ሰበር ዜና!!
የአፋብን 206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:10 አስደናቂ የቦንብ ጥቃት ፈፀመ::
አፋብን ቴዎድሮስ እዝ 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:10 በአንድ FSR መኪና ተጭነው ከስላሴ ካምፕ ወደ የጁቤ ሊንቀሳቀሱ የነበሩ የአረመኔዊት ሰራዊት ላይ በተደረገባቸው የቦንብ ጥቃት 1 የጦር አዛዥን ጨምሮ 14 የጠላት ኃይል ሲገደሉ 9 ከባድ እና 6 ቀላል ቁስለኞች ሆነው በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛሉ።
የቀጠናው ልዩ ክስተት የሆነው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደጋጋሚ በሌሊት፣ በቀን እና በምሽት በጠላት ላይ ያነጣጠረ የተሳካ የቦንብ ጥቃት በመፈፀም ድል እያስመዘገበ ቀጥሏል::
በተመሳሳይ ሰዓት የአብማ ክፍለ ከተማ ሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊ በሆነው አለኸኝ አስማረ መኗሪያ ቤት በተደረገ የቦንብ ጥቃት አለኸኝ አስማረ ከባድ ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
@የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

🙏4
በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ "የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ" በሚል አንድ ቤተሰብ ሙሉ በኦህዴድ ብልፅግና ጦር ተረሸኑ‼️
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ቀጠና ደቡብ ሜጫ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ የፋኖ ዘውዱ ሙላት ቤተሰቦችን የአገዛዙ ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏቸዋል።
አቶ ሙላት አድማስ ይኖሩበት በነበረው ደቡብ ሜጫ ከስራ ውጭ ምንም የማያቁ በማህበረሰቡ ዘንድ አንቱ የተባሉ የተከበሩ ሰው ነበሩ። ነገርግን ጠላት ደቡብ ሜጫ ወረዳ መሀለገነት ከተማ እንደገባ ጀምሮ ልጃችሁ ፋኖ ነው በሚል ስበብ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፎ አፈናቅሎ ቤታቸውን የሚኒሻ መኖሪያ አድርጎት ቆይቷል። አቶ ሙላት አድማስ ይኖሩበት ከነበረው መሀለገነት ከተማ ተፈናቅለው ተወልደው ወደ አደጉበት ቀበሌ አዲስ ዓለም ቀበሌ ተሰደው ይኖሩ ነበር።
ይህ አረመኔ ሰራዊት ግን በትላንትናው እለት ለደም ግብሩ ተሰደው ተጎሳቅለው ኑሯቸውን እየገፉ ባሉበት ቦታ ድረስ ሄዶ በቀን 16/05/2018 ዓም ከ16 ዓመት ልጃቸው እና የእህታቸው ልጅ ጨምሮ በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ገሏቸዋል።
ለዚህ ጥቃት ሰለባ የሆኑት የፋኖ ዘውዱ ወላጅ አባት አቶ ሙላት አድማስ እና ታናሽ ወንድሙ ይኸነው ሙላት:እንዲሁም የአቶ ሙላት የእህት ልጅ ውዱ መልኬ የተባሉ የ54እና 16 እንዲሁም 22 ዓመት እድሜ ክልል ያላቸው ናቸው::
"ይህ ስርዓት ጨፍጫፊ እና ፀረ አምሓራ ነው" የምንለው ለዚህ ነው : ይህ ስርዓት ደምግብሩ ነው የምንለው : ህፃን አዋቂ ሳይል ንፁሀንን በጅምላ በአምሓርነታችን ብቻ የሚገድል ክፉ አገዛዝ ነው፣ በምሬት ልንታገለውይገባል!
