመለሱ አይቀርምና ተስፋ የቆረጠው አገዛዝ ካድሬዎች የጦር መሪዎች ስግብግብ ነጋዴዎችና ህገወጥ ደላላዎች ተቀናጅተው ከሚሰሩት የመሬት ወረራና ዘረፋ ባለመሳተፍ ሃብታችሁን እንድትጠብቁ ብሎም ከህልውና ትግሉ ጎንም እንድትቆሙ ስንል ዛሬም እንደ ትላንቱ መልክታችንን እናስተላልፋለን!

*ማስታወሻ፦ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም የወሎ ቤተ-አማራ አካባቢዎች በአገዛዙ እየተዘረፉ ያሉ የህዝብ ሃብቶችን የሚከታተልና ማስረጃ የሚይዝ ህቡዕ (ስውር) አደረጃጀት እንዳለው ለህዝብ ማሳወቃችን የሚታወስ ነው::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 5/2018 ዓ.ም
2🔥2
ፋሽስቱን አገዛዝ ብልፅግና ወግነው ህዝባቸው ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ የነበሩ የሚሊሻ አባላት ነባራዊ ሁኔታውን በመረዳት በውጊያና በፈቃዳቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ ቀጥለዋል!

በዚህም ዘጠኝ የሚሊሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የሚሊሻ አባላቶቹ መካነ ሰላም ዙሪያ በነበረ አውደ ውጊያ በቀላል መስዋዕትነት እጃቸውን ለክፍለ ጦሩ በመስጠት ህይወታቸውንም ማትረፍ ችለዋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ወግዲ ወረዳ ዙሪያ ከንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት መቋቋም አቅቶት ከመቶ በላይ ንፁሃኖችን መጨፍጨፉ የሚታወቅ ሲሆን አሁንም በዚሁ በወግዲ ወረዳ ዙሪያ በዘሞድ ከተማ ከ150 ኩንታል በላይ የማህበረሰቡን እህል ዘርፎ በመውሰድ ፀረ-ህዝብነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
👍2🙏1
የአደረጃጀት ዜና!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክ/ጦር አመራር ለተከታታይ ቀናት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የአመራር መተካካትና አጠቃላይ ግምገማ አድርገዋል።

በተጨማሪም በባለፈው በነበረው አጠቃላይ የ102ኛ ኮር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የድርጅት አመራር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ዞብል አምባ ክፍለጦር ይባል የነበረውን ስያሜ 12ኛ ክፍለጦር በማለት እንዲጠራ የተወሰነ መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ- ሂስ(ግምገማ) በማድረግ በቀን 5/06/2018 ዓ.ም አዳድስ የስራ ሀላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል።

1.ወታደራዊ አዛዥ...........አርበኛ ሀብተማሪያም መንበሩ
2.ም/ወታደራዊ አዛዥ........አርበኛ ነጋ ከበደ
3.ዘመቻ መሪ ..................አርበኛ ጌታሁን ደመቀ
4.ም/ዘመቻ.መሪ..............አርበኛ አማረ ሞገስ
5.የፖለቲካ መምሪያ...........አርበኛ መ/ር በላይ አረፍ
6.ወታደራዊ አሰተዳር.........አርበኛ ሞላ ዝናቤ
7.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ አሸናፊ በላይ
8.ኦርድናንስ መምሪያ...........አርበኛ ሻምበል ሞላ
9.ም/ኦርድናንስ.................አርበኛ አድሱ ሞላ
10. ጤና መምሪያ.............አርበኛ ወርቁ ተበጀ
11.ስልጠና መምሪያ..........አርበኛ አለሙ መልኩ
12.ሎጂስቲክ መምሪያ........አርበኛ ኑርየ ይማም
13.ም/ሎጂስቲክ...............አርበኛ አማረ ይርዳው
14.ፋይናንስ ሀላፊ..............አርበኛ ሙሉጌታ ዘውዱ
15.የህዝብ ግንኙነት...........አርበኛ ዳዊት ጌትነት
16.ሀብት አፈላላጊ..............አርበኛ ነጋ ፈንታው
17.የህግ መምሪያ..............አርበኛ አበበ በላይ
18.ሴቶች ጉዳይ..................አርበኚት ቤቲ ተሾመ
19.የክ/ጦር ዳኛ................አርበኚት አበባ ሲሳይ
20.ንብረት ክፍል.........አርበኛ ጥላሁን አየነ (አባ ጫንቃ)

