ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
206ኛ ኮር ከጠላት የሚሰነዘር ማንኛውንም ጥቃት በመመከት አስፈላጊውን አጣፋዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችለውን የወትሮ ዝግጁነት ማጠናቀቁን አስታወቀ

በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የቀጠናውን ትግል በማቀጣጠል በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል የተቀናጀ ሲሆን ኮሩ በተመሰረተ ጥቂት ወራት በሁሉም ክ/ጦሮች በተደረገ ማጥቃት በተለያዩ ግንባሮች በጠላት ላይ የበላይነት መውሰዱን የኮሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።

ኮሩ የሚንቀሳቀስበት ቀጠና የጠላት የሎጀስቲክ፣ የሰው ኃይልና የካድሪ ማመላለሻ በመሆኑ ከፍተኛ ሜካናይዝድ ድጋፍ የሚሰጠው የጠላት ሰራዊት መንቀሳቀሱን መምሪያው የገመገመ ሲሆን የጠላትን የኃይል አሰላለፍ የሚመጥን የትግል ስልት መንደፉንም መምሪያው ገልጿል።

ከደጀን -ሞጣ መርጡለ ማርያም እና ከደጀን ደንበጫ ባሉ ሁለት አውራ ጎዳናዎችን ተጠቅሞ ሎጀስቲክ እና ወታደራዊ ድጋፍ የሚሰጥበት የትኖራ ወታደራዊ ካምፕ በኮሩ ቀጠና መገኘቱን የጠቀሰው ኮሩ፤ የ602ኛ እና 601ኛ ኮር ዋና ማዘዣ መሆኑ የጠላት ኃይል ክምችትና እንቅስቃሴ በስፋት እንዲኖር ማድረጉን ጠቅሷል።

የጠላት ሰራዊት የመዋጋትና የማድረግ አቅም ዝቅተኛ መሆን የአዋጊዎችና ወታደራዊ መኮንኖች ጦርነቱን ለግል ጥቅም ማካበቻ እያዋሉት መሆኑን የገመገመው 206ኛ ኮር ጠላት የሚያደርገውን ማንኛውንም ትንኮሳ በመመከት ከባድ አጠፋዊ ምላሽ መስጠት የሚያስችለውን የወትሮ ዝግጁነት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የአረመኔው ሰራዊት ከዚህ ቀደም ባደረጋጀው ትንኮሳዎች እና በወገን ኃይል ፍላጎት የተደረጉ ግዳጆችን የተመለከተው 206ኛ ኮር በደጀን፣ በጃማ፣ በስናን ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረ ኤልያስና ጎዛምን አካባቢዎች በተደረጉ ግንባሮች ክ/ጦሮች ባስመዘገቡት ትልቅ ድል የቀጠናውን ትግል ያቀጣጠለና የጠላትን የድንኳን ፕሮፓጋንዳ የበጣጠሰ መሆኑን ኮሩ አክሎ ገልጿል።

©በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
🙏1
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፊያለሁ ደሴ ኮር ከአንበሳው ጋይንት ክፍለጦር የተሰጠ መግለጫ

በመጀመሪያ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አንድነቱ ከብዙ ድካም በኋላ በመመስረቱ ለትግላችን ደጋፊወች እና ለሰፊ የአማራ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በመቀጠል ክፍለጦራችን በአለፉት ሁለት አመት ትኩል በላይ በአማራ ትግል ውስጥ ከፍተኛ ጀብድ ስንፈፅም የቆየን መሆናችን ይታወቃል።
በመሆኑም በሰሞኑ ክ/ጦሩንም ሆነ ኮራችን ሲመሩ የነበሩ መሪወች ጠላት በዘረጋው መረብ ተጠልፈው ለጨፍጫፊው ስርዓት እጃቸውን ሰተዋል።

ስለሆነም ትግላችን ለምትደገፉ ደጋፊዎቻችን በሙሉ ግልፅ እንዲሆንላችሁ እጅ የሰጡት የተወሰኑ ግለሰቦች እንጅ ጀግናው ሰራዊታችን አሁንም ትግሉ ውስጥ ያለ እና እየታገለ መሆኑን እናሳውቃለን።

እጅ መስጠት አማራዊ ባህላችን ልማዳችን ያልነበረ ከአባቶቻችን ያልወረስነው የተሸናፊወች ውሳኔ ነው !
''እኛ የአባቶቻችን ልጆች ራስ ጋይንቶች ነን!!''
የእነ ፊታውራሪ ገብርየ እና የዘመናችን ፈርጦች የእነ አርበኛ ከፊያለሁ ደሴ የአርበኛ ክንዳለም አለምነው ልጆች እንጅ የቁስ ሰቀቀናቸውን ለማርካት ሲሉ ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን ትግል ክደው እጃቸውን ለጠላት እንደሰጡት አይነት ስነልቦና የለለን ነን!!

