ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራን የህልውና ትግል ለሚደግፉ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች የተላለፈ ጊዜያዊ የአሰራር ስነ ስርዓት አቅጣጫ

እንደሚታወቀዉ ላለፉት 3 አመታት መሬት ላይ ያለዉ ትግል በአንድ ወጥ ድርጅት ያልታቀፈ ሆኖ መቆዬቱ የትግሉ ደጋፊ ሚዲያወች በተለያዬ ፍረጃ እና መካሰስ ውስጥ እንዲቆዩ ምክንያት ሆኗል።

በተለይም ቡድናዊ አሰላለፍ፣ ልዩ ፍላጎት እና የጥቅም ትስስር እንዲሁም ሌሎች ችግሮችን ባለመሻገሩ ምክንያት ሚዲያወቻችን ባላቸው አቅም ልክ ገንቢ ሚና እንዳይጫወቱ አድርጓቸዋል፡፡

ስለሆነም ጥር 09 ቀን 2018 ዓ.ም የተመሰረተው አታጋይ ድርጅታችን የትግሉ ደጋፊ ሚዲያ አካላትን በድርጅቱ የአሰራር መርህ መሠረት መደገፍ እና የመምራት ሀላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል።

በመሆኑም በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በሚመራው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል፣ በሚዲያ የትግል አግባብ ፣ በህዝብ ግንኙነት እና ፕሮፖጋንዳ እንዲሁም ፖለቲካል አክቲቪዝም ዘርፍ የምትሳተፉ የሚዲያ ባለቤት እና ባለሞያዎች የሆናችሁ አካላት ከታች የተዘረዘሩትን የአሰራር አቅጣጫወች ተከትላችሁ እንድትሰሩ በጥብቅ እናሳስባለን።

1) ድርጅት አምኖባቸዉ ሀላፊነት በሰጣቸው በየደረጃው ባሉ አመራሮቻችን ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ባስቸኳይ እንዲቆም ማድረግ፤ እንዲሁም አንድን አመራር በተለዬ መንገድ ማወደስ እና ለትግሉ ከሌላው የተለዬ አስተዋፅኦ እንዳለው አድርጎ ፕሮፖጋንዳ አለመስራት፤

2) የአፋብን አመራሮች ያከናወኑትን የይቅርታ መድረክ በሚዲያውም ዘርፍ ያሉት የይቅርታ መድረክ እንዲፈጥሩ ማድረግ እና የውስጥ መጠላለፉን በማስወገድ “መሬት ላይ አንድ ወገን አንድ ጠላት” የሚለዉን በተግባር በማከናወን የአብይ አህመድ አገዛዝ ላይ ብቻ ማነጣጠር፤

3) በዚህ የህልዉና ትግል ዉስጥ የድርጅቱን መርህ የማያከብሩ የሚዲያ አካላት ካሉ በአግባቡ መታገል የሚገባ ሲሆን ከዲሞክራሲያዊ መተጋገል አግባብ ውጭ ሆነው ከድርጅት መስመር እና መርህ በመጻረር የሚቆሙትን ድርጅቱ በሚሰጠው አጣጫ መሠረት ጠላትነታቸው በህዝቡ ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ፤

4) ትግሉን መደገፍ በድርጅት የትግል መስመር ገብቶ መታገልን ግድ የሚል መሆኑን በመረዳት  የሚዲያ ባለቤት እና ባለሞያዎች የድርጅት አሰራርን በማክበር፣ ከጣልቃ ገብነት በመራቅ፣ የራስን ሚና ለይቶ አውቆ በዚያ መስመር መሰለፍ፤

5) ለድርጅቱ ይጠቅማሉ የሚባሉ ገንቢ ሀሳቦችን ድርጅቱ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በሚገናኝባቸው መድረኮች ለውይይት ማቅረብ እና መሟገት፤

6) በድርጅቱ ውሳኔ እና ብያኔ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ወደ አደባባይ አለማውጣት እና በዘመቻ ተጽዕኖ አለማድረግ እንዲሁም ውሳኔ እና ብያኔ ባገኙ ጉዳዮች ላይ  ያልተገባ ጩኸት በማሰማት በሰራዊት እና በህዝቡ ውስጥ ያጥርጣሬ አለመፍጠር፤

እና መሰል መርሆወችን የኢዲቶሪያል ፖሊሲያችሁ አካል በማድረግ ትግሉን እና ድርጅታችሁን በመርህ መደገፍ እና የድርጅቱን ውሳኔ አክብሮ መስራት ከእናንተ የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው።

በመሆኑም ድርጅታችን በቀጣይ የሚዲያን የትግል አግባብ፣ አሰራር፣ ተግባር እና ሀላፊነትን በሚመለከት ግልፅ መመሪያ የሚያወጣ ሲሆን እስከዚያ ድረስ ይህ የአሰራር ስነ ስርአት ጊዜያዊ አቅጣጫ በሁሉም የድርጅት ደጋፊ ሚዲያ እና ባለሞያዎች እንዲተገበር ለማሳሰብ እንወዳለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
👍2
የአደረጃጀት መረጃ !

