ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.2K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እርምጃ ተወሰደባቸው!

ጥር:-21/2018 ዓ/ም

በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ስር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢንጅነር ለዓለም ብርሐኑ እና ላሊበላ ከተማ ሰፍሮ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ ተላላኪ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ሆቴል አዘግተው አስረሽ ምችው በሚሉበት ጊዜ ላሊበላ ከተማ ላይ ሰርገው በገቡ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው የእጅ ቦምብ ጥቃት ከፍተኛ አመራሮቹ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።

ጉዳቱ የደረሰው ጥር 20/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:30 ገደማ ላሊበላ ከተማ ለውዝ መገንጠያ ሀብትዬ መዝናኛ ካፌ ሲሆን በደረሰባቸው የእጅ ቦምብ ጥቃት አንድ ከፍተኛ የመከላከያ አመራር ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ ተጨማሪ ሰባት የመከላከያ አመራሮችና አባላት ከባድ አካላዊ ጉዳት አስተናግደዋል።

የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ኢንጅነር ለዓለም ብርሐኑም የጉዳቱ ሰለባ ሲሆኑ ጉዳቱ እንደደረሰ ወዲያውኑ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የመተንፈሻ ሳንባቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጎዳና ሰው ሰራሽ መተንፈሻ ተሰርቶላቸው እንዳሉ፣ጀርባቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደደቀቀና ራሳቸውን ስተው ኮማ ውስጥ እንዳሉ አሁንም በሞትና በህይወት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ በውስጥ መረጃዎቻችን በኩል ተረጋግጧል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር:-21/2018 ዓ/ም
🙏2
ስድስት የአገዛዙ የብልጽግና የሠራዊት አባላት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።

በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) መበሰር ተከትሎ የብልጽግናው ድኩማን ስብስብና ወራሪ ሠራዊቱ ጥልቅ በሆነ  ፍርሃትና ውጥረት ውስጥ ገብቶ እየተርበተበተ ይገኛል።

በአፈናና በአፈሳና በተለያዩ መደለያዎች ከትምሕርት ቤት፣ ከስራ ቦታ፣ ከመዝናኛ ቦታ፣ ከመንገድ...ወዘተ በግዳጅ ተወስደው  ማሰልጠኛ እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ በአማራ ጠልነት አስተሳሰብ በማጥመቅ በገዛ ወገናቸው ላይ የሰይጣናዊውን የዓቢይ የጭፍጨፋ ተግባር አስፈጻሚ እንዲሆኑ የተደረጉ አያሌ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ግድ እስከተጫነባቸው ድረስ አማራን ለማጥፋት የተሰጣቸውን የጥፋት ሰይፍ ታጥቀው፤ መርዛማ በሆነ ጸረ አማራ እሳቤ ተሞልተው አያሌ የአማራ ንጹሐንን ለመረሸን፣ ሴቶችን ለማዋረድ፣ የእምነትና የአገልግሎት ተቋማትን ለማውደምና ለመዝረፍ የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ በሚጠብቁበት ካምፖቸው ውስጥ ሆነው የፍርሃት ቆፈን ወሯቸዋል።

በዚህም ምክንያት በርካታ የመከላከያ፣ የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከዚህ የሞት መንደር የሕዝባችን ዋስትና ወደሆነው የፋኖ ተቋም እየተቀላቀሉ የበደሉትን ሕዝባቸውንም ይቅርታ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ከሰሞኑም ስድስት የብልጽግና ሠራዊት አባላት ከደብረ ኤልያስ፣ ከማይና ከረቡው ገበያ በመውጣት የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።

