ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የብልፅግና ወንበር ለማስቀጠል አንሞትም ያሉ ሰባት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ሐውጃኖ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።

በሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ ወረዳ በጮቢ በር ዙሪያ መሽጎ የሚገኘው የምርኮኛው የአስር አለቃ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል።

የ802ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻንበል አባላት እና የ11ኛ ዕዝ 83ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሬጅመንት የቃኝ አባላት የነበሩ ወታደሮች ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ብለው ሰባት የሰራዊቱ አባሎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበር ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ አሰፋ መለሰ

ጥር 25/2018 ዓ.ም
👍3
ሰበር ዜና
4ኛ ደጃዝማች ኮር በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ።
በቀን 11/05/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12 ላይ ከማእከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ወረዳ ጃንሱማ ቀበሌ ሽመል በር በተባለ ቦታ ላይ የኮሩ ልዩ ዘመቻ እና የተከዜ ክፍለ ጦር በጥምረት በወሰዱት እርምጃ ከፍተኛ በጠላት ላይ ኪሳራ ደርሶበታል።
የፋሽሽቱ ወንበር አስጠባቂ የሆነዉ የ92ኛ እና 78ኛ ክፍለ ጦር 2ሬጅመንት እና አንድ የሻለቃ አድማ በተን ወደ 70 የሚሆን ሰላም አስከባሪ በጥምረት ያሰማራዉን ሃይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአሳረኛዉ ፋኖ ተደምስሷል በዚህም መሰረት በሽመል በር (ጎጥ) በጠላት በኩል ከ70 በላይ ሙት ሲሆን 40 ቁስለኛዉ ታቅፎ ይገኛ ።
ለጊዜዉ ስማቸዉ ያለታወቀ ከፍተኛ አመራሮችም ተመተዋል።
በፋኖ ምት የተበሳጨዉ አገልጋዩ ሰራዊት ነኝ ባዩ በአካቢዉ ባሉ አርሶ አደሮች ላይ የተለመደዉን የበቀል እርምጃ ወስዷል ።
አርሶ አደሮች አገር ሰላም ብለዉ በተቀመጡበት ቤታቸዉ በመግባት 2 አርሶ አደሮችን የገደለ ሲሆን ቤት አቃጥሏለ እህል አቃጥሏል እንሰሳት ገሏለኝ ።
የዚህ ሁሉ የበቀል እርምጃ ዋናዉ አላማ አማራን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ የስነ ልቦና ስብራት ለመፋጠር መሆኑን የአማራዉ ፋኖ በመረዳቱ በአማራ ህዝብ እና በፋኖ የአርበኝነት ጀብድ እቅዱ ከሽፏል ።
ሰራዊታችንም በሙሉ ጤንነትና ቅፅበታዊ እርምጃ ለመዉሰድ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል
በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ አንድነት መመስረቱን ተከትሎ ጠላት እሚይዘዉ ሚጨብጠዉ አቷል ።

€ በመስዋትነታችን ድላችን እናረጋግጣለን
ባንዴራዉ ግርማይ የ4ኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት
🙏31
ሰበር የድል ዜና!!!

የመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር በሁለቱም አውደ ውጊያዎች ድልን ተቀናጀ!!!

በአርበኛ ማንዴላ እያዩ ሰብሳቢነትና በአርበኛ በሊሁን ጌታቸው/ ወታደራዊ አዛዥ የሚመራው መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር 4ቱንም ክ/ጦ በማጣመር/ ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ ፣ ካራማራ ክ/ጦ ፣ ፊታውራሪ ክ/ጦ እና አድዋ ክ/ጦ ሪፎርም ሰርተው ባጠናቀቁበት ማግስት የመጀመሪያውን አውደ ውጊያ በዛሬው እለት የአገዛዙ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ቅጥረኛ ሰራዊት በሰፈረበት አለፋ ወረዳ ወኩ _ገንገን ከተማ ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ ፣ አድዋ ክ/ጦ እና ፊታውራሪ ክ/ጦ ተጣምረው ከጧቱ 12:00 ጀምሮ እስከ 5:00 ውጊያው የቀጠለ ሲሆን፤ ቋራ ወረዳ በሙር ከተማ ዶቅሚት ከሚባል ቦታ ካራማራ ክ/ጦ አሳምነው ብርጌድ ከቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ በጋራ በመሆ ከሌሊቱ 9:20 ጀምሮ እስከ ጧቱ 2:00 ትንቅንቁ ተፏፉሞ ከቡድን መሳሪያ እስከ ጨበጣ ውጊያ ተደርጓል። በሁለቱም አቅጣጫ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ የምርኮኛው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ቀጠናው ያስገባው ፤ የሚሞትበትን አላማ በውል ያልተረዳው ሰራዊት ፤ በብልፅግና ስርአት በሰከሩ ጀኔራሎች ተገዶ የገባ ቢሆንም ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች ልክ እንደ ትናንቱ ዛሬም ታሪክ ለመድገም ጠላትን ክፉኛ እያበራዩት ይገኛሉ።

