ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
አገዛዙ በውጊያ የተገደሉ የራሱ ወታደሮችን አ*ስ*ከ*ሬ*ን በድሮን ደበደበ!

በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ከወልድያ ከተማ ዙሪያ አከባቢዎች ጀምሮ እስከ ቃሊምና ቃሊም ዙሪያ አከባቢዎች ድረስ በተደረገው ተጋድሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል።

ውጊያው የተካሄደው ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲሆን፡ ከ13 ሰዓታት በላይ የጨበጣ ትንቅንቅ ነው የተደረገው።

በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ፡ ከወልድያ ዙሪያ ማለትም ጥቁር ውሃ ምላሽን ይዞ እስከ ቃሊም ድረስ በወሰዱት ውጤታማ ነው በተባለ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን በመደምሰስና በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከነ ተተኳሹ በመማረክ ድል መቀዳጀታቸውን በእለቱ ጣቢያችን መዘገቡ አይዘነጋም።

ያለምንም ማቋረጥ ለተከታታይ 13 ሰዓታት በተደረገው የጨበጣ ውጊያ፡ ከወልድያ ከተማ ዙሪያ ሚጦና ጃርሳን ጨምሮ ከጥቁር ውሃ ምላሽ ጀምሮ አላገዶ፡ አፍሪኬር፡ ቃሊም መገንጠያ፡ ዘንዶ ጅራት(ከሳምት በፊት የአየር መቃዎሚያ እስከ ኦራሉ የወደመበት ቦታ)፣ ቃሊም መገንጠያና ቃሊም ድረስ የሸፈነ ተጋድሎ ተደርጓል።

አገዛዙ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ በወልድያ ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ስታዲየም እና በከተማዋ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ጄነራል መድፍ እንዲሁም በከተማዋ አዲሱ ማረሚያ ቤት እየተሰራ በሚገኝበት ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ሞርተር፣ ቢኤምና ዙ23 ታግዞ ከሁለት ዕዝ የተወጣጡ ከሦስት ክፍለጦር በላይ ወታደሮችን በሚኒሻና አድማ ብተና መንገድ መሪነት በማሰለፍ ሲዋጋ የዋለ ቢሆንም፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ግትልትል ኃይል የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራን በመከናነብ "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ሆኖ ቀርቷል።

በምኒልክ ዕዝ ስር ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በወሰዱት ስኬታማ በሆነ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን መደምሰስ ችለዋል።

የጠላት ኃይል በሚደመሰሱበት ወታደሮች ልክ ተጨማሪ ኃይል እያስገባ የዋለ ሲሆን፡ ምሽት ላይ ግን  የሚጨምረውን ኃይል በማቆም ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማሰማራት ተከታታይ የዘፈቀደ ድብደባዎችን ፈፅሟል።

በዚህም በሰዓታት ልዩነት ከ12 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን፡ አገዛዙ የእሱን ስልጣን ለማራዘም ሲሉ ሲዋጉ በፋኖ የተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አ*ስ*ከ*ሬ*ን ደብድቧል።

ይህም፡ የፋኖ አባላቱ በውጊያው ከተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክላሽና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶችን እንዳይሰበስቡበት በማሰብ የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ነው ሲሉ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።

በድሮን ጥቃቱ በፋኖ በኩል የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ንፁኋኖች ተገድለዋል።

በጥቃቱ ከተገደሉ ንፁኋኖች መካከል አንድ የቤተክርስቲያን ጠባቂ አባትን ጨምሮ ሌሎች በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴትና ህፃናት እንደሚገኙበት ታውቋል።

በተጨማሪም ከወልድያ ከተማ በሚወነጨፍ መድፍ ሕይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ንፁኋኖች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን፡ የመድፍ ጥቃቱ የቤት እንስሳቶችንና ተሰብስቦ የተከመረ የማሽላና የጤፍ ነዶ ማውደሙን ለማረጋገጥ ተችሏል።

@መረብ ሚዲያ
🙏21
ሰበር የድል ዜና

ከንቲባው በራንቦ ክፍለጦር አልሞ ተኳሾች ተገደለ ::

አገዛዙ የኦህዴድ ብልፅግና ስርዓት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሰፊ የወረራ እቅድ አውጥቶ ማህበረሰቡንና ገበሬውን በማዘረፍ እንዲሁም የገዛ ወገናቸው ላይ ስቃይና እንግልት ሲያደርሱ የነበሩ የአማራን ህዝብ በሆዳቸው የለወጡ ባንዳ የስርዓቱ ታማኝ አመራሮች በህዝባችን ላይ ለደረሰው ስቃይ ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛሉ።