በመሆኑም እጃቸውን ለጠላት የሰጡትን ተሸናፊዎች መሪዎች ምክናያት በማድረግ አደረጃጀት ሰርተናል።

እሱም:-
1) አርበኛ አንደበት ክንዳለም … የክ/ጦሩ ዋና አዛዥ
2) አርበኛ አስጊዶም ውበት … ም'አዛዥ
3) አርበኛ ታረቀኝ ውለታው … ዘመቻ መሪ
4) አርበኛ አለማየሁ ሰማ … ወ/አስተዳደር
5) አርበኛ ሻንበል ሙሉጌታ … ልዩ ዘመቻ
6) አርበኛ ዋለልኝ እሸቴ … ፖለቲካ ዘረፍ
7) አርበኛ ፋሲል ሙሉዓለም … ህ/ግንኙነት
8) አርበኛ ጌታሰው በሪሁን … ፅ/ሃላፊ
9) አርበኛ ተስፋየ ጌትነት … ህ/አስተዳደር
10) አርበኛ አዲስ መሰለ … ፋይናስ
11) አርበኛ ተመስገን ጥጋቤ … ሎጀስቲካ
12) አርበኛ ፋሲል ወርቁ … ግዥ ክፍል
13) አርበኛ ኤርሚያስ ምትኩ … ት/ስልጠና መምሪያ እና ሌሎች አድርገን መርጠናል።

ቀጣይ የትግል አቅጣጫወችን ድርጅታችን እና ዕዛችን በሚሰጠን አቅጣጫ የምንታገል ይሆናል።

ምንጭ፦ የአንበሳው ጋይንት ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
🙏1
የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በመቄትና ቋና በሁለት ግንባር በጥላት ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

የደጋው መብረቅ ኮር አሀድ የሆኑት አንሻ ክፍለ ጦርና ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በሁለቱ ግባሮች ላይ በርካታ የብርሀኑ ጁላን መከላከያ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል!

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አሀዶች ጥር 20/2018 ዓ/ም በሁለት ግባር ከሶስት ወረዳዎች ለከበባ በመጣ የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት ተፈፅሟል።

ከመቄት፣ከጋሸናና ከኮን በሶስት አቅጣጫ ለከበባ የመጣው የጥላት ሰራዊት የከበባ ጥቃት የከፈተ ቢሆንም ፤በፋኖዎቹ በተወሰደ አፀፋዊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በሁለቱም ግባር ከ15 በላይ የጥላት ሰራዊት ሲደመሰሱ፤ዘጠኙ ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ የቁስና የሞራል ኪሳራን ያስተናገደው የጥላት ሰራዊት ወደመጣበት ሲመለስ በንፁሀኖች ላይ የፈሪ በትሩን አሳርፎ በርካቶች የከባቢውን ንፁሀኖችን በገፍ ጨፍጭፏል። በፋኖዎቹ የመልሶ ማጥቃት ጥቃት ክፉኛ የተከፈተበት የፋሽስቱ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደየመጣበት ምሽጉ ተመልሷል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 20/2018 ዓ.ም
🙏31
ብልፅግና ወልቃይት ላይ የመዘዘው የመጨረሻ ካርዱ!

ከጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ በአማራ ክልል ወልቃይት ቀጠና በማይ-ዳጉሻ በኩል የተጀመረው ውጊያ አድማሱን አስፍቶ በምስራቅ ጠለምት እና በምዕራብ ጠለምት ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል።

ሦስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውጊያ በሰላሬ፣ በመቃብር አንበሳ፣ ማይበረና ሰራር የተባሉ አከባቢዎችን ጨምሮ በምጫራ ግንባር በአጠቃላይ በሦስት ግንባሮች በከባድ መሣሪያዎች ታግዞ እየተካሄደ መሆኑን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ብልፅግና፡ በባለቤቱ በአማራ ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ወልቃይትን ከሕወሓት ታጣቂዎች የሚከላከል መስሎ ተኩስ ከጀመረ በኋላ፡ እንደለመደው በስልታዊ ማፈግፈግ ስም ወልቃይትን ሙሉ ለሙሉ ለሕወሓት በማስረከብ "ወልቃይትን ከወረራ እንዳልከላከል ፋኖ እንቅፋት ሆኖብኛል" የሚል ካርድ ለመምዘዝ መዘጋጀቱም ታውቋል።