የአገዛዙ ስርአት በዘር ዛር ተጠምዶ ለስልጣን ማራዘሚያ የሀገሪቱን ወጣት ህሊናውን በእፅ እያደነዘዘ በአማራ ህዝብ ላይ ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ እየፈፀመ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ወቅት ህዝባችን መረዳት ያለበት አጉል መስዋትነት እየከፈለ በየ ጫካውና ሸንተረሩ እየወደቀ ያለውን ወጣት ህይወት መታደግ ስለሚገባ በመከላከያ ስም ወንጀል እየተፈፀመ ዝም ብሎ ማየቱ አግባብ ስላልሆነ ህዝቡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከመከላከያ ሰራዊት ልጆቹን መጠበቅ እንዳለበት የግዴታ ውዴታ ነው።

በሁለቱም የአውደ ውጊያ ውሎዎች የተገኘ ድል:
ሙት = 28
ቁስለኛ = 34

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር ም/የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥር 25/2018
🙏7
ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ወግዲ ወረዳ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

እንደሚታወቀው ፀረ አማራው ብልፅግና በሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ በደረሰበት ሽንፈት ወደ ደቡብ ወሎ ቀጠና እና አጎራባች ሸዋ ለመስፈር አሰቦ መካናይዝዱን ሳይቀር ሙሉ ጦሩን እያሽሽ እና እያንቀሳቀሰ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በዛሬው ዕለት ሙሉ ሀይሉን ሰብሰቦ በወግዲ ወረዳ አድርጎ ወደ ሸዋ ለመውጣት የሞት ሽረት ከባድ ትንቅንቅ ለማድረግ ቢሞክርም መብረቆቹ የሚቀያይረውን ሀይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ጠላት ሰብሮ ሊወጣ የነበረበትን ስትራቴጅካዊ ቦታ በወግዲ ወረዳ ጎርንጅ ቀጠና ከሌሊት 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በደፈጣና እና በፊት ለፊት ውጊያ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። በነበረውም ተጋድሎ ጠላትን ምድር ገበያ ላይ የገባው ሀይል በደፈጣ ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ መልሶ ቢደራጀም በድጋሜ ኢላላ እና አጋምሳ ከተባለ ቦታ ላይ በተሰነዘረ የፊት ለፊት ማጥቃት የብልፅግናው ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ካሰበበት ቦታ ሳይደረስ ወደ ኋላ በከባድ ኪሳራ ለመመለስ ተችሏል ። በተደረገውም ተጋድሎ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ወደመጣበት ተመልሷል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 27/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና
አርበኞች ክፍለ ጦር የአማራ አንድነት ድርጅት በተመሰረተ ማግስት በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ።
እንደሚታወቀዉ ከዚህ ቀደም ፋኖ ተቆጣጥሮ እያስተዳደራቸዉ ከሚገኙ ቦታዎች እንባ ጋላይ ቀበሌ አንዱ ሲሆን ከዳንሻ የተነሳዉ ጥምር ሃይል ወደ አንባ ጋላይ ፋኖን እደመስሳለሁ ብሎ በመንቀሳቀስ ፋኖም ቦታዉን በመልቀቅ ስቦ በማስገባ እርምጃ ወስዷል ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለ ጦር ከብርጌዶች ዉስጥ ፈጣን አጥቂ ሃይል በመመልመልና በማደራጀት በመረጃና ደህንነቶቻችን በተሰጠዉ መረጃ መሰረት የአማራ ደም መጣጩ ተላላኪ ላይ እርምጃ ተወሰደ።
በቀን 25/5/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ እንባ ጋላይ ቀበሌ ዘር መርጦ ገዳይ እና የአማራ ደም መጣጩ ጥምር ሃይል የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ በመሸገበት በተኛበት ተወርዋሪዉ ፋኖ ኮቲዉ የማይሰማ በቦንብ ግማሹ ሲደባይ ግማሹ እጁን ወደ ላይ አንስቶ ወደ ጀግናዉ ፋኖ ገቢ ሁኗል።
በዚህ በነበረዉ ወጊያ :-
# የሞተ ከ25 በላይ
# እስከ ነብሱ እጅ የሰጠ 14
# የቆሰለ 5
የተማረከ የጦር መሳሪያ
* ብሬን 1
* ነብስ ወከፍ (ክላሽ) 20
* ልዩ ልዬ ተተኳሽ ተማርኳል
የአማራ ፋኖ 4ኛ ደጃዝማች ኮር በበላይ አመራሩ የሚሰጡትን ግዳጆች ለመፈፀም ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል።
ጠያይሞቹ አልሞ ተኳሾች አንገት በጣሾች ዝግጁ
##መገናኛችን አዉቀነዋል ዝም ብላችሁ ጠብቁን
# ኩራት ታሪክ አስጠባቂዉ ፋኖ
# ድል ለጭቁኑ የአማራ ህዝብ
# ድል ለአማራዉ ፋኖ
ባንዴራዉ ግርማይ 4ኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