የመዋቅር ግንባታና ተሐድሶ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ራሱን በማደስ የአመራር ሽግሽግና አዲስ ምደባ አደረገ::

በአፋብን የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ዛሬም በጠራ የአደራጃጀት መዋቅር ብቅ ብሏል::

ትግል ቅብብሎሽ ነው። በትግል ውስጥ  መሰዋት፣ ጉዳትና መክዳት ያሉና የነበሩ ናቸው። ሁሉም የየራሳቸው መገለጫ ቢኖራቸውም በኛ የትግል ምራፍ ደግሞ መክዳት ከማህበረሰባችን ወግና ባህል  አንጻር ሲበዛ ሰላቶነት ፣ አቅመ ቢስነትና እና ወዶ ገብነት ነው።

ሰሞኑን የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር  የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ  የነበረ ለአገዛዙ  ያደረ በመሆኑ ዳግም አደረጃጀቱን በማስተካከል በሚታወቅበት ጠላትን እረፍት የመንሳትና የህዝባችንን የህልውና አደጋ የመቀልበስ ትግል በአዲስ መንፈስ እራሱን አደራጅቷል።

ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር በግለሰቦች ስብዕናና ዝና ያልተመሰረተ በመሆኑ እንደ ከዚህ ቀደሙ አስደማሚ  ግዳጅና ኦፕሬሽኖችን ለመስራት እራስን የማዘጋጀት ቅድመ ስራዎችን ጭምር አከናውኗል በመከወን ላይም ይገኛል ።

በመሆኑም ዛሬ ጥር 19/2018 ዓ.ም ክፍለ ጦሩ የሚከተለውን አዲስ አደረጃጀት አዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል።

1. አርበኛ ተመስገን አብርሀም ------ ዋና ወታደራዊ አዛዥ
2. አርበኛ ያብባል ፈለቀ ------ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ
3. አርበኛ ጌታቸው ሞገስ ----- ዋና ወታደራዊ ዘመቻ ኃላፊ
4. አርበኛ አያና ሆነ ------ ምክትል ወታደራዊ ዘመቻ ኃላፊ
5. አርበኛ ባይነሳኝ እንግዳው ----- ፋይናስ ኃላፊ
6. አርበኛ  ታደሰ አሰፋ ------- ምክትል ፋይናስ ኃላፊ
7. አርበኛ ባንቲደር እውነቱ ------- ቁጥር እና ኦዲት ኃላፊ
8. አርበኛ ጌትነት ስመኝ ------- ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
9. አርበኛ ገበየሁ አማረ ------ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
10. አርበኛ ነጋ ሆነልኝ ------ የሰው ኃይል ኃላፊ
11. አርበኛ ሻለቃ ታዴ አለባቸው ------ ሎጅስቲክስና ኦርዲናስ ኃላፊ ሆኖ ተደራጂቷል።

ስለሆነም ማህበረሰባችንም ሆነ የትግል ጓዶቻችን ትግላችን የህልውና ነውና በግለሰቦች  ፍላጎትና ጥቅም ላይ የተመሰረተ ባለመሆኑ የህዝባችንን ህልውና ሳናረጋግጥ እሚዝል ክንድ እሚደክም ጉልበት አልተላበስንምና ከእንደዚህ ቀደሙ በእልህና በቁጭት የምንታገል መሆኑን ጭምር መግለጽ እንፈልጋለን።

ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር!!!

ጥር 19 / 2018 ዓ.ም
የሙጃ ማርያም ከተማ ኗሪው ወጣት ባለሐብት በአገዛዙ ሰራዊት በጭካኔ ተገደለ!

በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ግዳን ወረዳ መናገሻ ሙጃ ማርያም ኗሪ የሆኑት ወጣት ባለሐብት አራጋው ሲሳይ በአረመኔው ብልፅግና ሰራዊትና አመራሮች ጥር 17/2018 ዓ/ም አመሻሽ 2:00 ሰዓት ላይ በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ አንድያ ህይወቱ ልታልፍ ችላለች።

በግዳን ወረደ ብልፅግና አመራሮችና በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት አዛዦች የጦስ ዶሮ የሆነው ወጣት ባለሐብት በተሸረበበት ሴራ 5ሚሊዮን ብር ለአብይ አህመድ ወንበር መፅናት ለሚታትሩ መከላከያ አመራሮች የሐብት ማከማቻ ግዛት እንዲከፍል፣ባይከፍል እንደሚገደል ውሳኔ ተወስኖ እንዲከፍል ሲነገረው እንደሚገድሉት ስላወቀ ካሶኒውን ሽጦ ቢከፍላቸውም የፋኖ ደጋፊ ስለሆነ መረሸን አለበት በሚል ውሳኔ በአረመኔዎቹ የጦስ ዶሮ ሊሆን ችሏል።

ይህንን ግድያ ያስተባበሩትና የውሳኔ አካል የሆኑት
1ኛ. እንዳለው አባተ:- የግዳን ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ
2ኛ. አማኑኤል አያሌው:- የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ
3ኛ. ሰማኝ ባዮ:- ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ እና
4ኛ. ሙጃ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሲሆኑ በቀጥታ በጄኔራል አሰፋ ቸኮል ትዕዛዝ ከዚህ በፊት እያንዳንዳቸው 1.5ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉና ካልከፈሉ እንደሚረሸኑ ተነግሯቸው የተጠየቁትን ከከፈሉ በኋላ ወጣቱ ባለሐብት እንዲረሸንና አፈፃፀሙን እንዲያስተባብሩ የተሰየሙ ጥቁር አማራዎች መሆናቸውን የውስጥ መረጃዎች አሳውቀዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው በመሩት የመንግስት ሰራተኞች መድረክ ላይ መንግስት አገልጋዩን ሰብስቦ ሰሞኑን የሚረሸን ሰው አለ በማለት የተናገረ ሲሆን በተናገረ ሁለት ቀን ባልሞላው ውስጥ ወጣቱን ባለሐብት አምስት መከላከያዎች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ደፈጣ ይዘው በአምስት ክላሽንኮፍ ጥይት በሳስተው ከገደሉት በኋላ ለሌሎች ትምህርት ይሆናል በማለት እጅና እግሩን በሳንጃ በመቆራረጥ፣እንዲሁም ብልቱን በመቁረጥ ህዝቡን እንዳሸማቀቁት ታውቋል።

ህዝቡም በዚህ ድርጊት ማዘኑንና ከአብራኩ በወጡት የአፉኝት ልጆች እየታረደ፣እየተሳደደ፣እየተደፈረ፣ሐብት ንብረቱ እየተዘረፈ መሆኑን በመረዳቱ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ መግባቱ ታውቋል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

@የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
4
ሰበር የግንባር መረጃዎች | በጎንደር ድል ተበሰረ - ከድተው ገቡ | የምሽጉ ጌታ ኮማንዶ ሙሉቀን ሲዘከር
የችሎት ውሎ

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ የሽብር ወንጀል ተከሳሾች የሰነድ ማስረጃ አስተያየት በጽሁፍ አቅርበዋል ፤ ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረቡ አቤቱታዎችና የመብት ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥር 28/2018 ቀጠሮ ይዟል።

ከአማራ ማንነታቸው ጋር በተያያዘ ታፍነው በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ከ300 በላይ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን ጉዳይ ሲመለከቱ የከረሙት ሶስት ዳኞች በሌላ ሶስት አዳዲስ ዳኞች ተቀይረው ነው የእለቱ ችሎት እንዲታይ የተደረገው።

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ ከአማረ መለሰ እና ደሳለኝ እጅጉ በስተቀር 14 ተከሳሾች በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጥር 19/2018 በነበረው ችሎት ከማ/ቤት ተገኝተዋል።

ተከሳሽ አማረ መለሰ በአዋሽ አርባ እና በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከምርመራ ጋር በተያያዘ በደረሰበት ግፍ እና በደል የአዕምሮ ሕመም አጋጥሞት በአማኑኤል ሕክምና እየተከታተለ ስለሚገኝ ዛሬን ጨምሮ ለበርካታ ወራት ፍ/ቤት እየተገኘ አይደለም።