እነርሡም፦
1. ዳዊት አህመድ የተባለ የመከላከያ ጋንታ መሪ
2. ባቱ ተና  የመከላከያ አባል
3. ጁነዲ አባነጋ  የመከላከያ አባል
4. አብዱ ሀሰን   የመከላከያ አባል
5/ አማረ ፍቃዱ   የመከላከያ አባል
6/ በቃሉ አንመው ገበየሁ የተባለ የሰላም አስከባሪ ጋንታ መሪ የነበረ ሲሆኑ እነዚህ አካላትም አቀባበል በተደረገላቸው ወቅት የብልጽግናው ሥርዓት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ስላለው በደል፣ ሰለ ሠራዊቱ የሞራል ዝቅጠትና አብዛኛው ሠራዊትም በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህን አፋጆ የሆነ ሥርዓት ትቶ ለፋኖ እጁን በሰላም መስጠት እንደሚፈልግ የተናገሩ ሲሆን በተለይ አአሁን ላይ የአማራ ፋኖ በአንድ መሪ ድርጅት መደራጀቱና አንድነቱንም በይፋ ማብሰሩ በብልጽግናው መንደር ታላቅ የራስ ምታት መሆኑን ገልጸውልናል።

በግዳጅም ቢሆን ማሕበረሰባቸውን ሲበደሉ እንደቆዩ የተናገሩት ወደ ክፍለ ጦራችን የተቀላቀሉት እኒህ አካላት ላደረሱት በደል ማሕበረሰባቸውን ይቅርታ እንደሚጠይቁም ተናግረዋል።

ድል ለአማራ ፋኖ!
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍልዥ
🙏1
አፋብን|ቴዎድሮስ ዕዝ የጥር 21/2018 ዓ.ም የግንባር ውሎ

… ፩ …

74ኛ ክፍለጦር በደፈጣ ጥቃት ጠላትን ደመሰስ።

ከደብረወቅ እና ፈለገ ብርሃን በመሰባሰብ የማህበረሰብን ንብረት ለመዝረፍ ሲንቀሳቀስ በነበረ የአረመኔው ሰራዊት ላይ በግዶ እና መጣያ መገንጠያ ላይ ደፈጣ በመጣል በረካታ ሰራዊት መደምሰስ ተችሏል።
201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለጦር ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት ተደናግጦ ወደ ፈለገ ብርሃን በመሸሽ ላይ እያለ በተመሳሳይ ደፈጣ በመያዝ በቦምብ ተጨማሪ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

… ፪ …

ጠላት በተከታታይ አፋብንን እየተቀላቀለ ይገኛል።

በርካታ የምሊሻ አባላት ፣የአድማ ብተና አባላትና የመከላከያ አባላት በየቀኑ እየፈረሱ ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው። በዛሬው እለትም 6 የአረመኔው ሰራዊት አባላት በራሳቸው ፍቃድ ከጠላት ካንፕ በመክዳት ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የአንድነቱ መበሰር ለዚህ እንደገፋፋቸው በሰጡት ቃለ መጠይቅ አብራርተዋል።

…_ ፫ …

ከ86 በላይ ንፁሀን አማራዎች መራዊ ከተማ ላይ በፋሽቱ አብይ አህመድ አረመኔ ሰራዊት የተጨፈጨፉት 2ኛ ዓመት በፋኖ ተዘክሮ ውሏል።

… _ ፬ …

በ6 ቀበሌዎች ሕዝባዊ ውይይት ተደረገ።

፪ እጁ እነሴ ወረዳ አጋም-ውሃ ፣ ደብረ-ማርያም፣ ደብር-ሚካኤል ፣መቃ፣የጭቃ እና ጓትራን ቀበሌ 54 ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል። ከሕዝብ ጋር የምናደርገው መምከር ትግሉን መጠበቅ ነው።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
1🙏1
የጥንቃቄ መልዕክት ለቆቦና ለአከባቢው!
የአገዛዙን የክፋትና የተንኮል እጆች እየተከታተሉ ለህዝብ ማድረስና እንዲጠነቀቅ ማድረግ ያስፈልጋል!

