ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ከጥር:-26 ጥር:- 28/05/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።

በተሐድሶው ላይ የተገኙት የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ አማን ጎበዜ ፣ምክትል አዛዥ አርበኛ ሸጋው ወርቄ ጉድለቶቻችን በማረም ቀጣይ ግዳጆችን በብቃት መፈፀም አለብን ብለዋል።
የወረዳው ጊዚያዊ ህዝብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ፋኖ መምህር በሪሁን ደምሌ በበኩሉ ወታደሩ በየወቅቱ አቅሙን እያሳደገ አቅዶ ጠላትን መምታት እንዳለበት ገልፆ የህዝብ ጉዳይን የህዝብ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ቀጣይም አቅሙን አጠናክሮ ህዝብን በቅን ልቦና ያገለግላል ብሏል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 29/2018 ዓ.ም
🙏3
ባለሽርጡ ክፍለ ጦር የሃብሩ ወረዳ ካድሬዎችን ያጀበ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::

የአገዛዙ ካድሬዎች ህዝብን በስብሰባ ለማደናገርና የሃሰት ቅስቀሳ ለማድረግ ብሎም ፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ተልዕኳቸውን ለማስፈፀም ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ልዩ ስሙ 032 ቀበሌ ኮሎቦ በብልፅግና መከላከያ ታጅበው ህዝብ ሊሰበስቡ ባሰቡበት ሁኔታ ከባለሽርጡ ክፍለ ጦር በደረሰባቸው ያላሰቡት ድንገተኛ ጥቃት ብትንትናቸው ወጥቶ ወደ መርሳ ከተማ ተመልሰዋል::

ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ቀጠናውን በመቆጣጠር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር ዘርግተው እያስተዳደሩት ያለ ሲሆን አገዛዙ ብልፅግና ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኝ በማድረግና በተደጋጋሚ ጊዜ ክንዳቸውን በማቅመስ ዛሬም ድላቸውን አስቀጥለዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 29/ 2018 ዓ.ም
🙏3
የሚኒሻ አባሉ ፋኖን ተቀላቀሉ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የማደርሰውን ግፍ አይተናል ከዚህ በኋላ የዚህ ስርዓት ተባባሪ ሁነን ህዝባችን ላይ በደል ማድረስ የለብነም በማለት ትናት የበደልነውን ህዝብ ፋኖን በመቀላቀል አሰከፊውን ስርዓት ለማስወገድ በአቅራባችን ያለውን ጣና ብርጌድ በመቀላቀል ህዝባችን
እክሳለን ብለዋል ።
1ኛ መሀበው ማራለም ከአንበሳሜ ከተማ ሚኒሻ የነበረ
2ኛ ሰውመሆን ካሳሁን ሐሙሲት ከተማ ሚኒሻ
የያዙት የትጥቅ ዓይነት
1ክላሽ
1 አብራረው ይዘው በመውጣት ፋኖን ተቀላቅለዋል
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ ፍቅሩ ባየ
🙏63
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር አሀድ የሆነችው ጣና ብርጌድ ሻለቃ አንድ ናሁ ሰነይ ሻለቃ ለወራት በአድማ ብተና ተይዞ የነበረውን የገጠር ከተማ የሆነችውን ጉማራ ላይ ጥር 30/05/2018 ከምሽቱ 1:00ሰዓት እሰከ 3:00 ሰዓት በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ምሽጉን ለቆ ወደ ሐሙሲት ከተማ ሲፈረጥጥ በጣላት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ተችላል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ
ፍቅሩ ባየ
🙏3
የደጋው መብረቅ ኮር ቀኛዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ለሶስተኛ ዙር በርካታ እግረኛ ፋኖዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቁ::

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራቶች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ፋኖዎች የካቲት 1/2018 ዓ/ም የኮሩ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ላይ አስመርቋል!

ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በርካታ እግረኛ ፋኖዎችን ለሶስተኛ ዙር ያስመረቀ ሲሆን በዚህ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የደጋው መብረቅ ኮር የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ ብርሃን አረጋ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደሳላችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን "የአማራ ህዝብ የብረት አጥር ናችሁ!! የአማራን ህዝብ ጥላት የሚያጠቃው በእናተ አስከሬን ላይ ተረማምዶ ነው። ስለዚህ እናተ የአማራ ህዝብ መታፈሪያና መከበሪያ የብረት አጥር ናችሁ!" በማለት ለተመራቂዎች መልክት ያስተላለፈ ሲሆን::

የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ መኩሪያ አጋዡ(መምህሩ) "እናተ አማራ ናችሁ! በአማራዊ የሞራል ልዕልና ቁማችሁ የተገኛችሁ!" በማለት ለተመራቂዎች መልክት አስተላልፈዋል።

የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ በለጠ መኩሪያው በበኩላቸው ለተመራቂ ፋኖዎች የአማራን ህዝብ ነፃ የማውጣት ሀላፊነት የዚህ ተመራቂ ጭምር ነው ሲሉ ለተመራቂዎች አሳስበዋል።

በዚሁ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የአሰልጣኞች ምስጋናና እየፈፀሙት ላለው ህያው ገድል የሽልማት ፕሮግራም የተበረከተ ሲሆን፤ይህ የአሰልጣኞች ማነሻሻ የምስጋና እውቅና ለቀጣይ የተልዕኮ መሰላል ይኖን ዘንድ ታስቦም የተደረገ ነው።

እየተዋጋን እንሰለጥናለን እየሰለጠን እንዋጋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ እዝ
የካቲት 1/2018 ዓ.ም
🙏3
ወቅታዊ መግለጫ ከሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
[የካቲት 01/2018ዓ.ም]

ጥበበኛው የዓምሐራ ፋኖ ሰልፉን ትቶ ሰይፉን ያነሳበት፣ ጠላቶቹን በነፍጡ ያምበረከከበት፣ የተደራጁ ጥቂቶች ያልተደራጁ ብዙዎችን ማሸነፍ እንደሚችል የተረዳበት፣ የዓምሐራን ሕዝብ የዘመናት ተጠየቆች ለመመለሥ እሣት ለብሶ እሳት ጎርሶ ሕዝባዊ አለኹነትን በተግባር የገለጠበትና ግዙፍ ዓምሐራዊ አደረጃጀትን ፈጥሮ ክቡር የሕይወት መሥዋዕትነትን እየከፈለ ለነጻነት አለኹ ያለ የዓምሐራ ሕዝብ ልጅ ነው። የአገዛዙ መዋቅር በዓምሐራ ልጆች የተባበረ ክንድ ፍርክሥክሡ ቢወጣም ጥቂት የማይባሉ ከአምሐራው አብራክ የወጡና ሌሎችም የዓምሐራን የባርነት ጊዜ የሚያራዝሙ ጉግማንጉጎች መኖራቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው።

