በምዕራብ ወሎ ግንባር ጠላት ይተማመንበት የነበረው ከባድ ምሽግ ተሰበረ!!
ትናንት ለዛሬ ሌሊት ማለትም ጥር 17 ለ 18 መካነሰላም ከተማ ውስጥ በተሰራ ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። ከአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሁለት ክፍለ ጦሮች ማለትም ከኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና ከመብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች መካነሰላም ከተማ ውስጥ የመሸገው ጠላት ይተማመንበት የነበረውን ከባድ ምሽግ ሌሊቱን ሰብረውታል። የጨላማ ውጊያ በመሆኑ የተነሳ በጠላት በኩል የደረሰውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ለማረጋገጥ ባንችልም የጠላት አከርካሪ እንደተሰበረ ለመረዳት ችለናል።
የምዕራብ ወሎዋ መካነሰላም ከተማን አስከብራለሁ በሚል እሳቤ ጠላት በርካታ ኃይል ከተማይቱ ውስጥ ቢያሰፍርም ፋኖ እንቅልፍ ነስቶታል፤ በመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሶዬ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ኔትወርኩ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ መሽጎ የነበረው ጠላት ነው በእነ ሞት አይፈሬ ሌሊቱን ተኩስ ተከፍቶበት ወታደራዊ ቁሳቁሱን ጭምር ጥሎ የፈረጠጠው።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር አካል የሆነው 43ተኛ ክፍለ ጦር በኮሎኔል ዮሀንሥ እየተመራ በርካታ ኃይሉን ወደ መካነሰላም ከተማ አስገብቶ ስለነበር ይህን የጠላት ግሳንግስ ሰራዊት የሚካኤል አሊ ልጆች በጥይት ሲያበጥሩት አድረዋል። በሌሊቱ ኦፕሬሽን ሰራዊታችን መካነሰላም ከተማ ውስጥ የገባ ሲሆን ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ግብአቶችን ከጠላት ጊዜያዊ ካምፕ ማውጣት ችሏል::
በ4 አቅጣጫ በተደረገው የሌሊቱ ኦፕሬሽን ጠላት ይዞታውን ላለመልቀቅ የመጨረሻ አቅሙን የተጠቀመ ቢሆንም ሰራዊታችን በአየር ማረፊያ እና በሶዬ በኩል ያለውን ምሽግ በመስበሩ የተነሳ አብዛኛው የጠላት ኃይል ወደ ደሴ መስመር መጓዙ ታውቋል። በኮሎኔል ዮሀንስ የሚመራው ኃይል አቅም ስላነሰው በሚል በዛሬው ዕለት በርከት ያለ ተሽከርካሪ ወደ መካነሰላም እየተጓዘ መሆኑንም ለማረጋገጥ ችለናል ሲል የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቃለአብ ወርቅዬ ለዕዙ በላከው የአውደ ውጊያ ሪፓርት ገልጿል።
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም

በወሎ ቤተአምሓራ የምኒሊክ ልጆች ተገርፎ ሸዋ መርሀቤቴ የገባው የ105ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ በጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በተሰራው ድንቅ ኦፕሬሽን ውጤታማ ድል መመዝገቡን ኮሩ አስታወቀ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከተሰማራባቸው የሸዋ ቀጠናዎች ውስጥ በመርሀቤቴ አውራጃ በ105ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ በትላንትናው ዕለት ጥር 17 ቀን 2018ዓ.ም ድል ተቀዳጅቷል።
በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ ጠላት መነሻውን ከሬማ ከተማ በማድረግ በግብር ስም ህዝባችንን ለመዝረፍ በከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የመጅት ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም ያልተመጣጠነ የግብር ተመን በመጣል በአስገዳጅ ገንዘብ እየሰበሰበ ባለበት ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር አካል የሆኑት በአስማረ ዳኜ 1ኛ ሻለቃ በተፈፀመው ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት ትላንት እሁድ ከቀኑ 6:00 ላይ የብልፅግናው አየር ወለድ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን አንድ የሻምበል አመራሩ ተገድሏል፣ ከ8 በላይ የእጅ ስልካቸውን ሳይቀር ጥለው ሲሸሹ፣ ከ10 በላይ ወታደራዊ ቦርሳዎችንና ከህዝብ በመሰብሰብ ላይ የነበረ በርካታ ገንዘብና የጤና መድን ደረሰኝ እና ሌሎች ዶክመንቶችን በድንገት ጥለው ወደመጡበት ሬማ ከተማ እግሬ አውጭኝ ብለው መሸሻቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በሸዋ ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ግድም ወረዳ የአላላ እና የይምለዋ ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑት በርካታ ንፁሀኖች በብልፅግናው ካዲሬዎች ትዕዛዝ ሰጭነት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር አባላት እና በቀጠናው የሚገኙ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአርበኞች ጦር ሰራዊት አባላት የሆኑ ቤተሰቦችን የፋኖ ቤተሰብ በመሆናቸው ብቻ መርጠው በግፍ ማሰራቸውን ክፍለጦሩ አስታውቋል።
ከግፍ እስረኞቹ ውስጥ በከፊል:-
1. አቶ ሹመት ማናስቦ (የፋኖ መለስ ሹመት ወላጅ አባት)
2. ወ/ሮ አጁባን አየለ (የፋኖ አሳልፍ አጁባን ወለጅ እናት)
3. አቶ ሞገስ በቀለ (የፋኖ ይግረም ሞገስ ወላጅ አባት)
4. ወ/ሮ አሳበች መንገሻ (የፋኖ መመኪያ መሸሻ ወላጅ እናት)
5. ወ/ሮ አስናቁ ከስም (የፋኖ ተስፋዬ ከፈለኝ ባለቤት)
6. ወ/ሮ ብርቄ አለማየሁ (የፋኖ ነጋሽ ማሞ ባለቤት)
7. ወ/ሮ ብዙ በቀለ (የፋኖ ሀብቴ ዘነበ ባለቤት)
8. ወ/ሮ ብዙነሽ አስፋው (የአባት አርበኛ ቻሌ አስፋው እሕት)
9. አቶ ፋንታ ጌታቸው (የአባት አርበኛ ሞገስ ፋንታ ወላጅ አባት)
10. አቶ ወንድም አያሌው (የአባት አርበኛ ግዛቸው ወንድም ወላጅ አባት)
11. ወ/ሮ ወርቅነሽ በቀለ (የአባት አርበኛ አረጋኸኝ ማስረሻ ባለቤት)
12. ወ/ሮ ስንቅነሽ ዳኜ (የአባት አርበኛ በየነ ፋሩ ባለቤት)
13. ወ/ሮ አረጋሽ ንጋቱ (የአርበኛ ጋይስ ወዳጆ ባለቤት)
14. የአርበኛ መለሰ ገረመው ቤተሰብን ጨምሮ በርካታ የፋኖ ታጋይ ቤተሰቦች በአገዛዙ በአጣዬ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ ታስረው ይገኛሉ።
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከግንባር መረጃዎችን አጠናቅሮ አድርሶናል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት❗️
አንድነታችን አሸናፊነታችን❗️
ድል ለአማራ❗️
ድል ለፋኖ ❗️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

❤3
ስል ዐምሓራ ሕዝብ የተከፈለ ውድ ዋጋ!