ተከሳሽ ደሳለኝ እጅጉም ከአልባሳት ጋር በተያያዘ ከማ/ቤቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በችሎት ሳይገኝ መቅረቱ ተገልጧል።

ጥር 19/2018 በነበረው በዚሁ ችሎት በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በቀደመ ቀጠሯቸው መሰረት የሰነድ ማስረጃ አስተያየት በጽሁፍ አቅርበዋል።

በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ፣ የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ እና የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ተሻገር በኩል የተለያዩ አቤቱታዎችና የመብት ጥያቄዎች ለችሎቱ ቀርበዋል።

የም/ቤት አባልነት ያለመከሰስ መብታቸው ከመነሳቱ በፊት ሊከሰሱ እንደማይገባ በመግለጽ መብታቸው ተነስቶ ከሆነም ሕጉን በጠበቀ መልኩ ስለመነሳቱ ፍ/ቤቱም ሆነ ተከሳሾች በቃለ ጉባኤ ጭምር ተረጋግጦ ሊያውቁት እንደሚገባ በመጥቀስ ማስረጃው ይሰጣቸው ዘንድ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

በተያያዘም በስልክ ጠለፋ ተገኘ የተባለው የድምፅ ሪከርድ በሕጋዊ መልኩ በፍ/ቤት በኩል ሂደቱን ጠብቆ የተከናወነ ስለመሆኑ የክሱ እና የክርክር መዝገቡ እንዲመጣልን በማለት ትዕዛዝ ጠይቀዋል።

በዐቃቤ ሕግ በኩል አሁን በከሳሽ በኩል ማስረጃ የሚቀርብበት እንጅ ተከሳሾች ማስረጃ የሚያቀርቡበት አይደለም ፤ ተከላከሉ ከተባሉም ያኔ የሚፈልጉትን መረጃ ከተለያዩ ተቋማት ጠይቀው ሊያስመጡ ይችላሉ ፤ በመሆኑም ማስረጃው ለምን እንደተፈለገ ግልፅ ባልሆነበት አስተያየት ለመስጠት ይቸግረናል የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የስልክ ጠለፋውን በተመለከተ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ከሰጠ ተፈጻሚ እንደሚያድርግ ነው ከሳሽ የገለፀው።

ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረቡ አቤቱታዎችና የመብት ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥር 28/2018 ቀጠሮ ይዟል።

ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾች በሰጡት የሰነድ አስተያየት ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት ፍ/ቤቱን የጠየቀ ሲሆን ችሎቱም የተከሳሾችን የሰነድ አስተያየት ተመልክቶ ምላሽ ያስፈልገዋል ብሎ ሲያምንበት ትዕዛዝ እንደሚሰጥ ገልጧል።

ተከሳሽ አማረ መለሰን በተመለከተም ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ተወስዶ እንዲታከም ለቀረበው አቤቱታ መጀመሪያ ተቋሙ በተሻለ የሕክምና ተቋም እንዲያሳክመውና ማሳከሙንም ሪፖርት እንዲያደርግ ያለው ፍ/ቤቱ አቤቱታውን ከዛ በኋላ የምናየው ይሆናል ሲል ገልጧል።

በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረቡ አቤቱታዎችንና የሰነድ አስተያየቶችን መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥር 28/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።

በተመሳሳይ በእለቱ ፍ/ቤት ከቀረቡ የሽብር ተከሳሾች መካከል ንብረት ሕብስት አንዱ ነበረ።

ዐቃቤ ሕግ በንብረት ላይ ያቀረበውን ክስ እንዲያሻሽሎ እንዲቀርብ በሚል ትዕዛዝ የተሰጠው ቢሆንም አሻሻልኩት ያለው ክስ ገና አልተሻሻለም ከመባሉ ጋር ተያይዞ ፍ/ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 21/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥር 19/2018)
1🙏1
ከአማራ ማህበራት ግብረሃይል በዩኬ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መመስረትን አስመልክቶ የተሰጠ የደስታ መግለጫ!
🙏2
ሰበር ዜና !

