ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አፋብን|ቴዎድሮስ ዕዝ የጥር 21/2018 ዓ.ም የግንባር ውሎ

… ፩ …

74ኛ ክፍለጦር በደፈጣ ጥቃት ጠላትን ደመሰስ።

ከደብረወቅ እና ፈለገ ብርሃን በመሰባሰብ የማህበረሰብን ንብረት ለመዝረፍ ሲንቀሳቀስ በነበረ የአረመኔው ሰራዊት ላይ በግዶ እና መጣያ መገንጠያ ላይ ደፈጣ በመጣል በረካታ ሰራዊት መደምሰስ ተችሏል።
201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለጦር ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት ተደናግጦ ወደ ፈለገ ብርሃን በመሸሽ ላይ እያለ በተመሳሳይ ደፈጣ በመያዝ በቦምብ ተጨማሪ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

… ፪ …

ጠላት በተከታታይ አፋብንን እየተቀላቀለ ይገኛል።

በርካታ የምሊሻ አባላት ፣የአድማ ብተና አባላትና የመከላከያ አባላት በየቀኑ እየፈረሱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው። በዛሬው እለትም 6 የአረመኔው ሰራዊት አባላት በራሳቸው ፍቃድ ከጠላት ካንፕ በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የአንድነቱ መበሰር ለዚህ እንደገፋፋቸው በሰጡት ቃለ መጠይቅ አብራርተዋል።

…_ ፫ …

ከ86 በላይ ንፁሀን አማራዎች መራዊ ከተማ ላይ በፋሽቱ አብይ አህመድ አረመኔ ሰራዊት የተጨፈጨፉት 2ኛ ዓመት በፋኖ ተዘክሮ ውሏል።

… _ ፬ …

በ6 ቀበሌዎች ሕዝባዊ ውይይት ተደረገ።

፪ እጁ እነሴ ወረዳ አጋም-ውሃ ፣ ደብረ-ማርያም፣ ደብር-ሚካኤል ፣መቃ፣የጭቃ እና ጓትራን ቀበሌ 54 ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል። ከሕዝብ ጋር የምናደርገው መምከር ትግሉን መጠበቅ ነው።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
1🙏1
የጥንቃቄ መልዕክት ለቆቦና ለአከባቢው!
የአገዛዙን የክፋትና የተንኮል እጆች እየተከታተሉ ለህዝብ ማድረስና እንዲጠነቀቅ ማድረግ ያስፈልጋል!

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ቆቦ ከተማና አካባቢው ላይ ከነ ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎች የተመለመሉ ጥቂት ሃይሎች አስገብቶ ንፁሃን ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ በማድረግ ''ህወሓት አጠቃችሁ'' የሚል ተለምዷዊውን ተራና ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ዝግጅት ማድረጋቸውንና ተልዕኮ መውሰዳቸውን ውስጥ አርበኞች መረጃ አድርሰውናል::

ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ለፖለቲካ ትርፍና ለስልጣኑ ሲል ዛሬም እንደ ትላንቱ ንፁሃን አማራዎችን ከማስጨፍጨፍ ወደኋላ አይልምና መላው ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲወስድ መልክታችንን እናስተላልፋለን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!
🙏2
ሰበር...ከአላማጣ ከተማ ሸሽተው ወደ ቆቦ ከተማ ከገቡት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል በርካቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መኮብለላቸው ተሰማ!

ይሄንን ተከትሎ በቆቦ ከተማ በአንዳአንድ ሰፈሮች ቤት ለቤት ፍተሻ ሲካሄድ አምሽቷል።

ወታደሮቹ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው ቆቦ ከተማ ከገቡ በኋላ ነው ደብዛቸው የጠፋው።

ወታደሮቹ ብዛታቸው ከሁለት ጋንታ በላይ እንደሚሆንና ከነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ጀምሮ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ነው የጠፉት።

የወታደሮቹን መጥፋት ተከትሎ በቆቦ ከተማ መግቢያና መውጫ አከባቢዎች ላይ ብርቱ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን፡ በአንዳንድ የከተማዋ አከባቢዎች ላይ የቤተ ለቤት ፍተሻ ሲደረግ ማምሸቱን ምንጮች ገልፀዋል።

በተጨማሪም በቆቦ ከተማ ወታደሮቹ ሰፍረውባቸው በሚገኙ ካምፖች ተጨማሪ ወታደር እንዳይከዳ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ከዕዝ መምሪያዎች አስቸኳይ ትዕዛዝ ወርዷል።

ከፋኖ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ አከርካሪው የተሰበረው መከላከያ ሰራዊቱ፡ ይህን በድል ሳይወጣ ሌላ አዲስ ጦርነት በመጀመሩ ለመማረክ እንኳን እድል እንደማያገኝ ስለተረዳ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሞልቶ እየተበተነ ይገኛል።

@መረብ
🙏2
ለብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አዛዦች አምስት ሚሊዮን ብር እንዲከፍል የተገደደው ባለሀብት ገንዘቡን ከከፈለ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ!