አርበኛ ሙልቀን መኳንንት በአማራ ፋኖ የኮማንዶና መሰረታዊ ዉትድርናን በማሰልጠን
ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ አሰልጣኝና በርካታ ዙሮችን ያለድካም ያሰለጠነ አዲስ ትዉልድ ቀራጭ ትጉ አርበኛ ነበር።
"እንዲሁም በአማራ ፋኖ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀደይ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ትምህርትቤት የተሰጠውን ከጎንደርና ከጎጃም ለተወጣጣ የጋራ ሀይል የተሰጠን ታሪካዊ የአማራ የአንድነት ምሳሌ የሆነውን የኮማንዶ ስልጠና በትምህርት ቤቱ አዛዥነትና በመሪ አሰልጣኝነት አስደናቂና አይረሴ በሆነ መንገድ አሰልጥኖ አስመርቋል።
"ከመሰረታዊ አባልነት እስከ ክፍለጦር አመራርነት ትልቅ ዋጋ በመክፈል በትግል ያደገ ጀግና በተዋጊነቱ በተሰበሩ ምሽጎች ጠላት የሚመሰክርለት መሬትን ባግባቡ መጠቀም የሚችል ብቁ ወታደራዊ መሪ ሆኖ የአማራን ህዝብ ወደነፃነት ለማድረስ በቃል የማይገለፅ ዋጋ ከፍሏል።
"ትናንት ጥር 17 /2018 ዓ/ም አንድ ታጋይ ለህዝቡና ለሀገሩ መክፈል የሚችለዉን ውድ የክብር መሰዋእትነት በመክፈል ለአማራና ለአማራነት ከፍታ የአባቶቹን ታሪክ በመድገም ለአዲሱ ትውልድ ክብርንና አርበኝነትን አውርሶን በክብር ተሰዉቷል።
"በዚህ አማራዉ በአንድነት ብሩህ ተስፋ ይዞ ትግሉ በአዲስ መንፈስ መቀጣጠል በጀመረበት ተላላኪዉ ፣ሰላቶዉና አስመሳዩ እየጠራ ሚናውን እየለየ ከየቤቱ ያለዉ አማራ ለመሰልጠንና ለመደራጀት እየተራወጠ ባለበት በዚህ ወቅት አርበኛ ሙሉቀን መኳንንት (ቅርጢ) እጅግ ከማንም በላይ በምታስፈልገን በዚህ ወቅት በክብር መሥዋዕትነት ቢለየንም በልጅ እድሜህ በወታደራዊ እዉቀት አባት ሆነህ ባፈራሀቸው ልጆችህ ተተኪውን ትውልድ በብቃት እናሰለጥነዋለን እናደራጀዋለን።
"እኛንም ለጠላት እጅ ከመስጠትና ምቾት ፈልጎ በአማራ ህዝብ ደምና እንባ ተረማምዶ ለጠላት ከማደር ጠብቆ ያንተንና የእነ ውባንተ አባተን የክብር መሰዋእትነት ለመቀበል ያብቃን።
ለትግል ወንድሞቹና ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እመኛለሁ። ክብር ለትግሉ ሰማእታት
@አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል
የአፋብን ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ!

ቃሉን ያልበላ ጀግና ጦረኛ!
ቃሉን ያልበላ ጀግናው ጦረኛ፡
ፋኖው ኮለኔል ፅኑው አርበኛ።
ከልጆቹ ጋር ፊት ተሰላፊ፡
ጥላት አንበርብድ ካርታ ነዳፊ።
የጓድህ አደራ እንቅልፍ እንደነሳህ፡
ይሄው ፍሬ አፈራ እንኳንስ ደስአለህ።
ጀግናው አባታችን ንፁሁ አማራ፡
አድርገሀናል በአንተ እንድንኮራ።
የጦሩ መሀንዲስ አርበኛ ኮሎኔል ሞገስ ዘገየ ድል ላንተና ለምትሳሳለት ሕዝብህ!
ገጣሚ፡- ፋኖ ድምፃዊ ኪሮስ ደርቤ- ከምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና!

ከጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር የተሰጠ አሰቸኳይ መግለጫ።
ግብሩ አማራን ማውደም የሆነው የአብይ አህመድ ስርዓት በደቡብ ጎንደር ሐሙሲት ከተማ አስተዳደር ታሪክ ይቅር የማይለው አስነዋሪ ተግባር እየፈፀመ ይገኛል::
ወንጨጥ ቀበሌ ላይ ልጅህ ፋኖ ነው በማለት አርሶ አደር መርሻ አረጋን የልጃቸውን ሰርግ አስርገው ወዳጅ ዘመዳቸውን እያስተናገዱ ባሉበት ከሰርጉ በማስወጣት አስከፊ በሆነ መንገድ ረሽናቸዋል።
ሐሙሲት ከተማ ላይ የፋኖ ቤተሰብ ናቹህ በማለት ማሰር እና ቤታቸውን በበላያቸው ላይ በማሸግ የለት ጉርስ እንዳያገኙ በማድረግ ሜዳ ላይ ጥላቸዋል።
አማራ ሁነው ማንነታቸውን ክደው የአማራ ህዝብ የገጠመውን ህልውና አደጋ ላይ ከፊት ሁነው እየመሩ ያሉ ተሻሚዎች ፖሊስ አድማ ብተና ሚኔሻ ከዚህ ድርጌታቸው የማይታቀቡ ከሆነ እነርሱ አየተገበሩት ያሉትን ማንኛውንም ነገር ከቤተሰቦቻቸው ላይ እኛም ሳንወድ በግድ ተገደን ርምጃ የምንወስድ መሆናችን እንገልፃለን።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
@አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ህ/ግ ሃላፊ ፍቅሩ ባየ

💔2
ሰበር ከግንባር - ህይወት የተከፈለበት መስዋእትነት | አየርወለድ ኮማንዶዎች ያለቁበት የሸዋ ግንባር | ፋኖ የሰበረው የመካነሰላም ምሽግ
❤2
ዜና ሰማዕታት/ አጭር የህይወት ታሪክ
አርበኛ ኮማንዶ ሙሉቀን መኮነን (ቅርጢ) ከአባቱ አቶ መኮነን እና ከእናቱ ወ/ሮ የሽናት በሬ በ1992 በማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ አፀደ ማርያም ከተማ ተወለደ።
እድሜው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ቦታው አፀደማርያም ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተማረ ሲሆን ከ8ኛ ክፍል እስከ10ኛ ክፍል ሻሁራ ከተማ ባሉ ት/ቤቶች ተምሯል።
በ2013 ዓ.ም ወደ ሐገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ማእከል የእግረኛ ስልጠናውን በጀግንነት በማጠናቀቁ ወደ ቀጣይ ብላቴ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ማእከል 38ኛ ዙር በቀዳሚነት በመመልመሉ ሙሉ ስልጠናውን በብቃት በተሻለ መልኩ ማጠናቀቅ ችሏል። ከዛም በልዩ ዘመቻ 102ኛ ክ/ጦ በመመደብ በብዙ አውደ ውጊያዎች ማለትም በጋሸና ፣ በወልድያ ፣ በጎብየ ፣ በቆቦ ፣ በሀራአራዶም ፣ በተኩለሽ ፣ በአላማጣ ፣ በግራ ካሱ ፣ በአሸንጌ ፣በማይጨው ፤ ከሸኔ ጋር በአምቦ ፣በወለጋ ፣ በወልደ ጉድሩ እና መሠል አውደ ውጊያዎች ላይ ጀብድ በመስራት የጀግንነት ጥግ ያሳየ ጀግና እንቁ ታጋይ ነበር።