👉 ለአገዛዙ ዕድሜ አርዛሚ ታጣቂዎች የመጨረሻ ጥሪ
የዓምሐራን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት 24:00 እየደከመ ላለው ለአቢይ መራሹ ፋሽሥት ኦሕዴድ ብልጽግና ዕድሜ ማራዘሚያ የሆናችኹ የአገዛዙ እሥትንፋሥ ተሸካሚ አካላት፦
የመከላከያ ሠራዊት አባል የሆናችኹ
የአድማ ብተና(አማራ በታኝ) አባል የሆናችኹ
የሕዝባዊ ፖሊሥ አባል የሆናችኹ
ሚሊሺያ የሆናችኹና በጥቅሉ ዓምሐራን እያጠፋ ላለው የምድሪቱ ጨካኝና አራጅ ለሆነው አገዛዝ ቀኝ እጅ የሆናችኹ ሁሉ ይህ ጥሪ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 07 ቀናት በአካባቢው ለሚገኘው የዓምሐራ ፋኖ እጃችኹን በመሥጠት የተሐድሶ ዓምሐራዊ ትምሕርት በመውሰድ አብረን እንደ አንድ ዓምሐራ እንታገል ሥንል የመጨረሻው መጨረሻ ማሣሠቢያችንን እናቀርብላችኋለን።
አኹናዊው የዓምሐራ ፋኖ ቁመና ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ዓምሐራ ራሱን ከፈጽሞ ጥቃት መከላከል ብቻ ሳይሆን ወደ ማጥቃት የተሸጋገረበት ጊዜ ነው። ማንም አልፎ ሂያጅ ጉልበት በተሰማው ቁጥር እንደ እሸት የሚቀነጥሰው እንዳልሆነ በተጨባጭ እያሥመሠከረ እንደሆነ ራሳችሁ ምሥክር ናችኹ። ሥለሆነም የዓምሐራ ፋኖ መሰረቱ ሕዝባዊ እንደሆነ ተረድታችኹ፣ ሕዝብን ያሸነፈ አገዛዝ እንደሌለ አውቃችኹ፣ ማሸነፍ የማትችሉትን ሕዝባዊ ኃይል እንደገጠማችኹ አውቃችኹ፣ አገዛዙ እንደ ቁሥ ተጠቅሞ እየወረወራችኹ እንደሆነ ተረድታችኹ፣ በዓምሐራ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ፋሽሥታዊ ግብር ቆም ብላችኹ ዓይታችኹ፣ እየገደላችኹት ያለው የታጠቀውን ዓምሐራ ፋኖ ሳይሆን ሲቪሉን የዓምሐራ ሕዝብ እንደሆነ ተመልክታችኹና በጥቅሉ በዓምሐራ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ጅምላ ግድያ፣ ነባር ዕምነቶችን ማውደም፣ በኢኮኖሚ ማድቀቅ፣ ርሥትና ማንነት ነጠቃ፣ የተዛባ ታሪክ ፈጠራ፣ በሕገ መንግሥታቸው ሰንዶ ሕዝብን ማረድና ማፈናቀል እንዲኹም በጠቅላላው በዓምሐራ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን መዋቅራዊ ጥቃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቀልበሥ፣ ሐለወቱን ለማረጋገጥ፣ ርሥትና ማንነቱን በደሙ ለማሥከበርና ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር ሕብረት ፈጥሮ መንግሥት ለመሆን ተጋድሎ እዬፈጸመ ያለውን የዓምሐራ ፋኖ ጊዜ ሳታባክኑ በተሰጣችኹ ውሥን 07 ቀናት በአካባቢያችኹ ለሚገኝ ፋኖ እጃችኹን እንድትሰጡና የዓምሐራ ቤታችንን እንድትቀላቀሉ እናሳስባለን። በመጨረሻም የመከላከያ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊሥና ሚሊሻ ቤተሰብ የሆናችኹ አምሐሮች ልጆቻችሁን ከአገዛዙ ጉያ እንዲወጡ አድርጋችኹ የዓምሐራ ፋኖን ተቀላቅለው የሁላችንም ጠላት የሆነው የኦሕዴድ አገዛዝ በጋራ ለዓምሐራዊ ነጻነት ከሕዝባቸው ጎን እንዲቆሙ አድርጉ።

👉ለመላው የዓምሐራ ሕዝብ አኹናዊ የትግል ጥሪ
ባርነትን ወይንም ጭቆናን ለመታገል ፖለቲከኛ ወይንም ወታደር መሆን አይጠይቅም። ጭቆናን የሚታገለው የተጨቆነ ሁሉ ነው። ግፍን ለመታገል የግድ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ወገን መገኘትም የግድ አይደለም። ግፍን የምትታገለው አንድም ኢ-ሰብአዊ በመሆኑ ነው። ሁለትም ጥቃቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሥለሚመለከትህ እንጅ። የወጣህበት የዓምሐራ ሕዝብ ሲሆንና በፈጽሞ ጥቃት ውሥጥ ሲገኝ ደግሞ ሌላ ነው። ነገሩ ክብርም ዓምሐራዊ ሕልውናም ነው። ድንገተኛና የአንድ ወቅት አጋጣሚ ሳይሆን ተከታታይ አሰራር የተጠና ፖለቲካዊ ጥቃት ሲሆን ዝም ማለት ግን ክህደት ነው። ጭቆናን መለማመድ ውድቀት ነው። ጭቆናን ማሥታመም እና መለማመድ የባርነት ልምምድ ብቻ አይደለም፤ የመጥፋት ምርጫም እንጅ።
የዓምሐራ ሕዝብ የሕልውና አደጋ ተጋርጦብሃል። በዓቢይ አሕመድ 08 ዓመታት ቆይታ በጅምላ ተገድለሃል፣ በጅምላ ተቀብረሃል፣ ተዘቅዝቀህ ተሰቅለሃል፣ ቤተዕምነትህ ፈርሷል፣ታሪክ አልባ ተደርገሃል፣ መርጠህ ባልተፈጠርክበት ነገደ ዓምሐራነትህ ተመርጠህ እየታረድህና በጅምላ ሙሉ ጦርነት ተከፍቶብህ ትገኛለህ። ይህንን ነውረኛና አውሬ አገዛዝ መላው ዓምሐራ በአንድነት ተነሥቶ ማፈራረሥና በትረ ሐገረ መንግሥትነቱን ማንበር አለበት። ይህ ትግል የዓምሐራ ፋኖ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓምሐራ ሕዝብ ትግል ነው። ከዓምሐራ ጋር ያልቆመ ዓምሐራነቱ ምን ያለ ነው? እሥራኤላዊያን እንዲህ አደረጉ። ''ከፅዮናዊነት ጋር የቆመ እና የሚታገል የእኛ ነው፤ ከዚህ ውጭ የቆመ ጠላት ነው''። አዎ አይሁዳዊያን ያን ሁሉ መከራ ሲቀበሉ ዳር የቆመ፣ ያፈገፈገ፣ ዝም ያለ ሁሉ ከጠላት ወገን ነው የተባለበት ነው።