©የኮሩ ሕዝብ ግንኙነት

💔3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መመስረቱን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ትብብር ንቅናቄ የፋኖ ኃይሎች ጥር 09፣ 2018 ዓ.ም. የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በሚል ስያሜ ውህደት መፍጠራቸውን በማበሰራቸው የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ይገልጻል።
የአማራ ሕዝብ በጠባብ ብሄረተኞች አገዛዝና አምባገነናዊ የፖለቲካ ስርአቶች ላለፉት 30 ዓመታት ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የደረሰበት መሆኑን ይታወቃል።
ዛሬ ድረስ የአማራ ህዝብ በማንነቱ ሲገደል፣ ሲፈናቀል፣ ሲሳደድ እያየን ነው። ይባስ ብሎ አሁን ያለው የአብይ አህመድ አገዛዝ በግልጽ "ነፍጠኛን ወገቡን ሰብረነዋል ገናም እንሰብረዋልን" በማለት ከመሳለቅና ከመዛት አልፎ ጦርነት አውጆበት፣ የአማራን ምድር የሰቆቃና የመከራ ምድር አድርጎታል።
አማራ ከኦሮሞ አካባቢዎች በገፍ ተገድሏል፣ ንብረቱ በግፍ ተነጥቋል፣ በብዙ ሺዎች ተፈናቅለዋል። ግማሹ በመጠለያ፣ ግማሹ መጠለያ አልባ እንዲሆን ተደርጓል።
የአማራ ሕዝብ በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ በአብይ አገዛዝ ሲከለከል እንደነበር የማይዘነጋ ነው፣ በኦሮሞ ታጣቂ ኃይሎችም በተደጋጋሚ ጠለፋና ግድያ ተፈጽሞበታል።
ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ አማራን ትጥቁንና ቀብቶውንም እናስፈታለን በማለት ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል ወታደር አዝምተውበታል።
ስለሆነም አማራ ህልናውንና ማንነቱን ለማስጠበቅ በፋኖነት እየታገለ ይገኛል።
ከዚሁም በመነሳት ንቅናቄያችን የአማራ ሕዝብ ትግል ፍትሃዊ በመሆኑ ሊደገፍ ይገባል ይላል፣ እየደገፈም ይገኛል። የፋኖ ትግል 3 ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ሕዝባዊነቱን አረጋግጧል።
በአስደናቂ ፍጥነት ትልቅ ኃይል መስርቶ መንግስትን እያንገዳገደ ይገኛል። ጥሩ ድስፕሊን ያለው፣ የተማረኩ ጠላቶችን ሰብኣዊ በሆነ መንገድ የሚይዝና ሕዝቦችን ለማቀራረብ የሚሰራ መሆኑን ለዓለም አስመስክሯል። ልዩ ልዩ የአለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙሃን ይህን ሀቅ ዘግበዋል።
ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብም አሁን ካለው ዘረኛና ጨካኝ አምባገነን የአብይ አህመድ አገዛዝ ስርዓት፣ ፋኖ ሊታደገን ይችላል በሚል በተስፋ እየተጠባበቀ መሆኑን እንገነዘባለን። ፋኖ በዚሁ አጭር ጊዜ አስደናቂ በሆነ ፍጥነት ከትንንሽ ስኳዶችና ኃይሎች ወደ እዞች ድረስ ለመደራጀት ችሏል።
ሆኖም አደረጃጀቱ በየቀጠናውና በተለያዩ ኃይሎች ሆኖ ያልተማከለና ያልተቀናጀ በመሆኑ ሊገኝ የነበረውን ጥቅምና እድገት ከመገደቡ በላይ፣ በነዚህ ኃይሎች መከከል ፉክክርና ግጭት እንዳይፈጠር ስጋት ሆኖ ቆይቶ ነበር። በዚህም ሂደት ጠላት ቀዳዳ ለመፍጠር ያልሞከረው ሴራ፣ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም።
በገንዝብ ለመደለል፣ በድርድር ስም በተናጠል ሽምግልና በመላክና እርስ በርስ እንዲጠራጠሩ ለማድረግ፣ ትንሽ የልዩነት ፍንጭ ሲያገኝ በስፋት በሚድያ ውዥንብር እንዲፈጠር ለማድረግ ሞክርዋል።
ሆኖም ጠላት እንደተመኘውና ብዙ ሕዝብ በስጋት ውስጥ የመውደቁን ያህል የተፈራው ሳይሆን፣ ደልዳላ መሰረት እንዳለው ያስመሰከረበት አጋጣሚ ሆኗል።
በፋኖዎች ልዩነት ስለተፈጠረ እየተዳከሙ ነው በሚባለበት ወቅት፣ በሁሉም ቀጠናዎችና እዞች አስደማሚ የሆኑ ድሎችን እየተቀናጁ እንደመጡ አይተናል፣ እያየንም ነው።
ዛሬ ላይ በፋኖ የተመሰረተው ውህድ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በንቅናቄያችንና በመላው ትግሉን በሚደግፍ ሕዝብ ላይ የነበረውን ስጋት ያስወገደ እና በጎ ምኞታችንን እውን ያደረገ፣ ተስፋችንን ያለመለመ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማናል።
ይህ ውህደት ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ (ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ) እድገቱን ወደ አንድ እምርታ ያደረገ መሆኑን እናምናለን።
ለሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ተስፋ እንደሆነና በውስጥም በውጭም የሚገኙ ደጋፊ ኃይሎችም ትግላቸውን እንዲያስተባበሩና እንዲጠናከሩ መንገድ ከፍቷል ብለን እናምናለን።
በመጨረሻም የትግሉ መቋጫ፣ ያለውን ስርዓት አስወግዶ ፍትሓዊና አሳታፊ የሆነ የፓለቲካ ስርዓት መመስረት መሆኑን በመገንዘብ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በአጭር ጊዜ የትግሉን ፍኖተ ካርታ በመዘርጋት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በማሳተፍ ሃላፊነቱን ይወጣል ብለን እናምናለን።
ድል ለአማራ ሕዝብ ፍትሃዊ ትግል!