ብልፅግናም ሆነ የብልፅግና ተላላኪው በአዴን የወልቃይት ጉዳይ ጉዳያቸው አይደለም። እነዚ ሁለት ፀረ አማራ ኃይሎች ወልቃይትን የሚፈልጉት ለፖለቲካዊ ትኩሳታቸው ማብረጃ ብቻ ነው።

ወዲህ ደግሞ በአዴን የወልቃይትን አጀንዳ የሚያነሳው ፋኖን እርስ በእርሱ ለመከፋፈልና ከሕዝቡ ጋር የመነጠል ስራ ለመስራት ነው።

እንጂማ በአዴን በየትኛው ጊዜና ሰዓት ነው የፌደራል መንግስቱ እግር አጣቢ ከመሆን ወጥቶ ለሕዝብ አስቦና ተቆርቁሮ የሚያውቀው።

የአማራን እርስት አሳልፈው የሰጡ በአዴኖች፣ ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ ውክልና እንዳያገኝ በማድረግ ለዘር ፍጅት የዳረጉት በአዴኖች፣ ለመጣ ለሄደው የፌደራል መንግስት ዘዋሪ ቡድን ማጎብደድና መላላክ የማይሰለቻቸው በአዴኖች፣ የፌደራል መንግስቱ ከድሮንና ጄት ጀምሮ በአለም አቀፍ የጦር ሕግ የተከለከሉ መርዛማ መሳሪያዎችን ጭምር ታጥቆ የክልሉ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲፈፅም የፈቀዱና አሁንም ይሄንን ዘግናኝ ድርጊት እየመሩና እያስተባበሩ የሚገኙት በአዴኖች፣ ሕዝቡ አማራዊ ስነልቦና እንዳይኖረው በአጥንትና ጉልጥምት ቆጠራ ተዘፍቆ፡ በጎጥና በመንደር ተወሽቆ እንዲቀር ለማድረግ ሌት ተቀን የሚታትሩት በአዴኖች ናቸው።

ከአማራ ባሕል ያፈነገጡ፣ አማራዊ ስነ ሰብ ያልተላበሱና ስልብ ስነልቦና ያላቸው፣ መላላክን እና መገረድን እንደክብር የሚቆጥሩት የበአዴን ሰዎች እንዴት አያሌ መስዋዕትነት ስለተከፈለበት ወልቃይት ሊያስቡ ይችላሉ?

የበአዴን ሰዎች ከአማራ ተቆርሰው ለተወሰዱ ለየትኛውም እርስቶች እዝነትም ሆነ መቆርቆር ፈጥሮባቸው አያውቅም።እንደውም  ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ሙሉ ወሎን በወራሪው ኦህዴድ ጠቅልሎ ለማስወሰድ ጫፍ ደርሰዋል።

ይህ ቡድን ሙሉጊዜውን በግርድና በማሳለፉ አሁን የአማራ ሕዝብ ላለበት ሁኔታ አጋልጦታል።

ይሄው የአማራ ሕዝብ የመከራ ምንጭ የሆነው በአዴን ከፌደራል መንግስቱ ጋር በመመሳጠር ከጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ በወልቃይት በኩል አዲስ ጥቃት በመክፈት እንደለመዱት በስልታዊ ማፈግፈግ ስም ገና ነፃነቱን አጣጥሞ ያልጨረሰውን የወልቃይት አማራን ሕዝብ ዳግም ለወረራ ሊዳርጉት ቋምጠው ተነስተዋል።

ቡድኑ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ያስችለው ዘንድ፡ ከርስት በላይ የሆነውን የወልቃይትን ጉዳይ በመግፋት ሕዝቡን ለጥቃት ከመዳረጉም በላይ የፋኖን ኃይል ለማዳከምና እርሱ በእርሱ ለመከፋፈል "ፋኖ ከሕወሓት ጋር ተባብሮ" ወልቃይትን አስወረረብን የሚል አጀንዳ መምዘዙ እጅግ አስገራሚ ያደርገዋል።