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ቆቦ ከተማና አካባቢው ላይ ከነ ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎች የተመለመሉ ጥቂት ሃይሎች አስገብቶ ንፁሃን ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ በማድረግ ''ህወሓት አጠቃችሁ'' የሚል ተለምዷዊውን ተራና ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ዝግጅት ማድረጋቸውንና ተልዕኮ መውሰዳቸውን ውስጥ አርበኞች መረጃ አድርሰውናል::

ጀምበር የጠለቀችበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ለፖለቲካ ትርፍና ለስልጣኑ ሲል ዛሬም እንደ ትላንቱ ንፁሃን አማራዎችን ከማስጨፍጨፍ ወደኋላ አይልምና መላው ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲወስድ መልክታችንን እናስተላልፋለን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!
🙏2
ሰበር...ከአላማጣ ከተማ ሸሽተው ወደ ቆቦ ከተማ ከገቡት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል በርካቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መኮብለላቸው ተሰማ!

ይሄንን ተከትሎ በቆቦ ከተማ በአንዳአንድ ሰፈሮች ቤት ለቤት ፍተሻ ሲካሄድ አምሽቷል።

ወታደሮቹ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ ንጋት ባለው ቆቦ ከተማ ከገቡ በኋላ ነው ደብዛቸው የጠፋው።

ወታደሮቹ ብዛታቸው ከሁለት ጋንታ በላይ እንደሚሆንና ከነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ጀምሮ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ነው የጠፉት።

የወታደሮቹን መጥፋት ተከትሎ በቆቦ ከተማ መግቢያና መውጫ አከባቢዎች ላይ ብርቱ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን፡ በአንዳንድ የከተማዋ አከባቢዎች ላይ የቤተ ለቤት ፍተሻ ሲደረግ ማምሸቱን ምንጮች ገልፀዋል።

በተጨማሪም በቆቦ ከተማ ወታደሮቹ ሰፍረውባቸው በሚገኙ ካምፖች ተጨማሪ ወታደር እንዳይከዳ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ከዕዝ መምሪያዎች አስቸኳይ ትዕዛዝ ወርዷል።

ከፋኖ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ውጊያ አከርካሪው የተሰበረው መከላከያ ሰራዊቱ፡ ይህን በድል ሳይወጣ ሌላ አዲስ ጦርነት በመጀመሩ ለመማረክ እንኳን እድል እንደማያገኝ ስለተረዳ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሞልቶ እየተበተነ ይገኛል።

@መረብ
🙏2
ለብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አዛዦች አምስት ሚሊዮን ብር እንዲከፍል የተገደደው ባለሀብት ገንዘቡን ከከፈለ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ!

ከባለሀብቱ 5ሚሊዮን ብሩን የተቀበሉት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች፡ "ገንዘቡን ስትሰጠን ደስ የሚል ፈገግታ አላሳየኸንም" በሚል ነው ግድያውን የፈፀሙበት ተብሏል።

ባለሀብቱን በጥይት ደጋግመው በመተኮስ ያልረኩት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦቹ አስከሬኑን በስለት ቆራረጠው የጭካኔና የአረመኔነት ጥጋቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት የአይን እማኞች።

በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና የግዳን ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ሙጃ ማርያም ከተማ ነዋሪ የነበረው ባለሃብቱ አራጋው ሲሳይ ጥር 17/2018 ዓ/ም ምሽት ከመከላከያ ሰራዊት በተተኮሰበት ተደጋጋሚ ጥይት ሕይወቱ አልፏል።

ባለሀብቱ ለብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አዛዦች ስጦታ መግዣ የሚሆን 5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል በወረዳ አመራሮችና በሰራዊቱ አዛዦች በኩል መጠየቁንና ገንዘቡን በተጠየቀው ጊዜ የማይከፍል ከሆነ "የፋኖ ደጋፊ ነህ" በሚል እንደሚገድሉትና ሀብት ንብረቱንም እንደሚወርሱበት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እንደነበር ከአከባቢው ነዋሪዎች የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ባለሀብቱ አቶ አራጋው ሲሣይ፡ ከሚገድሉኝ በሚል የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ከዚህ ቀደም ገዝቶት የነበረውን የጭነት ተሽከርካሪ በመሸጥ ገንዘቡን ለጠየቁት ወታደራዊ አዛዦችና የወረዳ አመራሮች በተታዘዘው ቀን ያስረክባል።