ድል ለተጨቆኑ የኢትዮጵያ ማህበረስቦች ሁሉ!
የኢትዮጵያውያን ትብብር ንቅናቄ!
(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥር 17/2018)

❤2🙏2
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር አሃድ የሆነው አንዳቤት ብርጌድ 2 ቀናት የፈጀ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክክር አድርጎል።
መርሃ ግብሩን የመሩት የጉና ክፍለ ጦር ሰብሳቢ አርበኛ ወንዱአንተ አሰፋ ፣ ም/ ወታደራዊ አዛዥ እንጂነር አበራ ንብረቱ እና ሁሉም የስራ ሃላፊዎች በሰሳተፉበት ለብርጌዱ የፋኖ አባላት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ግንዛቤ በስፋት ተሰጥቷል።
እንዲሁም በቀጣይ በወታደራዊ ስራዎች፣ በሃብት አሰባስብ፣ በህዝብ ፍትህ አሰጣጥ፣ በወታደር ፕወዛ፣ ከህዝብ ጋር በሚደረጉ መድረኮች በመሳሰሉት ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ተካሄዷል።
ህልውናችን በተባበር ክንዳችን ሲል መረጃውን ለአለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ ያደረሰን የጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ መ/ር ያሬድ ገደፍው ነው::

🙏4👍2
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከታፈሱ 1330 ወጣቶች መካከል 850 የሚደርሱት ከደብረ ማርቆስ ማሰልጠኛ ካምፕ መጥፋታቸው ተረጋግጧል"
እነዚህ አራት ወጣቶች ደረጀ ጎሹ፣ ደሳለኝ ወርቁ፣ እንዳለ ይበልጣልና ዝጋለ ሰጤ ይባላሉ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ከመርጡለ ማርያም ከተማ መሐል አደባባይ ታፍሰው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ ከተጓዙ 110 ወጣቶች መካከል ይገኙ ነበር።
ደሳለኝ ወርቁ በመርጡለ ማርያም ከተማ ዙሪያ የሸዋት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ከአመታት በፊት በደረሰበት የአንጀት መታጠፍ በቀዶ ጥገና ህክምና ህይወቱ የተረፈች መሆኑን የሚመሰክር ለምጽ በሆዱ መሀል ተመልክተናል። ቀሪ ሶስት ወጣቶች ከተሰማሩበት የጉልበት ስራ በሚኒሻዎች ታፍሰው ከደሳለኝ ወርቁ ጋር በአንድ መኪና ተጭነው ደብረ ማርቆስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እራሳቸውን ማግኘታቸውንም ከታፋሾች አንደበት ሰምተናል።
ሚኒሻዎች እየደበደቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱን በኋላ ስልካችንን ቀምተው ምሽት በአንድ መኪና አጭቀው የወሰዱን 60 የመርጡለ ማርያም ከተማ ወጣቶችና 50 የዙሪያ ቀበሌ ወጣቶች በድምራችን 110 ሁነን ደብረ ማርቆስ ከተማ ስንደርስ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ወረዳዎች ታፍሰው ከመጡት ጋር 1330 እንሆን ነበር ያሉት ወጣቶቹ በወታደራዊ ካምፕ ለ10 ቀናት መቆየታቸውን ያስታውሳሉ ።
በደብረ ማርቆስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ በገባን በሁለተኛው ቀን ለሁለት ከፍለው ወደ አዳራሽ ወስደው የሀይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ሽማግሌዎች የሚደበደቡበትን video እንድንመለከት ካደረጉን በኋላ ከዚህ ወጣችሁ ብትጠፉ ጥንፈኛው እንደዚህ ያሰቃያችኋል እያሉ ሲያሸማቅቁን እኛ እየሳቅን እንመለከታቸው ነበር እያሉ በፈገግታ የገጠማቸውን ነገር ሁሉ እያወጉን አረፈድን።
ለቀን ስራ ይሆናል ብለን በለበስነው ልብስ ስፖርት ሲያሰሩን የነበሩትም ከታፈሱት ውስጥ ግዙፍ ሰውነት ያላቸው ተመርጠው ሲሆን ከ45 ቀን በኋላ ፓራ ኮማንዶ ሁነን እንደምንመረቅ ተነግሮን ስልጠና ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ ቀን በቀን ወጣቶች እየጠፉ ወደ ሀገራቸው ሲሔዱ እኛም ጠፍተን ወደ እናተ መጠናል አዚህ ከመጣን በኋላ አስፈላጊው እንክብካቤ ተደርጎልናል በማለት ለ206ኛ ኮር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
