ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ራያ ቆቦ ጎብየ ከተማ በምሽት ጠላት ላይ ጥቃት በመፈፀም ድል አስመዘገቡ::

አሳምነው ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ የተወሰኑ አባሎች የካቲት 2/2018 ዓ.ም ምሽት 2:00 ራያ ቆቦ ጎብየ ከተማ በመግባት ጠላት ካምፕ ካደረገው ጎብየ 2ኛ ደረጃ ትምርት ቤት ሰርገው በመግባት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ሻምበል አመራሩን ጨምሮ ሁለት ጓድ ጠላት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር እዛው ጎብየ ከተማ ጦር መሳሪያ ያልታጠቀ ግለሰብ በግፍ ረሽኗል:: ንፁሃኖችን በመግደል ያልረካው የአገዛዙ ሰራዊት ግመልና በሬዎችን ጭምር በጥይት ደብድቦ ገድሏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 3/2018 ዓ.ም
🙏2
እጅ ስጡ ራሳችሁን አትርፉ!!
የዓብይ አህመድን ሴራ አክሽፉ!!

አፋብን በላይ ዕዝ

ጣና ገላውዲዎስ ክፍለ ጦር
[የካቲት 03/2018ዓ.ም ምሽት 1:00]

🔸01 ዲሽቃ
🔸01 ኦባማ ሙሉ የክላሽና ዲሽቃ ተተኳሽ
🔸ከ100+ በላይ ክላሽ የጦር መሳሪያ ተማርኳል።ከባህርዳር 40 ኪ.ሜ ርቀት ተረካክበን ጨርሰናል።

ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
6🙏1
ከትናት የቀጠለው የጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦርየድል ጉዞ የካቲት 02/06/2018 ከአንበሳሜ ከተማ ሲወጣ ተቆርጦ የተደባየው የጠላት ሀይል ሐሙሲት ከተማ ከአለው ጠላት ከተቀላቀለ በኋሏ የካቲት03/06/2018 ከሐሙሲት ከተማ 2ኪ/ሜ ወጣ ብሎ ቡራት ወይም ንፋስ ስልክ ከተባ ቦታ ላይ ምሽግ ሲቆፍር የወላው የጠላት ሀይል ክንዱ የማይዝለው የገብርየ የቀኝ እጅ የሆነው ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ከቀኑ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:30 በጨረሸ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ምሽጉ ሲሰበር ጠላት እንትናቱ አስክሬኑን እና ፖሮሎቹን እያጠባጠበ ወደ ሀሙሲት ከተማ ቢገባም ፋኖ እንደ አራስ ነበር እየተከተ ብርቱ ክንዱን ሳሳርፍበት አምሽታል።
በአውደው ጊያው የተገኘ ምርኮ
1ኛ=ድሽቃ 1
2ኛ=ክላሽ 115
3ኛ=የድሽቃ ተተኳሽ አንድ አይሱዙ መኪና
4ኛ=ፖትሮል=1
5ኛ=ኦባማ አይሱዙ 1
ምርኮኛ አድማ ብትን =8
ሙት እና ቁስለኛ ያልተለየ ሲሆን ጠላት ከባድ ኪሳራ ስለደረሰበት ወደ ባህር ዳር ጓዙን ጠቅልሎ ሂዳል

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ ፋኖ ፍቅሩ ባየ
4🙏1
ሰበር የድል ዜና !!

6 ቀኑን ያስቆጠረው የጉና ክፍለ ጦር የተጋድሎ አውደ ውጊያ የብልፅግናን አገዛዝ ጥምር ጦር ደብረ ታቦር ላይ አከርካሪው ተመታ !!

ለዝርዝር መረጃ እንመለሳለን።
2🙏1
ለሰማዕታት ክብር
ለቀጣዩ ግብ ፅናት!

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ንጉስ ቸኮለ ሻለቃ የተደረገው የመታሰቢያና የቃል ኪዳን ፕሮግራም!

​በሐውጃኖ ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው ሶስተኛ ሻለቃ (ንጉስ ቸኮለ) ሻለቃ፤ በታላቅ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ላለፉት ሶስት አመታት ለአማራ ህልውና ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የገበሩ የጀግኖችን ዝክረ-ሰማዕት አካሂዷል። ይህ ፕሮግራም የሀዘን መግለጫ ሳይሆን፣ "ጀግና ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!" የሚለው የጸና እምነት በተግባር የተረጋገጠበት የታሪክ መድረክ ሆኖ ውሏል።

የጀግኖች ገድል እና የከፈሉት ዋጋ ባለፉት ሶስት አመታት በየመድረኩና በየውጊያ አውደ-ግንባሩ ለአማራ ህዝብ ክብርና ማንነት ሲሉ የወደቁ ሰማዕታት፣ በደማቸው የፃፉት ገድል ዛሬም በሻለቃው አባላት ዘንድ በከፍተኛ አክብሮት ተነስቷል።

"ሰማዕታቱ የከፈሉት ዋጋ ለዛሬው ጥንካሬያችን መሰረት ነው" በሚል መንፈስ፣ ሻለቃው የእነሱን አደራ ለመሸከም ያለውን ዝግጁነት አሳይቷል። እያንዳንዱ ሰማዕት የወደቀው ለትልቅ አላማ መሆኑንና ያ አላማ ዛሬ በጓዶቻቸው ትከሻ ላይ በፅናት መቀጠሉ ተገልጿል።

​አዲስ መንፈስ እና የቃል ኪዳን መታደስ
​የመታሰቢያ ፕሮግራሙ ዋነኛ ኩነት ሻለቃው የገባው አዲስ ቃል ኪዳን ነው። "ጀግና ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!" በሚለው የትግል መርህ መሰረት፣ የሰማዕታቱ አላማ ግቡን ሳይመታ እንደማይቀርና የጓዶቻቸው ደም በከንቱ እንዳይቀር ለመስራት መላው የሻለቃው አባላት ተማምለዋል።