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ለመክበብና ለመደምሰስ ህዝባችንን ለመዝረፍ በተለይም በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በቀወት  ዙሪያ በተሬና ራሳ ንፁሀኖችን ከመጨፍጨፍ ባሻገር የገበሬዎችን እህል ጤፍ ሰሊጥና ማሽላ በአይሱዙ በማስጫን እንዲሁም እዛው ይፋት ጣርማበር ዙሪያ አጋምበርና አካባቢው ያለ ማህበረሰብን በማዘረፍ የጣርማበር ወረዳና የደብረሲና ከተማ ከንቲቦች በገዛ ህዝባቸው ላይ አሰቃቂ ግፍ ፈፅመዋል።

በተመሳሳይ በተጉለት ቀጠናዎች ሳሲትና ዙሪያው ሰፊ የወረራ ወንጀል የፈፀሙና ያስፈፁሙ የብልፅግና የጦር ወንጀለኛ ሰራዊት እና ከአማራ አብራክ የወጡ ካድሬዎች ወንድሞቻችን በክብር የወደቁበት ደም ሳይደርቅ ዋናዎቹ የህዝብ ጠላቶች በአልሞ ተኳሾች እየተቀነደሹ ነው።

ዛሬ ለሊቱን ወደ ደብረሲና ከተማ ዘልቀው የገቡት የጀግናው የአፄ አምደፂዎን ኮር ራንቦ ክፋለጦር ጀግኖች የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ወንድምሲገኝ ማሙዬን እስከወዲያኛው ሸኝተውታል ።

ይህ ግለሰብ በከተማውና በገጠሩ የሸዋ አማራ ላይ መጠነሰፊ ወንጀል የፈፀመ የገጠሩን አርሶ አደር ጤፍና ማሽላ በአይሱዙ እያስጫነና ንፁሀኖችን በወራሪው ሰራዊት ያስጨፈጨፈ አደገኛ ባንዳ ነበር ዛሬ በጀግኖቹ የራንቦ ተኳሾች ተገድሏል።

ክብር ለትግሉ ሰማዕታት 🕯️🕯️
ድል ለአማራ ፋኖ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!

@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ጥር 08/2018 ዓ.ም
2🙏2
206ኛ ኮር ትምህርትን ለማስጀመር ከመምህራንና ከርዕሰ መምህራን ጋር እያደረገ ያለው ውይይት የአረመኔው ሰራዊት በመምህራን ላይ በሚያደርገው አፈናና እስር ምክንያት ተደናቅፏል።

የ206ኛ ኮር በድርጅቱ በአፋብኃ መመሪያና ደንብ መሰረት ትምህርትን በተመለከተ ባቀረበው ጥናታዊ ሰነድ ተንተርሶ 206ኛ ኮር የመማር ማስተማሩን ሒደት ለማጀመር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ሰንብቷል። ኮሩ በሚንቀሳቀስባቸው ሁሉም ወረዳዎች መምህራንን በማወያየትና ሰነዱን ለታሳታፊዎች በማቅረብ ትምህርትን ለማስጀመር የጋራ ኮሚቴ አቋቁሙ ወደ ስራ በሚገባበት ወቅት የአረመኔው ስርዓት መምህራንን በማፈን ደሞዛቸውን በመንጠቅ ከፍተኛ በደል እየፈፀመባቸው ይገኛል።

ኮሩ በተቆጣጠረባቸው ቀጠናዎች በአረመኔው ሰራዊት የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማትን ክፍት በማድረግ መምህራን እንዲጎበኙ ሲሆን የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በልዩ ሁኔታ ጥበቃ በሚያደርገው 206ኛ ኮር ቀጠና ባንኮች፣ ጤና ጣቢያዎችና የንግድ ተቋማት ለህዝብ ክፍት ሁነው አገልግሎት ሲሰጡ መምህራን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የትግላችንን አላማ በማጠልሸት የተጠመደው የብልፅግና ተራ ፕሮፓጋንዳ በገሀድ መጋለጥ ሲጀምር መምህራንን በማሰርና በማሰቃየት ተጀምረው የነበሩ እንቅስቃሴዎችን አደናቅፏል።

ኮሩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የሚያደርገውን ሙከራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ተከታታይ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ለተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጥሪ ያደርጋል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
@የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን መቀላቀሉ ቀጥሏል::

አፋብኃ ሚኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉ የብልፅግና የመከለካያ ሰራዊት አማራ በመሆናችን እኛም ተገፍተነል አማረኛ ተናጋሪ ዋርድያ እንኳን በዱላ ነው እሚጠብቀው ሲል የፋሽስቱን ስርዓት አማራ ጠልነት ገልፆ በስርዓቱ ዘረኛነት እየደረሰ ያለው ግፍ ተነግሮ አያልቅም ስርዓቱ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚበጅ አይደለም ብሏል::

በጎጃም ግንባር ደግሞ ሁለት ቃኝ እና መሀንዲስ የአገዛዙ ሰራዊት ፋኖን ተቀላቅለዋል::

ኤሊያስ ጫሌ.... አዳነ ከ6ኛ ዕዝ 602 ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት  እና መኳንት መላኩ....25ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት ከሰዴ ወረዳ አገዛዙ በአማራ ላይ እያካሄደ ያለውን አስነዋሪ ተግባር እና ስራ በማስጠላቱ ጥር 08/2018 ዓ.ም  የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና 54ኝቅ ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል።

መረጃው የምንሊክ እዝ እና ቴወድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው
1
የፋኖ ወታደራዊ አባል የሆነው ወጣት ሞላልኝ አብዩ በተቋሙ ወታደራዊ አገልግሎት እና በትግል ልምድ በአካባቢው የታወቀ ጀብደኛ ነው። ይህ ወጣት ከዚህ በፊት በቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለጦር ውስጥ ለሶስት አመታት ገደማ አገልግሏል። በአገልግሎት ዘመኑ በብሬን እና በስናይፐር ተኳሽነት፣ እንዲሁም በክላሽንኮፍ መሳሪያዎች አማካይነት ብዙ ተግባራዊ ውጤቶችን አስመዝግቧል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ራሳቸውን የመከላከያና የአድማብተና መኮንን እያሉ የሚጠሩ አመራሮችን ጨምሮ የጠላት የሠራዊት አባላትን መግደል ችሏል። በተጨማሪም በወቅቱ የጠላት ወረዳ በነበረችው በሰከላ ወረዳ በተደጋጋሚ ጊዜ ሠርጎ በመግባት መረጃ በማሠባሰብና የጠላት ኃይሎችን በማስወገድ ይታወቃል።

በወታደራዊ አገልግሎቱ ወቅት በሠርጎ ገብ ጥቃት፣ በእጅ በእጅ ውጊያ እና በስቦ ማስከዳት ወታደራዊ ስልት በአጠቃላይ 19 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን መረከቡ ተመዝግቧል። ይህም ወጣቱ በወታደራዊ ልምድ እና በእቅድ ቀማሪነት ዙሪያ ያለውን ክህሎት ያሳያል።

በዚህም ስራው የአፋብኃ ወታደራዊ ክንፉና 105ኛ ኮር ለረጅም ጊዜ ስራውን ሲከታተል ቆይቶ ጀብዱውን የሚመሠክር የእውቅና ወረቀት አበርክቶለታል።
1👍1🙏1
የአማራ ተወላጅ የሆኑ 17 የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ተማሪዎችን የበላው ጅብ መጮህ የጀመረ ይመስላል!

ታግተው ደብዛቸው ጠፍቶ በቀረው 17 የአማራ ተወላጅ የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ተማሪዎች እገታ ዙሪያ መረጃ እንዳለውና በተማሪዎቹ ጠፍቶ መቅረትም ሲሳለቅና ሲዘባበት የነበረው የቀድሞው የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ፕረዝዳንት፡ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ጁሌ ባረፈበት ሆቴል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በማንነታቸው ምክኒያ ከሚማሩበት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ህዳር 25/2012 ዓ/ም የታገቱት 17 ተማሪዎች ደብዛቸው ጠፍቶ ከቀረ ስድስት ዓመታትን አስቆጥረዋል።

ከቤተሰብና ከዘመድ አዝማድ፡ ከወገን ጋር ተላቅሶ መቅበር <ዳስ ጥሎ ኩሎ የመዳር> ያህል የሚቆጥሩት የታጋች ቤተሰቦች እርማቸውን ማውጣት ከብዷቸው ዛሬም በሀዘን ተውጠው ተቀምጠዋል።

በወቅቱ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፡ ታግተው ደብዛቸው ስለጠፋው ተማሪዎች ለሚዲያ መረጃ ሰተዋል ተብለው የተጠረጠሩ በዛው በዩኒቨርስቲው ውስጥ ይማሩ የነበሩ ሌሎች የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በዩኒቨርቲው ፀጥታ አካላት ተይዘው ከባድ ድብደባ ከተፈፀመባቸው በኋላ ህይወታቸው አልፏል።አንዳንዶቹም በዩኒቨርቲው ፀጥታ አካላት ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው ጠፍቶ ቀርቷል።

ገሚሶቹ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችም፡ ያለማንም ከልካይ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል።አንዳንዶቹም  በተዓምር ሕይወታቸው ተርፎ ትምህርታቸውን አቋርጠው ተመልሰዋል።

የአማራ ተወላጅ ተማሪዎቹ በማንነታቸው ምክኒያት ይህ ሁሉ የመከራ መዓት ሲወርድባቸው በወቅቱ የዩኒቨርስቲው ፕረዝዳንት የነበረው ዶ/ር ለታ ተስፋዩ፡ ከኦነግ ኃይሎች ጋር ተባብሮ የድርጊቱ ዋና አቀናባሪና አስፈፃሚ እንደነበረ ሲነገርበት የቆየ ሲሆን፡ ከተማሪዎቹ እገታ በኋላ መረጃ የማጥፋትና የመደበቅ ስራ ላይ ተጠምዶ እንደነበር መረብ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት ለማረጋገጥ ችሏል።

ሌላው ቢቀር የልጆቻቸውን አስከሬን ከዘመድ አዝማድ ጋር ተላቅሶ ቀብሮ እርም ማውጣት ያልቻሉት የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች እንባ ከፈጣሪ ዘንድ ደርሶ ጎርፍ ሆኖ የተመለሰ ይመስላል። 

እነዛን ለጋ የቤተሰብና የሀገር ተስፋዎችን ቅርጥፍ አድርጎ የበላውም ጅብ መጮህ ጀምሯል።

ታግተው ደብዛቸው የጠፋው የ17 ተማሪዎችን ጨምሮ ስለታገቱት ተማሪዎች መረጃ አውጥታችኋል በሚል በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉ ተማሪዎች ደም እጁ የጨቀየው ዶ/ር ለታ ተስፋዩ በድንገት ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የቀድሞው የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት፡ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እንዲሁም የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ጁሌ፡ ከቀናት በፊት ለስራ ጉዳይ ከሌሎች የልኡካን ቡድኑ አባላት ጋር ሆኖ ወደ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አቅንቶ ነበር።

ለታ ተስፋየ ባረፈበት በቨርጂኒያ ልዩ ቦታው ሂልተን ሆቴል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን መረብ ሚዲያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ካወጧቸው የሀዘን መግለጫዎች ተመልክቷል።

የዐብይ አህመድ የሴራ ገመድ ፈታይ ከሆኑ አመራሮች መካከል አንዱና ዋናው ለታ ተስፋዬ ጁሌ፡ ከኦነግ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ቅርጥፍ አድርጎ የዋጣቸውን የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ሳይተፋ ድፍት ብሏል።

የአማራ ተወላጆችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ሐገሪቱ እንድትፈርስ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሴራ ከመጎንጎን ውጭ ከማያውቀውና  የትውልድ አምካኝ ጭራቅ ከሆነው ከብልፅግና ቡድን ወገን የሆኑ ባለስልጣናት፡ እየተምዘገዘገ እየመጣባቸው ከሚገኘው ከፋኖ ፍርድ ቀን ከመድረሳቸው በፊት፡ ፅዋው ካፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ እስኪፈስ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው።

@መረብ ሚዲያ
6
አገዛዙ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪዎችን በአስገዳጅ ሁኔታ ከሰበሰበ በኋላ በፈፀመባቸው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ከ100 በላይ የሚሆኑት ተገደሉ!

ከፋኖ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ያልቻለው አገዛዙ፡ "ሕዝባዊ ኮንፈረንስ" በሚል ስም ንፁኋንን ከየመኖሪያ ቤታቸው በግዳጅ ከሰበሰበ በኋላ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የበቀል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን፡ ይህ ድርጊት በቀጣይ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎችም እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ጥር 07/2018 ዓ/ም ረፋድ በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ሳህላ ሰየምት ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ልዩ ስሙ ሰየም ድልድይ በተባለ ቦታ ላይ ነው።

ከጎንደር በለሳ ጀምሮ እስከ ዋግኽምራ ሰሀላ ሰየምት ወረዳ ድረስ ያካለለ የድሮን አሰሳ ከቀናት በፊት ጀምሮ እየተደረገ መሰንበቱን ነው የአከባቢው ነዋሪዎች የገለፁት።

የድሮን አሰሳ በተደረገበት አከባቢ ህፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ እንደማይደረግ እየታወቀ፡ ነገር ግን "ከበላይ አካላት የመጣ ትዕዛዝ ነው" በሚል ለአደጋ ተጋላጭ በሆነ ቦታ ሕዝቡን ለጥቃት አመቻችተው ነው የሰበሰቡት ብለዋል ምንጮች አክለው።

ሕዝቡን በግዳጅ ለስብሰባ ሲጠሩ የነበሩ ካድሬዎችና የሚኒሻ አባላቱ አከባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ የድሮን አሰሳ እየተደረገ መሰንበቱን በሚገባ ያውቃሉ የሚሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው አንድ የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪ፡ "የድሮን ጥቃት ሊፈፀምብን ይችላል" በሚል ስብሰባው ከመካሄዱ በፊት  ስጋታቸውን የገለፁ ሰዎች "የፅንፈኛ ደጋፊ ናችሁ" በሚል አስቀድሞ ታስረዋል ብለዋል።

"ሕዝባዊ ኮንፈረንስ" በሚል በዞኑ ስር ኩታ ገጠም ከሆኑ ከደሀና ወረዳ፣ ከስሀላ ሰየምትና ከአበርገሌ ወረዳ ቀበሌዎች በግዳጅ የሰበሰቧቸውን ንፁኋኖች የድሮን አሰሳ እንደተደረገበትና የስጋት ቀጠና መሆኑ በታወቀ ቀጠና ላይ በማስቀመጥ ስብሰባው ከተጀመረ ግማሽ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል ነው ያሉት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው በወረዳው ስር ካሉ ጤና ጣቢያዎች ባንዱ የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያ ሌላኛው የመረጃ ምንጫችን።

በዚህም ከ100 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፡ ከሟቾቹ መካከል አረጋውያን፣ ህፃናትን ያዘሉ እናቶችና ነፍሰጡር ሴቶች እንደሚገኙበት ታውቋል።

በድሮን ጥቃቱ ከተገደሉ ንፁኋኖች በተጨማሪ ሰብስባውን በአስገዳጅነት የጠሩትና ሲመሩ ከነበሩት የሚኒሻና የፖሊስ እንዲሁም የወረዳ ካቢኔ አባላት መካከል በርካቶች ተገድለዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ በአከባቢው ከፍተኛ የሆነ የሕክምና እጥረት የተከሰተ ሲሆን፡ የተጎጂዎቹን ሕይወት ለማትረፍ በጭነት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ጎንደር በለሳና እብናት እንዲሁም ሰቆጣ ከተማ እስከ ትናንት አመሻሽ ድረስ ሲወሰዱ እንደነበር ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከፋኖ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ያልቻለው ኦህዴድ መሩ የብልፅግና ቡድን፡ "ሕዝባዊ ኮንፈረንስ" በሚል ስም ንፁኋንን ከየመኖሪያ ቤታቸው በግዳጅ ከሰበሰበ በኋላ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የበቀል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን፡ ይህ ድርጊት በቀጣይ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎችም እንደሚቀጥል የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

መረብ ሚዲያ
💔1
በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ “ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ” ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግሯል።

በእነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ ተከሳሾች መካከል አንደኛዋ የሆኑት መስከረም ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ህመም ገጥሟቸው የማያውቅ መሆኑን ጠበቃቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዓይናቸው እጅጉን መታመሙን ጠቅሰዋል።

ይሁንና “ ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ዓይኗ ይቀላል፤ በጣም ስጋው ይታያል፤ ያማት ነበር፤ እንድትታከም ፍርድ ቤቱን ጠይቄ፣ ሄዳ ተመርምራ ነበር ” በማለት የጤና ክትትሉን አስታውሰዋል። በኋላም ሁለተኛ ምርመራ ማድረጋቸውን ያወሳሉ።

ጠበቃ ሰለሞን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ‛ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ’ በመሄድ መምህርቷን በአካል ያገኟቸዋል። ከዚህ ቀደም አንድ ዓይናቸውን ብቻ ቢሆንም ሲያገኟት ግን ሁለቱም መታመማቸውን ይመለከታሉ።

“ሁለቱም ዓይኖቿ ታምመዋል፤ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው ያለችው ” ያሉት ሰለሞን ከዚያም ትናንት ዓርብ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ።

“ የፍርድ ቤቱ የመሃል ዳኛም ያለምንም ማወላወል፣ በፍጥነት ትታከም የሚል ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፤ ነገር ግን የትዕዛዙ ወረቀት ሳይወጣ ቀርቷል ” ብለዋል።

እናም ዛሬ ቅዳሜ፣ ነገም እሁድ፣ ሰኞም በዓል በመሆኑ መምህርት መስከረም አስቸኳይ ህክምና የማግኘታቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን አመልክተዋል።

መምህርቷ ግን በጽኑ መታመማቸውን አጽዕኖት ሰጥተዋል።

©አዲስ ማለዳ