ከባለሀብቱ 5ሚሊዮን ብሩን የተቀበሉት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች፡ "ገንዘቡን ስትሰጠን ደስ የሚል ፈገግታ አላሳየኸንም" በሚል ነው ግድያውን የፈፀሙበት ተብሏል።

ባለሀብቱን በጥይት ደጋግመው በመተኮስ ያልረኩት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦቹ አስከሬኑን በስለት ቆራረጠው የጭካኔና የአረመኔነት ጥጋቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት የአይን እማኞች።

በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና የግዳን ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ሙጃ ማርያም ከተማ ነዋሪ የነበረው ባለሃብቱ አራጋው ሲሳይ ጥር 17/2018 ዓ/ም ምሽት ከመከላከያ ሰራዊት በተተኮሰበት ተደጋጋሚ ጥይት ሕይወቱ አልፏል።

ባለሀብቱ ለብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አዛዦች ስጦታ መግዣ የሚሆን 5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል በወረዳ አመራሮችና በሰራዊቱ አዛዦች በኩል መጠየቁንና ገንዘቡን በተጠየቀው ጊዜ የማይከፍል ከሆነ "የፋኖ ደጋፊ ነህ" በሚል እንደሚገድሉትና ሀብት ንብረቱንም እንደሚወርሱበት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እንደነበር ከአከባቢው ነዋሪዎች የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ባለሀብቱ አቶ አራጋው ሲሣይ፡ ከሚገድሉኝ በሚል የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ከዚህ ቀደም ገዝቶት የነበረውን የጭነት ተሽከርካሪ በመሸጥ ገንዘቡን ለጠየቁት ወታደራዊ አዛዦችና የወረዳ አመራሮች በተታዘዘው ቀን ያስረክባል።

የጠየቁት 5 ሚሊየን ብር ከእጃቸው ላይ መድረሱን ቆጥረው ያረጋገጡት ወታደራዊ አዛዦቹና የወረዳ አመራሮቹ "ገንዘቡን ስትሰጠን ደስ የሚል ፈገግታ አላሳየኸንም፡ ሌላ ተንኮል ያሰብክ ይመስላል" በሚል ምራቃቸውን ተፍተውበት ከቢሯቸው እንዲወጣ ባስደረጉት በዚያኑ ሰሞን ጥር 17/2018 ዓ/ም ምሽት ወደቤቱ ሲገባ ጠብቀው በተደጋጋሚ ጥይት በመተኮስ እንደገደሉት ገልፀዋል።

ባለሀብቱን በጥይት ደጋግመው በመተኮስ ያልረኩት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦቹ አስከሬኑን በስለት(ቢለዋ) ቆራረጠው የጭካኔና የአረመኔነት ጥጋቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት ምንጮቻችን።

ገንዘቡን ከመጠየቅ ጀምሮ እስከመቀበልና እስከመግደል ድረስ በዋናነት በድርጊቱ ከተሳተፉት መካከል በሙጃ ማርያም ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችን ጨምሮ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አማኑኤል አያሌው፣ የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ሰማኝ ባዩ፣ የግዳን ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ እንዳለው አባተና ሌሎቹም እንደሚገኙበት ነው የተጠቆመው።

በባለሀብቱ አቶ አራጋው ላይ ግድያው ከመፈፀሙ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው "ብልፅግናን እንደግፍ" በሚል በወረዳው የመንግስት ሰራተኞችን ሰብስቦ ባነጋገረበት መድረክ ላይ "ሰሞኑን የምንረሽነው ሰው አለ" በማለት መናገሩን የጠቀሱት ምንጮች፡ አመራሩ ይህንን ንግግር በተናገረ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው ባለሀብቱን ገንዘቡን ተቀብለው የረሸኑት ብለዋል።

አቶ አራጋው ሲሣይ በ50ዎቹ እድሜ መጀመሪያ የሚገኝ ጎልማሣ ሲሆን፡ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት እንደሆነም ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።

ባለሀብቱ አቶ አራጋው ደግና እሩህሩህ እንዲሁም ሰው አክባሪ ነበር ያሉት ምንጮቻችን፡ በሐይማኖቱም ምስጉንና በሕብረተሰቡም ዘንድ የታፈረና የተከበረ ነበር ብለዋል።