ነገር ግን የአገዛዙን ሐገር አፍራሽነት የብልፅግናን ስርአት አስከፊነትና ፀረ አማራዊ ፣ፀረ ኢትዮጲያዊ አሰላለፍ ገና በልጅነት እድሜው ቀድሞ በመረዳቱና ሴራዎችን በመገንዘቡ ከሐገር መከላጰያ ሰራዊትነት በ2015 ወጦ ወደ ቀየው በመመለስ ለወራት ያህል የግል ስራውን በጋራጅ ባለሙያነት ሲሰራ ከቆየ በኃላ የአማራን ህመምና መከራ ቀድሞ የተረዳው የጦር ጠበብቱ አርበኛ ኮማንዶ ሙሉቀን መኮነን ከጀግኖቹ ጎን በመሰለፍ የትግሉን ችቦ ለኩሶ የወገኔን መከራና ስቃይ ከዚህ በላይ አልታገስም በማለት ውድ ህይወቱን ረክዞ ነሀሴ 1/2015 ወደ ፋኖ ትግል ተቀላቅሏል።
አርበኛ ኮማንዶ ሙሉቀን መኮነን (ቅርጢ) የግል ስብዕናው አስተማሪ ፣ ሳቂታና ተጫዋች ፣ ለለውጥና ለእውቀት የሚጓጓ ፣ ታማኝነቱ ወደር የሌለው ፣ ታታሪ ፣ ታጋሽ ፣ ለወገኑ ትሁት ለጠላት ግርማው አስፈሪ ፣ የስልጠና አሰጣጡ ልዩ ፣ ከጠላት ጋር ሲፋለም የተለየ አስፈሪ ፣ ለተማረከ የአገዛዙ ሰራዊት የሚራራ ሰባዊነት የሚሰማው ፣ ከመለያየት አንድነትን አጥብቆ የሚወድ ፣ ጀግንነቱ ወደር የሌለው ፣ የተለየ የመፍትሄ ሀሳብ አፍላቂ ፣ የባለ ብዙ እውቀት ባለቤት ለነገ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የጦር ጠበብት ነበር።
በአማራ የህልውና ትግል የሰራቸው አንኳር ተግባራት:
1.ባሰልጣኝነት: ለአድዋ ክ/ጦ 8ዙር ፣ ለቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ 2ዙር ፣ ለጥቁር አንበሳ ክ/ጦ 2ዙር እና አንድ ዙር የአማራ ፋኖ በጎንደርንና የአማራ ፋኖ በጎጃምን በአንድ የኮማንዶ ስልጠና ሲዘጋጅ መሪዎች የሰጡትን የማሰልጠን ኃላፊነት በብቃት እውቀቱን ሳይሰስት የሰጠ ኮኮብ አሰልጣኝ በመሆን በመሪዎች ምስጋና የተቸረውና ተደጋጋሚ ሽልማቶችን ያገኘ እንቁ የአማራ የቁርጥ ልጅ ተናፋቂ ግርማው አስፈሪ ኮማንዶ አርበኛ ሙሉቀን መኮነን በስልጠና አሰጣጡ የተለየ ከመሆኑ ባሻገር ጠንክሮ በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተስፋ ሰጭ ሀሳቦችንና ምክሮችን ለሰልጣኞች የሚሰጥ ባለ ራዕይ ታላቅ አርበኛ ነበር።
2.በመሪነት: በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ በሻለቃ መሪነት እና የንጋት ጮራ ብርጌድ ዋና አዛዥ በመሆን የበኩሉን ያደረገ፤ በሚመራው ጦር ተወዳጅ የሆነ ስምሪት አዋቂ ጠንቃቃና መካሪ መሪ የነበር ሲሆን የተሰጠውን የመሪነት ትእዛዝ በመፈፀም ረገድ ተወዳዳሪ የሌለው ፍፁም ቅን እዝ እና ሰንሰለትን አዋቂ ታላቅ አርበኛ የአማራ የቁርጥ ቀን ጀግና..
3.በተዋጊነት: መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ በተፋለመችበት 90% አውደ ውጊያ ላይ በመምራትና በተዋጊነት ረገድ የሚቀድመው የሌለ አብሪ ኮከብ ታማኝነትና ጀግንነት እስከ ቀራንዮ በሞቱ ሀገርን መውለድ ራዕዩ የሆነ ታላቃ አርበኛ ኮማንዶ ሙሉቀን መኮነን ውድ ህይወቱን ለወገኑ አሳልፎ የሰጠ በአማራ ነፃነት ፣ መብትና ክብር የማይደራደር ጀግና ሐገሩን እስከ ደም ጠብታው የሚወድ አንድነትን እየሰበከ ጦሩን በፍቅር እየመራ በሞቱ ፍቅሩን የገለፀ የአማራ የቁርጥ ልጅ ...