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
5👍1
አንድነታችን ሸዋ፣ ወሎ እና ጎጃም ላይ የተከፈተብንን ጥቃት በመመከት ጎንደር ላይ ባገኘነው የድል ማህተም ታትሟል።

የካቲት 07 ቀን 2018 ዓ.ም

የጎንደሩን ድል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
ሀ) መግቢያ
``````

የጨፍጫፊው ብልፅግና አገዛዝ የሰሞኑ አዲስ ቀጠናዊ ጦርነት ድግስ ምስጢር አማራን የማጥፋት ፕሮጀክት ነው። በሁለት ቀን ትጥቅ አስፈትቸ አማራውን በባርነት እገዛለሁ ርስቶቹንም መደራደሪያ አደርጋለሁ በሚል እብሪት በህዝባችን ላይ ጦርነት ያወጀው አገዛዝ ቅስሙ የተሰበረው ገና ጦርነቱን በለኮሰው የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ነበር።

የመጀመሪያውን ኮሎኔል ባህርዳር ከተማ ላይ የማረክነው ጠላት በጎጃም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በወሎ እና በወለጋ ቀጠናወች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያወችን፣ ሚሊዮን ተተኳሾችን፣ ታንክና ዙ-23 ን ጨምሮ ከባድ መሳሪያወችን ማርከነዋል።
በርካታ አሃዶችን በተለይም በክፍለ ጦር እና በሬጅመንት ደረጃ ያሉትን ከእነ አመራሮቹ በተደጋጋሚ ደምስሰናል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምርኮኞወችን ወደ ቤተሰባቸው ልከናል ከፊሉንም ለቀይ መስቀል አስረክበናል። የክልሉን ዋና ከተማ ጨምሮ በሁሉም ከተሞች ጠላት ላይ ከባድ ምቶችን አሳርፈናል። በዚህ የትውልዱ አስደናቂ ተጋድሎ ነባሩን የብአዴን መዋቅር በማፈራረስ አገዛዙን አየር ላይ የተንሳፈፈ ፊኛ ማድረጋችንን መሬት ያለው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም በገሃድ የመሰከረው ሐቅ ነው።
በዚህም ምክንያት አገዛዙ በውጊያ እንደማያሸንፈን ሲያውቅ ሌሎች የጥፋት እና የማደናገሪያ ስልቶችን ሲጠቀም ቆይቷል። ከእነዚህ የጥፋት ፕሮጀክቶቹ መካከልም:-
1) ንፁሃን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት

የአማራን ህዝብ ማንበርከክ የአገዛዙ የጦርነት ተልዕኮ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በህዝቡ ላክ በድሮን፣ በጀትና በሌሎችም ከባድ መሳሪያዎች ድብደባ በማድረግ የኃይል የበላይነትን ማሳዬት እና የወገን ኃይል ላይ የስነ ልቦና ጫና መፍጠርን እንደ ስልት ለመጠቀም ሞክሯል። በዚህም የንፁሃን መኖሪያ መንደሮችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ቤተ-እምነቶችንና ጤና ተቋማትን ጨምሮ ኃላፊነት በማይሰማው መልኩ ጭፍጨፋዎችን ፈጽሟል፡፡ 
በዚም ምክንያት በርካታ ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዉያንን ጨምሮ ሲቪሊያንን በገፍ ጨፍጭፏል። ይሁን እንጅ የአገዛዙ ጭካኔ ህዝባዊ መሰረታችንን ከማጠንከር እና አረመኔነቱን ከማረጋገጥ ያለፈ ፋይዳ አላመጣለትም።

2) ብሔራዊ አጀንዳወችን እንደ ማደናገሪያ ስልት
````````````````````````````````````````````````