የጠየቁት 5 ሚሊየን ብር ከእጃቸው ላይ መድረሱን ቆጥረው ያረጋገጡት ወታደራዊ አዛዦቹና የወረዳ አመራሮቹ "ገንዘቡን ስትሰጠን ደስ የሚል ፈገግታ አላሳየኸንም፡ ሌላ ተንኮል ያሰብክ ይመስላል" በሚል ምራቃቸውን ተፍተውበት ከቢሯቸው እንዲወጣ ባስደረጉት በዚያኑ ሰሞን ጥር 17/2018 ዓ/ም ምሽት ወደቤቱ ሲገባ ጠብቀው በተደጋጋሚ ጥይት በመተኮስ እንደገደሉት ገልፀዋል።

ባለሀብቱን በጥይት ደጋግመው በመተኮስ ያልረኩት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦቹ አስከሬኑን በስለት(ቢለዋ) ቆራረጠው የጭካኔና የአረመኔነት ጥጋቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት ምንጮቻችን።

ገንዘቡን ከመጠየቅ ጀምሮ እስከመቀበልና እስከመግደል ድረስ በዋናነት በድርጊቱ ከተሳተፉት መካከል በሙጃ ማርያም ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችን ጨምሮ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አማኑኤል አያሌው፣ የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ሰማኝ ባዩ፣ የግዳን ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ እንዳለው አባተና ሌሎቹም እንደሚገኙበት ነው የተጠቆመው።

በባለሀብቱ አቶ አራጋው ላይ ግድያው ከመፈፀሙ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው "ብልፅግናን እንደግፍ" በሚል በወረዳው የመንግስት ሰራተኞችን ሰብስቦ ባነጋገረበት መድረክ ላይ "ሰሞኑን የምንረሽነው ሰው አለ" በማለት መናገሩን የጠቀሱት ምንጮች፡ አመራሩ ይህንን ንግግር በተናገረ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው ባለሀብቱን ገንዘቡን ተቀብለው የረሸኑት ብለዋል።

አቶ አራጋው ሲሣይ በ50ዎቹ እድሜ መጀመሪያ የሚገኝ ጎልማሣ ሲሆን፡ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት እንደሆነም ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።

ባለሀብቱ አቶ አራጋው ደግና እሩህሩህ እንዲሁም ሰው አክባሪ ነበር ያሉት ምንጮቻችን፡ በሐይማኖቱም ምስጉንና በሕብረተሰቡም ዘንድ የታፈረና የተከበረ ነበር ብለዋል።

@መረብ ሚዲያ
4💔2
ቀን 22/05/2018ዓ/ም
የአብይ አህመድ ዙፋን ጠበቄ የመከላከያ ሰራዊት በደቡብዊ ጎንደር ደራ ወረዳ ወፋርግፍ ቀበሌ የአማራን ህዝብ ዘር የማጥፋት ተግባሩን ለሰርግ ከተጠሩት ሚዚዎች እና ሙሽራውን ጨምሮ መሳራቹሁን አምጡ እያለ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ በመፈፀም
1ኛ አርሶ አደር ጋሸው ጥላሁንን በመረሸን የግል ትጥቁን የወሰደ ሲሆን
2ኛ አርሶ አደር እንዳለው ደሌ በተመሳሳይ በአሰቃቄ ሁኔታ የተረሸ ሲሆን ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩት እና ለግዜው ስማቸው ያልደረሰን አርሳደሮችን ጨምሮ 10 ክላሽ እና 1 አብራረው የአርሶ አደሮች በላባቸው ደክመው መሬት ገፍተው የገዙቱን የግል ትጥቃቸውን ሀገር አስተዳድራለው በሚለው አረመናዊው የአብይ አህመድ የግል ወታደር ትጥቃቸውን ተዘርፈዋል
3ኛ ሀብታሙ ጥላሁን ክላሽ
4ኛ አበጀ ደጀን ክላሽ
5ኛ ወለላው አበጀ ክላሽ

ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን

አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር
ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ
ፍቅሩ ባየ
💔2