በአማራ የህልውና ትግል ለአብነት የተዋጋባቸው አውደ ውጊያዎች: ከደንቢያ ሳንኪሳ ፤ ከአለፋ አምቹሃ፣ አፀደማርያም ፣ ሻሁራ ከተማ ፣ዛብዛ ፣ሳንቃበር ፣ ፍንጀት ፣ወኩ፣ ጋዝጌ በነዚህ የውጊያ ቦታዎች ተደጋጋሚ በርካታ ጊዜ አውደ ውጊያ የተደረገባቸው ሲሆን በመሪነትና በተዋጊነት በጠላት ላይ ፈርጣማ ክንዱን አሳርፏል።በተለይ የህዳር 18/2016 ፣የህዳር 23/2016፣ ነሀሴ16/2017 ሻሁራ ከተማ ማንዴላ ሰፈር የተደረገው አውደውጊያ ጠላት ክፉኛ የተቀጠቀጠበት እና የተማረከበት ትልቅ ድል የተገኘበት አይረሴ የጀግኖች ማስታዎሻ አሻራ ነው። ከጎጃም ምድር ሰሜን አቸፈር ይስማላ ላይ አኩሪ ድል ሲመዘገብ የታላቁ አርበኛ አስተዋፅኦ እና ጀግንነት የላቀ ድርሻ ነበረው።ከቋራ ምድር በሙር እና ደለጎ የሰፈረውን የአገዛዙ አራዊት ላይ ተደጋጋሚ ኦፕሬሽን ሲሰራ በመሪነትና በተዋጊነት የሰራው ጀብድ የተለየ ነበር። በተለይ በተቋም እና በኮር አመራሮች ልዩ ኦፕሬሽን የተመራው በዋናነት በአድዋና ኦሜድላ ክ/ጦ ስምሪት ተቀብለው በፈፀሙት አውደ ውጊያ ከነሀሴ 08_11/2017 በተደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ነሀሴ 09/2017 የበሙርን የቁም ምሽግ በደቂቃዎች የሰአት ልዩነት ከአድዋ ክ/ጦ ነብሮ ብርጌድ 1ሻንበል ተወርዋሪ ይዞ በመግባት በቀላሉ ይሰበራል ተብሎ የማይገመትን ከባድ ምሽግ ከ5 ደቂቃ በታች በሆነ ውጊያ ቦምብ እየወረወረ በልዩ ወታደራዊ ጥበቡ ወደ ምሽግ በመግባት የአገዛዙን ጥምር ሰራዊት በአንድ አፍታ እንደ ንብ ፈርሶ ዙ23ቱን እና ጀኔራል መድፉን ላለመማረክ ተደፋድፎ አስክሬኑንና ቁስለኛውን ሳያነሳ ወደ ደለጎ ፈርጥጦ ገብቷል፣ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ፣ ተተኳሾችን ከመማረክ ባሻገር እጅ የሰጡ የአገዛዙን ምርኮኞች ተንከባክቦ ለመሪዎች አስረክቧል። በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን ታላቁ አርበኛ ከጠላት ምሽግ ላይ 3ጓዶች ሲሰውበት 4ቱ ደግሞ ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ሆኖበት አውደውጊያውን በአስደማሚ ሁኔታ በከፍተኛ ድል ማጠናቀቅ ተችሏል።
ታላቁ አርበኛ በውጊያ የሰራው ጀብድ ከብዙ በትንሹ ከረጅም ባጭሩ ይሄን ይመስላል ቀጣይ በሌላ መሰናዶ በዶክመንታሪ መልኩ የምናቀርብ ይሆናል።
አቤት አነጣጠር ፣ደግሞ አተኳኮሱ
ከጠላት ግንባር ውጭ አይመታም እርሳሱ።
በአለፋ ሰማይ ስር፣አዋጅ ተነገረ
በጎንደር ሰማይ ስር ፣ አዋጅ ተነገረ
በአማራ ሰማይ ስር፣ አዋጅ ተነገረ
አርበኛ ሙሉቀን ወንድ አንድ ሰው ቀረ።
ትግልህ ከእኛ ነው ፣ አልሞትህም የኛው ጓድ
ስምህ አብሮ አልገባም ስጋህ እንጅ ጉድጓድ።
ኮማንዶ ሙሉቀን ፣ ወንዱ አባ ደፋሩ
መቸ ይቆም ነበር ጠላት በግንባሩ።
የአያት ቅድመ አያቱን ታሪኩን አጥንቶ
ደማቅ ታሪክ ሰራ ፣ ቦንቡን አፈንድቶ።
ጥር 17/2018 የአገዛዙ ጥምር ሀይል ከሻሁራና አፀደማርያም ተነስቶ ወደ ወኩ ለመግባት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ይህ ታላቅ አርበኛ ብሬን ታጥቆ ከአድዋ ክ/ጦ ተወርዋሪ አሀድ ጋር ወደ ጠላት ቀጠና በመግባት በርካታ ቁጥር ያለው የአገዛዙን ግብስብስ ሀይል ክፋኛ ሲያበራየው ካረፈደ በኃላ በመጨረሻም በጨበጣ ውጊያ ከ5 ያላነሰ ቦምብ በመጣል አብረውት የነበሩ ጀግኖችን ቦታ እንዲያሻሽሉ እና የውጊያ ስልቱን እየቀየረ ባለበት ሰአት ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ተመቶ ታላቅ ጀብድ ፈፅሞ በተወለደ በ26 አመቱ ለወገኑ ሲል እንቁ የህይወት ዋጋ ከፍሎ በሰማእታትነት