​ዋነኛ የቃል ኪዳኑ ነጥቦች፦
​የአላማ ፅናት፦ ሰማዕታቱ የወደቁለትን የአማራነት ግብ ዳር ለማድረስ እስከ መጨረሻው መታገል!
​አዲስ መንፈስ፦ ካለፈው ትግል ልምድ በመቅሰም፣ በአዲስ ወታደራዊ ወኔና ስነ-ልቦና ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ መሸጋገር!
​መስዋዕትነት፦ ለአማራ ህዝብ ነጻነትና ህልውና ሲባል አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዳግም ራስን ማዘጋጀት!

​"የጓዶቻችንን አላማ ግብ እናደርሳለን!"
​በዕለቱ የክፍለ ጦር አመራሮች ፣የሻለቃው አመራሮችና አባላት በጋራ በገቡት ቃል፣ የሰማዕታቱን መንፈስ ተላብሰው ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። "እነሱ የወደቁት እኛ እንድንቆም ነው፤ እኛ የምንቆመው ደግሞ ህዝባችን እንዲከበር ነው" በሚል መሪ ቃልና በታላቅ የቆራጥነት መንፈስ ፕሮግራሙ ተደምድሟል።
​ይህ በንጉስ ቸኮለ ሻለቃ የተካሄደው መርሃ-ግብር፣ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በፅኑ መሰረት ላይ መቆሙንና ተተኪው ትውልድና ጓዶቻቸው አደራውን ለመረከብ ቆርጠው መነሳታቸውን ለወዳጅም ለጠላትም ያስመሰከሩበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።

ጀግና ይሰዋል፣ ትግል ይቀጥላል!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ አሰፋ መለስ
የካቲት 4/2018 ዓ.ም
5🙏2
"ጎንደር ላይ ምሽጉ እንደ ገል ሲሰበር፡
ባንዳ ሲነፋረቅ  ጀግና ይስቅ ነበር"

በደብረታቦር ከተማ መኃል ለመኃል ሰንጥቆ የገባው ጀግናው የአፋብን ሰራዊት፣ በርካታ የጠላት ምሽጎችን ደረማምሶ ብልፅግና የተባለ ጉድፍን ከደብረታቦር አፅድቷል።

ብልፅግና የሚሉት በንፁኋን ደም የጨቀየ፣ በደሃ እምባ የረሰረሰ ሀገር አፍራሽ ቡድን ጎንደር ላይ ግብዓተ መሬቱ እየተፈፀመ ነው።

1፦ደብረታቦር፣
2፦ እብናት
3፦ አለም በር
4፦ስማዳ
5፦ እስቴ/እንዳቤት
6፦ ንፋስ መውጫ-ጋይንት
7፦ አርብ ገበያ
8፦ ሀሙሲት
9፦ ደጎማ
10 ፦አርባያ
11፦ ስላሬ
12፦ ሚካኤል ደብር
13፦ ማሰሮ ደንብ
14፦ ሰዴሙጃ
15፦ ማህደረ-ማሪያም
16፦ ገላውዴዎስ
17፦ ልጫ

እና ሌሎች አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባታቸው የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
8👍2🙏1
ሰበር!...ባሕርዳር መኮድ ካምፕ!
የሰሜን ምዕራብ ዕዝን ጨምሮ የአገዛዙ ወታደራዊ ኃይል ዋና ማዘዣ ጣቢያ በሆነው መኮድ ካምፕ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!

የግጭቱ መነሻ ዛሬ የካቲት 04/2018 ዓ/ም ማርፈጃውን በተካሄደ ወታደራዊ የግምገማ መድረክ "በፋኖ ቁጥጥር ስር እየገቡ በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ንፁኋንን ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት እንዲፈፀምና በዚህም ሕዝቡ አስመታችሁን በሚል ፋኖን እንዲቃዎም ማስደረግ" የሚል መመሪያ የወረደ ሲሆን፡ "የገጠምነው ከፋኖ ጋር እንጂ ንፁኋኖች ምን አደረጉን?" በሚል መመሪያውን የተቃዎሙ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮነኖች ከግምገማ መድረኩ በኋላ መረሸናቸውን የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።

ይሄንን ተከትሎ በካምፑ ውስጥ በሚገኘው ሰራዊት መካከል ከባድ የሆነ የእርስ በእርስ ውጊያ ተቀስቅሶ በርካታ ወታደሮች መገደላቸው ተሰምቷል።

በአሁን ሰዓት በካምፑ ውስጥ የአማራ ተወላጅ የሰራዊት አባላትና የጦር መኮነኖች እየተመረጡ ትጥቅ እንዲያወርዱ ተደርገው እየታሰሩ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ፋኖ ወደ ከተማዋ መጠጋቱን ተከትሎ ሊከዱ ይችላሉ በሚል የሚጠረጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በስውር እያፈነ የሚገድል ስኳድ ቡድን በካምፑ ውስጥ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል።

በካምፑ ውስጥ የተቀሰቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ውጊያም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት 8:20 ሰዓት ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል።

"አማራዋ እናቴ ላይ የድሮን እሳት ሲዘንብ ከጠላቴ ጋር ተባባሪ አልሆንም" ያሉ በርካታ ወታደሮችም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለሊቱን ከወታደራዊ ካምፑ ወጥተው ጠፍተዋል።

መረበኞች ነን መረጃ አጥማጆች!

የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/MerebMedia24
4🙏1