@መረብ ሚዲያ
4💔2
ቀን 22/05/2018ዓ/ም
የአብይ አህመድ ዙፋን ጠበቄ የመከላከያ ሰራዊት በደቡብዊ ጎንደር ደራ ወረዳ ወፋርግፍ ቀበሌ የአማራን ህዝብ ዘር የማጥፋት ተግባሩን ለሰርግ ከተጠሩት ሚዚዎች እና ሙሽራውን ጨምሮ መሳራቹሁን አምጡ እያለ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ በመፈፀም
1ኛ አርሶ አደር ጋሸው ጥላሁንን በመረሸን የግል ትጥቁን የወሰደ ሲሆን
2ኛ አርሶ አደር እንዳለው ደሌ በተመሳሳይ በአሰቃቄ ሁኔታ የተረሸ ሲሆን ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት እና ለግዜው ስማቸው ያልደረሰን አርሳደሮችን ጨምሮ 10 ክላሽ እና 1 አብራረው የአርሶ አደሮች በላባቸው ደክመው መሬት ገፍተው የገዙቱን የግል ትጥቃቸውን ሀገር አስተዳድራለው በሚለው አረመናዊው የአብይ አህመድ የግል ወታደር ትጥቃቸውን ተዘርፈዋል
3ኛ ሀብታሙ ጥላሁን ክላሽ
4ኛ አበጀ ደጀን ክላሽ
5ኛ ወለላው አበጀ ክላሽ

ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር
ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ
ፍቅሩ ባየ
💔2
የደጋው መብረቅ ኮር የፌደራል ጥቁር አስፓልትን ይዞ ሲጓዝ በነበረ የጥላት ጥምር ጦር ላይ ከባድ ጥቃት በመፈፀም ድል አስመዘገቡ::

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅኮር ከጋሸና ወደ ወልድያ ሲቀሳቀስ በነበረ ጥምር የጥላት ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት ሲፈፀም የብርሀኑ ጁላ መከላከያዎች በንፁሀንና በእንስሶች ላይ ፀያፍ ጥቃትን በበኩሏቸው ፈፅመዋል!!

ጥር 22/2018 ዓ/ም መነሻውን ከጋሸናና መቄት ፍላቂት ያደረገው የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊትና የአረጋ ከበደ አድማበትን ሰራዊት ጥቁር የፌደራል አስፓልት መንገድን ይዞ ሲቀሳቀስ በነበረ ሰራዊት ላይ በደጅን ክፍለጦርና የኮሩ ቃኝ ሻለቃ ግስላዎች በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት የፋሽስቱ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።

በጋዞ ወረዳ እስታይሽ ከተማ ዙሪያ ላይ በተደረገ የደፈጣ ኦፕሬሽን 21 የጥላት ጥምር ጦር ሲደመሰሱ፤37ቱ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል። ከድሽቃ እስከ ሞርተር የቀላቀለው የደፈጣ ኦፕሬሽን በጥላት ላይ አገት ያስደፋ ጥቃትን መፈፀም ሲቻል ይሄንን ከባድ ጉዳትና ውድቀት ያስተናገደው የጥላት ሰራዊት ከእስታይሽ ከተማ ፈርጥጦ ሲወጣ በደመነፍስ ከአራት በላይ ንፁሀኖች ላይ ጥቃት ሲፈፅም፤በርካታ የገበሬዎችን እንስሳቶችን ጭምር ጨፍጭፎ ገድሏል።የአማራ የሁሉም ነገር ጥላት ሆኖ የተነሳው የፋሽስቱ ስርዓት ንፁሀኖችንና እንስሶችንም ታርጌት በማድረግ ጥቃት ፈፅሟል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 22/2018 ዓ.ም
🙏1
የአደረጃጀት / የሪፎርም ዜና

የአፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የኮር አመራሮች ፣ የአራቱም ክ/ጦ አመራሮች/ አድዋ ክ/ጦ ፣ ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ ፣ ፊታውራሪ ክ/ጦ እና ካራማራ ክ/ጦ
ከቀጠናው የተቋም ግብረሀይል አርበኛ ዮሀንስ/ ሰብሳቢ ፣ አርበኛ ባሻ ስጦታው ፣ አርበኛ ታደሰ ወርቁ ፣ አረበኛ የሻንበል አምሳሉ ማዘንጊያ፣ አርበኛ መቶ አለቃ ቢራራ ታሪክ ፣ አርበኛ ኢንጅነር በየነ አለማው ባሉበት ለ5 ቀን ያህል ጥልቅ ውይይቶችንና ግምገማዎችን በማድረግ አቅምንና እውቀትን ባማከለ መልኩ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር በተሻለና ግልፅ በሆነ መንገድ ኃላፊነት የሚሰማቸውን በየ መክሊታቸው እና በስራ አፈፃፀማቸው ነባር የኮር አመራርንና የ4ቱን ክ/ጦ አመራር በማወዳደር እንደሚከተለው የኮሩን ሪፎርም መስራት ተችሏል።