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአጼ አምደፅዮን ኮር እያደረገ ባለው ተከታታይ ውጊያዎች በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ።
       
በዛሬው ዕለት ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጠላት ያለ የሌለ የአየር ወለድ ሰራዊቱን ከሰላድንጋይ ከተማ እና ከጣርማበር ወረዳ በማሰባሰብ የወገንን ሃይል የማፈን ምናባዊ አላማ አንግቦ ወደ ሳሲት እና አይሶፌ ቀጠናዎች በማቅናት ላይ እያለ መረጃው ቀድሞ የደረሰው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር አካል የሆነው ራንቦ ክፍለጦር ልዩ ስሙ አጃና ሚካኤል መገንጠያ ላይ በጣለው የደፈጣ ጥቃት ከ19 በላይ የሚሆኑት የብልፅግናው ሰራዊት እስከወዲያኛው ሲሸኙ፣ በርካቶችን ቁስለኛ በማድረግ ከፍተኛ ኪሳራ ሲያደርስበት፣ በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ወደ ጨበጣ ውጊያ ተቀይሮ አድማሱን በማስፋት ክፍለጦሩ ታላቅ ድል ተጎናፅፏል።

በጀግናው ሰራዊታችን ደፈጣ ለይ የወደቀው የአየር ወለድ ክፍለጦር አባላቱ በጉዞ ላይ እያሉ በተፈፀመበት የቦንብ ጥቃትና እንደ እሳት በዘነበበት የጥይት አሩር በርካቶቹ ሲገደሉ ቀሪው የሰላድንጋይ ሆስፒታልን አጨናንቋል::

በመኪና ተጭኖ ወደ ሰላድንጋይ የተወሰደው የሰራዊቱ አስክሬን መቅበሪያ በከተማው በስተምስራቅ አቅጣጫ በግሬደር እየተቆፈረ እየተዘጋጀ ይገኛል።

በሌላ በኩል የአፄ አምደ ፂዮን ኮር አካል የሆኑት የእምዬ ምኒሊክ ልጆች በትላንትናው ዕለት ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በሌላኛው የውጊያ ግንባር ከመንዝ ቀያ ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ከዘመሮ ከተማ ተነስቶ ወደ ክምር ድንጋይ በማቅናት ላይ እያለ ባደረጉት የተቀናጀ ተጋድሎ ድል ሲቀዳጁ 3 የሚሊሻ አባላት በምኒሊክ ክፍለጦር መማረካቸውን ክፍለጦሩ በላከው የግንባር መረጃው አስታውቋል።

በምኒሊክ ክፍለጦር የተማረኩ የባንዳ አባላት ስም ዝርዝር:-
1ኛ. በቅርቡ የሚሊሻ አባል የሆነው  አቶ ላይችል ከፈለኝ (በፋኖ ውስጥ በአባልነት የቆየ)
2ኛ. አቶ ቃኘው ደምሴ የ 02 ቀበሌ ሊቀመንበርና እና
3ኛ. በቅርቡ የሚሊሻ አባል የሆነው አቶ መክብብ ገብሬ (በፋኖ ውስጥ በአባልነት የቆየ) ናቸው።

ይሕ በእንዲሕ እንዳለ ሌላኛው የአፄ አምደ ፂዮን ኮር አካል የሆነው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር በተደጋጋሚ ወንጀል ሲፈልጋቸው የነበሩ የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የአገዛዙ ቀኝ እጅ የሆኑትን የሚሊሻ አባላት በልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መጀመሩን ክፍለጦሩ ገልጿል።

በፋኖ ቁጥርጥር ስር የዋሉ የሚሊሻ አባላቱ:-
1ኛ. አቶ ጌታሁን ተፈራ የጎዝጎዛ ቀበሌ ሎጅሰቲክ 
2ኛ. አቶ አሰደግድግ  ለማ የሞተለሚ ቀበሌ ሀብት ሰብሳቢ ግርግር ጎጥ እና
3ኛ. አቶ እንዳለልኝ ሀብታሙ  ሞተለሚ ቀበሌ እናት ጉያ  ጎጥ ሀብት የአገዛዙ ሰብሳቢ ናቸው።

ከፍለጦሩ በቁጥጥር ስር ስላዋላቸው የሚሊሻ አባላት በሰጠው ማብራሪያ መሰረት ግለሰቦቹ ከዚሕ ቀደም በፋኖ መዋቅር ስር ሆነው እየሰሩ የነበሩ እና በመሀል ክህደት ፈፅመው ወደ ጠላት የገቡ፤ ከዛም ፋኖ ይቅርታ አድርጎላቸው በድጋሚ ወደ ፋኖ አደረጃጀት ተመልሰው በስራ ለይ እያሉ ዳግም ክህደት በመፈፀም ደብረብርሀን ከተማ ድረስ በመሄድ በአገዛዙ ቤት የማጭበርበሪያ ተሀድሶና 94,000 ብር ወስደው የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ላለው አገዛዝ ታምነው በሚሊሻ ስምሪት ላይ በነበሩበት ወቅት በራስ አበበ አረጋይ የክፍለጦር ቃኝዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ክፍለጦሩ አረጋግጧል።

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከግንባር መረጃዎችን አጠናቅሮ አድርሶናል።

  ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
      ድል ለአፋብን!!
     ድል ለአማራ ህዝብ!!
     ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!  
    አንድነታችን አሸናፊነታች!!
           
@የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
1👍1
የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት መቶ አለቃን ጨምሮ ሌሎች ወታደሮች ተደመሰሱ!!

ከጥር 18ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ጠላት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሰበሰበውን ኃይል ወደ ምዕራብ ወሎ ሲያንቀሳቅስ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት ጥቃት እየተሰነዘረበት ይገኛል።

በዚህም መሰረት ከትናንት በስቲያ ማለትም ጥር 1ቀን 2018 ዓ/ም በለጩማ ላይ ታሪክ ተሰርቷል።

በበርካታ ተሽከርካሪዎች ጭኖ ወታደሮችን ወደ ምዕራብ ወሎ እያጓጓዘ ያለው ፋሽስታዊው መንግሥት በለጩማ ሲደርስ ያልታሰበ አደጋ ገጥሞታል። የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት የምዕራብ ወሎ ቀጠና ሰሞኑን ብዛት ያለው የጠላት ኃይል ከከባድ መሳሪያ ጋር እየተጋጓዘ እንደሆነ ይታወቃል። በቀጠናው የነበረው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር ሰራዊት ድጋፍ የፋኖን ጫና መቋቋም ስላልቻለ በቅርቡ የተመሰረተው 11ኛ ዕዝ ሰራዊት በድጋፍ ሰጭነት ወደ ቀጠናው ሲገባ  የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ ፋኖዎች በሰነዘሩበት የደፈጣ ጥቃት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። ከደሴ ተነስቶ በስተ ምዕራብ በኩል ሲጓጓዝ ከነበረው በርካታ ኃይል መካከል ወደ አማራ ሳይንት ሊገባ በ6 ኦራል እና በ4 ፓትሮል ተጭኖ ሲጓጓዝ  የነበረ የጠላት ኃይል ላይ እነ ሞት አይፈሬ በሰነዘሩት ጥቃት የደረሰው ጉዳት የሚከተለውን ይመስላል:-

የተደመሰሰ 5 የመከላከያ መስመራዊ ወታደሮች እና 1 መቶ አለቃ እንድሁም 3 አድማ ብተና፤ በድምር 9 የጠላት ኃይል እስከወድያኛው ሲሸኝ 7 መከላከያ እና 9 አድማ ብተና በድምሩ 16 ጠላት ቁስለኛ ተደርጓል። የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ደምመላሾች በብርሀን ፍጥነት በድምሩ 25 የጠላት ኃይልን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል።

ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!

የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

ጥር 20 ቀን 2018 ዓ/ም
🙏1
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የ2 ወር የግዳጅ አፈጻጸሞችን ገመገመ:-
==============================
ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በ3 ግዙፍ ክ/ጦሮች የተዋቀረ ሲሆን  መልሶ ማደራጀቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅና በስሩ የሚገኙ ክ/ጦሮችን በመገምገም እና ለአመራሩ አጭር ስልጠና በመስጠት ማጠናቀቁ ይታወቃል።

ኮሩ በመልሶ ማደራጀቱ  ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ጠንካራ ጎኖች በማንሳት ለ2 ቀናት ጥልቅ ግምገማ ያደረገ ሲሆን የወደፊት የትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል።

ስለሆነም የውስጥና የውጭውን የጠላትን ከፍተኛ ጫና በመቋቋም የ109ኛ ኮር መልሶ ማደራጀት በተሳካ ሁኔታ እውን እንዲሆን ተግታችሁ ለሰራችሁ ለቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለ109ኛ ኮር አመራሮች፣ ለ88ኛ፣ ለ99ኛ እና ለ77ኛ ክፍለጦር አመራሮች፣ በሁሉም ክ/ጦሮች ስር ተጠርንፋችሁ እየታገላችሁ ላላችሁ አባሎች፣ ለቴዎድሮስ ዕዝ ኮማንዶ ዩኒት እንዲሁም ለአካባቢው ማሕብረሰብ የ109ኛ ኮር ስራ አመራር ከፍተኛ አክብሮት እና ላቀ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!
109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
🙏21