ዛሬ ዓምሐራ በጅምላ እየተጨፈጨፈ በይፋና በአገዛዛዊ መዋቅር የጥፋት አዋጅ ታውጆበታል። ከሰው በታች ተደርጎ ለማኝ ሲደረግ አያገባኝም የሚል የዓማራ ባለሐብት፣ ታዛቢ የሚሆን የዓማራ ምሑር፣ ዳር የቆመ የዓማራ ፖለቲከኛ፣ ጎጠኝነትን የሚሰራ ውሉደ ብአዴን አረም፣ ዝም ያለ የዓማራ ወታደር፣ አልተነካሁም ባይ የአማራ ነጋዴ ወ.ዘ.ተረፈ ከጠላት እንጅ ከእኛ ከዓምሐሮች ወገን አይደለም።

ምርጫው ወይ ከዓምሐራነት ወይንም ደግሞ ከጠላት ጋር የመቆም ነው።

ከአገዛዙ ጋር የቆማችሁ የደም አማሮች የግብር ፀረ አማሮች ቢያንሥ አማራ ሁናችሁ ሙቱ። ካልቻላችኹ ደግሞ ከፋሽሥት አቢይ አሕመድ ተላላኪነት ተቆጠቡ። ዓምሐራ መሆን፣ ለዓምሐራ መቆርቆር፤ ለዓምሐራ መታገል ጽንፈኝነት ከተባለ ማናችንም ከዚህ ፍረጃ አናመልጥም። በራሱ በብልጽግና ውሥጥ ያሉትም ከሌሎቻችን የተለዬ ዕጣ ፈንታ የላቸውም። ምክንያቱም ክሱ ከመሰረቱ ዓምሐራነትን ወንጀል የሚያደርግ በመሆኑ የትኛውም ዓይነት ተባባሪነትም ሆነ ተነጣይነት ከጥቃት አያድንም።

መዳኛችን የዋዋ(ጎቤ መልኬ)ን ቋሚ ምሥል(ፎቶ) በመያዝ እንጅ የገዳያችን፣ የአራጃችን፣ የሐገር አፍራሹንና የፋሽሥቱ ዓቢይ አሕመድን ፎቶ በመያዝ አይደለም
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA

አፋብን
ሰሜን ዓምሐራ ቀጠና
በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ/ክፍል

ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው

ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
5🙏1
ቅርቃር ውስጥ የገባው የብልፅግና ወታደርን ማዥንጡን በመቁረጥ ታላቅ ድል ተመዘገበ!! ========================

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜ/ጀ/ር ውባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር መንትዮቹ እስቴ ደንሳ እና ስማዳ ሃገረ ቢዘን ብርጌድ እንዲሁም የጉና ክፍለ ጦር ስራ አስፃሜዎች ታላቅ ድል ሲጎናፀፉ ውለዋል።