ብልፅግና በወልቃይት ጥቃት እንዲመጀመር ማስደረጉ ዋነኛ ምክኒያት ከሰሞኑ የአማራ ፋኖ ወጥ የሆነ አደረጃጀት መመስረቱን ተከትሎ የፈጠረበት ከባድ ድንጋጤና ጭንቀት ነው።

የፋኖን የወደፊት አቅጣጫ ያዛባልናል ብለው ካሰቡት አንዱ የወልቃይትን ጉዳይ አጀንዳ በማድረግና ዳግም በማስወረር፡ አስወረርከን የሚል አማራ ከተነሳም፡ የሕወሓት ታጣቂዎችን ከወልቃይት እንዳላስወጣ ፋኖ እንቅፋት ሆኖብኛል የሚል ካርድ ለመምዘዝ አልሞ ነው።

ነውረኛውና ልፍስፍሱ ብልፅግና የሕወሓት ታጣቂዎች በወልቃይት የከፈቱትን ወረራ ለመቀልበስ መከላከያ ሰራዊቱን ካሰማራው ፋኖ ቀጥታ ያለከልካይ ወደ አራት ኪሎ ያመራብኛል የሚል የቂል መልስ እንደሚሰጥም ይጠበቃል።

ለዛም ነው ብልፅግና በወልቃይት ጥቃት መከፈቱን ተከትሎ አፀፋዊ ምላሽ ወሰድኩ የሚል የተለመደ ቀደዳውን በአክቲቪስቶቹ በኩል እያስነገር የሚገኘው።

ነገ ደግሞ "ስልታዊ" ብሎ የሚጠራውን የማፈግፈግ አይነት ያፈገፍግና ለምን የሚል ጥያቄ ሲነሳበት ወልቃይት ላይ የተቃጣውን ወረራ እንዳልመክት ፋኖ እንቅፋት ፈጠረብኝ በሚል የለቅሶ ፖለቲካ ለመስራት ካሁኑ ድንኳን ተከላ ጀምሯል።

ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ ጣፈጠም መረረም የአማራ ፋኖ እያደረገ ባለው የሕልውና ትግል ቀዳሚ አላማው የተከበረ፣ እርስቶቹ የተጠበቁለትና ማንነቱ የማያስጠቃው አማራ እንዲኖር ማድረግ፣ ሕልቆ መሣፍርት ግፍና መከራን ጨምሮ የዘር ጭፍጨፋ ለተፈፀመበት የአማራ ሕዝብ ፍትሕ ርትዕ ማስፈን መሆኑን ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው።

@መረብ ሚዲያ
👍2
በሆዳቸው ወድቀው ለብልፅግና መገረድን  ምርጫቸው ያደረጉ (ትግሉን የከዱ ባንዳወችም፣ ቀድመው የፈረሙቱ የአብን ሰወችም ሆኑ ሌሎች ከህሊናቸዉ የተፋቱ የአብይ አማሮች) የሚግባቡበት የጋራ ቋንቋ አላቸው።  ፋኖን በተላላኪነት መፈረጅ።

ይህንን ነገር ደጋግመው የሚያጮሁት መደበቂያ ፍለጋ ነው። የዘር ማጥፋት ጦርነት ታውጆበት እየተጨፈጨፈ ያለን ህዝብ በመካዳቸው እርቃናቸውን ቆመዋል። ከሞራል፣ ከህሊና እና ከታሪክ ጥያቄወች የሚሸሸጉበት ዋሻ ፈልገዋል። ይህንን ዋሻ ያጡ ባንዳወች እና የተላላኪነት ምልክቶች ህይወቱን እየሰጠ ህዝቡን ከጥፋት በማዳን ላይ ያለን ታጋይ በማጠልሸት እና አቻ ፍለጋ ላይ በመሰማራት ራሳቸውን ሊያስደስቱ እየደከሙ ነው።
እነሱ እርቃናቸውን ስለቆሙ ከትግላችን አነሳስ እና ባህሪ ጋር በማይገናኝ መንገድ ፋኖን የሆነ አካል ይመራዋል ብሎ በመፈረጅ እንደነሱ ህሊናችን እንዲታረዝላቸው ይፈልጋሉ።

