ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
የአማራ ተወላጅ የሆኑ 17 የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ተማሪዎችን የበላው ጅብ መጮህ የጀመረ ይመስላል!

ታግተው ደብዛቸው ጠፍቶ በቀረው 17 የአማራ ተወላጅ የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ተማሪዎች እገታ ዙሪያ መረጃ እንዳለውና በተማሪዎቹ ጠፍቶ መቅረትም ሲሳለቅና ሲዘባበት የነበረው የቀድሞው የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ፕረዝዳንት፡ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ጁሌ ባረፈበት ሆቴል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በማንነታቸው ምክኒያ ከሚማሩበት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ህዳር 25/2012 ዓ/ም የታገቱት 17 ተማሪዎች ደብዛቸው ጠፍቶ ከቀረ ስድስት ዓመታትን አስቆጥረዋል።

ከቤተሰብና ከዘመድ አዝማድ፡ ከወገን ጋር ተላቅሶ መቅበር <ዳስ ጥሎ ኩሎ የመዳር> ያህል የሚቆጥሩት የታጋች ቤተሰቦች እርማቸውን ማውጣት ከብዷቸው ዛሬም በሀዘን ተውጠው ተቀምጠዋል።

በወቅቱ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፡ ታግተው ደብዛቸው ስለጠፋው ተማሪዎች ለሚዲያ መረጃ ሰተዋል ተብለው የተጠረጠሩ በዛው በዩኒቨርስቲው ውስጥ ይማሩ የነበሩ ሌሎች የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በዩኒቨርቲው ፀጥታ አካላት ተይዘው ከባድ ድብደባ ከተፈፀመባቸው በኋላ ህይወታቸው አልፏል።አንዳንዶቹም በዩኒቨርቲው ፀጥታ አካላት ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው ጠፍቶ ቀርቷል።

ገሚሶቹ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችም፡ ያለማንም ከልካይ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል።አንዳንዶቹም  በተዓምር ሕይወታቸው ተርፎ ትምህርታቸውን አቋርጠው ተመልሰዋል።

የአማራ ተወላጅ ተማሪዎቹ በማንነታቸው ምክኒያት ይህ ሁሉ የመከራ መዓት ሲወርድባቸው በወቅቱ የዩኒቨርስቲው ፕረዝዳንት የነበረው ዶ/ር ለታ ተስፋዩ፡ ከኦነግ ኃይሎች ጋር ተባብሮ የድርጊቱ ዋና አቀናባሪና አስፈፃሚ እንደነበረ ሲነገርበት የቆየ ሲሆን፡ ከተማሪዎቹ እገታ በኋላ መረጃ የማጥፋትና የመደበቅ ስራ ላይ ተጠምዶ እንደነበር መረብ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት ለማረጋገጥ ችሏል።

ሌላው ቢቀር የልጆቻቸውን አስከሬን ከዘመድ አዝማድ ጋር ተላቅሶ ቀብሮ እርም ማውጣት ያልቻሉት የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች እንባ ከፈጣሪ ዘንድ ደርሶ ጎርፍ ሆኖ የተመለሰ ይመስላል። 

እነዛን ለጋ የቤተሰብና የሀገር ተስፋዎችን ቅርጥፍ አድርጎ የበላውም ጅብ መጮህ ጀምሯል።

ታግተው ደብዛቸው የጠፋው የ17 ተማሪዎችን ጨምሮ ስለታገቱት ተማሪዎች መረጃ አውጥታችኋል በሚል በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉ ተማሪዎች ደም እጁ የጨቀየው ዶ/ር ለታ ተስፋዩ በድንገት ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የቀድሞው የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት፡ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እንዲሁም የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ጁሌ፡ ከቀናት በፊት ለስራ ጉዳይ ከሌሎች የልኡካን ቡድኑ አባላት ጋር ሆኖ ወደ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አቅንቶ ነበር።

ለታ ተስፋየ ባረፈበት በቨርጂኒያ ልዩ ቦታው ሂልተን ሆቴል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን መረብ ሚዲያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ካወጧቸው የሀዘን መግለጫዎች ተመልክቷል።

የዐብይ አህመድ የሴራ ገመድ ፈታይ ከሆኑ አመራሮች መካከል አንዱና ዋናው ለታ ተስፋዬ ጁሌ፡ ከኦነግ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ቅርጥፍ አድርጎ የዋጣቸውን የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ሳይተፋ ድፍት ብሏል።

የአማራ ተወላጆችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ሐገሪቱ እንድትፈርስ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሴራ ከመጎንጎን ውጭ ከማያውቀውና  የትውልድ አምካኝ ጭራቅ ከሆነው ከብልፅግና ቡድን ወገን የሆኑ ባለስልጣናት፡ እየተምዘገዘገ እየመጣባቸው ከሚገኘው ከፋኖ ፍርድ ቀን ከመድረሳቸው በፊት፡ ፅዋው ካፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ እስኪፈስ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው።

@መረብ ሚዲያ
6
አገዛዙ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪዎችን በአስገዳጅ ሁኔታ ከሰበሰበ በኋላ በፈፀመባቸው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ከ100 በላይ የሚሆኑት ተገደሉ!