1.የኮር ዋና ሰብሳቢ .......አርበኛ ማንዴላ እያዩ
2.የኮር ም/ሰብሳቢ.........አርበኛ ባበይ አንባየ
3.የኮር ወ/አዛዥ.............አርበኛ በሊሁን ጌታቸው
4.የኮር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ.......አርበኛ በላይሁን ይትባረክ
5.የኮር ጽ/ቤት ኃላፊ.............አርበኛ ኢንጅነር አትርሰው ሙሉቀን
6.የኮር አስተዳደር ኃላፊ.........አርበኛ ሀይሉ ግርማው
7.የኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ.........አርበኛ ጌታቸው ነጋ
8.የኮር ዘመቻ ኃላፊ........................አርበኛ ጌታቸው አማረ
9.የኮር ልዩ ኦፕሬሽን ኃላፊ......... አርበኛ አስፋው ባዬ
10.የኮር ስልጠና ክፍል ኃላፊ .......አርበኛ ዮሀንስ አሰፋ
11.የኮር ህዝብ አስተዳደር ኃላፊ .......አርበኛ ሳሙኤል ሙላው
12.የኮር ሎጀስቲክ አቅርቦት ኃላፊ......... አርበኛ ታድዮስ በለጠ
13.የኮር ህግና ስነመግባር ኃላፊ...........አርበኛ ጌትነት ጌጡ
14.የኮር ወታደራዊ እቅድና እስትራቴጂ.......አርበኛ ማንደፍሮ አራጌ
15.የኮር መረጃና ደንነት .................አርበኛ--------------
16.የኮር ቀጠናዊ ትስስር.......................አርበኛ ባበይ ጌታነህ
17.የኮር አደረጃጀት .............................አርበኛ ሙሉጌታ አበበ
18.የኮር የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ.................አርበኛ ታድላ ስማቸው
19.የኮር ዋና አማካሪ...........................አርበኛ መላክ ስሜነህ
20.የኮር ም/ወ/አዛዥ...........................አርበኛ አስቻለው ዘመነ
21.የኮር ም/ ዘመቻ...............................አርበኛ ቻሌ ንጉሴ እና አርበኛ አየልኝ ገድፍ
22.የኮር ም/ ልዩ ኦፕሬሽን........................አርበኛ ሀብታሙ ብዙነህ
23.የኮር ም/ ፖለቲካ............................. አርበኛ እንዳልካቸው አስማማው
24.የኮር ም/ፅ/ቤት ..............................አርበኛ እርስቱ አባይ
25.ም/ኮር አስተዳደር.............................አርበኛ እንግዳው መዝገብ
26.ም/ህዝብ አስተዳደር....................... አርበኛ አስተዋለ አቃናው
27.ም/ መረጃና ደንነት..........................‑------============
28.ም/ አደረጃጀት...............................አርበኛ መ/ር አለምቀን መለሰ
29.ም/ ስልጠና ክፍል.......................አርበኛ ዳዊት ዘመነ
30.ም/ሎጀስቲክ...............................አርበኛ መላክ ሞላ
31.ም/ህግና ስነመግባር.....................አርበኛ ንጋት መዝገቡ
32.ም/ህ/ግንኙነት ............................አርበኛ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
33.በኮር አስተዳደር ስር ፋይናንስ ............አርበኛ ክንድየ ፀጋየ
34.በኮር አስተዳደር ስር ግዥ.................አርበኛ ማሩ በሪሁን
35.በኮር አስተዳደር ስር የሰው ኃይል.........አርበኛ ዲ/ን እስጢፋኖስ ሙላት
36.በሎጀስቲክ ስር ኦርዲናስ....................አርበኛ ደምስ ለገሰ

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአርበኛ ዮሀንስ ሰብሳቢነት የሚመራው የቀጠናው የተቋም ግብረሀይል ከተመደቡበት ጀምሮ እስከ አሁኗ ስአት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቀንም ማታም ተደጋጋሚ መድረኮችን በመፍጠር ረገድ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ቀጠናውን የተሻለ አደረጃጀትና መርህ እንዲኖረው ዘርፈ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈው ለዚህ ታሪካዊ ዳራ በመድረሳቸው ሁሉም ክ/ጦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አርበኛ ሻለቃ ሙላት ሲሳይ በመጨረሻው ቀን በቦታው በመገኘት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል መነጋገር ፣ መወያየት ፣ የተሻለን አደረጃጀት በጋራ ማፅደቅ ፣ በብስለት መምራት እና መርህን ትኩረት ማድረግ ፣ ትግሉን የተሻለና ተሻጋሪ ከማድረግ አንፃር ተግቶ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ለኮሩ አመራርም ቃለ መሀላ መስጠት ችለዋል።

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ም/ህ/ግንኙነት ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ጥር 24/2018
🙏41