ፋኖ በታሪክ ፊት በክብር የሚያቆመዉን ፀረ- አገዛዝ ተጋድሎ እያደረገ ነው። መላላክ እና በራስ ህዝብ ላይ መቆመር የባንዳወች የህይወት መመሪያ ነው። ፋኖ የአማራን ህዝብ ከመጥፋት ለመታደግ ክቡር መስዋዕትነት የሚከፍል በዚህ ዘመን ካሉ ግዙፍ የነፃነት፣ የሰብአዊ መብት ታጋዮች ቀዳሚው ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚያስከትለው ወይም በጋራ የሚያሰልፈው እንጅ ለብልፅግና እንዳደሩቱ የሚገብርለት ወይም ጁኒየር የሚሆንለት አጋር የለዉም። በህልውናችን ላይ በመጣ ግዜ ህወሃትን ጨምሮ የትኛውንም አካል ለመዋጋት የሚቀድመን እንደሌለ ህዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ይህንን ደግሞ ከአብይ ጉያ ስር ተወሽቀን ሳይሆን በራሳችን መንገድ ያደረግነው፣ ማድረግም የምንችለው እንደሆነ በተግባር አረጋግጠናል።

የህልዉና ጦርነት ውስጥ የከተተን የብልፅግና አገዛዝ ፕሮፖጋንዳም የውጊያ መስመርም ሊያዘጋጅልን አይችልም። በUAE ጀት እና ድሮን አማራን ለሚጨፈጭፈው አብይ አህመድ ስልጣን በፈቃደኝነት የሚፈስ የአማራ ደም አይኖርም። መስዋዕትነት የምንከፍለው አረመኔውን አገዛዝ በማስወገድ የህልውና ጥያቄያችንን በምሉዕነት ለማረጋገጥ ነው።

የአፍሪካ ቀንድ ሰላም የሚመጣው ብልፅግና ሲወገድ ብቻ ነው።

©አርበኛ አስረስ ማረ
👍2
ጀግኖች ለአላማቸው ይሰዋሉ! ትግላቸውና አላማቸው ይቀጥላል!

ጥር 20/2018 ዓ/ም ጀግናው መኩሪያ ፈንቴ ለአላማውና የህልውና አደጋ ላይ ላለው ህዝቡ አንድያ ህይወቱን ለግሷል!

አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ የመጀመሪያ ዲግሪውን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን፤ሁለተኛ ድግሪውን በወልድያ ዩኒቨርስቲ ተመርቋል:: በ2013 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ንቅናቄንና ምስረታዎችን በመቀላቀል የአርበኝነቱን ህይዎት ያኔ ጀመረ። የአርበኝነት ጅማሮው ከአምስት አመታቶች በላይ በጫካና በዱር ያሳለፈ በፅናትና በታማኝነት ለአማራ ህዝብ የቆመ ነበር።

አርበኛ መኩሪያ የደጋው መብረቅ ኮር ህዝብ አደረጃጀት መምሪያ እና በሚኒሊክ ዕዝ ማህበራዊ ዘርፍ ም/ሃላፊ ነበር። አርበኛው ከአዋጊነት እስከ ተዋጊነት የተዋጣለት መሪም ነበር። ጥር 20/2018 ዓ/ም ከማለዳው12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት በዘለቀው አውደ ውጊያ በርካታ የፋሽስቱን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ፤በርካታዎችን ምርኮኛና ቁስለኛም በማድረግ ጀግናው ፊት ለፊት ከጥላት ጋር አንገት ለአገት ተናንቆ በጀግንነት ተሰውቷል።

አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ከአማራ ህዝብ በፊት እኔ እሞታለሁ ብሎ ደረቱን ለጥላት የሰጠ የቁርጥ ቀን አርበኛ ነበር። ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦርን ከጓዶቹ ጋር በመመስረትና ለአማራ ህዝብ የነፃነት ሀይል አድርጎ በመገባት ትልቅ ሚና ነበረው። አርበኛው አንድያ ህይዎቱን ለአማራ ህዝብ በአውደ ውጊያ ሜዳ ላይ የሰጠ ሲሆን የአርበኞች መሰዋዕትነት የአማራ ፋኖ ትግል መራር ዋጋ የሚከፈልበት ህያው ዋጋ መሆኑ ሲሆን ለዚህ ትልቅ የታሪክ ህያው ምስክር ሆኖ አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ለአላማውና ለህዝቡ ተሰውቷል።

#ኑረን ለምናገለግለው ሞተን ለምናሻግረው ህዝባችን ምንስ የማንሆንለት ይኖራልና!

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!
ጥር 21/5/2018 ዓ.ም
1💔1
ቤተ-ክርስቲያን አገልጋዩ የሐይማኖት አባት በብልፅግና ሰራዊት በግፍ ተረሸኑ!