ከፋኖ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ያልቻለው አገዛዙ፡ "ሕዝባዊ ኮንፈረንስ" በሚል ስም ንፁኋንን ከየመኖሪያ ቤታቸው በግዳጅ ከሰበሰበ በኋላ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የበቀል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን፡ ይህ ድርጊት በቀጣይ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎችም እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ጥር 07/2018 ዓ/ም ረፋድ በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ሳህላ ሰየምት ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ልዩ ስሙ ሰየም ድልድይ በተባለ ቦታ ላይ ነው።

ከጎንደር በለሳ ጀምሮ እስከ ዋግኽምራ ሰሀላ ሰየምት ወረዳ ድረስ ያካለለ የድሮን አሰሳ ከቀናት በፊት ጀምሮ እየተደረገ መሰንበቱን ነው የአከባቢው ነዋሪዎች የገለፁት።

የድሮን አሰሳ በተደረገበት አከባቢ ህፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ እንደማይደረግ እየታወቀ፡ ነገር ግን "ከበላይ አካላት የመጣ ትዕዛዝ ነው" በሚል ለአደጋ ተጋላጭ በሆነ ቦታ ሕዝቡን ለጥቃት አመቻችተው ነው የሰበሰቡት ብለዋል ምንጮች አክለው።

ሕዝቡን በግዳጅ ለስብሰባ ሲጠሩ የነበሩ ካድሬዎችና የሚኒሻ አባላቱ አከባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ የድሮን አሰሳ እየተደረገ መሰንበቱን በሚገባ ያውቃሉ የሚሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው አንድ የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪ፡ "የድሮን ጥቃት ሊፈፀምብን ይችላል" በሚል ስብሰባው ከመካሄዱ በፊት  ስጋታቸውን የገለፁ ሰዎች "የፅንፈኛ ደጋፊ ናችሁ" በሚል አስቀድሞ ታስረዋል ብለዋል።

"ሕዝባዊ ኮንፈረንስ" በሚል በዞኑ ስር ኩታ ገጠም ከሆኑ ከደሀና ወረዳ፣ ከስሀላ ሰየምትና ከአበርገሌ ወረዳ ቀበሌዎች በግዳጅ የሰበሰቧቸውን ንፁኋኖች የድሮን አሰሳ እንደተደረገበትና የስጋት ቀጠና መሆኑ በታወቀ ቀጠና ላይ በማስቀመጥ ስብሰባው ከተጀመረ ግማሽ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል ነው ያሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው በወረዳው ስር ካሉ ጤና ጣቢያዎች ባንዱ የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያ ሌላኛው የመረጃ ምንጫችን።

በዚህም ከ100 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፡ ከሟቾቹ መካከል አረጋውያን፣ ህፃናትን ያዘሉ እናቶችና ነፍሰጡር ሴቶች እንደሚገኙበት ታውቋል።

በድሮን ጥቃቱ ከተገደሉ ንፁኋኖች በተጨማሪ ሰብስባውን በአስገዳጅነት የጠሩትና ሲመሩ ከነበሩት የሚኒሻና የፖሊስ እንዲሁም የወረዳ ካቢኔ አባላት መካከል በርካቶች ተገድለዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ በአከባቢው ከፍተኛ የሆነ የሕክምና እጥረት የተከሰተ ሲሆን፡ የተጎጂዎቹን ሕይወት ለማትረፍ በጭነት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ጎንደር በለሳና እብናት እንዲሁም ሰቆጣ ከተማ እስከ ትናንት አመሻሽ ድረስ ሲወሰዱ እንደነበር ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከፋኖ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ያልቻለው ኦህዴድ መሩ የብልፅግና ቡድን፡ "ሕዝባዊ ኮንፈረንስ" በሚል ስም ንፁኋንን ከየመኖሪያ ቤታቸው በግዳጅ ከሰበሰበ በኋላ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የበቀል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን፡ ይህ ድርጊት በቀጣይ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎችም እንደሚቀጥል የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

መረብ ሚዲያ
💔1
በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ “ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ” ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግሯል።

በእነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ ተከሳሾች መካከል አንደኛዋ የሆኑት መስከረም ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ህመም ገጥሟቸው የማያውቅ መሆኑን ጠበቃቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዓይናቸው እጅጉን መታመሙን ጠቅሰዋል።