የአማራ ፋኖ አንድነት ብስራት ያስጨነቀው የብልፅግናው አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ በአምስት አቅጣጫዎች በመክበብ ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ሸርፍ ጎዳ ተራራ፣ አቦ ቤተክርስቲያን የኮንክሪት ምሽግ የጥፋት ዕቅዱን ቅዠት በማድረግ በጉና ክፍለ ጦር ሰብሳቢ አርበኛ ወንዱአንተ አሰፋ እና ወታደራዊ መሪ አርበኛ አዛዥ ደሳለኝ የጦር ጠብብቶች እየተመራ በጠላት ሃይል ላይ ከማለደው 2:20 ጀምሮ እስከ ቀኑ 10:00 በቀጠለው አውደ ውጊያ በጠላት ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረስ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳቤት ወረዳ እና " ግንዳ ጠመም" በክንደ ነበልባሎች ጉና ክፍለ ጦር ተደጋጋሜ በደረሰበት ጥቃት ተከትሎ ከዘራፊው ብልፅግና አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆን ችለዋል።

በቀጣይ የመረጃ ሰዓታችን የድል ውጤቱን ሙሉ ዝርዝር መረጃዎችን እናደርሳለን።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የካቲት 01/2018 ዓ.ም
ፋኖ መ/ር ያሬድ ገደፍው የጉና ክፍለ ጦር ህ/ግ ሃላፊ
👍2🙏1
ጉና ክፍለ ጦር
የዓምሐራ ፋኖ በሥማዳ መዳረሻ ወገዳ ከተማና ዙሪያ ገባው ድልን ተቀዳጅቷል
[የካቲት 01/2018ዓ.ም]

ዓምሐራን የነካ
የለውም በረካ
እንዲል የቤተ ዓምሐራው ዓምሐራ በዓምሐራ ሕዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥፋትን ሲፈጽም የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ጠርንፎ ለመውጣት በተዘጋጀበት ሰዓት የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የባዬው መልካሙ፣ የፍቃዴ አለባቸው፣ የአበበ፣ የሸጋው (ገብርዬ)ና ጥንቅሹ የግብር ልጅ የሆነችው ጠንካራዋና አይበገሬዋ እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ እና የሢሣይነው ራዕይ አሥቀጣይ የሆነችው ሥማዳ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ በጋራ የተቀናጀ አውደ ውጊያን ሲያደርጉ ውለዋል። የዓምሐራ ፋኖ የአገዛዙን የተለያዩ ምሽጎችን በክንዱ ሰባብሯል፤ ተቆጣጥሯል። ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እሥከ ቀኑ 11:00 በዋለው እልህ አሥጨራሽ ትንቅንቅ የዓምሐራ ፋኖ ድልን ተቀዳጅቷል። ዓምሐራ ፋኖ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል፣ የቁሥና የሥነልቦና ኪሳራ አድርሷል። የአገዛዙ ታጣቂዎችና የአገዛዙ የቡድን መሣሪያ እሥከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ ምርኮ ሆኗል። የወገዳ ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጠላት የምጽአት ቀን ይደርሥለት ዘንድ ''ሸረፍ ጎዴ'' ተራራን እየተማጸነ ይገኛል።

በኮንክሪት የተሰራው የአቦ ምሽግ በዓምሐራ ልጆች ተጋድሎ ተሰብሯል። የጠላት ብዙዎቹ ምሽጎች ሲሰባበሩ ጠላት የመጨረሻ መዳኛዬ ወዳለውና የቁም ምሽግ ወደሰራበት ''ሸረፍ ጎዴ'' 360° ተራራ ሩጦ ገብቷል። ጠላት ሸረፍ ጎዴ ተራራን አድነኝ ሲል በተማጽኖ ይገኛል።


ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑

አፋብን
ሰሜን ዓምሐራ ቀጠና
በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው

ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
የካቲት 01/20178ዓ.ም
👍2🙏1
የአፓርታይዱ የአብይ አህመድ አገዛዝ በንፁሃን ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመ።

ጥር 30/2018 በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 011 ቀበሌ ሰርኮ አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ስርዓት ንፁሃንን በድሮን በመጨፍጨፍ ጠላቻውን በአደባባይ ገልጿል።

በድሮን ጥቃቱ አንድ ወጣት ህይዎቱ ሲያልፍ ከ 6 ቱ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በጥቃቱ በርካታ እንስሳቶች መገደላቸውንም ማረጋገጥ ተችሏል። የአማራ የሆነን ሁሉ ማጥፋት የሚያስደስተው ጨፍጫፊ ስርዓት ስድስት የንፁሃንን ቤት ማውደሙም ተረጋግጧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 1/2018 ዓ.ም
💔2