በራሱ ህዝብ ላይ ጨካኝ አረመኔ ተግባራትን የሚፈፅም አገዛዝ ለሀገር ክብር እና ብሔራዊ አጀንዳወች ትኩረት ሊሰጥ አይችልም። በተለይም ግጭት ጠማቂው የብልጽግና አገዛዝ የሀገርን ሉዓላዊነት አሳልፎ ለመስጠት የማያመነታ ስለመሆኑ ባለፉት ሰባት ዓመታት ሀገር ውስጥ አንዱን በአንዱ ላይ በማስነሳት ግጭትን በመለኮስ በፍቅር የሚኖሩትን ማህበረሰቦች ሳይቀር ለራሱ ፕሮጀክት በሚመቸው መልኩ ስውር ጦር በማስገባት ሲወጋና ሲያስወጋ ቆይቷል፡፡
ከዚህም ባሻገር ለዘመናት በመከባበርና በፍቅር የኖሩ አጎራባች ሀገራት ድረስ በመዝለቅ እርስ በእርስ እንዲከፋፈሉ አለማቀፍ የሉአላዊነት ህግን በመጣስ ታጣቂዎችን በማሰልጠንና በማሰመራት ለጎረቤቶቻችን ጠንቅ እየተከለ ይገኛል፡፡

አብይ አህመድ የቀጠናው የሰላም ፀርና አተራማሽ ስለመሆኑ በየጊዜው ያደረጋቸው መርህ አልባ ስምምነቶች፣ የአደባባይ መግለጫዎች እና መሃላዎች በቂ አመላካች ናቸው። ከምንም በላይ የቱርክ፣ የዩናይትድ አረብ ኤምሬት፣ የቻይና፣ የአዘርባጃን ድሮኖች እና ሌሎች ዘመናዊ የጦር መሳሪያወችን በአማራ ህዝብ ላይ በመሞከር የሀገሪቱን ህዝብ የአዳዲስ የጦር መሳሪያ መሞከሪያ ያደረገው አገዛዝ የኢትዮጵያን ክብር እና ሉዓላዊነት ተራ ሸቀጥ እንዳደረገው ሌላኛው ማሳያ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንድ ጊዜ በባህር በር ጉዳይ፣ ሌላ ጊዜ በሉዓላዊነት እና የወደብ ጉዳይን አጀንዳ በማድረግ የህልውና ተጋድሎ ውስጥ የገባን ህዝብ ለማዘናጋትና በሌላ ትኩረት ተጠምዶ ዋናውን አጀንዳውን ቸል እንዲለው እና የትግላችንን ማህበራዊ መሰረት ለመናድ ጥረት አድርጓል።
በእርሻ ማሳው፣ በንግድ ቦታው፣ በአምልኮ ቦታወች እና በመኖሪያ ቤቱም ጭምር እያለ የሚጨፈጭፈውን ህዝብ በዚህ መልኩ ለማታለል ያደረገው ሙከራም አገዛዙ በፖለቲካ መቀንጨር መጠቃቱን ያረጋገጠ እና የከሸፈ ጉዳይ ነው።

3) የስሁት ትርክቶች ግንባታ ሙከራ

የፋኖ ኃይል ከአብይ አህመድ ሰራዊት ጋር ጦርነት በጀመረበት ወቅት አገዛዙ ከሌሎች ኃይሎች ጋር አፍላ ፍቅር ላይ ነበር። በተለይም ከአገዛዙ ሰራዊት የመጀመሪያዎቹን በርከት ያሉ የቡድን መሳሪያወች በመማረክ ኃይላችንን ባጠናከርንበት ወቅት አገዛዙ ከትግራይ ኃይልም ጋር ሆነ ከሌሎች የቀጠናው ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ አልገባም ነበር። ፋኖ በራሱ አቅም ወራሪውን ሰራዊት በመመከት ወደ መልሶ ማጥቃት ይሸጋገራል ብሎ ማሰብ የተሳነው የብልፅግና ቡድን ተከታታይ ባዳ እና ባንዳ የሚሉ መሰረተ ቢስ ፍረጃወችንም ሊያለማምድ ሞክሯል። 

የማጥቃት ዘመቻወችን በራሱ የእብሪት እቅድ ጀምሮ በሂደት መቋቋም ያልቻለውን ኃይል በስም ማጥፋት እና በሀሰት ትርክት ዘመቻ ለማዳከም ሞክሯል። አንድ አይሆንም በትነነዋል የተባለው ፋኖ በረቀቀ የአመራር ጥበብ እንደ አለት የጠነከረ ድርጅት ሲፈጥር "በሌሎች ኃይሎች ትዕዛዝ" ነው፤ "የጠላት ድጋፍ" ነው፤"አንደኛው ወደዚህ ሌላኛው ግን ወደዚያ" ነው በሚል መቀባጠር ጀመረ። ይህም አልበቃ ብሎት ሎጅስቲክ፣ ፕሮፖጋንዳ፣ እና ፖለቲካ የሚሰፍርልን ሐይል እንዳለ አድርጎ ያለማቋረጥ በመለፈፍ ላይ ይገኛል።

ከገባበት የእብሪት ጦርነት መውጫ ያጣው አገዛዝ ለአማራ ህዝብ አጀንዳዎች በመታመን፣ በብሔራዊ ጀግንነትም ሆነ በራስ በቅነት በመታገል የፋኖን ሰራዊት እና አመራር የሚቀድም እንደሌለ ጠንቅቆ ያውቃል።
4)የጦርነቱን ገፅታ ቀጠናዊ የማድረግ ግብግብ
`````````````````````````````````````````````````

ኢትዮዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ የምትታወቅባቸውን የውጭ ግንኙነት መርሆወችን በመጣስ በሶማሊያ፣ በሱዳን እና ኤርትራን ጨምሮ የዲፕሎማሲ ሀ ሁን በጣሰ መንገድ የትንኮሳ ተግባራትን ፈፅሟል። ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ እና ዚምባቡዌን ጨምሮ ለአፍሪካ አገሮች ነፃነት የቀዳሚነት ሚና የተጫወተችው ኢትዮጵያን ገፅታ እና ታሪክ በማይመጥን ሁኔታ በሌሎች ሀገራት ላይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶችን ጭምር አድርጓል። በዚህም ከአማራ ህዝብ ጋር የገባበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ቀጠናዊ እና ዓለማቀፋዊ መልክ እንዲኖረው ሞክሯል።

የአማራን ህዝብ የተጋድሎ ትርክት በቀጠናዊ ጦርነት ውስጥ እንዲዋጥ በማድረግ በስኬት ላይ ያለውን የህልውና የተጋድሎ በአርቴፊሻል ብሔራዊ ጀብደኝነት ለማደብዘዝ ጥረት አድርጓል። ይህም እንደሌሎች ማደናገሪያዎች ከጅምሩ የከሸፈ ነው።
ለ) የድርጅታችን ውልደት

አገዛዙ ቢሊዮን በጀት መድቦ ብዙ የደከመበት ጉዳይ የፋኖ ኃይል አንድ ወጥ ድርጅት እንዳይኖረው ድርጅት ከተፈጠረም እንዳይፀና ማድረግ ነበር። ገና የአንድነቱ ውይይት መስመር መያዝ ሲጀምር የቆዩ የጠላት ተላላኪዎች ሮጠው ጠላት ጉያ በመሸሸግ የአሉባልታ ናዳ የሚያወርዱት የድርጅቱ መፈጠር የተልዕኳቸውን ክሽፈት ስለሚያንፀባርቅባቸው ነበር። ፋኖ መስለው በመተወን ከመወለድ ያላስቀሩትን ተቋም በሐሜት ሊያፈርሱ መሞከራቸው ከንቱ ድካም ሆኖባቸው ህዝብም ታሪክም እየሳቀባቸው ይገኛል።
የውስጥ ሰርጎ ገቡን ሴራም የውጭ ጠላትን ሁሉን አቀፍ የብረት አጥር ሰባብሮ አንድ ተቋም መውለድ የትውልዱ ታሪካዊ ግዴታ ነበር እና በድል ተወጥተነዋል።

ሐ) ከድርጅት ምስረታው ማግስት የተዘጋጀ የጥፋት ድግስ
````````````````````````````````````````````````````

የድርጅቱ መወለድ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የከተተው አገዛዝ አለኝ የሚለውን የጦር መሳሪያና የማጥቃት ስልት ተጠቅሞ ዘመቻዎችን በማድረግ በዋናነትም ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጥቃት በማድረስ የድርጅት ምስረታ ሂደቱን ማደብዘዝ እና የፕሮፖጋንዳ እና የስነ ልቦና የበላይነት ለመያዝ ተፍጨርጭሯል።