ይሁንና “ ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ዓይኗ ይቀላል፤ በጣም ስጋው ይታያል፤ ያማት ነበር፤ እንድትታከም ፍርድ ቤቱን ጠይቄ፣ ሄዳ ተመርምራ ነበር ” በማለት የጤና ክትትሉን አስታውሰዋል። በኋላም ሁለተኛ ምርመራ ማድረጋቸውን ያወሳሉ።

ጠበቃ ሰለሞን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ‛ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ’ በመሄድ መምህርቷን በአካል ያገኟቸዋል። ከዚህ ቀደም አንድ ዓይናቸውን ብቻ ቢሆንም ሲያገኟት ግን ሁለቱም መታመማቸውን ይመለከታሉ።

“ሁለቱም ዓይኖቿ ታምመዋል፤ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው ያለችው ” ያሉት ሰለሞን ከዚያም ትናንት ዓርብ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ።

“ የፍርድ ቤቱ የመሃል ዳኛም ያለምንም ማወላወል፣ በፍጥነት ትታከም የሚል ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፤ ነገር ግን የትዕዛዙ ወረቀት ሳይወጣ ቀርቷል ” ብለዋል።

እናም ዛሬ ቅዳሜ፣ ነገም እሁድ፣ ሰኞም በዓል በመሆኑ መምህርት መስከረም አስቸኳይ ህክምና የማግኘታቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን አመልክተዋል።

መምህርቷ ግን በጽኑ መታመማቸውን አጽዕኖት ሰጥተዋል።

©አዲስ ማለዳ
አሳዛኝ መረጃ ከዋግኽምራ ሰቆጣ!

የአገዛዙ ወታደሮች ሲሸሹ በየመንደሩ ጥለውት የነበረው የመድፍ ቅንቡላ ፈንድቶ ከአንድ ቤተሰብ የአምስት ሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ!

አደጋው የደረሰው በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ 03 ቀበሌ ልዩ ስሙ በልታርፍ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን፡ የአገዛዙ ወታደሮች ያለጥንቃቄ ጥለውት የነበረውን የመድፍ ቅንቡላ አንድ የአከባቢው ሰው አንስቶ ወደቤቱ በማስገባት ለመቀመጫ አገልግሎት ለማዋል ሲሞክር ፈንድቶበታል።

በዚህም ከአንድ ቤተሰብ ብቻ ህፃናትና ታዳጊዎችን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አደጋው የደረሰው ጥር 07/2018 ዓ/ም ሲሆን፡ ሕይወታቸው ካለፈው አምስት ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት መረብ ሚዲያ ነዋሪዎች።

በተጨማሪም የቤት እንስሳት ተገድለዋል፡ መኖሪያ ቤቱም ወድሟል።

በአማራ ክልል የተሰማሩት የአገዛዙ ወታደሮች  ተቀጣጣይ ፈንጆችን ጨምሮ ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ሆን ብለው ጭምር ህፃናት በሚበዙበት አከባቢዎች ጥለው ይሄዳሉ።

ህፃናቱም መጫወቻ መስሏቸው ያነሱትና እጃቸው ላይ ፈንድቶ ሕይወታቸውንና አካላቸውን ይቀጥፋል።

ህፃናት ብቻ ሳይሆኑ ነፍስ አዋቂዎችም ጭምር ከግንዛቤ እጥረት ወድቆ የሚያገኙትን መሣሪያ "ማረሻና ቢለዋ" ለማሰራት በሚል በሚያነሱበት ወቅት እጃቸው ላይ ፈንድቶ ሕይወትን እስከማሳጣትና ንብረትን እስከማውደም የደረሰ የከፋ ጉዳት ሲያደርስባቸው ይስተዋላል።

በየትኛውም የክልሉ አከባቢዎች የአገዛዙ ወታደሮች ሆን ብለው ጭምር የሚጥሉት የጦር መሣሪያ ተተኳሽ ወይንም ተቀጣጣይ ፈንጅ ወድቆ ሲገኝ በአቅራቢያው ለሚገኙ የፋኖ ኃይሎች ጥቆማ በመስጠት፡ የፋኖ ፈንጅ አምካኞች ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲያስወግዱት ማስደረግ እንዲቻል ይህንን መረጃ የምትመለከቱ ሁሉ መረጃውን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የበኩላችሁን እንድትወጡ መረብ ሚዲያ ጥሪ ያቀርባል።

@መረብ ሚዲያ
💔2
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

በመላው ዓለም ላለችሁ የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች በአራቱም ማዕዘን ለነፃነት ውድ ህይወታቹሁን እየገበራቹህ የምትገኙ የፋኖ መሪዎች፣ አባላት እንዲሁም ለመላው አማራዊያንና ኢትዮጵያዊያን ደጋፊዎች በሙሉ ፦

እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለጌታችን፣ መድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን ማለት እንወዳለን ።