"ፓራ ኮማንዶ "ወይንስ "ፋራ ኮማንዶ" የሚለው ሳይገባን በቀን ስራ ልብሳችን እና በባዶ እግራችን አሰልጥነው ወደ ጦርነት ሊማግዱን መሆኑን በመረዳት በማሰልጠኛ ከነበረው 1330 ታፋኝ መካከል 850 የምንሆነው እየጠፋን ወደ ፋኖ ተቀላቅለናል ያሉት እነዚህ ወጣቶች የአረመኔው ስርዓት ሰሞኑን በከተማዎች እያደረገ ያለውን የወጣቶችን አፈሳ እና ስቃይ ትክዝ እያሉ አጫውተውናል ።
በስርዓቱ ታፍሰው ከማሰልጠኛ የወጡትን ወጣቶች በመንከባከብ ላይ የሚገኘው 206ኛ ኮር በመርጡለ ማርያም ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ወጣት ልጆቻችሁን የተነጠቃችሁ እና የጠፉባችሁ የእነዚህ ወጣት ቤተሰቦች
ዛሬ ልጆቻችሁ ከወንድሞቻቸው ጎን በአስተማማኝ ሁኔታ ይገኛሉና ልጆቻችሁን ትረከቡ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!

🙏1
በምዕራብ ወሎ ግንባር ጠላት ይተማመንበት የነበረው ከባድ ምሽግ ተሰበረ!!
ትናንት ለዛሬ ሌሊት ማለትም ጥር 17 ለ 18 መካነሰላም ከተማ ውስጥ በተሰራ ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። ከአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሁለት ክፍለ ጦሮች ማለትም ከኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና ከመብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች መካነሰላም ከተማ ውስጥ የመሸገው ጠላት ይተማመንበት የነበረውን ከባድ ምሽግ ሌሊቱን ሰብረውታል። የጨላማ ውጊያ በመሆኑ የተነሳ በጠላት በኩል የደረሰውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ለማረጋገጥ ባንችልም የጠላት አከርካሪ እንደተሰበረ ለመረዳት ችለናል።
የምዕራብ ወሎዋ መካነሰላም ከተማን አስከብራለሁ በሚል እሳቤ ጠላት በርካታ ኃይል ከተማይቱ ውስጥ ቢያሰፍርም ፋኖ እንቅልፍ ነስቶታል፤ በመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሶዬ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ኔትወርኩ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ መሽጎ የነበረው ጠላት ነው በእነ ሞት አይፈሬ ሌሊቱን ተኩስ ተከፍቶበት ወታደራዊ ቁሳቁሱን ጭምር ጥሎ የፈረጠጠው።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር አካል የሆነው 43ተኛ ክፍለ ጦር በኮሎኔል ዮሀንሥ እየተመራ በርካታ ኃይሉን ወደ መካነሰላም ከተማ አስገብቶ ስለነበር ይህን የጠላት ግሳንግስ ሰራዊት የሚካኤል አሊ ልጆች በጥይት ሲያበጥሩት አድረዋል። በሌሊቱ ኦፕሬሽን ሰራዊታችን መካነሰላም ከተማ ውስጥ የገባ ሲሆን ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ግብአቶችን ከጠላት ጊዜያዊ ካምፕ ማውጣት ችሏል::
በ4 አቅጣጫ በተደረገው የሌሊቱ ኦፕሬሽን ጠላት ይዞታውን ላለመልቀቅ የመጨረሻ አቅሙን የተጠቀመ ቢሆንም ሰራዊታችን በአየር ማረፊያ እና በሶዬ በኩል ያለውን ምሽግ በመስበሩ የተነሳ አብዛኛው የጠላት ኃይል ወደ ደሴ መስመር መጓዙ ታውቋል። በኮሎኔል ዮሀንስ የሚመራው ኃይል አቅም ስላነሰው በሚል በዛሬው ዕለት በርከት ያለ ተሽከርካሪ ወደ መካነሰላም እየተጓዘ መሆኑንም ለማረጋገጥ ችለናል ሲል የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቃለአብ ወርቅዬ ለዕዙ በላከው የአውደ ውጊያ ሪፓርት ገልጿል።
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም

በወሎ ቤተአምሓራ የምኒሊክ ልጆች ተገርፎ ሸዋ መርሀቤቴ የገባው የ105ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ በጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በተሰራው ድንቅ ኦፕሬሽን ውጤታማ ድል መመዝገቡን ኮሩ አስታወቀ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከተሰማራባቸው የሸዋ ቀጠናዎች ውስጥ በመርሀቤቴ አውራጃ በ105ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ በትላንትናው ዕለት ጥር 17 ቀን 2018ዓ.ም ድል ተቀዳጅቷል።
በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ ጠላት መነሻውን ከሬማ ከተማ በማድረግ በግብር ስም ህዝባችንን ለመዝረፍ በከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የመጅት ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም ያልተመጣጠነ የግብር ተመን በመጣል በአስገዳጅ ገንዘብ እየሰበሰበ ባለበት ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር አካል የሆኑት በአስማረ ዳኜ 1ኛ ሻለቃ በተፈፀመው ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት ትላንት እሁድ ከቀኑ 6:00 ላይ የብልፅግናው አየር ወለድ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን አንድ የሻምበል አመራሩ ተገድሏል፣ ከ8 በላይ የእጅ ስልካቸውን ሳይቀር ጥለው ሲሸሹ፣ ከ10 በላይ ወታደራዊ ቦርሳዎችንና ከህዝብ በመሰብሰብ ላይ የነበረ በርካታ ገንዘብና የጤና መድን ደረሰኝ እና ሌሎች ዶክመንቶችን በድንገት ጥለው ወደመጡበት ሬማ ከተማ እግሬ አውጭኝ ብለው መሸሻቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በሸዋ ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ ኤፍራታና ግድም ወረዳ የአላላ እና የይምለዋ ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑት በርካታ ንፁሀኖች በብልፅግናው ካዲሬዎች ትዕዛዝ ሰጭነት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፂዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር አባላት እና በቀጠናው የሚገኙ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአርበኞች ጦር ሰራዊት አባላት የሆኑ ቤተሰቦችን የፋኖ ቤተሰብ በመሆናቸው ብቻ መርጠው በግፍ ማሰራቸውን ክፍለጦሩ አስታውቋል።
ከግፍ እስረኞቹ ውስጥ በከፊል:-
1. አቶ ሹመት ማናስቦ (የፋኖ መለስ ሹመት ወላጅ አባት)
2. ወ/ሮ አጁባን አየለ (የፋኖ አሳልፍ አጁባን ወለጅ እናት)
3. አቶ ሞገስ በቀለ (የፋኖ ይግረም ሞገስ ወላጅ አባት)
4. ወ/ሮ አሳበች መንገሻ (የፋኖ መመኪያ መሸሻ ወላጅ እናት)
5. ወ/ሮ አስናቁ ከስም (የፋኖ ተስፋዬ ከፈለኝ ባለቤት)
6. ወ/ሮ ብርቄ አለማየሁ (የፋኖ ነጋሽ ማሞ ባለቤት)
7. ወ/ሮ ብዙ በቀለ (የፋኖ ሀብቴ ዘነበ ባለቤት)
8. ወ/ሮ ብዙነሽ አስፋው (የአባት አርበኛ ቻሌ አስፋው እሕት)
9. አቶ ፋንታ ጌታቸው (የአባት አርበኛ ሞገስ ፋንታ ወላጅ አባት)
10. አቶ ወንድም አያሌው (የአባት አርበኛ ግዛቸው ወንድም ወላጅ አባት)
11. ወ/ሮ ወርቅነሽ በቀለ (የአባት አርበኛ አረጋኸኝ ማስረሻ ባለቤት)
12. ወ/ሮ ስንቅነሽ ዳኜ (የአባት አርበኛ በየነ ፋሩ ባለቤት)
13. ወ/ሮ አረጋሽ ንጋቱ (የአርበኛ ጋይስ ወዳጆ ባለቤት)
14. የአርበኛ መለሰ ገረመው ቤተሰብን ጨምሮ በርካታ የፋኖ ታጋይ ቤተሰቦች በአገዛዙ በአጣዬ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ ታስረው ይገኛሉ።
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከግንባር መረጃዎችን አጠናቅሮ አድርሶናል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት❗️
አንድነታችን አሸናፊነታችን❗️
ድል ለአማራ❗️
ድል ለፋኖ ❗️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

❤3
ስል ዐምሓራ ሕዝብ የተከፈለ ውድ ዋጋ!