በተለይም በሸዋ፣ በወሎ እና በጎጃም ቀጠናዎች ኔትወርኮችን በማጥፋት የተጀመረው ዘመቻ በሁሉም ቀጠና ባለው ሰራዊት የተጠናከረ መከላከል ተደርጎበታል። አልፎ አልፎም በመልሶ ማጥቃት ድሎችን መጎናፀፍ ተችሏል። በተለይ በሸዋ የተሰማራው የአገዛዙ ኤሊት ኃይል ያሰበውን ሳያሳካ በሚገባ ተመክቷል። በእነዚህ አካባቢዎች በተፈፀመ ቀጥተኛ የንፁሃን ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ከመረሸናቸውም ባሻገር መንደሮች በከባድ መሳሪያ ወድመዋል፤ የቤት እንስሳት ተጨፍጭፈዋል። ይህም የአገዛዙን አረማኔያዊ ባህሪ በግልፅ ያሳዬ ሆኗል።

መ) የአገዛዙ የበቀል እርምጃ በደብረ ታቦር እና
አካባቢው:-

ይህ የሽብር እና የቀውስ አገዛዝ ብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮችን በሸፈነው የጎንደሩ ተጋድሎ የደረሰበትን ከባድ ውርደት በጦር ሜዳ ውሎ ማካካስ ስላልቻለ ሆን ተብሎ በታቀደ ሁኔታ ከውጊያው ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ንፁሐን በመጨፍጨፍ በሽብር መንገድ ወታደራዊ ሽንፈቱን ለመቀልበስ ሰፊ ጥረት አድርጓል። በተለይም የደብረ-ታቦር ከተማ እና አካባቢው ህዝብ እና የህዝብ ተቋማት ላይ የአለማቀፍ ሕግን በመጣስ ተከታታይ የድሮን ድብደባዎችን አድርጓል።
በዚህም ደብረ-ታቦር ከተማ ላይ ብቻ ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአስራ ስድስት ጊዜ በላይ ስትራቴጅክ ድሮኖችን ያለምህረት በመጠቀም የአረመኔነት ባህሪውን አሳይቷል።

በዚህ ጥቃት የፋርጣ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ፣ የገብርየ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ፣ የዞን ጤና መምሪያ፣ የዞን ሲቪል ሰርቪስ እና ፋይናንስ ቢሮ፣ የቴዎድሮስ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ማህበራዊ ተቋማትን እና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ተቋማት አውድሟል። በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ እና በየቤታቸው የነበሩ የከተማ ነዋሪወችንም በድሮን ጨፍጭፏል።

ይህ አሳፋሪ ተግባር በሰራዊታችን ላይ ያደረሰው ተጨባጭ ጉዳት ካለመኖሩም በተጨማሪ የውጊያውን ውጤት በመለወጥ ደረጃም ሆነ ሰራዊታችን ደብረ ታቦርን ጨምሮ በሁሉም አካባቢወች የተደረገለትን ህዝባዊ እና ደማቅ አቀባበል ማደብዘዝ እንኳን አልቻለም። የድሮን ቦንቦች ጥቃት ያልበገረው የድርጅቱ ሰራዊት የከተማው እምብርት ድረስ በመግባት የሚፈልጋቸውን ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በሚገባ በማከናወን አይበገሬነቱን እና ጀግንነቱን አሳይቷል።

