ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ

ጥር 27/2018ዓ.ም
የወርቅ-ሜዳ ከተማ የሰላም አየር አግኝታለች !!!

በጃዊ ወረዳ ወርቅ ሜዳ ከተማ አንድ አመት ከ5 ወር ያክል በአረመኔዉ የመንግስት ስርዓት ሰራዊት የከተማዋን ማህበረሰብ ሲያሳቅቅ፣ ሲዘርፍ፣ ሴቶችን ሲደፍር፣ ዘረፈ ብዙ ሰቆቃዎችን ሲያደርስበት ቆይቷል።

ይሁን እንጅ በቀጠናዉ የሚንቀሳቀሰው የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር የፋኖ ሰራዊት በአረመኔው የአብይ ገረድ ሰራዊት ላይ በሚያደርገዉ ተደጋጋሚ ጦርነት የጠላትን ሃይል በመምታት፣ ስቦ በማስከዳት፣ የከተማዋን ሙሉ ህዝብ ከፋኖ ጎን እንዲቆም በማድረግ ከፍተኛ የበላይነት ስለተወሰደበት እና ኪሳራ ስላጋጠመዉ በቀን 23/05/2018 ዓ.ም ከተማዋን ለቆ ወጥቷል።

ብልፅግና ሰራዊቱን ወደ ቀጠናዉ

ከአንድ አመት በላይ የተሰቃየዉ የወርቅ ሜዳ ህዝብ በቀን 26/05/2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር አመራሮች እና ከፓዊ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ዉይይት በማድረግ ለማንኛዉም ልማት እና እድገት መሰረቱ ሰላም ስለሆነ ሰላምን ለማምጣት እና ይህንን አረመኔ የአብይ ስርዓት ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ቆርጠን እንሰራለን ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

እንዲሁም የቀበሌ ጊዜያዊ መንግስት አደረጃጀቶት መዋቅሮችንም መዘርጋት ተችሏል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
🙏2
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት በየ አቅጣጫው ጦርነት መሆኑን ተከትሎ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ሲሆን ሁለት የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::

ወገናችንን በድለናል ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ህዝባች ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ነው ይሄንን ደግሞ ቦታው ላይ ሆነን አይተናል! ስለዚህ ፋኖን ተቀላቅለናል:: ፋኖን የተቀላቀሉት አድማ ብተናዎችም ከዚህ በኋላ የህዝባችንን መከራ ለማስቆምና ህልውናውን ለማስከበርና ለማስጠበቅ ውድ ህይወታችንን አስይዘን እንታገላለን በማለት ቃል ገብተዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
1
ለወልድያ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የጥንቃቄ መልክት!

የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አመራሮች ፋኖን ከህዝብ እንነጥላለን በሚል ስሌት ባለፉት ሁለት አመትና ከዛ በላይ ጊዜያት ህዝቡ ላይ በርካታ ግፎች መፈፀማቸውን በማስረጃ ማጋለጣችን ይታወቃል::

ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትና በተጠቀሱት ስምና ስልክ ቁጥሮች እየተደወለ በፋኖ ስም ከማህበረሰቡ ገንዘብ አምጡ እያሉ እንደሆነ በማስረጃ ለማረጋገጥ ችለናል:: ይህንን ድርጊትም የሚፈፅሙት በስውር በሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላቶች እንደሆነ አረጋግጠናል!

ስለሆነም ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጣረ ሞት ላይ በመሆኑ ስልጣኔን ያቆይልኛል ያለውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብምና ህዝባችን ይህንን በመገንዘብ መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ሁሉ እንዲወስድ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ጋር የተፋለሙት 11ኛ ዕዝ እና የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ አባላት ድባቅ ተመቱ!

በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ በ2 ጄኔራሎች የተመራ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የዘለቀ ከባድ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን በዚህ ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል ተደምስሷል::

2 መድፍ፣ 2 ሞርተር 120፣ 4 ዙ-23 እና ከ60 በላይ በሚሆን ተሽከርካሪ የተጫነ እግረኛ ሰራዊትን በመያዝ የ11ኛ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜ/ጄኔራል ዘውዱ ሰጣርጌ እንድሁም የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ኮር 2 አዛዥ ብ/ጄኔራል ሞሲሳ ቶሎሳ በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ በርካታ ቀጠናዎችን የሸፈነ ውጊያ ቢከፍቱም የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ሰራዊት ባካሄደው የመልሶ ማጥቃት ውጊያ የወገን ኃይል ድል ቀንቶታል::