ጥር:-21/2018 ዓ/ም

በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ቡግና ወረዳ 09 ጉልሐ ቀበሌ ነዋሪ እና የጀርጀንቦይ መድሐኒአለም ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት የ58 አመት ዕድሜ ያላቸው መርጌታ ጌጡ በላይ የብልፅግና አገልጋይ በሆኑት መከላከያ ሰራዊት አባላት ጥር 20/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ገደማ በግፍ ተረሽነዋል።

የቤተ-ክርስቲያኑ አገልጋይ አባት መርጌታ ጌጡ በላይ አይና እየሱስ ከተማ እህል በወፍጮ አስፈጭተው በመመለስ ላይ እንዳሉ እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ጫካ ውስጥ አራት ጥይት አከታትለው በመተኮስ እንደረሸኗቸው ታውቋል።

የተረሸኑበት ምክኒያትም ሰሞኑን ከፋኖ ኃይሎች ጋር አስታርቁን በሚል ሽፋን ከተመለመሉት የሐይማኖት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ራሳችሁ ባጠፋችሁት ጥፋት፣መነኩሴን ለሚደፍር፣የቆሎ ተማሪን ለሚረሽን፣ቤተ-ክርስቲያንን ለሚያረክስ ስርዓት አልላክም በማለታቸው በቡግና ወረዳ ብልፅግና አመራሮች ሴራ ጠንሳሽነትና አስተባባሪነት በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ትዕዛዝ ፈፃሚነት የሐይማኖት አባቱ እንደተረሸኑ የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
💔1
የአማራ ህዝብ ማወቅ ያለበት ራያ አካባቢ ያለው ነባራዊ ሁኔታና እውነታ!

አላማጣ ከተማ ራያ አላማጣ እና ኮረም ዙሪያ የነበረው የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ጥር 21/2018 ዓ.ም አካባቢውን ለቆ ወጥቷል::

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ራያ ላይ የነበረውን መዋቅር በሴራ አፍርሶ አካባቢውን አሳልፎ በመስጠት በኋላም የተወሰነ ሃይሉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ በማስፈር አካባቢውን ከትግራይ ሃይሎች ጋር ይዞ መቆየቱ የሚታወቅ ነው::

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከትግራይ ሃይሎች ጋር በጋራ ሰፍሮ ይኖር የነበረውን ሰራዊቱን ጥር 21/2018 ዓ.ም ያለ ምንም የጥይት ተኩስ ለቆ እንዲወጣ አድርጎ ቦታውን ሙሉ ለሙሉ ለትግራይ ሃይሎች አስረክቧል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም አገዛዙ በዚህ መንገድ ለቆና አስረክቦ የወጣውን የራያ አካባቢዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ሴራ ሊሰራበት እንደተዘጋጀ መረጃው አለን:: ይህንን ካሁን በፊት እንዳደረገውና አሁንም እንደሚያደርግ ግን ለህዝብ የተደበቀ አይደለም::

ብልፅግና ይዞት የነበረውን የራያ መሬት በዚህ መንገድ ያስረከበ መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ህዝብ ላይ የተለመደ ፀረ ፋኖ የውሸት ፕሮፓጋንዳውን በመስራትና አዲስ የውጊያ አጀንዳ በመፍጠር ብሎም በፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ሚዲያዎቹ በማስተጋባት ለአማራው ከእልቂት በስተቀር አንዳች መፍትሄ ወደሌለው ጦርነት በማስገባት እድሜውን ለማራዘም እየሰራ ይገኛል::

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሚሊሻ ስም የሰበሰበውን የአማራ ገበሬ እና አድማ ብተና ቀድሞ ወልድያ እና ራያ ቆቦ ዙሪያ ያሰፈረ ሲሆን ከሰሜን ወሎ ሚሊሻ ጋር በማድረግ በቀጣይ ከትግራይ ሃይሎች ጋር ሊያደርገው ባሰበው ጦርነት ከፊት ሊማግዳቸው ዝግጅቱን ጨርሷል::

*ማስታወሻ፦ አገዛዙ ባሁኑ ሰዓት ሰሜን ወሎ ዞን ባሉ ወረዳዎች የግል ታጣቂዎችን ሳይቀር ለጥር 22/2018 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ እየጠራ ይገኛል::

እየሆነ ያለው እውነታ ይሄው ነው::

ጥር 21/2018 ዓ.ም

አርበኛ አበበ ፈንታው
የአፋብን አጋርነትና ትብብር መምሪያ ኃላፊ!
👍1