ሠ) በጎንደሩ የወንድማማቾች ድል የተገመደው አፋብን
`````````````````````````````````````````````````````

በሸዋ፣ በጎጃም እና በወሎ ኔትወርክ በማጥፋት የጀመረው የአገዛዙ ጥቃት ሸዋ ላይ በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ እና በአሳምነው እዝ ሰራዊት በቅንጅት፤ በደቡብ እና ምዕራብ ወሎም በምኒልክ እዝ ብርቱ ተጋድሎ ተመክቷል።

ጎንደር ላይ መሀል አርማጭሆን እና ሁለቱን በለሳወች ባካለለው ማእከላዊ የጎንደር ክፍል፤ ከስማዳ እስከ ደብረ ታቦር፤ ከደራ ሀሙሲት እስከ እብናት፤ ከጋይንት እስከ አለምበር ድረስ በሸፈነው ደቡባዊ የጎንደር ክፍል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የበላይ ዘለቀ እዝ እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በጋራ በፈፀሙት ልዩ ተጋድሎ ከደቡብ እና ማእከላዊ ጎንደር በርካታ ወረዳወች የአገዛዙን ሰራዊት በመጠራረግ የድርጅታችን አንድነት በድል እንዲታጀብ አድርገውታል። ከ2540 በላይ የጠላት ኃይል ምርኮኛ ሲሆን በርካቶችም እጅ ለመስጠት በመዘግየታቸው ምክንያት ተደምስሰዋል፡፡

በዚያው ልክም የአፋብን ሰራዊት ከነፍስወከፍ እስከ ድሽቃ ድረስ ለማስታጠቅ ተችሏል፡፡ የሎጅስቲክ እጥረቱንም እንደተለመደው ከጠላት በመረከብ ተንበሽብሷሻል፡፡

በዚህ የጠላት አቅም እና አቋም ልፍስፍስነት ገሃድ በወጣበት ወታደራዊ ኦፕሬሽን የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ ቋንቋ ሲደበላለቅ ታይቷል። የአገዛዙ ባሪያ የሆነው ካድሬ በሚያሰማራቸው አክቲቪስቶቹ በኩል እርስ በእርሱ መካሰስ አልበቃ ብሎት ለህዝብ የሚያስብ በመምሰል ፋኖ ከተማ ላይ ውጊያ ማድረግ እንደሌለበት ለመምከርም ሞክሯል። የእምነት ተቋማትን ምሽግ አድርጎ የሚዋጋን ጨፍጫፊ ሰራዊት የፕሮፖጋንዳ ድጋፍ የሚሰጥ ስብስብ እንደ ጨዋ ለመጫወት መሞከሩ በመጨረሻዋ ሰዓት ላይ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎችን ግልጽ አድርጎ አሳይቶናል።

ህሊናቸውን እና ህዝባቸውን በሆዳቸው ይሸጡ የነባሩ ብአዴናዊ በሽታ ተጠቂዎችን ማደናገሪያ በመረማመድ የልዩነቱን ሸለቆ የደፈነው ባለማተብ ትውልድ መራር መስዋዕትነት በከፈለበት የጎንደሩ ተጋድሎ መላው የአማራ ህዝብ እና የድርጅታችን አመራር ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶታል። በተመሳሳይ ጊዜ ምዕራቡን የጎንደር ክፍል ሊያካልል በጃዊ እና መተከል የዘለቀውን የጠላት ኃይል ላይ ከባድ ምት በማሳረፍ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያችን የማረከው የቴወድሮስ ዕዝ ለጎንደሩ ድል ሌላ ድምቀት ጨምሮለታል።

የድላችን የምስጢር ቁልፍ አንድነታችን ላይ መሆኑ በተግባር በተተረጎመበት የጎንደሩ ተጋድሎ ለማረክነው የጠላት ሰራዊት ርህራሔን፣ ሰብአዊነትን እና ወገናዊነትን በማሳዬት እጅ ሊሰጥ ያልፈቀደውን ደግሞ እስከ መጨረሻው በመዋጋት የአማራን ህዝብ የሞራል ልዕልና ያሳዬንበትም ሁኔታ ነበር። የጠላትን ስስ ብልት በተደጋጋሚ በመምታት ትግሉን በፅኑ አለት ላይ ያቆሙት የጎንደር ቀጠና የሰራዊቱ አባላት በራስ በቅነት አመራር እና ስምሪት በመስጠት ኩራት የሆኑትን ወታደራዊ አመራሮች ለበለጠ ድል የሚያነሳሳ ሞራል ጭምር ኖኗል።

በመጨረሻም ሰራዊታችን በየደረሰበት ሁሉ ተባባሪ በመሆን እና ፍቅር በመስጠት ከጎናችን ለቆመው የጎንደር ህዝብ ልዩ ምስጋና እያቀረብን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ነፃ በወጡ አካባቢዎች የህዝብ አስተዳደር መዋቅሮችን በመዘርጋት፣ ጠላትን ደግሞ በፅናት በመፋለም ለአማራ ህዝብ ነፃነት ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የወትሮ ዝግጁነትን ባነገበ አመራር እና ሰራዊት የታነፀ መሆኑን እናረጋግጣለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
🙏1