በማከፍታ ቀጠና ሰኮሩ ታዳጊ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውና ታሪካዊው የበላይ ዘለቀ ምሽግ የሚገኝበት ቦታ ላይ ጭምር ከፍተኛ ተጋድሎ የተደረገ ሲሆን የጠላት ኃይል ላይ መጠነ ሰፊ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል:: ከበላይ ዘለቀ ምሽግ በተጨማሪ በጎረንጅ፣ ጎለሌ፣ ሸመኔ እና ሌሎች አካባቢዎች ውጊያ ሲካሄድ ውሎ አድሯል::

ወግድ ወረዳ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ውጊያ መሃል ከባድ ሽንፈት የገጠመው አገዛዙ ለፋኖ መረጃ ሰጥታችኃል የተባሉ ሁለት የብልፅግና አመራሮች እና ንፁሓን መታሰራቸውንም ለማረጋገጥ ችለናል::

በዚህም መሰረት:-

1ኛ. አብይ አያሌው የወረዳው ብልጽግና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
2ኛ. እንዳልካቸው አቢ የወረዳቅ ኦድት ኮሚሽን ኃላፊ

3ኛ. አረቡ ቀዮ የተባለ ባለሀብት

4ኛ. ተሰፋዬ ጀማል የተባለ የቡና ባንክ ጥበቃ እና ሌሎች ንፁሓን በዛሬው ዕለት ታፍነው ታስረዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
3🙏1
በስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ የጠላት ብልፅግና ወታደርን ወሽመጥ በመቁረጥ ውጤታማ ድል ተመዘገበ!

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር ላይ ጥቅታ ለማድረስ ከጉቢሳ ወደ ኮለቦ፣ ከጭሰ አባሊማ ወደ ሲልኮ፣ከጊራና ወደ ጉባ ፣ከመርሳ ወደ ሀብሩና ፋጂ የተንቀሳቀሰው የጠላትን ሀይል በቀን 26/05/2018 ከኮለቦና ሩጋ ያለውን የጠላት ሀይል ስቦ በማስገባት መነዮ ቀሊና ላይ ምሽት 1:30 ላይ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።

የባለሽርጡ ክፍለጦርን ሊያጠቃና የክፍለጦሩን ነባር ይዞታዎች ሊወር የመጣው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በአምስት አቅጣጫ ለማፈን ቢሞክርም የጠላትን የጥፋት እቅድ ቅዠት በማድረግ 50 ሙትና 78 ቁስለኛ በማድረግ ከትላንት ከጥዋቱ 12:30 እስከ ዛሬ 27/05/2018 ዓ.ም በቆየ አውደ ውጊያ የጠላትን ከበባ ያለምንም መስዋዕትነት በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌና በሌሎች በሳል የክፍለጦሩ ወታደራዊ ጠበብቶች በመስበር በጥላት ላይ ከፍተኛ ስብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

በዚህ አውደ ውጊያ የተበሳጨው የጠላት ሀይል በደቡብ ወሎ ዞን ተወለደሬ ወረዳ ሲልኮ እየተባለ በሚጠራው ቦታ 450 የሚደርሱ ወጣቶችን፣ አርሶ አደሮችን እና የቀን ሰራተኛዎችን በማፈን ስልጠና ሰልጥናችሁ አገራችሁን ትጠብቃላችሁ በሚል ሰበብ ወደ ማጓሪያ ቀጠና አስገብቶ ፋኖን ማረኩ በሚል የሀሰት ዶክመንተሪ ዝግጂት ላይ ይገኛል።
በተያያዘም በሀይል ላፈናቸው ንፁሀን በየቤቱ እየገባ የግል ታጣቂ ግለሰቦችን መሳሪያ ለማስወረድ ድንገተኛ ፍተሻና ድብደባ እያካሄደ ይገኛል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበር ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 28/2018 ዓ.ም
3🙏2
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው እሸት ክፍለ ጦር ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ሁሉን አቀፍ ተሐድሶ ካደረገ በኃላ የአመራር ሪፎርም ስራ ሰርቷል ።

በተሐድሶው ላይ የተገኙት የምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ ፣የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስትራቴጅክ ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ ተመቸ ቢራራ እና ሌሎች የኮር አመራሮች ተገኝተዉ ለሰራዊቱ አቅም ግንባታና ማበረታቻ የሰጡ ሲሆን ሰራዊቱም የነበሩባቸውን ጥቃቅን ክፍተቶች እንደሞሉበት ታውቋል።