የጌታችን ጥምቀት የሰው ልጅ የዕዳ ደብዳቤ የተቀደደበት፣ ከሁሉም በላይ የእግዚአብሄር ደጅ የተከፈተበት በመንፈሳዊ ታሪካችን በአደባበይ ከሚከበሩት በዓል ውስጥ ለህዝባችን አዎንታዊ ድርሻ ያለው፣ አቻ የማይገኝለት ትልቅ በዓል ነው።

በመሆኑም የጀመርነው የህልውና ተጋድሎ 3 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም የአለምን ህዝብ ያስደመመ ፤ በርካታ ድሎች ከአንፀባራቂ መብረቃዊ ጀብድ ጋር ብናስተናግድም ፤ የህልውና ትግል ነውና ብዙ ፈተናዎች አይተንበታል።

ቢሆንም በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚ ፣ በሰው ሀይል ፣ በማህበራዊ ዘርፍና በውጭም በውስጥም በተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት 90% በሚባል በአገዛዙ ለይ ውጤት አስመዝገበናል።

የኦሮሙማውን የብልፅግናን ብሮጀክት እስከ ዳግም ልደት የኦሮሙማው ስርአት መግዛትና መስፋፋት አለበት የሚል መሪ ሀሳብ ቢኖረው ዝነኛውና ባለታሪኩ የአማራ ፋኖ እንኳን እስከ ዳግም ልደት ሊገዛ ይቅትና የስርአቱ ጋሻጃሬዎች የተደወለዱበትን ልደት እንዳያከብሩ አድርጓቸዋል።

ጀግንነትና አርበኛነት ከአባቶች የወረስነው የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ግብር የተላበስን የአማራ ፋኖ የቁርጥ ቀን ልጆች ነን። አርበኝነት ፈሪዎች የማይደርሱበት የጎበዞች መንበር ነው። አርበኝነት የትውልድ ቅብብል ውጤት ነው።

ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲሉ የሞቀ ኑሮቸውን ትተው በዱር በገደሉ አጥንታቸው ለከሰከሱ አይተኬ የሆነውን ውድ ህይወታቸውን ለገበሩ ሰማዕታት ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ እያልን እልፍ ጀግኖች ያጣም ቢሆንም በደምና አጥንት የተፃፈ የትግል ሻማ የፋኖን አንድነት በቅርብ ሰዓታቶች ለህዝባችን የምናበስር መሆኑን እና የፋኖ አንድ መሆኑን መጠናቀቅ ያሰጋቸው የውሰጥ የጭቃ እሾህ መግባታቸው ትግላችንም ከትናንቱ ዛሬ ጎምርቶ እንዲቀጥል ያደርገዋል ።

ስለሆነም ህዝባችን የጥምቀት በዓልን ሲያከብር እንደተለመደው ወዘ ልውጦችን በመከታተል ለፋኖ አሳልፎ በመስጠት መሆን እንዳለበት እንገልፃለን።

ህልውናችን በተባበር ክንዳችን!!

ድል ለአማራ ፍኖ!!

@የጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ መ/ር ያሬድ ገደፍው

ጥር/10/2018 ዓ.ም
🙏2
ምስል:- አርበኛ ወንድ አንተ አሰፋ የጉና ክፍለ ጦር ሰቢሳቢ እና አዛዥ ደሳለኝ የጉና ወታደራዊ መሪ ናቸው።



🔥ምኒልክ ዕዝ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በከፍተኛ እና በየደረጃው ባሉ የድርጅቱ አመራሮች የተመሩ የህዝብ አስተዳደር መዋቅሩን የሚያጠናክሩ በርካታ ህዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛሉ‼️

ምኒልክ ዕዝ በተጋድሎው ነፃ ያወጣቸው ቀጠናዎች ላይ በድርጅት አመራሮቹ የተመሩ በርካታ ውይይቶች እየተደረጉ ሲሆን በጥር 9/2018ዓ/ም የጎፍ ክ/ጦር አመራሮች ከህዝቡ የሚመጡ አስተያየቶችንና ፍላጎቶችን መሰረት ያደረገ መመሪያ ጭምር በማውረድ የህዝብ አስተዳደር መዋቅሩን እያጠናከረ ይገኛል::

በዚህም ከህዝቡ ጋር በሚደረጉ ሰፊ ውይይቶች በፋኖ የሚመራው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ያለበትን ትልቅ ደረጃ ለህዝቡ የማስረዳትና የማስገንዘብ ብሎም ህዝቡ ደጀንነቱን እስከ ድልና ነፃነት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጭምር በመነጋገር የጋራ አቋም ተወስዶበታል::

*ምስል ደቡብ ወሎ ወረኢሉ ወረዳ ከ016 አዳቲ ቀበሌ ህዝብ ጋር ከተደረገ ውይይት የተወሰደ።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
1