❤1
አልፏል። ለሞቱ እማይሳሳው አባ ደፋር ቅርጢ ጓዶቹን ሲመክርና ሲያጠናክር፣ አንድነትንና ጠንክሮ መስራትን እያስተማረ ባለበት ወቅት የራሱን ተፈጥሮአዊ ከአምላኩ ጋር የሚያገናኘውን የምህረት ቃሉን ፈፅሞ በታላቅ ጀብድ ከጠላት ጋር ሲፋለም ካረፈደ በኃላ ከጧቱ 4:00 ገደማ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ በሰማዕታትነት አልፏል። ለወገኑ በከፈለው ውድ የህይወት ዋጋ ነብሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን!!!
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ጥር 19/2018
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ጥር 19/2018
🙏3
ሰበር የድል ዜና!!!
ሚኒሻው አከርካሪውን ተመታ!!!
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የአድዋ ክ/ጦ ተወርዋሪ በትናንትናው እለት ጥር 18/2018 የአገዛዙ አሸርጋጅ ሆድ አደር ሚኒሻ ከአፀደማርያም ተነስቶ ወደ ጋራስጌ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ደፈጣ በመያዝ ዘከር ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። ይሄን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የአማራ አስገዳይ ደላላ ሆድ አደር ሚኒሻ የድረሱልኝ ጩኸቱን እየቀባጠረ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል።
በዚህ የደፈጣ ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት=4
ከባድና ቁስለኛ =6

አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር የፋኖ ሰራዊት ጋር የሚኒሻና የመከላከያ አባላት እዬተቀላቀሉ ነው‼️
የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ከአሁን በፊት ከ60 በላይ የሚሊሻና የመከላከያ አባላትን ወደ ክፍለጦሩ ስቦ ያሥገባ እንደሆነ የገለፅን ሲሆን በዚህ ሁለት ቀን ብቻ (8) የሚኒሻና የመከላከያ አባለትን ስቦ አሥከድቷል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አንድነት ከተመሰረተ ማግሥት ወደ ክፍለ ጦራችን የተቀላቀሉ የሚኒሻና የመከላከያ አባላት እንዳሉት እሥከ አሁን ሥንጠብቀው የነበረው የአማራ ፋኖ አንድነት በመመሥረቱና የፋኖ አንድ ላይ መሆን የአማራን ትግል በአንድ ላይ ሆነን እንድንታገልና እንድናስመልሥ ምቹ እድል መሆኑን አውቀን ከነ ሙሉ ትጥቃችን ተቀላቅለናል ብለዋል።
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን)
ከሰም ፪ኛኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክፍለጦር ዜና ክፍል!

👍3