እሸት ክፍለ ጦር ወቅቱን የዋጄ በግዳጅ አፈፃፀም የላቀ ሰራዊት እየገነባ ያለ ክፍለ ጦር ሲሆን ከተራ ተዋጊ አባል እስከ ክፍለ ጦር መሪ ቅልቅልና አዲስ አደረጃጀት በመስራት ለቀጣይ ግዳጅ በወትሮ ዝግጁነታቸው እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በመጨረሻም የተመደቡት አመራሮች ይህን የተጣለብነን አደራ በአግባቡ ተወጥተን የአማራን ህዝብ የተደቀነበትን የህልዉና አደጋና ዘርፈ ቡዙ ችግሮች አላቀን አማራ በማንነቱ እማይሸማቀቅበት እና ሁሉን አካታች ይምትሆን ሀገረ መንግስት እንደምንገነባ ቃል እንገነባለን ሲሉ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በዚህ ጥልቅ ተሐድሶ የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንደሚከተለዉ ተዘርዝረዋል።

1.የክ/ጦር አዛዥ..... መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ
2. የክ/ም/አዛዥ ..... አርበኛ ፍቃድ አበባዉ
3. የክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ.......አርበኛ ደሰላ ወንዴ
4. የክ/ጦር ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ.........10 አለቃ አንደበት ወንድምነዉ
5. ዘመቻ ኃላፊ.............አርበኛ ኮስትር አሸነፍ
6 . ሕ/ግንኙነት ኃላፊ......... መቶ አለቃ ደስታዉ አንባዉ
7. ፋይናስ አርበኛ ዮሐንስ አዱኛዉ (ጆን)
8. የሰዉ ሃይል አርበኛ ቡግሳ ተስፋ
9. ስልጠና ክፍል ኃላፊ ......አርበኛ ጌትነት አለምነዉ
10. ሎጀስቲክ ኃላፊ.......አርበኛ እያያዉ ደረሰ
11. ህግ ክፍል ኃላፊ.........አርበኛ ጌታሁን ወዳይ
12. ጤና መምሪያ ኃላፊ......አርበኛ አበበ ሞላ
13. መረጃና ደህንነት         .............. አርበኛ XXXX

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 29/2018 ዓ.ም
👍4
ሰበር የድል ዜና!!!

የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት በቋራ ምድር ተደመሰሰ

የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ኛ ቀኑን ያስቆጠረ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያዎችን በቀጠናው እየተፋለመ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። በትናንትናው እለት ጥር 28/2018 ከሌሊቱ 8:00 ስአት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ስአት ቋራ ወረዳ አባድግሱ ከምትባል ቦታ የተሰራው ጀብድ በአገዛዙ ግብስብስ ሀይል ላይ ከፍተኛ ሽንፈትን እንዲያስተናግድ አድርጓል።በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ማንዴላ እያዩና በኮሩ ከፍተኛ አመራሮች የተመራው ይህ አውደ ውጊያ ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ክፉኛ ሲርበተበት ውሎ ያመሸ ሲሆን የፋኖ ሰራዊት አሰላለፍ: አድዋ ክ/ጦ ከጀርባ በስተምዕራብ ፣ የኮሩ ተወርዋሪ ከፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ከተውጣጡ ሰራዊቶች ጋር በመሆን በቀኝ በኩል ፣ ኦሜድላ ክ/ጦ ነብሮ ብርጌድ በግራ በኩል እና ካራማራ ክ/ጦ አሳምነው ብርጌድ ከጠላት ፊት ለፊት ሆነው የተሰለፉ ሲሆን ፤ ይህ የፋኖ አሰላለፍ ያስደነገጠው የአገዛዙ የብርሀኑ ጁላ ደም መጣጭ ሰራዊት በጭንቀት መውጫ መግቢያ ሲያጣ በአንድ በኩል ከፊት ለፊት ለመውጣት ሙከራ ቢያደርግም የበረሀው ፈርጦች የአሳምነው ልጆች ወይ ፍንክች በማለት ትንቅንቁን አፏፉመውት የጠላት ሀይል ነብስ ውጭ ነብስ ግቢ ሆኖበት አዳሩን በእሳት አለንጋ ሲለበለብ አድሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ያልቻለውን በየቦታው እያዝረከረከ በየቦታው የድረሱልኝ ጥሪውን እየቀባጠረ ወደ መጣበት ወደ ፋርሽዋ ሊመለስ ችሏል።

በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ከፍተኛ አመራሮች 50 አለቃ ማዕረግ ያለው እስከ ወዲያኛው የተሸኘ ሲሆን በየቦታው ያዝረከረከውን አስክሬን የፋኖ ሰራዊት የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር ሊቀብር ችሏል።

በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል:
ሙት = 36
ቁስለኛ = 45
የተማረከ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ = 12
1የዲሽቃ አፈሙዝ
ተተኳሽ = 650 የክላሽ

በዚህ አንድ ሳምንት ከአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ጋር በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አገዛዙ ከሽንፈት የማያድነውን የኔት ወርክ መዝጋት ዘመቻ እንደ አንድ አማራጭ በማድረጉ በግንኙነት ማነስ ከህዝብ ጀሮ ያላደረስናቸው አውደ ውጊያዎች የሚከተሉት ናቸው:

1.ጥር 26_27/2018 የአድዋ ክ/ጦ በጋዝጌ ቀጠና ሮብ ገበያ እና ኤረፍት በተደረገው የሁለት ቀን አውደ ውጊያ የአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት ተብየው እና ጋሻአጃግሬው ሚኒሻ ክፉኛ ሽንፈትን አስተናግዷል።

በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን ሰሜን አቸፈር ሊበን ተነስቶ ወደ ጋዝጌ ቀጠና አርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ ለመፈፀም አስቦ ቢንቀሳቀስም የመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ከፍተኛ ኪሳራን ከማስተናገዱ ባሻገር ከበባ ውስጥ ገብቶ እጅ መስጠት ሲጀምር በሁለት አቅጣጫ ከጃዊ ጃይማላ እና ከአለፋ ሻሁራ ተጨማሪ ሀይል ደርሶ ሊያስለቅቀው ችሏል።

በሁለት ቀን አውደ ውጊያ የተገኘ ድል: ከ20በላይ የታሰሩ ንፁሀን አርሶአደር መሳሪያ አላችሁ አስረክቡ በማለት በግፍ የታሰሩትን ማስፈታት ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ እንደሚከተለው ይሆናል።
ሙት = 30
ቁስለኛ =ከ38 በላይ
5 ምርኮኛ ሰራዊት
የነፍስ ወከፍ መሳሪያ = 10
ከ3000በላይ ተተኳሽ
የአንድ ሬጅመንት ሙሉ የእጅ ስልክ


2.ስቦ በመምታት ኦፕሬሽን ከአድዋ ክ/ጦ ፣ ከፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ጦ እና ከኮሩ ተወርዋሪ በተውጣጡ የፋኖ ሀይሎች የአገዛዙ ሰራዊት ከአባድግሱ ወደ ባርባስ ወደ ምትባል ገዥ ቦታ ለኩሶ ወደ ኃላ በመውጣት የሙት ወረዳ ላይ/ባርባስ ጥር 26/2018 ከቀኑ 9:00 ስአት ጀምሮ ለ2ስአት ያህል በተደረገው አውደ ወጊያ የጠላት ሀይል ኩምሽሽ ብሎ ሙት እና ቁስለኛ በመሆን እንደ ገና ወደ ኃላ አባድግሱ ወደ ምትባል ቦታ ሊመለስ ችሏል።

በዚህ አውደውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 5
ቁስለኛ = 12

3.በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ አቸራበር በፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ታጠቅ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ ቃኝ በሆነችው ሻንበል1 አንድ አስደማሚ ኦፕሬሽን ተደርጓል።

ለአገዛዙ ሰራዊት አጋር የሆነው ሆድ አደር ሚኒሻ መነሻውን ከጭልጋ ወረዳ ወደ ነጋዴ ባህር ሲንቀሳቀስ ቀድመው መረጃን በማፈንፈን የሻለቃዋ ቃኝ በፍጥነት ደፈጣ በመያዝ በሚኒሻው ላይ መብረቃዊ ጥቃት በማድረስ ከቦታው መሰወር ችላለች።

በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል:
ሙት = 5
ቁስለኛ = 8
5 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ መሉ ትጥቁ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈርጣጩ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት በማፊያ አመራሮች እየተመራ ፋኖን እናፅዳ እያለ እራሱ እየፀዳ የሀገሪቱን ወጣት በስሜት በሀገር መከላከያ ስም እየነገደ አማራ ላይ የተሰጠውን የአውሬውን ተልእኮ ለመፈፀም ቢሞክርም ከመጥፋት ግን አላዳነውም፤ የሀገሪቱን እንቁ ሀብት እያግበሰበሰ የወጣቱን ደም እየለገሰ በስልጣን መቆየት እንደማይቻል ክንደ ብርቱው የፋኖ ሰራዊት የሚያስመዘግበው ውጤት ማሳያ ነው።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር
ጥር 29/2018
🙏61