አርበኛ ሙልቀን መኳንንት በአማራ ፋኖ የኮማንዶና መሰረታዊ ዉትድርናን በማሰልጠን
ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ አሰልጣኝና በርካታ ዙሮችን ያለድካም ያሰለጠነ አዲስ ትዉልድ ቀራጭ ትጉ አርበኛ ነበር።
"እንዲሁም በአማራ ፋኖ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀደይ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ትምህርትቤት የተሰጠውን ከጎንደርና ከጎጃም ለተወጣጣ የጋራ ሀይል የተሰጠን ታሪካዊ የአማራ የአንድነት ምሳሌ የሆነውን የኮማንዶ ስልጠና በትምህርት ቤቱ አዛዥነትና በመሪ አሰልጣኝነት አስደናቂና አይረሴ በሆነ መንገድ አሰልጥኖ አስመርቋል።
"ከመሰረታዊ አባልነት እስከ ክፍለጦር አመራርነት ትልቅ ዋጋ በመክፈል በትግል ያደገ ጀግና በተዋጊነቱ በተሰበሩ ምሽጎች ጠላት የሚመሰክርለት መሬትን ባግባቡ መጠቀም የሚችል ብቁ ወታደራዊ መሪ ሆኖ የአማራን ህዝብ ወደነፃነት ለማድረስ በቃል የማይገለፅ ዋጋ ከፍሏል።
"ትናንት ጥር 17 /2018 ዓ/ም አንድ ታጋይ ለህዝቡና ለሀገሩ መክፈል የሚችለዉን ውድ የክብር መሰዋእትነት በመክፈል ለአማራና ለአማራነት ከፍታ የአባቶቹን ታሪክ በመድገም ለአዲሱ ትውልድ ክብርንና አርበኝነትን አውርሶን በክብር ተሰዉቷል።
"በዚህ አማራዉ በአንድነት ብሩህ ተስፋ ይዞ ትግሉ በአዲስ መንፈስ መቀጣጠል በጀመረበት ተላላኪዉ ፣ሰላቶዉና አስመሳዩ እየጠራ ሚናውን እየለየ ከየቤቱ ያለዉ አማራ ለመሰልጠንና ለመደራጀት እየተራወጠ ባለበት በዚህ ወቅት አርበኛ ሙሉቀን መኳንንት (ቅርጢ) እጅግ ከማንም በላይ በምታስፈልገን በዚህ ወቅት በክብር መሥዋዕትነት ቢለየንም በልጅ እድሜህ በወታደራዊ እዉቀት አባት ሆነህ ባፈራሀቸው ልጆችህ ተተኪውን ትውልድ በብቃት እናሰለጥነዋለን እናደራጀዋለን።
"እኛንም ለጠላት እጅ ከመስጠትና ምቾት ፈልጎ በአማራ ህዝብ ደምና እንባ ተረማምዶ ለጠላት ከማደር ጠብቆ ያንተንና የእነ ውባንተ አባተን የክብር መሰዋእትነት ለመቀበል ያብቃን።
ለትግል ወንድሞቹና ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እመኛለሁ። ክብር ለትግሉ ሰማእታት
@አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል
የአፋብን ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ!