ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
1.34K subscribers
4.16K photos
331 videos
17 files
2.21K links
የፋኖ ድምፅ
Download Telegram
በድሮን ጥቃት ከ105 በላይ የአገዛዙ ሚሊሻዎችና ንፁሃን ወገኖች በበለሳ ተገደሉ!!  

     በቅርቡ በዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጥር 01/2018 ዓ.ም  ከባድ ድምሰሳ ሽንፈት የተጎነጨው የአብይ ሰራዊት የሞራል ማካካሻ የአየር ጥቃት ለማድረስ በማቀድ ከሰሞኑ በሳህላ እና በበለሳ ቀጠና ተደጋጋሚ የአየር ቅኝት እያደረገ የሰነበተ ሲሆን በዛሬው ዕለት ጥር 07/2018 ዓ.ም ረፋድ ዋግ ህምራ ዞን ሳህላ ወረዳ ሰየም ድልድይ የተባለ ቦታ በርካታ የራሱ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ ዓባላትና ተገደው የተሰበሰቡ ንፁሃን ወገኖቻችንን የሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮን) ጥቃት አድርሶባቸዋል።

  እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ከ65 በላይ የሚሊሻ ዓባላት የሞቱ ሲሆን ከ40 በላይ ንፁሃን ወገኖች በአየር ጥቃቱ የህይወት መስዕዋትነት እንደከፈሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ  ቁስለኛ መሆናቸውም ታውቋል።

      የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዕዝ የሰራዊት ዓባላትን ለማጥቃት ሲቃጥት የሰነበተው አገዛዙ በዛሬው ዕለት የአካባቢውን ሚሊሻና ንፁሃን ወገኖችን እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በጅምላ ጨፍጭፏቸዋል።

    በቀጣይ መረጃዎችን ለህዝባችን በይፋ እየተከታተልን የምናሳውቅ ሁኖ የንፁሃን ወገኖቻችንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በአገዛዙ ላይ በማነጣጠር የአፀፋ ምላሽ እንደምንሰጥ እያሳወቅን በጅምላ የአየር ጥቃት ህይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን በላይ ዕዝና ጎንደር ጠ/ግዛት ዕዝ በሚንቀሳቀሱበት የሰሜን አማራ ቀጠና (ጎንደር) በቀጣይ ቀናት ለሰማዓት ወገኖቻችን የሚመጥኑ ህዝባዊ የሀዘን አዋጅ ሊታወጅ እንደሚችል እናሳውቃለን።

       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
@አፋብኃ በላይ ዕዝ ህ/ግንኙነት መምሪያ
2
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ አጠር ያለ መግለጫ!

የምኒልክ ዕዝን ክንድ መቋቋም ያቃተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከተግባር ይልቅ "ውሸት"ን ትልቅ የአውደ ውጊያ ግንባር ካደረገው አመታቶች የተቆጠሩ ሲሆን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበት በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስም የሃሰት መግለጫ እያወጣ ይገኛል::

በመሆኑም እኔን እና የአሳመነዉ ኮር ም/አዛዥ የሆነዉን ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬን ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ከሚኒልክ ዕዝ በድርጅቱ ትዕዛዝ እንደታገድን አድርገዉ ምላሱ ብቻ የቀረዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በትላንታናዉ ዕለት የማስመሰል መግላጫ አዉጥቷል።

እንኳን በወሬ ልንፈታ እና ልንደነግጥ ቀርቶ ድሮኑን እና ታንኩንም አልፈራንም እናም በመላዉ ዓለም ለምትገኙ አማራዊያን እና የትግላችን ደጋፊዎች ይህ የአገዛዙ የዉሸት መግለጫ መሆኑን እንድታዉቁ እና አሁን ላይ እኔም ሆንኩ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬ የተጣለብንን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣን እንገኛለን።

እናንተም በውሸታችሁ ቀጥሉ እኛም በሐቀኛ ተግባራችን! በያዝናቸው አመርቂ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎቻችን ታጅበን ለመጨረሻው ግብ ድልና ነፃነታችን እየታገልን እንገኛለን::

ግፈኞች ሆይ ጦራችሁም ወሬያችሁም አይፈታንም:: አላማችንንም ላፍታም ቢሆን አያደናቅፈውም!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 7/2018 ዓ.ም
በድሮን ጥቃት ከ105 በላይ የአገዛዙ ሚሊሻዎችና ንፁሃን ወገኖች በበለሳ ተገደሉ!!  

     በቅርቡ በዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጥር 01/2018 ዓ.ም  ከባድ ድምሰሳ ሽንፈት የተጎነጨው የአብይ ሰራዊት የሞራል ማካካሻ የአየር ጥቃት ለማድረስ በማቀድ ከሰሞኑ በሳህላ እና በበለሳ ቀጠና ተደጋጋሚ የአየር ቅኝት እያደረገ የሰነበተ ሲሆን በዛሬው ዕለት ጥር 07/2018 ዓ.ም ረፋድ ዋግ ህምራ ዞን ሳህላ ወረዳ ሰየም ድልድይ የተባለ ቦታ በርካታ የራሱ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ ዓባላትና ተገደው የተሰበሰቡ ንፁሃን ወገኖቻችንን የሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮን) ጥቃት አድርሶባቸዋል።

  እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ከ65 በላይ የሚሊሻ ዓባላት የሞቱ ሲሆን ከ40 በላይ ንፁሃን ወገኖች በአየር ጥቃቱ የህይወት መስዕዋትነት እንደከፈሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ  ቁስለኛ መሆናቸውም ታውቋል።

      የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዕዝ የሰራዊት ዓባላትን ለማጥቃት ሲቃጥት የሰነበተው አገዛዙ በዛሬው ዕለት የአካባቢውን ሚሊሻና ንፁሃን ወገኖችን እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በጅምላ ጨፍጭፏቸዋል።

    በቀጣይ መረጃዎችን ለህዝባችን በይፋ እየተከታተልን የምናሳውቅ ሁኖ የንፁሃን ወገኖቻችንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በአገዛዙ ላይ በማነጣጠር የአፀፋ ምላሽ እንደምንሰጥ እያሳወቅን በጅምላ የአየር ጥቃት ህይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን በላይ ዕዝና ጎንደር ጠ/ግዛት ዕዝ በሚንቀሳቀሱበት የሰሜን አማራ ቀጠና (ጎንደር) በቀጣይ ቀናት ለሰማዓት ወገኖቻችን የሚመጥኑ ህዝባዊ የሀዘን አዋጅ ሊታወጅ እንደሚችል እናሳውቃለን።

       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!


      አፋብኃ በላይ ዕዝ
      ጥር  07/2018 ዓ.ም
      አፋብኃ በላይ ዕዝ ህ/ግንኙነት መምሪያ
🙏21
ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ 15 የጠላት ኃይል በመደምሰሰ፣አንድ ብሬንና ስድስት ክላሽንኮፍ በመማረክ ተከዜ ክፍለ ጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፉ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ተከዜ ክፍለ ጦር ላስታ ወረዳ ኩልመስክ ከተማ ጥር 06/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅ የብልፅግና ዙፋን አስጠባቂ የጁላን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ተከዜዎቹ ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።

የብልፅግና ሰራዊት ከሙጃ እስከ ኩልመስክ ያካለለ በመድፍ የታገዘ ውጊያ ያደረገ ቢሆንም የአካባቢያቸውን መልከዓምድር ጠንቅቀው የሚያውቁት ተከዜዎቹ እንደፈለጉ ወጥተው ወርደው ጠላትን እነርሱ በሚፈልጉት አግባብ ቃኝተው የጠላትን አንገት በማስደፋት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።

በዚህ አውደ ውጊያ 15 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ10 በላይ ቁስለኛ እንደሆነ ታውቋል፤በተያያዘም አንድ ብሬን፣ስድስት ክላሽንኮፍ፣500 የብሬን ተተኳሽና 650 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
🙏2
‎የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር አመራሮች እና ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስተዳደር በተገኙበት በዛሬዉ ዕለት ሰፊ ሕዝባዊ ዉይይቱ ተካሄደ::

በስብሰባውም ቀጠዊ የፖለቲካ፤ የመልካም አስተዳደር ግንዛቤ በመፍጠር የተቻለ ሲሆን ህዝቡ እኛም ሆነ ልጆቻችን ወጥተን ለመግባት የተቸገርን ስለሆነ  ትግሉን እስከወዲያኛው ለመገርሰስ ድጋፋችን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት አጋሬነታቸውን የገለፁ ሲሆን  የትግሉን የህዝባዊ ፊታውራሪነት ማስቀጠል እንዳለበትና የጮቄን ተራራ በአማራዊ እሴት መጠበቅ እንዳለብን የጋራ ተግባቦትና መረዳት ተፈጥሯል።

በሌላ ዜና
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ከባህርዳር ሻለቃ ጋር  ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ስራና የግዳጅ እንቅስቃሴዎች እራሱን ዝግጁ አደረገ።

የኮርና የክፍለጦር አመራሩ በ102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር  በባህርዳር ሻለቃ መካከል በመገኘት ለሰራዊቱ በትጥቅና በስና ልቦና የጠነከረ ሀይል እንዲኖር የፓለቲካና ወታደራዊ ስልጠናዎችን በመስጠትና ከምንጊዜውም በለይ ሰራዊቱን በማንቃት ለግዳጅ ዝግጁ አድርጎ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

@የቴዎድሮስ እዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
🙏2
አገዛዙ በውጊያ የተገደሉ የራሱ ወታደሮችን አ*ስ*ከ*ሬ*ን በድሮን ደበደበ!

በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ከወልድያ ከተማ ዙሪያ አከባቢዎች ጀምሮ እስከ ቃሊምና ቃሊም ዙሪያ አከባቢዎች ድረስ በተደረገው ተጋድሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል።

ውጊያው የተካሄደው ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲሆን፡ ከ13 ሰዓታት በላይ የጨበጣ ትንቅንቅ ነው የተደረገው።

በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ፡ ከወልድያ ዙሪያ ማለትም ጥቁር ውሃ ምላሽን ይዞ እስከ ቃሊም ድረስ በወሰዱት ውጤታማ ነው በተባለ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን በመደምሰስና በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከነ ተተኳሹ በመማረክ ድል መቀዳጀታቸውን በእለቱ ጣቢያችን መዘገቡ አይዘነጋም።

ያለምንም ማቋረጥ ለተከታታይ 13 ሰዓታት በተደረገው የጨበጣ ውጊያ፡ ከወልድያ ከተማ ዙሪያ ሚጦና ጃርሳን ጨምሮ ከጥቁር ውሃ ምላሽ ጀምሮ አላገዶ፡ አፍሪኬር፡ ቃሊም መገንጠያ፡ ዘንዶ ጅራት(ከሳምት በፊት የአየር መቃዎሚያ እስከ ኦራሉ የወደመበት ቦታ)፣ ቃሊም መገንጠያና ቃሊም ድረስ የሸፈነ ተጋድሎ ተደርጓል።

አገዛዙ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ በወልድያ ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ስታዲየም እና በከተማዋ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ጄነራል መድፍ እንዲሁም በከተማዋ አዲሱ ማረሚያ ቤት እየተሰራ በሚገኝበት ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ሞርተር፣ ቢኤምና ዙ23 ታግዞ ከሁለት ዕዝ የተወጣጡ ከሦስት ክፍለጦር በላይ ወታደሮችን በሚኒሻና አድማ ብተና መንገድ መሪነት በማሰለፍ ሲዋጋ የዋለ ቢሆንም፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ግትልትል ኃይል የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራን በመከናነብ "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ሆኖ ቀርቷል።

በምኒልክ ዕዝ ስር ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በወሰዱት ስኬታማ በሆነ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን መደምሰስ ችለዋል።

የጠላት ኃይል በሚደመሰሱበት ወታደሮች ልክ ተጨማሪ ኃይል እያስገባ የዋለ ሲሆን፡ ምሽት ላይ ግን  የሚጨምረውን ኃይል በማቆም ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማሰማራት ተከታታይ የዘፈቀደ ድብደባዎችን ፈፅሟል።

በዚህም በሰዓታት ልዩነት ከ12 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን፡ አገዛዙ የእሱን ስልጣን ለማራዘም ሲሉ ሲዋጉ በፋኖ የተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አ*ስ*ከ*ሬ*ን ደብድቧል።

ይህም፡ የፋኖ አባላቱ በውጊያው ከተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክላሽና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶችን እንዳይሰበስቡበት በማሰብ የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ነው ሲሉ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።

በድሮን ጥቃቱ በፋኖ በኩል የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ንፁኋኖች ተገድለዋል።

በጥቃቱ ከተገደሉ ንፁኋኖች መካከል አንድ የቤተክርስቲያን ጠባቂ አባትን ጨምሮ ሌሎች በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴትና ህፃናት እንደሚገኙበት ታውቋል።

በተጨማሪም ከወልድያ ከተማ በሚወነጨፍ መድፍ ሕይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ንፁኋኖች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን፡ የመድፍ ጥቃቱ የቤት እንስሳቶችንና ተሰብስቦ የተከመረ የማሽላና የጤፍ ነዶ ማውደሙን ለማረጋገጥ ተችሏል።

@መረብ ሚዲያ
🙏21
ሰበር የድል ዜና

ከንቲባው በራንቦ ክፍለጦር አልሞ ተኳሾች ተገደለ ::

አገዛዙ የኦህዴድ ብልፅግና ስርዓት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሰፊ የወረራ እቅድ አውጥቶ ማህበረሰቡንና ገበሬውን በማዘረፍ እንዲሁም የገዛ ወገናቸው ላይ ስቃይና እንግልት ሲያደርሱ የነበሩ የአማራን ህዝብ በሆዳቸው የለወጡ ባንዳ የስርዓቱ ታማኝ አመራሮች በህዝባችን ላይ ለደረሰው ስቃይ ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛሉ።

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝን ለመክበብና ለመደምሰስ ህዝባችንን ለመዝረፍ በተለይም በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በቀወት  ዙሪያ በተሬና ራሳ ንፁሀኖችን ከመጨፍጨፍ ባሻገር የገበሬዎችን እህል ጤፍ ሰሊጥና ማሽላ በአይሱዙ በማስጫን እንዲሁም እዛው ይፋት ጣርማበር ዙሪያ አጋምበርና አካባቢው ያለ ማህበረሰብን በማዘረፍ የጣርማበር ወረዳና የደብረሲና ከተማ ከንቲቦች በገዛ ህዝባቸው ላይ አሰቃቂ ግፍ ፈፅመዋል።

በተመሳሳይ በተጉለት ቀጠናዎች ሳሲትና ዙሪያው ሰፊ የወረራ ወንጀል የፈፀሙና ያስፈፁሙ የብልፅግና የጦር ወንጀለኛ ሰራዊት እና ከአማራ አብራክ የወጡ ካድሬዎች ወንድሞቻችን በክብር የወደቁበት ደም ሳይደርቅ ዋናዎቹ የህዝብ ጠላቶች በአልሞ ተኳሾች እየተቀነደሹ ነው።

ዛሬ ለሊቱን ወደ ደብረሲና ከተማ ዘልቀው የገቡት የጀግናው የአፄ አምደፂዎን ኮር ራንቦ ክፋለጦር ጀግኖች የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ወንድምሲገኝ ማሙዬን እስከወዲያኛው ሸኝተውታል ።

ይህ ግለሰብ በከተማውና በገጠሩ የሸዋ አማራ ላይ መጠነሰፊ ወንጀል የፈፀመ የገጠሩን አርሶ አደር ጤፍና ማሽላ በአይሱዙ እያስጫነና ንፁሀኖችን በወራሪው ሰራዊት ያስጨፈጨፈ አደገኛ ባንዳ ነበር ዛሬ በጀግኖቹ የራንቦ ተኳሾች ተገድሏል።

ክብር ለትግሉ ሰማዕታት 🕯️🕯️
ድል ለአማራ ፋኖ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!

@ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ጥር 08/2018 ዓ.ም
2🙏2